cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከፍቅር ደጅ 💕💞

@ke_feker_deje_©በዚ group: ~#የተለያዩ የህይወት ገጠመኝ እና ታሪኮች፤ ~#የፍቅር ግጥሞችና ደብዳቤዎች፤ ~#የታዋቂ ሰዎች ምርጥ ንግግርና ፍልስፍና፤ ~#የፍቅር ገጠመኞች ~ #ሀገርኛ ጉዳዮች፤ ~ #ስለ ጤና እና ቴክኖሎጂ መረጃ፤ ~#በ ሃገርኛ እና ኢንተርናሽናል ቋንቋዎች፤ ~Amharic,English, Afan Oromo,Tigregna

Show more
Advertising posts
585
Subscribers
-124 hours
-37 days
-730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

❤👁በ'ነሱ ቤት👁❤ 🍃🍄ክፍልሰላሣ ሠባት🍄🍃 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 ሆስፒታል ሲደርሱ አስተናጋጁ ሰሚር ነበር የተቀበላቸው ፣እናም በፍጥነት ያለችበትን ክፍል ጠየቁት እሱም አብላካት የተኛችበትን ክፍል ካሳያቸው በዋላ እውስጥ ሰው ስላለ ትንሽ መጠበቅ እንዳለባቸው ሊያስረዳቸው ሞከረ ። ጌታነህ ማነው ሰው ብሎ ቆጣ አለበት ፣ሰሚር ሲፈራ ሲቸር  ነገረው "አይ ሰመረ ነው ማለት..." "ሰመረ "አለው እና ዝም አለ ። የአብላካት እናት መሳይ "ማነው ሰመረ ?"ብላ ጠየቀች "ከዚ በፊት እኮ ስለሱ ነግራሽ ታውቃለች ያ መንገድ ላይ አግኝቷት የረዳት ኧረ እንደውም እኮ የጌታነህም ጓደኛ ነው "አለ አስተናጋጁ ሰሚር ጭንቅ እያለው ።የጌታነህ ቤተሰቦች እርስ በእርስ ተያይተው ።"ሰመረ የኛ እንዴ እሱም ያውቃል "አሉ ። አስተናጋጁ ሰሚር አንገቱን ነቅንቆ አዎ የሚል ምልክት አሳያቸው። "እና መግባት አንችልም ነው እሱ ካልወጣ "በማለት ጌታነህ እየተመናቀረ ሄዶ አብላካት የተኛችበትን ክፍል አንኳኳ! ከውስጥ ሰመረ የአብላካትን እጅ በእጁ አቆላልፎ አይኖቹ ዕንባ እንዳዘሉ በቀስታ የምታወራውን ያዳምጣል ፣አብላካት ለራሷ የመጨረሻዬ ነው ብላ ስላሰበች ለሰመረ የሚሰማትን ስሜት ሳትደብቅ ነበር እየነገረችው ያለችው ፣ሰመረ አንዳች ነገር ሳይናገር እጇን እያሻሸ ግንባሯን እየነካካ ያዳምጣታል እናም ደሞ ዕንባው አምልጦት ከፊቷ አልቅሶ ደክሞ እንዳያደክማት እየተጠነቀቀ ነው ።ግን አልችል ብሏል የአብላካት ለሱ ያላት ስሜት ትልቅ መሆኑን ሲያውቅ ልቡ መረበሹን አበዛበት እናም ጎንበስ ብሎ ግንባሯን ሳም ካደረጋት በዋላ"ሚጣ ተይ እሺ እንዳበቃለት ሰው አታውሪ ምንም አትሆኚም "አላት "ግንኮ ዛሬ አብቅቶልኝ ነበር ነገም ምን ሊፈጠር እንደሚችል አላውቅም ፣ለዚነው እንዲ በፍጥነት ላንተ ያለኝን ስሜት የምነግርህ ፣ጤነኛ ብሆን ኖሮ መቼም የምነግርህ ነገር አልነበረም ፣እንዲሁ ፍቅሬን ይዤው ነበር የምኖረው ፣ አሁንግን ሁሉንም ይዤው ከምሞት ብነግርህ ይሻላል ፣በርግጥ ዛሬ አንተ ባትመጣ አልናገረውም ነበር ግን መጣህ እድሜ ለሰሚር ፣እሱን በጣም ነው የማመሰግነው እኔ አይሆንም ያልኩትን ነገር ሁሉ ቢያደርግም ፣ግን ውጤቱ ክፋት የለውም ፣አንተን በመጥራቱ ሁሉም ነገር ቀሎኛል "አለችው እና ተነፈሰች "የኔ ሚጢጢ"አላት "አብላካት ነው ስሜ "ብላ ፈገግ አለች ጠጋ ብሎ ጉንጯን ሳም አድርጓት ሲመለስ በሩ ተንኳኩቶ ምላሽ ሳይጠብቅ ተከፈተ ። እናም ጌታነህ ገብቶ ሲያፈጥ ሁለቱም እርስ በእርስ ተያዩ ፣አብላካት ተገረመች እና ደሞ የሰሚር ስራ ነው ሁሉንም ሰበሰበ እሺ ይሁን እኔን ለማዳን ካለው ጉጉት የተነሳ ነው ደሞም እናቴ ልታገኘው ሄዳ አልነበር እንግዲ መፍትሄ አገኘው ብሎ ሊያደርቀኝ ይሆናል ።