cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ETHIO-MEREJA®

Addisababa, Ethiopia🇪🇹 News & Media Company® . USA : Washington . . . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot

Show more
Advertising posts
128 214
Subscribers
-624 hours
+497 days
-87530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

05:33
Video unavailableShow in Telegram
''ገንዘቡን ንቄ አይደለም፣ እኔም የደሀ ቤተሰብ ነኝ....ቅር ያሰኘኝ እውቅና አሰጣጡ ነበር !'' - አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ዛሬ በማሪዮት ሆቴል የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሽልማት ስነስርዓት ላይ ንግግር አድርገዋል። ባለፈው መንግስት ሽልማት ባበረከተበት ወቅት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ይቅርታ በመጠየቅ ገንዘቡን አይመጥነኝም በማለት መልሰው መነጋገሪያ ሆነው በበነጋታው ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል ። አሰልጣኙ ዛሬ እንደተናገሩት በኦሎምፒኩ አትሌቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ከውድድሩ በፊት ወደ ፓሪስ በማቅናት በግል ወጪ የውድድር ኮርሱ (መርጫ ስፍራ) መመልከታቸውን ይፋ አድርገዋል ። በወቅቱ ከልፋታቸው አንፃር የተበረከተላቸው ብር ቅር አሰኝቷቸው እንደነበር አስታውሰው መጠኑ ብር ሜዳልያ ላመጡበት ቢሆን አግባብ ነው ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመዋል ። እነሆ ሙሉ የቪዲዮ ንግግራቸው
Show all...
21.80 MB
😁 33👍 24 4👎 2
የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የኦሎምፒክ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴን አገደ መስከረም 8 2017 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 333122 የዋለው ችሎት በይግባኝ ባዮች በእነ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ (4 ሰዎች) እና መልስ ሰጪ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (5 ሰዎች) ጉዳይ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ባዮች በዋናነት ያነሱት - ግንቦት 5 2016 እና ሰኔ 4 2016 የተከናወኑ ህገወጥ የጠቅላላ ጉባኤ እና የስራ አስፈፃሚ ምርጫ እንዲታገድ - የህዝብ እና የሀገር ሀብት እንዳይባክን ከደመወዝ ክፍያ ውጪ የባንክ አካውንት እንዲታገድ ጠይቀዋል የይግባኝ መነሻቸውን ፍርድ ቤቱ የመረመረ ሲሆን አመልካቾችና ጠበቆች በሰጡት ምልሽ በዋናነት ህግና ስርዓት ተከብሮ ተቋሙን የመታደግ አላማና ወደነበረበት ከፍታ ለመመለስ ከመሻት የመነጨ ፍላጎት እና ቁጭት እንጂ የጥቅምም ሆነ የስልጣን ፍላጎት እንደሌላቸው ለፍርድ ቤት አስረድተዋል፡፡ ከስራ አስፈፃሚዎች ነውጠኝነትና ለስርዓትና ለህግ ያለመገዛት አዝማሚያ በስራ ማስኬጃ ሰበብ ብክነት እንዳይኖር እንዲሁም በሪፎርም በሚል ምክንያት የታቀዱ ብክነቶች ስለመኖራቸው መረጃ ስላለን ፍርድ ቤቱ አካውንቱን እንዲያግድ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ ትእዛዝ ለባንኮችና ለዋና መስሪያ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ ሌላኛው ትእዛዝ ለኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በቀን 04/10/2016 ዓ.ም የተደረገው ምርጫ የታገደ መሆኑን እንዲያውቁና እግዱን እንዲፈፅሙም ታዟል፡፡ የመልስ ሰጪዎችን ምላሽ ለመስማት ለመስከረም20 ፍርድቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
Show all...
👍 63 3🤯 2
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በፓሪስ ኦሎምፒክ ሜዳልያ ላመጡ አትሌቶች ሽልማት አበረከተ ። በማሪዮት ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የሽልማት ስነስርዓት በኦሎምፒክ ሪከርድ በመስበር ወርቅ ያመጣው አትሌት ታምራት ቶላ 2 ሚሊዮን ብር ተሸልሟል። በማራቶን ብር ላስገኘችው ትዕግስት አሰፋ ፣ በ800 ፅጌ ድጉማ እና በ10ሺ ብር ላመጣው በሪሁ አረጋዊ የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ለአሰልጣኞችም ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ለሁለቱ የማራቶን አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ 1.8 ሚሊዮን ብር ተበርክቶላቸዋል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና አትሌት ለሜቻ ግርማ ልዩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ዛሬ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የባንክ አካውንት በድጋሚ እንዲታገድ ውሳኔ መተላለፏ ይታወቃል ።
Show all...
