cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ምግብ እና የኬክ አዘገጃጀት

ሀላል ምግቦች ፣ጣፋጭና ለጤና ተስማሚ

Show more
Advertising posts
1 754
Subscribers
No data24 hours
+17 days
+2230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ታክሲው ከሳሪስ አቦ ወደ ቦሌ የሚሄድ ነው እና ሁሌም ከታች ሞልቶ መጥቶ አዲስ ሰፈር ሚካኤል በትርፍ ይጭናል። እና እንደተለመደው ሲመጣ ከረዳቱ ፊት ለፊት ሞተሩ ላይ የተቀመጠች ሴት ነበረች እና ስገባ ተነስታ የመጀመሪያው ወንበር ላይ ከተቀመጡት ሁለት ወንዶች መሀል ገባች እኔ እሷ የነበረችበት ተቀመጥኩ ከኔ በኋላ የሆነ ልጅ ገባ እህቴም ነበረች ገባች እና አብረን እንደሆንን ስላወቀ ልጁን በቃ ሞላ ብሎ አስወረደው ከሱ በኋላ የገባችውን እህቴን ግን ዝም አላት ሁለተኛው ወንበር ላይ ተደርባ ተቀመጠች እኔ ቦርሳዬ በእጅ የሚያዝ ነው እና ዚፑ ወደውጭ ነው የዞረው የመጀመሪያው ወንበር ላይ ጫፍ ላይ የተቀመጠው ሰውዬ ቦርሳ ይዟል። 1. የታክሲው በር አይዘጋም ወይም እንዳይዘጋ አርገውታል እና እንዳትወረወሪ ብሎ ወደ እነሱ ተጠጊ አለኝ ሞተሩ ላይ ማለት ነው 2. ልጠጋ ስል ያ ቦርሳ የያዘው ሰውዬ ቦርሳዬን ሊተባበረኝ መስሎ ሊቀበል እኔ ደሞ አይ ብዬ እንደያዝኩት መጠጋት 3.መሀል የተቀመጠችው ሴት ነይ እዚ ጋር ግቢ መሀል ማለት አራተኛ ወይም ልቀይርሽ እኔ ደሞ አይ ቅርብ ስለሆንኩ ችግር የለውም አልኳት አይ "ሞተሩ እንዳያቃጥልሽ" አለች አይ አልኩና በሆዴ እሷን አያቃጥላትም እንዴ...እያልኩ አደያበባ ደረስን ኢሄ ሁሉ አንድ ፌርማታ ነው ከገባሁ ጀምሮ ከዛ ደሞ እህቴን ትራፊክ አለ ብለው ወደ 3ኛ ወንበር ወሰዷት ከኔ ራቀች አታይም በዛ ላይ ረዳቱ ምን ያክላል እና ትንሽ ስለሆነ ሚቀረን ትራፊክ ከሚይዝህ እንውረድልህ ልለው እኔን ብሎ አዛኝ እያሰብኩ በሩን ይታገላል ለመዝጋት በዛ መሀል እጄን ቆረጠኝ ፎጣ ስጠኝ አለው ሹፌሩን እኔሆዬ የቱ ጋር ብዬ ትኩረቴ ወደ እሱ ሚስ ዳይሬክሽን በዛች መሀል ቦርሳ የያዘው ሰውዬ ቦርሳዬን በቦርሳው ሸፍኖ የተወሰነ ከፍቶታል እና ሳብ ሳረገው የተወሰነ ተከፍቷል ቀና ብዬ ሰውየው ላይ ማፍጠጥ እሱ ባላየ ገዛ ከፍቼ ሳይ ሁሉም ነገሬ አለ አዲስ ሰፈርም ደረስን ወረድን ፍጥነታቸው ያላወጣው ቦርሳዬን ማንጠልጠያውን ይዤው ስለነበር እስከመጨረሻው አልከፈተውም ስልኬን የከተትኩበት ኪስ ደሞ በተቃራኒው ነው እና አላገኘውም እና በጠዋቱ ቀልቤን ገፈፉኝ። እህቴ ደሞ ታጥፎ ሚዘጋ ነበር ቦርሳዋ እና አልተመቻቸውም እንጂ አራተኛ ላይ ከሚቀመጡት ውስጥ በጣም ወደኔ ሲጠጋ ነበር አለች እሷ አልነቃችም እኔም ቦርሳዬ ተከፍቶ ሳይ ነው ያ ሁሉ ድራማቸው እንደሆነ የገባኝ
Show all...