ብላ አሰበች ጌታነህ እራሱን ተቆጣጥሮ ሰመረን ሰላም ካለው በዋላ እሷን ጎንበስ ብሎ አይን አይኗን ሲያይ ቆይቶ "አይዞሽ ሁሉም ነገር በቅርቡ ያበቃል ደና ትሆኛለሽ እሺ እርዳታ ሊያደርጉልሽ ፍቃደኛ የሆኑት ቤተሰቦቼም አብረውኝ እዚ መጥተዋል አንቺ ብቻ በርቺ እሺ"አላት እና ፀጉሯን ደባበሳት ፣አንገቷን ነቀነቀች በመስማማት ሰመረ በመገረም ሲያየው  ግድ ሳይሰጠው ። "እባክህ ቤተሰቦቼ እና የአብላካት እናት ቆመዋል አስገባቸው "አለው "ከልብህ ነው እነሱ ሊረዷት ይፈልጋሉ ሙሉ ወጪ ችለው "አለው "እሱን በደንብ እናወራበታለን ከነምክንያቱ አሁን ተጨንቀዋል አስገባቸው "አለው ።ግራ የተጋባው ሰመረ ወጣ ብሎ እነሱን አሰገባቸው ለሰላምታ እንኳ ጊዜ ሳይሰጡት ተቻኩለው ወደውስጥ ገቡ ፣እናት ስፍስፍ ብላ ከአልጋው አጠገብ በርከክ ብላ አብላካት ላይ ተደፋች ፣መስፍን ለመጀመሪያጊዜ የካዳት ልጁን ሲያያት ልቡ በፀፀት ዘለለበት የጌታነህ ወላጆች በቁንጅናዋ ለየት ያለችው የልጅልጃቸው አንሰፈሰፈቻቸው ። አብላካት ግራ እንደገባት ነው ሁሉንም በተራ ተራ እያየቻቸው ነበር ፣በተለይ በሩን ተደግፎ ዕንባውን ኮለል እያደረገ የሚያወርደውን ጎልማሳ አይታ አይኗን መንቀል አቃታት,,,,,,, ይቀጥላል......     ሰላም እና ፍቅር ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንግዜም ከዘመንህ አይለይ🙏 @natani273 ይቀጥላል......     ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️ ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
Show all...
👁በ'ነሱ ቤት👁 🍄ክፍል🍄🍄 ❤ሠላሳ ሥድስት❤ 🌻🍃🌻🍃🌻🍃 በነ ጌታነህ ቤት ሰላም የወረደ ይመስላል ፣ ቤተሰቡ ከእንግዳዋ መሳይ ጋር የተረጋጋ ወሬ ይዘዋል ፣ በመሃል በመሃል መሳይ ላይ ቅሬታ ቢታይም ። ግንኙነታቸውን ጤናማ ለማድረግ የበኩላቸውን እየጣሩ ነው የሚገኙት ። ጌታነህ በመሃል ሆኖ ሁለቱንም ወገን ለማስማማት መልካም አሳብ ሲያጋራ ነው የቆየው  በዚ ደሞ ውጤታማ ሆኗል ። በተለይ መስፍን እና መሳይ ሲተያዩ ሊፈጠር የነበረውን የሰላም መደፍረስ እንዲቀር አድርጓል ።  በዚም እናቱ ኮርታበታለች ። ያለውን ቁርሾ ሁሉ ትተው የታዳጊዋን ሕይወት ማትረፉላይ ማተኮር እንዳለባቸው ተመካከሩ እናም ።መሳይ ሁሉን ትታ ስለልጇ ተሸንፋ ተስማማች ፣ ለመጀመሪያ ጊዜም ለልጇ መመኪያ የሚሆናት ግዙፍ ቤተሰብ እንዳላት አስባ ስለልጇ ተፅናናች ። በመጨረሻም ወደቤቷ ለመሄድ ተነሳች ፣ መስፍን ፈጠን ብሎ ሊሸኛት ተነሳ እሷ አያስፈልግም አለች ፣አስራ ስምንት አመታቶችን በሱ ምክንያት አፈር በልታለች ምን እንደሰራት በአጭር ጊዜ ለዛውም በሰአታት ምንም እንዳልተፈጠረ መርሳት አልችል አለች ። ጌታነህ ነገሩ ስለገባው ፣ጠጋብሎ 'መስፍን ተረጋጋ እንዲ በፍጥነት አይሆንም ። ጌዜ ያስፈልጋታል ባንተ የተነሳ ምን እንዳሳለፈች አታውቅም 'አለውና እኔ እሸኛታለው ፣ አብላካትንም በዛው አያታለው ከዶክተሯ ጋርም ስላለው ነገር እነጋገራለው ። እናም በአፋጣኝ ወደውጪ ሄዳ እንድትታከም እናደርጋለን እናንተም ተዘጋጁ አላቸው። የጌታነህ ወላጆች በአንድ ቃል ሁሉንም ነገር ተዘጋጅተናል ጊዜ የለም ልጃችን በሕይወት እንድትቆይ ማድረግ ያለብንን ሁሉ እናደርጋለን ። መስፍን በመሃል ጣልቃ ገብቶ 'እኔ ኩላሊት ልሰጣት ዝግጁ ነኝ እንኳን አንዱን ሁለቱንም ሰጥቻት ብሞት አይቆጨኝም ፣ ልጄን እንደገደልኩ የማነሳትም እኔነኝ እላለው እባካቹ ይህን ማድረግ አትከልክሉኝ 'ብሎ ለመነ ሁሉም በዝምታ አለፉት ። መሳይ ያ ኩሩና ትህቢተኛው የሀብታም ልጅ መስፍን አልመስል አላት ።