cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሁሌ መረጃ.com/hule merja

የሰው ልጅ መረጃ የማግኘት መብቱ መገደብ የለበትም...እኛም ይህንን ፍላጎት ለመሙላት እዚ አለን፡፡ሁሌ መረጃ ሁሌ እውነት

Show more
Advertising posts
690
Subscribers
+224 hours
+27 days
-1230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንድ እናት በ42 ዓመት ዕድሜያቸው አራት ህፃናትን በሰላም ተገላገሉ። ወይዘሮ አደባባይ የሺነህ 42 ዓመት ዕድሜያቸው በፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል አራት ህፃናትን በሠላም ተገላግለዋል። ሶስት ወንድና አንድ ሴት በድምሩ አራት ህፃናትን በሰላም የተገላገሉት እናት የአሁኑን ጨምሮ ለስድስተኛ ጊዜ ነው የወለዱት። የተወለዱት አራት ህፃናትም በአሁኑ ሰዓት ሰባት ወራት ጊዜያቸው ሳይደርስ የተወለዱ ስለሆነ በህፃናት ፅኑ ህሙማን ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ ተበልሏል። በአሁኑ ስዓት በሙሉ ጤንነት እንደሚገኙ የገለጹት ወላጅ እናት በሰላም እንድትገላገል ለረዷት ለሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎችና የፓዊ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ላደረጉላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዘገባው የፓዊ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።
Show all...
በሊባኖስ በቀናት ልዩነት ለሁለተኛ ጊዜ በደረሰ የኮሙኒኬሽን መሳሪያ ፍንዳታ 20 ሰዎች ሲገደሉ 450 ያህሉ ቆሰሉ በሊባኖስ ውስጥ በገመድ አልባ የመገናኛ መሳሪያዎች በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 20 ሰዎች ሲገደሉ ከ450 በላይ ቆስለዋል ሲል የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በዋና ከተማይቱ ቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻዎች፣በካአ ሸለቆ እና በደቡባዊ ሊባኖስ እንደ ምሽግ በሚታዩ አካባቢዎች ታጣቂው ቡድን ሂዝቦላ የሚጠቀምባቸው የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች ላይ ፍንዳታው ደርሷል። ፍንዳታው የተከሰተው ማክሰኞ የሂዝቦላህ አባላት ላይ ፔጀርስ ፈንድተው የተገደሉ 12 ሰዎች በቀብር ስነ-ስርዓት ወቅት ነው። ለዚያ ጥቃት ሂዝቦላህ እስራኤልን ተጠያቂ አድርጓል። እስራኤል በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም። ጥቃቶቹ የደረሱት የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት “በጦርነቱ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ” መጀመሩን ካስታውቁ እና የእስራኤል ጦር ክፍል ወደ ሰሜናዊ ክፍል እንዲሰማራ ትዕዛዝ ከሰጡ በኃላ ነው። የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ በሊባኖስ ቡድን ሂዝቦላህ ትእዛዝ ማስተላለፊያ የኮሙኒኬሽን መስመር ላይ በታይዋን የተሰሩ 5 ሺ ፔጃሮች ውስጥ አነስተኛ መጠን ያለው ፈንጂ በመትከል  የማክሰኞው ፍንዳታ እንዲሳካ ማድረጉን የሊባኖስ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ ገልጿል። ይህ ሴራ ብዙ ወራትን ያስቆጠረ ነው። ጥቃቱ በሂዝቦላህ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን በሊባኖስ የሚገኙ ሆስፒታሎችን እንዲጨናነቅ አድርጓል ። አንዳንድ ተጎጂዎች ለዓይነ ስውርነት ሲዳረጉ ሌሎች ደግሞ የሰውነት አካል መቆረጥ ያስፈልጋቸዋል ።በሊባኖስ እና በሶሪያ ከተከሰቱት ገዳይ ፍንዳታዎች ጋር የተገናኘው የታይዋኑ ፔጀርስ አምራች ጎልድ አፖሎ ፔጀሮቹ የተሰሩትየጀሮ ማ በአውሮፓውያን ባሲ ድርጅት ነው ብሏል። የታይዋኑ ኩባንያ ፔጀሮቹ በሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ላይ መቀመጫውን ላደረገው ባሲ ምርቱን እንዲሰራ ፍቃድ ሰጥቶታል። ፔጀር የሬዲዮ ዌቭ የሚጠቀም የመገናኛ ዘዴ ነው። ሰዎች መረጃ ሲልኩ የሚተላለፈውም የሬዲዮ ፍሪክዌንሲ በመጠቀም ነው። መልዕክት የተላከለት ሰው መልዕክቱ እንደደረሰው በንዝረት መልዕክት መስጠት የሚችል ሲሆን አጭር የጽሑፍ ወይም የድምፅ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ይችላል።እ.አ.አ 1980ዎቹ እንዲሁም 90ዎቹ በስፋት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ የግንኙነት መሳሪያ አሁን ላይ በሞባይል ስልክ ቢተካም አሁንም ድረስ በተለያዩ ቦታዎች ጥቅም ላይ ይውላል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
ወልዲያ <<ወረርሽኙ በፍጥነት በመዛመቱ 85 ሰዎች ታመው በሦስት ጤና ተቋማት ሕክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ከታማሚዎቹ መካከል 11 ያህሉ በፅኑ መታከሚያ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። እስከ ትናንት ማክሰኞ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።የኮሌራ በሸታው ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም. በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ክፍለ ከተማ አድማስ ባሻገር ተክለ ሃይማኖት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የተከሰተው።በሚመለከተው አካል ርብርብ ካልተደረገ ውጤቱ ጥሩ አይሆንም፡፡>> የወልዲያ ከተማ ጤና መምርያ ሜዲካል ኦፊሰር ሲስተር ዘሬ በቀለ ለሪፖርተር ከተናገሩት የተወሰደ
Show all...