👍 16 5👎 1😱 1
ሰላም ሰላም ዛሬ ዋፍል ይዠላችሁ መጥቻለሁ ወደ አሰራሩ ስንሄድ 5/6 እንቁላል 300 ስኳር 250 ( ሩብ ሊትር ) ዘይት 1 ማማ ወተት ግማሽ ሊትር 750 ሩብ የጎደለው ለአንድ ኩሎ ዱቄት 2 የሾርባ ማንኪያ ፔኪን ፓውደር 1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ ትንሽ ጨው ወደ አሰራሩ ስንሄድ *መጀመርያ እንቁላሉና ስኳሩን በደንብ እንመታዋለን ከዛ ዘይቱን እና ወተቱን ጨምረን እናዋህደዋለን ሲቀጥል ዱቄቱንና ፔኪንግ ፓውደሩን ቫኒላውንም ጨውኑም አንድላይ ነፍተን እንቁላሉ ላይ ቀስ አርገን እየጨመረን በደንብ  እናዋህደዋለን *መጨረሻ ላይ የምንጋግርበት የዋፍል መስርያችን አግለን አንዳንድ ጭልፋ እየጨመር ን መጋገር #ሊጡ ከቀጠነብን ትንሽ ዱቄት እንጨምራለን
Show all...
👍 8 4
ለመክሰስ በቀላሉ የሰራሁት ምርጥ ቆቀር 2 ተኩል የውሃ ብርጭቆ ዱቄት 2የሾርባ ማንኪያ ዘይት 1ሾርባ ማንኪያ እርሾ(ቤኪንግ ሶዳ) 3 ሾርባ ማንኪያ ስኳር ትንሽ ጨው ዱቄቱን አየር እንዲያስገባልኝ ነፋሁትና ሁሉንም አንድላይ ጨማምሬ ውሃ ሳላደርግ በደንብ አሸሁት ተዋህዶ ፍርፍር ፍርፍር እሰከሚል ከዛ ትንሽ ትንሽ ለብ ያለ ውሃ ጠብ እያደረኩ በደንብ እንዲዳመጥ አድርጌ አሸሁትና ለ1 ሰአት ሸፍኜ ሞቃት ቦታ አስቀመጥኩት ከዛ መዳመጫዬ ለይ በቁመቱ በእጄ አሽከርክሬ(ፎቶ ላይ እንዳለው)በቢላ ቆራርጬ በጣም ባልጋለ ዘይት ጠበስኩት ሲጠበስ እራሱ ይሰነጣጠቃል ዘይት አይጠጣም ውስጡ ክፍትፍት ይላል ሞክሩት በጣም ቀላልና ጣፋጭ ነው😋😋😋
Show all...
👍 6 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቀሲል ዱቄት ለፀጉር ያለው ጥቅም 1, ለፀጉር እድገት የቀሲል ዱቄት በ ውስጡ የ ዚንክ ንጥረ ነገር ስላለ ለፀጉር እድገት ጥሩ ነው :: ቀሲል በተፈጥሮ አንቲ ኢንፍላማቶሪ በሃሪው የፀጉርን መነቃቀል እና የ ራስ ቅላችንን ጤና ይጠብቅልናል :: 2,ፎሮፎርን ይከላከልናል ቀሲል እንዳልነው አንቲ ኢንፍላማቶሪ በኃሪ አለው ብለናል እሱ የፀጉር ቆዳችንን ጤና ይጠብቅልናል :: ለፊታችን ያለው ጥቅም 1, ለፊት መታጠቢያ 2, ለብጉር 3,ለፊትን ልስላሴ 4, ለፊትን መሸብሸብ 5,ለጥቁር ነጠብጣብ 6,ፊት መቅላት ይቀንሳል 7,ለፊታችንን ቃና (tone) ይጠብቅልናል።
Show all...
👍 7 2
Photo unavailableShow in Telegram
#አቮካዶን የመመገብ ጥቅሞች በጥቂቱ🥑🥑🥑🥑 🍁 የኮሌስትሮል መጠን ይቀንሳል አቮካዶ በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር (betasisterol) በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘዉን የኮሌስትሮል መጠን እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ 🍁ለዓይናችን ጤና ጠቃሚ ነው በውስጡ የሚገኘው ካሮቲኖይድ ሉቲየን (carotenoid lutien) ዓይናችንን ከዕድሜ ጋር በተያያዘ ምክንያት የሚመጡ ሕመሞችን እንድንከላከል ይረዳል፡፡ 🍁 በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን ይቀንሳል በአቮካዶ ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው (folate) ፎሌት በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን እንደሚቀንስ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ 🍁ከካንሰር ይከላከላል አቮካዶ የሚመገቡ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው እንደሚቀንስና ወንዶችን ደግሞ ከፕሮስቴት ካንሰር የመከላከል አቅም እንዳለው የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ 🍁መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል አቮካዶ ተፈጥሮአዊ ከሆኑ የመጥፎ አፍ ጠረን መከላከያዎች አንዱ ነው፡፡ 🍁 ለቆዳችን ጥቅም የኦቮካዶ ቅባት በብዙ የውበት መጠበቂያዎች ውስጥ የሚገባና ለቆዳ ተስማሚ እና ጤናማነት ጠቃሚነት ያለው የፍራፍሬ ዓይነት ነው፡፡
Show all...