ወይ ጊዜ ስንት ነገር ይቀይራል ብላ ተገረመች ። በዚ መሃል ስልኳ ጮኾ አነሳችው በፍርሃት ፣ስልኩ ላይ ሰሚር አብላካት ሆስፒታል መግባቷን ሲነግራት ስልኩን በቁሟ ለቀቀችው ሁሉም ደነገጡ ። ጌታነህ በፍርሃት የወደቀውን ስልክ ሲያነሳው የሰሚር ድምፅ መጣ "ሃሉ ምንድነው "አለው ጌታነህ "ሃሉ ኧረ ደና ነች እኮ አሁን"አለው "ሰሚር ነህ ምን ተፈጠረ" "አይ ድንገት እራሷን ስታብኝ አኪም ቤት ወስደናት ነበር እክምና ተደርጎላት አሁን ደና ነች" "ጥሩ መጣን በቃ"አለው "እሺ አብሮኝ ሰመረ አለ ጓደኛህ "አለ ሰሚር ድንገት ሲገናኙ ቅሬታ እንዳይፈጥር በማሰብ "ምን ከየት አወቀ የት አገኘህ ለሱ ደውለህ ነው እንዴ "አለው ግራ በመጋባት "አይ ልክ እንደ እናንተ ሳገኘው ስለሷ ነግሬው ነበር ባጋጣሚ ሊረዳት ሲመጣ ታማ አገኛት እና አብረን ነው አኪም ቤት ይዘናት የሄድነው ።እሱ መኪና ይዞ ባይመጣ ነገሩ ሌላ ነበር "አለው እንዳይቆጣው እየፈራ "አንተ ግን እሱ ጋር ማስቸገር አልነበረብህም እኔ እንደምጨርሰው ነግሬህ ነበር ።እሺ ይሁን መጣን"አለውና ስልኩን ዘጋው ።አፋቸውን ከፍተው ሲሰሙት የነበሩት ቤተሰቦቹ ሰላም መሆኑን ሲነግራቸው እፎይ አሉ ከዛም አንድላይ ለመሄድ ተነሱ ።,,,,,,,,,,,,,,, ይቀጥላል......     ሰላም እና ፍቅር ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንግዜም ከዘመንህ አይለይ🙏 @natani273 ይቀጥላል......     ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
Show all...
🍄በ'ነሱ ቤት🍄 👁ክፍል ሠላሳ አምስት👁 🌻❤🌻❤🌻❤🌻❤ አስተናጋጁ ሰሚር አብላካትን ታቅፎ ይዟት ከቤት ወጣ በፍርሃት ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ አካባቢውን ወዲወዲያ አየ ። የነአብላካት ጎረቤቶች ያለወትሮ ቤታቸው ተከተዋል  አይኖቹን አሻግሮ ሲያይ የሰፈር ጎረምሶች ተቀምጠው ሲጫወቱ አየ እናም ጮክ ብሎ "እባካቹ እርዱኝ እባካቹ "አለ  ጎረምሶቹ ተሯሯጡ "ምንድነው፣ ምን ሆነች ?አብላካት ነች ?ምን ተፈጥሮ ነው ?ኧረ በደንብ ያዛት !"  የተለያየ ጥያቄ እያከታተሉ በአስተናጋጁ ሰሚር ዙሪያ ተሰባሰቡ ። "እባካቹ ልትሞትብኝ ነው ! ድንገት እራሷን ሳተች አኪም ቤት መድረስ አለባት መኪና ጥሩ ልኝ ፍጠኑ እባካቹ "እያለ ወደፊት ተሸክሟት እንደመሮጥ አለ "እሺ እሺ  ዳንኤል እቤት ካለ መኪና እንዲያመጣ እንንገረው  "አለ አንደኛው ወደ ጎረቤት ቤት እየሮጠ "እባካቹ ቶሎ በሉ !?አቢዬ ጠንከር በይ አይዞሽ ተንፍሺ ...." እያለ ሰሚር ፈጠን ለማለት ሞከረ  እንዲ ሲዋከብ የሰፈር ጎረምሶችም ፣በድንጋጤ እርዳታ ፍለጋ ወዲወዲያ እያሉ  ሲከተሉት ከርቀት አንድ መኪና በነሱ አቅጣጫ ሲመጣ አዩት ሦስት ጎረምሶች አስገድደው ሊያሰቆሞቱ ወደሱ ተሯሯጡ እናም አስቆሙት ትንሽ እንደማንገራገር ሲል አስተናጋጁ ሰሚር እጁላይ አብላካትን ታቅፎ ሲመጣ የሰፈር ሰው አጅቦት ሲለቃቀስ አየ ።