👍 27😁 6 5
00:18
Video unavailableShow in Telegram
🏃‍♂️🏃🏃‍♂️በመሃል ፒያሳ ሊሴገብረማርያም ት / ቤት ዘመናዊ ቤት ከ ቴመር ፕሮፐርቲ 👉ስቱዲዮ .....48 and 46 ባለ አንድ መኝታ.....66...64....71...75 ባለ ሁለት መኝታ.....75....78...71....99...92...91 ባለ ሶስት .....111....106 🏠 ተጨማሪ የንግድ ሱቅ ፒያሳ አድዋ ሙዝየም ፊትለፊት በሚኒሊክ አደባባይ ከ12 ካሬ እስከ 22 ካሬ ለወርቅቤት #ቡቲክ #ፋርማሲ #office .....የሚውሉ 💴 483,000 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ!!! ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.me/+33kkNORhQ_JmMDlk ለበለጠ መረጃ ይደውሉ ፡ ☎️0904657777/0902597777 ያግኙን
Show all...
files/Last.mp41.36 MB
👍 11
Call 📞
Join Us
Save Ad
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት ***************************** የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ ሽልማቱ የተበረከተው ኮርፖሬሽኑ 35ኛ ዓመቱን ባከበረበት መርሐ-ግብር ላይ ሲሆን አየር መንገዱ ላበረከተው የላቀ አገልግሎት እና የላቀ የስራ አጋርነት ዕውቅና የተሰጠበት መሆኑ ተገልጿል፡፡ ይህ ሽልማት ለዛምቢያ ኤርፖርት ዕድገት በመንገደኛ እና በዕቃ ጭነት አገልግሎት ዘርፎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያበረከተው አስተዋፅዖ እና ያልተቋረጠ ድጋፍ ማሳያ መሆኑም ተመላክቷል።
Show all...
👍 37👎 6 4👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
🔔ዋጋ Price ➤ 94,900ብር  🔅የ 2 አመት የጽሑፍ ዋስትና እና 🔅ከ 20+ አመት በላይ ልምድ ሞዴል Model  M123 ለዋጋ መረጃና ሌሎች ምርቶቻችን የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👇 👇 👇 t.me/AlphaFurniture 📍 አድራሻችን 1️⃣ 🏠  በቅሎ ቤት ግሎባል ፊት ለፊት               አልፋ ሕንፃ              Beklo Bet • Infront of Global              Alpha Building   ☎ 0911 445604 / 0979 420042         ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 2️⃣  🏠 ጉርድሾላ ቴሌ ፊት ለፊት              Gurdshola • Infront of Tele   ☎  0979 426642 / 0944 555511 ስለ ዳሸን ባንክ ዱቤ አለ በማንኛውም ዳሸን ባንክ ይጠይቁ ተጠቃሚ ይሁኑ https://dashenbanksc.com/dube-ale/
Show all...
👍 11😁 5 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
አዲሱ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ አተገባበርን በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ! ከመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ ለቀጣይ 4 ዓመታት በየሶስት ወር ተከፋፍሎ በ16 ጊዜ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይታወቃል፡፡ ይህም አነስተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን የሚጠቀሙ ደንበኞችን እንዳይጎዳ፣ አሁናዊ የኑሮ ደረጃን ያገናዘበና ድጎማን መሰረት ያደረገ ማስተካከያ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ የታሪፍ ማስተካከያ የመኖሪያ ቤት፣ ንግድ ተቋማት፣ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ፣ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራት ተጠቃሚ ደንበኞች በሚል የተከፋፈለ ነው፡፡ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚዎችን በተመለከተ ሰባት እርከኖች ያሉት ሲሆን፤ እንደ አጠቃቀማቸው መሰረት ያደረገ ድጎማ ተደርጎበታል፡፡ በዚህም ከ0 እስከ 200 ኪሎዋት ሰዓት የሚጠቀሙ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች የድጎማው ተጠቃሚ ናቸው፡፡ ለአብነት በአገራችን ካሉ የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎች ውስጥ 75 በመቶ የሚደርሱት ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውሉ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ካሉት አጠቃላይ ደንበኞች ደግሞ ግማሽ የሚሆኑት በወር 50 ኪሎዋት ሰዓት እና ከዚያ በታች የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ እንደ አጠቃቀም ደረጃ ካየነው በወር እስከ 100 ኪሎዋት ሰዓት የሚጠቀመው ደግሞ ቁጥሩ 65 በመቶ ድርሻ አለው፡፡ ከፍ አድርገን  እስከ 200 ኪሎዋት ሰዓት በወር ኤሌክትሪክ የሚጠቀመውን ብንመለከት ከአጠቃላይ የተቋሙ ደንበኛ እስከ 80 በመቶ ይደርሳል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Show all...