👍 7 1
Photo unavailableShow in Telegram
🔶የእንጆሪ ጁስ 👇የተጠቀምኩት 🔸እንጆሪ 🔸ቴምር ወይም ስኳር 🔸ወተት ወይም ውሀ በስኩዋር ፋንታ ቴምር ተጠቅሜ ነው የሰራሁት መጠኑን እንደምትፈልጉት በወተት ፋንታ ውሀ ማድረግ ይቻላል መልካም ቀን የኔ ውዶች ❤❤
Show all...
👍 13 6
እቺን ቸኮሌት😍😍😍 እናንተም ሞክሩት😋 ወድጃታለሁ አሰራር 4 የሾርባ ማንኪያ ካካዎ ፓውደር 1ማንኪያ የበቆሎ ዱቄት 1 የቡና ሲኒ ስኳር 1 ሲኒ ወተት ቫኒላ በክዳኑ ሁሉንም ካቀላቀልን በኋላ አነስ ባለ እሳት ላይ ጥደን እስከሚወፍር ማማሰል ወይም በጁሰር መፍጨት  ሲወፍር አውጥተን ትነሽ ቀዝቀዝ ሲል በፈለግነው ቅርፅ ወይም እቃ አድርገን ፍሪጅ ማስገባት ሲደርቅ አውጥተን ትንሽ አቆይተን ማጣጣም ነው😋😋😋
Show all...
👍 10
ሰላም ሰላም ብዙዎቻችሁ ስጠይቁ ነበር የሽምብራ ዱቄቱ እንዴት እንደሚዘጋጅ ሽምብራውን ይታመስና እንደሽሮ ክክ አስከክተን አበጥሮ ከዛ ትንሽ ኮረሪማና ስጋ መጥበሻ ጨምሮ አስፈጭው ከዛ ተነፍቶ በሚፈለገው መጠን ትንሽ ጨው ጨምሮ በወፍራሙ አቡክቶ በስሱ እያድበለበሉ በዘይት መጥበስ ነው ❤️❤️
Show all...
👍 3
5 ኩባያ ዱቄት 1 ኩባያ ዘይት 1 ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር 10 ማንኪያ ስኳር ሁለት ሲኒ ወተት ትንሽ ጨው አብኩቶ ዳምጦ በቢላ በአራት መዓዘን ወይም በዳይመንድ መቁረጥ በመቀስ ከመድከም በጣም ቀላል ጊዜ ቆጣቢ ነው በዚህ ድካም ላይ ስለውበቱ መጨነቅ አያስፈልግም😊በኦቭን ወይም በእንጀራ ምጣድ መቁላት 👉የፆም ከፈለጋችሁ ወተቱን መተውና በውሃ መጠቀም
Show all...
👍 3
የሽንብራ ዓሳ ወጥ አሰራሩ👉ለብስኩቱ 👉 የሽንብራ ዱቄት 👉ኮረሪማ 👉የተፈጨ ዝንጅብል 👉ጨዉ ለስልሱ 👉ቀይ ሽንኩርት 👉ዘይት 👉ቲማቲም እንደ ፍላጎታችሁ 👉በርበሬ 👉ነጭ ሽንኩርት ወደ አሰራሩ ስንመጣ 👉በጎድጓዳ ሳህን የሽንብራ ዱቄቱን ዝንጅብሉን ኮረሪማና ጨዉን ጨምሮ ማቡካት👉ያቦካነዉን በፈለግነዉ ቅርፅ ማዉጣት 👉 መጥበሻ ላይ ዘይት አግለን መጥበስ ወይም በምጣድ ማብሰል👉ጠብሰን ከጨረስ በኋላ ሳህን ላይ እናቆየዋለን👉እላይ እንደገለፅኩት ሽንኩሩቱን ዘይቱን እያደረግን በቅደም ተከተል እናቁላላለን ከተቁላላ በኋላ የጠበስነዉን ብስኩት እንጨምራለን ብስኩቱ በሰል ሲል ነጭ ሽንኩርትና ጨዉ ጨምረን እናወጣዋለን 👉ብስኩቱ መፍረስ የለበትም።
Show all...
👍 7
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.