ከመኪናው በፍጥነት ወጣ ። አስተናጋጁ ሰሚር ሲያየው እንባ ተናነቀው "ሰሚር ምን ተፈጠረ ደና ነች ና ና ልቀበልህ" ብሎ ተጠጋው "ሰመረ ፍጠን እንኳን መጣህልን ቶሎ አኪም ጋር መድረስ አለባት ትንፋሿ እየተቆራረጠነው "አለ ሰመረ ከእጁ ተቀበለውና የመኪናው የዋላ ወንበር ላይ በጥንቃቄ አስተኛት አስተናጋጁ ሰሚር ገብቶ እግሩላይ ጭንቅላቷን አስደገፋት ። ሰመረ በፍጥነት ገብቶ መኪናውን አስፈነጠራት በጣም ደንግጧል አልቦታል ደጋግሞ ለፈጣሪው ይፀልያል ..... "ምን ተፈጥሮ ነው ስደውል ደናነች ብለኽኝ ነበር" "አዎ ድንገት ነው ለመነሳት ስትሞክር አቃስታ የወደቀችብኝ "አለ አስተናጋጁ ሰሚር "ምግብ አልበላችም ?" "ያን ያክል አልወሰደችም " አለ አስተናጋጁ ሰሚር ። ሰመረ የልብ ምቱ አስፈራው አብላካት በዚ ዕድሜዋ ያሳለፈችው ፈተና አስጨነቀው የዛሬን ደና ከሆነች ሊጠብቃት ቃል ገባ ብቻ ምንም አትሁን እንጂ የሚከፈለውን መስዋት ከፍዬ አሳክማታለው  ወላጆቼንም ቢሆን አስቸግሬ በነሱ ዙሪያ ያሉትንም ሰዎች አሰባስቤም ቢሆን ፈጣሪ እባክህ እንድትሞት አታድርግ ,,,,,,,,,,,,, ሰላም እና ፍቅር ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንግዜም ከዘመንህ አይለይ🙏 @natani273 ይቀጥላል......     ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
Show all...
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ 🌼አዲስ ሀሳብ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ ከትላንት ስህተቶች የምንማርበት፣ አዲስ አላማ ቀርፀን የምናሳካበት፣ ጥላቻና ልዩነትን አስወግደን በአንድነትና በፍቅር ወደ ተሻለ እድገት የምንሸጋገርበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን !  🌻ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ 2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ፤ ሰላም እና ፍቅር ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንግዜም ከዘመንህ አይለይ🙏 ❤️በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የፍቅር አመት እንዲሆን እንመኛለን።    መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችን           💛ከፍቅር ደጅ 💕💞 💛 @natani273
Show all...
🍃በ'ነሱ ቤት🍃 🍄ክፍል ሠላሳ አራት🍄 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 መሳይ ጌታነህን ስታገኘው  በመጀመሪያ የመጣላት ነገር ከበጎ አድራጊዎቹ ጋር አገናኝቷት ጉዳይዋን በማሳዘን እንድትነግራቸው መክሯት ዞር የሚል መስሏት ነበር ።ነገር ግን መኪናው ውስጥ አስገብቷት  እርዳታ ሊያደርጉላት የሚፈልጉት ሰዎች ቤተሰቡ መሆናቸውን እና ይህንን ድጋፍ የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው በመተማመን ሲያወራ ግራ መጋባት ውስጥ ከተታት ። እናም ልቧ ፈራ ይሄልጅ የእውነት ቁም ነገረኛ ነው ወይስ አይምሮው ንክ ነው ሲያወራ እራሱ  ያልተረጋጋ መሆኑ ያሳብቅበታል ብላ ማሰቧን አላቆመችም ። ከረጅም ጉዞ በዋላ ከዚበፊት በምታውቀው መንደር ውስጥ ታጥፎ ገባ እናም አካባቢው ላይ ያላት ትውስታ አንድ በአንድ መጣባት ።