307
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
- Subscribers
- Post coverage
- ER - engagement ratio
Data loading in progress...
Subscriber growth rate
Data loading in progress...
እንፀልይ
ሰላም ለሀገራችን ሰላም ለኢትዮጵያ።
ከድህነት አውጣት ከጦርነት ትቢያ።
እባክህ ፈጣሪ መከራዋን ቋጨው።
በዝቷል እያደረ ለሞት የሚታጨው።
ያ የደጉን ዘመን መልስና ካሳት።
ሀገራችን ይብቃት ደዌና ትኩሳት።
የጦሩን ጫፍ ሰብሮ ተራምዶት ይቅርታ።
ሰይጣንም ይዋረድ በፀሎት ይረታ።
እናም እንፀልይ በ አንድነት ቆመን።
የባሪያ ግዳጁ ጌታውን መለመን።
ጌታው ደግሞ ማድረግ ነውና ግዳጁ።
ሰላሙም አማኑም ሁሉም ነገር በእጁ።
እናም ፈጣሪየ
በጦርነት ህዝብ ያልቃል።
ሰው ቀየውን ግድ ይለቃል።
እንስሳውም ይጨነቃል።
እባክህን ፈጣሪየ መከራችን ይበቃል።
ይብቃችሁ በለን በ አንድ ቃል።
የአንተው ቃል ሰውን ከፈጠረ።
ሰማዩንም በከዋክብት ካሳመረ።
መከራ ይብቃሽ በላት ለዚች ዓለም።
ባንተ ቃል ሁሉ ይድናል
ካንተ በላይ ሀይል የለም።
ከሜ
@lebalba
የክብ.....ካብ
"""""""''''''''''''''""
እንጀራችን ክቡ፥
ዕድላችን ክቡ፥
መንገዳችን ክቡ...
በመከበብ ዕጣ፥ዕድል ተለውሶ፤
ከቶ አይደርስም ያሉት
እየተቃበዘ ይመጣል መልሶ...
በል ስራህን መርምር
አላማህን መትር እጆችህን አጥና፤
አርምጃህ ሀቅ ይሁን
ከሰው ጫንቃ ውረድ ውልህ ይሁን ቀና...
ዕቅድህን እየው...
ዕቅድህን እየው
አይምሮህን ቃኘው
በማጥ አትዳክር ህልም አለምህ ጠቦ፤
ህይወት አዙሪት ነው
የግፍ እንባ እንደ እባብ ይመጣል ተስቦ...
ተው
ተው እስቲ እረፍ
ነፍስያህን በእውነት ግረፍ
አትድንም
አትተርፍም
ከህዝብ ዕንባ ከሰው ደም ጦስ፤
ቢታጠብስ መቼ ፀዳ
ከኢየሱስ ደም ያ ጲላጦስ?
አፅዳ...
ፈትግ....
አንፃ ሀሳብህ ህሊናህን ቃኘው፤
ባሰብከው ልክ ነው
የሰማይ ቤት ዕዳህ ፍርድህ የሚዳኘው....
አስብ አለምህን
አስብ ህይወትህን
አስብ እምነትህን
አስብ...
አስብ...
አስብ...
ከመኖርህ ጉድጓድ መልካምነት ሰብስብ...!
ሸፍን ገመናህን
ህሊናህን ገንባ በፍቅር ምሰሶ፤
የክብ ነው ነፍስህ
የሰራኸው ሁሉ ይደርሳል መልሶ!