<<“በሶማሊሌ ክልል አንድ ዞን የሼሪዓ መንግስት ተመሰረተ” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚነገው ሀሠት ነው" የክልሉ መንግስት የሶማሊ ክልል መንግስት ባወጣው መግለጫ "የሼሪዓ መንግስት ተመሰረተ”በሚል የሚነዛው ሀሠት ነው ብሏል። በትላንትናው ዕለትም የሀገር ሽማግሌዎች፣ ገራዶች፣ ሱልጣኖች በጋራ ስብሰባ በማካሄድ በሶስት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ይሄ ውይይታቸውን ባልተገባ መልኩ መግለፅ ለእነሱ ክብር አለመስጠት ነው ያለው ክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ገራዶች፣ ሱልጣኖች ውይይታቸው ሶስት ዋና ነጥቦች ናቸው፡- 👉1.የኒካህ (ጋብቻ) ጥሎሽ መቀነስን በተመለከተ፤ ልጆቻችን ለጥሎሽ የሚጠየቁት ዋጋ ከፍተኛ መሆን ወዳልተገባና አላህ ወደ ማይወደው የዝሙት ሊያመራ ስለሚችል ለኒካህ(ጋብቻ) የሚሰጥ ክፍያን መወሰን፤ 👉2.የሰው ህይወት በድንገተኛ ሁኔታ ( በመኪና አደጋና በመሳሰሉት) ያጠፋ ሰው ለቀብር ተብሎ የሚጠየቀው ክፍያን በተመለከተ ገደብ ማስቀመጥ፤ 👉3.በጎሳዎች መካካል በሚፈጠሩ ግጭቶች የሚከሰቱ ጉዳቶች የካሳ አከፋፋል ምን መሆን አለበት በሚሉ ነጥቦች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን አሳልፈዋል፡፡ ነገር ግን ይህን እውነታ ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ ጦርነት፣ እልቂት፣ ድርቅና ችግር መርዶ እንጂ የሰላም ዜና የሚያሳምማቸው አንዳንድ ትላንትን ናፋቂ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያዎች “በሶማሊ ክልል አንድ ዞን በሼሪአ እንዲተዳደር ተደረገ” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ ለመመልከት ተችሏል፡፡ይሄ ሀሠተኛ ስም የማጥፋት መረጃ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን ሲል የሶማሊ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ መግለጫውን አጋርቷል።
Show all...
ስለ አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፆች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ የተሳሳተ ነው ከመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በኪሎ ዋት እስከ * 95 ብር ድረስ ጭማሪ ሊደረግበት ነው በሚል በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንና በማህበራዊ የትስስር ገፆች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ የተሳሳተ ነው፡፡ ተቋሙ በታሪፍ ማሻሻያው ደንበኞች ለኑሮ ጫና እንዳይጋለጡ፣ የገበያ ዋጋ እንዳይንር፣ ታሪፉን በየሩብ ዓመቱ ሸንሽኖ ተግባራዊ ከማድረጉም ባሻገር ከ0 እስከ 200 ኪዋት/ሰ የሚጠቀሙ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚዎ ድጎማ ተደርጓል፡፡ በዚህም ከ0 እስከ 200 ኪዋት/ሰ የሚጠቀሙ ደንበኞች የድጎማው ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን፤ ድጎማውም የመጨረሻው የትግበራ ዓመት ድረስ ይቀጥላል፡፡ 1. ከ50 ኪዋት/ሰ በታች ለሚጠቀሙ ደንበኞች 75 በመቶ ይደጎማሉ፣ 2. ከ50 ኪዋት/ሰ እስከ 100 ኪዋት/ሰ ለሚጠቀሙ ደንበኞች 40 በመቶ ይደጎማሉ፣ 3. ከ200 ኪዋት/ሰ እስከ 300 ኪዋት/ሰ ለሚጠቀሙ ደንበኞች 4 በመቶ ይደጎማሉ፣ 4. ከ400 ኪዋት/ሰ እስከ 500 ኪዋት/ሰ የሚሆነውን ማሻሻያውን ያለምንም ድጎማ የሚከፍሉ ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ በወር 50 ኪዋሰ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሆነ አንድ ደንበኛ ቀድሞ በነበረው ታሪፍ በአንድ ወር ውስጥ * 24 ብር ብቻ ይከፍል ነበር፡፡ አዲሱ ታሪፍ በሚጀምርበት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 1. የአንድ ወር ክፍያው 28 ብር 2. በ2ኛው ሩብ ዓመት የአንድ ወር ክፍያው 32 ብር 3. በ3ኛው ሩብ ዓመት የአንድ ወር ክፍያው 37 ብር 4. በ4ኛው ሩብ ዓመት 41 ብር ይከፍላል፡፡ Via የኢትዮጵያኤሌክትሪክ አገልግሎት
Show all...
ፍርድ ቤቱ እነ ዮሀንስ ዳንኤል የጠየቁትን የዋስትና መብት ከለከለ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ የግዜ ቀጠሮ የወንጀል ችሎት እነ ዮሀንስ ዳንኤል የጠየቁትን የዋስትና መብት ከልክሏል። ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት ጠይቀው የነበረ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም በዛሬው ችሎት የዋስትና መብቱን ከልክሏል። ችሎቱ የክስ መዝገቡን ለመመልከት ለጥቅምት 4 ቀን 2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡ የፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ ዳንኤል ዮሐንስን ጨምሮ በስድስት ግለሰቦች ላይ ሶስት ክሶችን መመስረቱ ይታወሳል፡፡
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.