ከአስራ ስምንት አመት በፊት በዚ መንደር ውስጥ ተመላልሳበታለች ። በመጨረሻም ልጇን አርግዛ ስትባረር በዚሁ ድንብርብር እያለች ወጥታበታለች ። በጣም በተጠጋች ቁጥር ያ የአብታሞች መንደር የቀለም ለውጥ ከማድረጋቸው በስተቀር እንዳሉ ናቸው ፣ ልቧ መምታት ጀመረ ፊቷን ወደ ጌታነህ አዙራ ተመለከተችው ። በዝምታ ወደፊት ለፊቱ እያየ ነዳ ትንሽ ሄድ ብሎም አንድ ግዙፍ የተንጣለለ ጊቢ ጋር ሲደርስ አቆመ ።የመሳይ ልብ አብሮ የቆመ መሰለ ።ይህንን ጊቢ ታውቀዋለች ።ጌታነህ ከመኪናው ወርዶ እየከፈተላት እንድትወርድ ጠየቃት መንቀሳቀስ አልቻለችም ።እጇን ያዝ አድርጎ እንድትወርድ ለመናት ፣ሰውነቷ መንቀጥቀጥ ጀመረ ። "እባክህ....."አለች ቃላት እያማጠች "እባክሽ ውረጂና ከቤተሰቦቼ ጋር ላስተዋውቅሽ እኔ የዛ ባለጌ ወንድም ነኝ የመስፍን ከዚቤት የሚገባሽን እንድታገኚ እስከመጨረሻው ልረዳሽ ዝግጁ ነኝ አትፍሪ "አላት  መሳይ እንደምንም ከመኪናው በመውረድ ጌታነህ ላይ አፈጠጠች "ባቢ አንተ ነህ እንዲ ትልቅ የሆንከው "አለችው "አንቺ ታውቂኛለሽ እኔ ግን ምንም ነገር አላስታወስኩሽም ነበር "አላት በመገረም እያያት "እኔ አልረሳም ትንሽ ልጅ ነበርክ ልታስታውሰኝ አትችልም ግን እንዴት አወቅክ "አለችው ተገርማ ጌታነህ አብላካትን እንዴት መጀመሪያ ከጓደኞቹጋር እንዳገኛት ፣ከዛ ምን ሲፈጠር እንደነበረ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ፈጠን ፈጠን እያለ ነግሯት በረጅሙ ተነፈሰ ።የአብላካት መጨረሻ ሞት እንዳይሆን ፈርቷል።  መሳይ የሚንቀጠቀጠውን እጇን ማስቆም አቅቷታል ። ጌታነህ ሁኔታዋን ሲያይ ትንሽ ማረጋጋት ያስፈልጋል ብሎ በማሰብ ተመልሰው መኪናውስጥ ገብተው መነጋገር እንደሚችሉ ነግሯት መኪናውስጥ ገቡ እናም ስለቤተሰቦቹ ሁኔታ አወራት አብላካተሸ መታመሟን እና እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ስታወራ በቴሌቭዥን ቤተሰቡ ሁሉ እንዳይዋት እና ማንነቷንም እንዳወቁ ከዛ በጣም መደናገጣቸውን ።ከዛ ልጅቷ የራሳቸው ዘር መሆኗን አምነው ለማሳከም እንደፈለጉ አወራት ። መሳይ ያለፈውን አስታውሳ እልህ ያዛት አይሆንም ብላ ጌታነህ ላይ ጮኽች ። "እንዴት አይሆንም ትያለሽ እኛም እኮ በልጅቷ ላይ መብት አለን ቤተሰባችን ናት ዝም ብለን ስትሞት ልናይ ነው"አላት ተቆጥቶ "እኛ አትበል አውጥተው ጥለውኛል ከመስፍን አላረገሺም እርሺው ብለው ነው የወረወሩኝ አሁን ምን ተገኘ"ብላ አለቀሰች "እየነገርኩሽ ነው እንኳን ወላጆቼ መስፍንም ተፀፅቷል ልጁ እንደሆነች አምኗል በወቅቱ የነበረው ነገር አሁን ላይ የለም "አላት ሊያግባባት እየጣረ "አይ ከነሱ አምሳንቲም አልፈልግም "አለች በደከመ ድምፅ ውስጧ ግን ሲሸነፍ ይታወቃታል "ላንቺ አይደለም ለአብላካት ነው  መዳን አለባት እኔም ከዚ በዋላ እህት ይኖረኛል  እባክሽ እራስ ወዳድ አትሁኚ "አላት ቀናብላ ስታየው ቆይታ ።አንገቷን በመነቅነቅ ።ውስጧ እያዘነ ተስማማች ። ሌላስ ምን መላ አላት የታመመች ልጅ ይዛ ብትኮራ ምን ሊያዋጣት ። ጌታነህን ተከትላ ወደ ጊቢው ዘለቀች ።