#አስብ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
@HAKiKA1
Repost from ግጥም 🇪🇹
እኔ እና አንተ
ወደ ጎንህ እንደተኛህ
እኔ እንቅልፍህ
ያንተው አካል
በሴት አምሳል
በመንፈስ
እኔ
ያንተ ፈውስ
ና
አንድ ሁነን እንንፈስ
አንተ
ለኔ ህይወት
ሙሉነት ወንድነት
ከእሳቱ እንሙቅ
ከውሃው እንጥለቅ
ከአየሩ እንምጠቅ
እስከ አፈር እንዝለቅ
አንተ ንፈስ በኔ ነፍስ
እኔ ልንፈስ ባንተ ነፍስ
ና አንድ ሁነን
በረቂቅ ንፋስ
በተዐምር እንንፈስ
Repost from ግጥም 🇪🇹
#ሳዛዝን
አንቺ ጭፍን ሁነሽ እኔ አልታይሽም
ወዳጅ ስለሌለኝ ስለኔ መልካሙን አስሚም
ፍልጋዬን ፍቅሬ እንግዲህ አልተው
በሄድሽበት ሄዳለው
ስትቆሚም ቆማለው
ከሩቅ ያንቺን ጠረን ማሽተት
ማ በነገረሽ ልቤ እንደሚደስት
መክረሜ ነውና ከቤታቹ ደጅ
ፍቀጂልኝና...ማረፊያዬን ላዘጋጅ።
ከ #ዳዊት
በተለያየ ምክንያት ውስጣቹ የተጎዳ ልባቹ የተሰበረ ጭንቀት ፣ ድብርት ፣ ውጥረት ካዛም በላይ ጥልቅ ጨለማ ውስጥ ያላቹ
በሙሉ።
ይህ ቀን ያልፋል አዎ ይህ ቀን ያልፋል ብረት በእሳት ተፈትኖ ነው የሚያልፈው ፤ ይሄ ቀን ውስጣቹ ካለው ጨለማ ድል ነስታቹ ብርሀን የምትሆኑበት ወቅት ነው። እጅ መስጠት መፍትሄው ሽንፈት ነው።
በዚህ ምድር ስንወለድ ስቀን አይደለም የተወለድነው አልቅሰን ነው እንጂ። ሞት ለምንም ነገር መፍትሄ አይሆንም። በጊዜው ሲመጣ ኮርተን እንቀበለዋለን። አሁን ባላቹበት የስሜት ውዥንብርም ሆነ የመንፈስ መቃወስ ብዙሀኑ ተፈትኖበት አልፏል ለናንተ በጣም አስቸጋሪ የመሰላችሁ ይህ ወቅት ለአንዳንዱ ግና የስቃዩ ጅማሬ ነበር።
እናም ይሄ ቀን ያልፋል ሁሉ ለበጎ ነው እለፉበት እንጂ ይዞአቹ እንዳያልፍ።
@rasnflega
💌 #ማ_ይንገርሽ 💌
♡
♡
ብዙ አስብና ማፍቀሬን ልነግርሽ
መኖሬ ላንቺ ነው ወድሻለሁ ልልሽ
ግና ገና ሳይሽ
ያ ሁሉ ስቃየን አይደለም ልናገር
ላንቺ የሆንኩትን እንኳን ልመሰክር
ጉልበቴም ይዝላል 😥
አካሌም ይደክማል
ልሳኔም ይዘጋል 😐
ልቤም ያው ይፈራል💓
ታዲያ የኔ ፍቅር
የልቤን ፍላጎት አፌ ካላወራው
ፍቅርሽን መራቤን ልቤ ካላወጣው
ገና ሳይሽ አንቺን ጉልበቴ ከዛለ
አካል እስትንፋሴ ባንቺ ከተከለለ
ማን ይንገርሽ እና እንዴትስ ታቂያለሽ
እስከ ሞቴ ድረስ እኔ እንደምወድሽ🙍♂❤️
┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️
😘😍@Yenefekir😘😍
💝@Yenefekir💝
ል.ዕ.ል.ት
ል▪ ቤ ይመታል አንቺን ሲያይ ይስታል
መንገዱን
እ▪ ውነት ፍቅር ብሎ ይታይሽ ላንቺ
መሸነፉን
ል▪ ሸነፍ ላንቺ ልረታ ዘውትር
ለማስብሽ ሁሌም ለማልምሽ
ት▪ ርጉም አልባ አይደለም በፍጹም
ፍቅር ነው ልቤ የወደደሽ
Abrsh🌈
17 -09-2014
ክፍል 2
@lebalba
Choose a Different Plan
Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.