👍 66 12😭 9
Photo unavailableShow in Telegram
በትናንቱ የጎንደር ዉግያ በትንሹ አምስት ሰዎች መገደላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ ። ነዋሪዎቹ እንዳሉት ትናንት በመንግስት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በዉጊያ ስትናጥ የዋለችው ከተማዋ ዛሬ አንጻራዊ መረጋጋት ቢታይባትም ማህበራዊ እንቅስቃሴው እንደተስተጓጎለ ነው። የከተማዋ አስተዳደር ግን ሁሉም እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን ነው ያስታወቀው። ዛሬ ያነጋገርናቸው አንድ የከተማዋ ነዋሪ እንዳሉት ትናንት ማክሰኞ አዘዞ ተክለኃይማኖት አካባቢ ሲደረግ በነበረ ውጊያ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን እና ሁለት ሰዎች የት እንደደረሱ እንደማያዉቁ ነው። በከተማዋ ቡልኮ በተባለ አካባቢ በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የሁለት ህጻናት ሕይወት ማለፉን ደግሞ ሌላ የከተማዋ ነዋሪ ተናግረዋል። ከትናንት በስቲያ ሰኞ እና ትናንት ማክሰኞ በከተማዋ በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ ዉጊያ መደረጉን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ ላቀው ከትናንቱ ውጊያ በኋላ ዛሬ በከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ መቀጠሉን ገልጸዋል።
Show all...
👍 40😭 9 4😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው እና በላይ ማናዬ ከሀገር ተሰደዱ ከሶስት ወራት በፊት ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው እና በላይ ማናዬ፤ ሀገራቸውን ለቅቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ሁለቱ ጋዜጠኞቹ የተሰደዱት፤ በመንግስት የጸጥታ አባላት በተሰጣቸው “ለህይወታቸው የሚያሰጋ” “ማስጠንቀቂያ” እና ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሚደረግባቸው “ክትትል” ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል። ጋዜጠኛ በላይ እና በቃሉ 11 ቀናት የፈጀ “አስቸጋሪ ጉዞ” በማድረግ ከሀገር የወጡት፤ ባለፈው ሳምንት ሰኞ ጳጉሜ 4፤ 2016 መሆኑን አስረድተዋል። ሆኖም ጋዜጠኞቹ በአሁኑ ወቅት ያሉበትን ሀገር፤ “ከደህንነት ስጋት” ጋር በተያያዘ ከመግለጽ ተቆጥበዋል። ሁለቱ ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገው የነበረው፤ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ባበቃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ነበር። በአማራ ክልል እና እንዳስፈላጊነቱ ደግሞ “በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ” ተፈጻሚነት የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የተላለፈው ሐምሌ 28፤ 2015 ነበር። “አልፋ ሚዲያ” የተሰኘው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን መስራች እና አዘጋጅ የሆነው በቃሉ፤ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አንድ ቀን በኋላ በቁጥጥር ስር ውሏል። ጋዜጠኛው በዚያው ዓመት ነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ ወደ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ተወስዶ ለዘጠኝ ወራት በእስር ላይ ቆይቷል። እንደ በቃሉ ሁሉ በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስሮ የነበረው ጋዜጠኛ በላይ፤ “በየቀኑ በህይወት የመቆየት እና ያለመቆየት እድላችን ሁልጊዜ ጠባብ እንደሆነ እያሰብን ነው ያን ሁሉ ጊዜ የቆየነው” ሲል ይገልጻል።
Show all...
👍 67😢 10 5🤯 3👎 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.