ጊቢው ውስጥ እንደገቡ መናፈሻ በመሰለው ስፍራ ላይ ክብ ጠረቤዛ ከበው ተቀምጠው የነበሩት የጌታነህ ወላጆች ቆም ብለው ጠበቋቸው ። ሲቀርቧቸው የጌታነህ እናት የነበረባትን ትምክህት ጣል አድርጋ  ይቅር በይኝ በማለት የመሳይ እግር ላይ ተደፋች መሳይ ያልጠበቀችው ነገር ስለነበር ድንብርብሯ ጠፋ ደጅ ላይ የፎከረችው ነገር ጥሏት ጠፋ የጌታነህን እናት ከመሬት ላይ በማንሳት ፣አቅፋት አለቀሰች ። ጌታነህ ሁኔታው አስለቀሰው ። መሳይን ወላጆቹ ደጋግመው ይቅርታ እየጠየቁ ሲያይ ወላጆቹን እንዲ ተቀይረው በማየቱ ጉድ አለ ። ለማንም ግድ የሌላቸው የሱ ኩሩ ወላጆች ተንበረከኩ ።ይሄ መቼስ ስለ አብላካት ነው ሌላ አይደለም 'ይሄ ቆሞ የቀረ ልጃቸው የልጅ አባት ሊሆን ነው'ብሎ በውስጡ ሳቀ ። ብቻ በፍጥነት ሄዳ ትታከም ...... ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨?፨?፨?? አብላካት እናቷ የሄደችበት ጉዳይ ተሳክቶ ሁሉም ነገር ሰላም እንዲሆን በልቧ ደጋግማ ፀለየች ። እናቷን እዚ ምድር ላይ ብቻዋን ጥሎ መሄድ በጣም ያማል ያ እንዲሆን ፈጣሪዋ እንደማይፈቅድ ለራሷ እየተናገረች ትፅናናለች ። ሰሚር ስልኩን እየነካካ አልፎ አልፎ ትክዝ ብላ የተቀመጠችውን አብላካትን ያያል ። ከቆይታ በዋላ ስልኩ ተደወለ አንስቶ ሲያየው ሰመረ ነው ተነስቶ ሊወጣ ፈልጎ ነበር መልሶ ተወው እና አነሳው "ሃሉ " "ሰሚር የት ነው ያለኽው እባክህ ልምጣ ሚጣ ጋር ውሰደኝ "አለው ቅስሙ ስብር ብሎ "እኔ አሁን እሷው ጋር ነኝ እናቷ ስለወጣች አብሬያት ልቆይ ብዬ ነው" "እሺ አቅጣጫውን ንገረኝ እመጣለው "አለው ሰሚር የሰመረ ሁኔታ አሳዘነው እሱ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለአብላካት ጥሩ ነበር ታዲያ ለምን አብሯት እንዳይሆን ይከላከላል ?በጭራሽ!   ።አቅጣጫውን ነገረው ሰመረ እሺ ብሎ ስልኩን ዘጋው ። "እሺ ለማን ነው ደሞ ቤቴን የምትነግረው ኪኪኪ ስንት ሺብር ይዘን መጣን አሉክ ?"አለችው አብላካት እግሯን እያሻሸች "ሲመጡ ታያለሽ ምን አስቸኮለሽ " "ስንት ናቸው" "አንድ ነው ስታይው የምትወጂው ይመስለኛል"ብሎ ሳቀ "ማነው "አለች ኮስተር ብላ "ሲመጣ ማንነቱን እራሱ ያስተዋውቀናል" "ደረቅ "ብላ ለመነሳት ስትል ወጋት በከባዱ አቃሰተች አስተናጋጁ ሰሚር በድንጋጤ ሄዶ አቀፋት እጆቹ ላይ ልፍስፍስ ስትልበት "አቢ አቢ ደና አይደለሽም አቢ..........."እያለ ተጣራ ,,,,,,,,,,,, ይቀጥላል......     ሰላም እና ፍቅር ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንግዜም ከዘመንህ አይለይ🙏 @natani273 ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
Show all...
👁በ'ነሱ ቤት👁 ❤ክፍል ሠላሳ ሦስት❤ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 አስተናጋጁ ሰሚር ደጋግሞ የሰመረን ስልክ ሞከረ ይጠራል አይነሳም  በጣም ጓጉቶ ስለነበር ሰመረ ባለማንሳቱ ቅር አለው ። ለአብላካት አንድ የተሻለ ነገር እንደሚፈጥርላት ተማምኗል ፣ የተለየ ነገር ባያደርግ እንኳ ብዙ ገንዘብ ሊረዳት ይችላል ። እነ አብላካት ቤት ሲደርስ ቆም ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ ፣አብላካት ፊት ሲቀርብ ጭንቀት ማሳየት አይፈልግም ልክ እንደወትሮው  እየቀለደ ዘና ሊያደርጋት ነው የሚፈልገው ።    እናም በር ከፍቶ ሲገባ መሳይ ቡና እያፈላች ከአብላካት ጋር እየተጫወቱ አገኛቸው ይህንን ስሜት ሲያይ የአብላካትን እናት አመሰገናት ፣ በዚ ጉዳይ ላይ ደጋግሞ መክሯታል ልጇን ማዳን ከፈለገች በፊትለፊቷ ማልቀስና ደካማነቷን ማሳወቅ ሳይሆን ፣ በተቻላት መጠን ስለህመሟ እንዳታስብ ማዝናናት ጠንካራመሆኗን መንገር ከፈጣሪ ጋር ሁሉ ነገር እንደሚቀየር መንገር ነው ብሏታል።እና ዛሬ እንደዛ ስታደርግ ስላየ ተደሰተ ። ሁለቱንም ጉንጫቸውን ስሞ ተቀመጠ እና አብላካትን ፣ በቀልድ "አንቺ ሚጣ ምንድነው እንደዚ የሚያስቅሽ"አላት "ስነስርሃት ሚጣ እንዳትለኝ ፣ደሞ ያሰመረን ተገላገልኩ ስል አንተም ሚጣ ትለኛለህ ዋ.."አለች "አውቄ ነው ኪኪኪኪ የኔ ትልቅ ገና ትልቅ ትሆኛለሽ አምናለው ሀላ ያውቃል አንቺ ብቻ ፈገግ በይ"አላት በሰአን ላይ የቀረበውን የቡና ቁርስ ፈንዲሻ እየዘገነ "አይ ሰሚ ምላስህ እኮ "አለች አብላካት የሆዷን በሆዷ ይዛ ለነሱ ስትል እየሳቀች "ሰሚሬ አንተ እኮ እንደታናሽ ወንድሜ ነህ አንተ ባትኖር ምን ይውጠኝ ነበር ፈጣሪ ይጠብቅ "አለች መሳይ። ሰሚር ፈገግ ብሎ መልስ ሊሰጥ ሲል ስልኩ ጮኽ በፍጥነት አንስቶ "ሃሉ "አለ "ሃሉ ማን ልበል ወንድም ደውለህልኝ ነበር"አለው "አዎ አዎ"ብሎ ተነስቶ ወደደጅ ወጣ ። "እኮ ማን ልበል " "ሰሚር እባላለው የአብላካት ጓደኛ ነኝ አስታወስከኝ"አለው "እህ አዎ አዎ ሰሚር አስተናጋጁ " "አዎ እንደቴ ነህ ሰላም ነው"አለው ሰሚር "ደና ነኝ እንዴት ናቹ እናንተ ፣" "ደና ነን" "ሚጣ እንዴት ናት ማለቴ አብላካት" "ደና ነች እእ ያው..."ብሎ ሰሚር ዝም አለ "ያው ምን አብላካት ደና አደለችም እንዴ ?"አለው ሰመረ "ያው ትንሽ ታማለች እእ ብቻ አስቸጋሪ ሁኔታላይ ነው ያለችው "አለው ሰሚር እየተጠነቀቀ "ምንድነው እሱ የት ነው ያለችው ስልኳን ደጋግሜ ብሞክር የማታነሳው ለዛ ነው የት ነው ያለችው ሆስፒታል ናት"ሰመረ ተርበተበተ። አስተናጋጁ ሰሚር የሰመረን ድምፅ መለዋወጥ ሲሰማ ገባው በቃ ሰመረ ይወዳታል ስለዚህ ልነግረው ይገባል ምናልባትም ፈጣሪ የአብላካትን መጪ ሁኔታ ተመልክቶ ቢሆንስ ሰመረን ያዘጋጀላት ብሎ አሰበ "ሆስፒታል አደለችም ለጊዜው ነገር ግን በሳምንት ሦስት ቀን ሆስፒታል የሚያስኬዳት ህመም ነው ያለባት በጣም አሳዛኝ ሁኔታላይ ነው ያለችው"አለው "ምን ምን እያልክ ነው ?!የምትለውን ታውቃለ ይሄን ያክል ምንድነው እየቀለድክብኝ ነው እንዴ"አለው ሰመረ በቁጣ "ከምሬን ነው ዛሬም ልደውልልህ የተገደድኩት እርዳታ ስለሚያስፈልጋት ነው በፍጥነት የኩላሊት ንቅለተከላ ካላደረገች ቅስሟ ተሰባብሮ ቶሎ ትሞታለች "አለ ሰሚር እንባ እያነቀው "ምን ምምን ኩላሊቷ...."ብሎ ዝም አለ ስልኩም ተቋረጠ ። ስልኩን አየው ተዘግቷል ።ጠበቀ ጠበቀ እና መልሶ ደወለ ካገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ነው ይላል ። ቅር እያለው ወደቤት ገባ ። መሳይ አየቸው እና ቀስብላ መጥታ እርዳታ አገኘን እንዴ አለችው ። አስተናጋጁ ሰሚር ከነ ጌታነህ ያገኘውን ገንዘብ አውጥቶ ዘረገፈው ፣ ብዙ ነው ነገር ግን ለጊዜው ነው ። አብላካት የናቷ ፊት ሲፈካ ስታይ ።ልቧ ተነካ  ፈጣሪ ለሷ ሲል ቢምራት ተመኘች ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ጌታነህ ምሽቱን ሙሉ ከቤተሰቦቹ ጋር አንዴ በቁጣ አንዴ በተረጋጋ መንፈስ ሲማከር ነው የቆየው ፣ በመጨረሻ የተስማሙበት ጉዳይ መሳይን እንደምንም ብሎ ማናገርን ነው ከዛ በዋላ በፍጥነት ልጅቷን ወደውጪ ሄዳ የምትታከምበትን መንገድ ማመቻቸት ።ከዛ በዋላ ሁሉንም ነገር እንድታውቅ ማድረግ በዚ አሳብ ተስማምተው ሁሉም እያብሰለሰሉ ወደመኝታቸው ሄዱ ። ጌታነህ ነገሩ ሁሉ ሌላ ሰው አድርጎታል ልቡ በጭራሽ አላርፍ አለው ፣አስተናጋጁ ሰሚር የሰጠውን የእርዳታ ወረቀት አውጥቶ ተመለከተው ስልክ ቁጥሮች አሉት ። ነገ ደውሎ አድራሻቸውን እንዲያሳውቁት ሊጠይቃቸው ወሰነ ።እንቅልፍ መተኛት እስኪያቅተው ድረስ ስለ አብላካት አሰበ ፣ፈጣሪ ያቺን ልጅ እንዳላገኛት ስላላደረገኝ አመሰግነዋለው እሺ ብትለኝ ኖሮ ትልቅ ስህተት ውስጥ ገብቼ ነበር ። ይሄ የተረገመ ወንድሜ አጥፍቶ አጥፍቶኝ ነበር ። እንደስራዬ ያልከፈልከኝ ፈጣሪ አመሰገናለው ።አለ ደጋግሞ ።ስለ ጓደኞቹም አስቦ ይህንን ጉድ ሲሰሙ ምን ይሉ ይሆን ። ብሎ አሰበ ። ብቻ እንድቺው ሲገለባበጥ ሲጨነቅ አደረ... ይቀጥላል......     .......... ይቀጥላል......ሰላም እና ፍቅር ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንግዜም ከዘመንህ አይለይ🙏 @natani273
Show all...
#ጷጉሜ 🌼   እንኳን አደረሳቹ   🌼 ሰላም እንዴት ናቹ ጓደኞቼ በቅድሚያ እንኳን ለጷጉሜ (13)ኛ ወር አደረሳቹ!!!እስኪ ዛሬ ስለ የጷጉሜ (Qaammee) ወር አመጣጥ ትንሽ ልበላቹ!ለመሆኑ የጿጉሜ ወር አመጣጥ እንዴት ነው? መረጃውን ያገኘውት ከመምህር ሮዳስ ታደሰ ሲሆን የጷጉሜን አመጣጥ እንዲ ያስረዱናል፦ "❤️ጷጉሜ የተባለችው 13ኛዉ ወር በፅርዕ ኤፓጉሜኔ ስትባል ሊቃውንት ተረፍ ይሏታል፡፡የአምስት (5) ቀናትን ጷጉሜን አመጣጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጠንቅቀው ቀምረው በባህረ ሃሳብ ብራናቸው ላይ ፅፈውልናል፡፡" "❤️ይኽውም ከመስከረም 1 እስከ ነሃሴ 30 ያሉት 12ቱ ወራት ባጠቃላ ያላቸው360 እለታት  ነው፡፡ በቀደምት ኢትዮጲያውያን ሊቃውንት ጥልቅ ትንተና 1 ቀን የሚባለው 24 ሰአት 52 ካልኢት ከ31 ሳልሲት ነው፡፡" "❤️ 1 ካልኢት ማለት 24 ሰኮንድ ሲሆን 52 ካልዒት ማለት 1248  ሰከንድ ነው፡፡31 ሳልሲት ማለት 12.4 ሰከንድ(ቅፅበት) ይሆናል፡፡ በመሆኑም በአንድ ቀን ውስጥ 1 ደቂቃ ከ 0.4 ሰከንድ ትርፍ መኖሩን ያስረዳል፡፡" "❤️በመሆኑም ከመስከረም 1 እስከ ነሃሴ 30 ባሉት 360 ቀናት ያሉትን 52 ካልዒት ወይም1248 ሰከንድ እንደዚ እናባዛቸዋለን 52 ካልዒት×360 ዕለታት=18,720 ካልዒት ወይም 449,280ሰከንድ ይሆናል፡፡ ወደ ደቂቃ ስንለውጠው 7488 ደቂቃ ወይም 5 ዕለት ይሆናልና፡ የጷጉሜ አመጣጥ ይች ናት፡፡" : : :         እኔን በጣም ያስገረመኝ እና ያስደነቀኝ የጳጉሜ 5 ሚስጥር 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 "❤️አራት የአመት ወቅቶች ማለትም፦መፀው፣ሐጋይ፣ፀደይ እና ክረምት 91,91 የሚሆኑት ከጷጉሜ 1 ቀን እየተሰጣቸው ሲሆን ባጠቃላይ 364 ቀናት ወይም 52 ሳምንት ኾኖ አንዲት እለት ትተርፋለች ፤ይቺኽም ጷጉሜ 5 ስትሆን በኢትዮጵያ ቀደምት የዘመን ቀመር ሊቃውንት "እለተ ምርያ አዕዋዲት" ትባላለች፡፡ "❤️እለተ ምርያ ማለት  እለተ መድኃኒት ማለት ነዉ፤ ምክኒያቱም ጷጉሜን አምስት (5)  የመዳኍኒታን የእየሱስ ክርስቶስ ልደትን የምናውቅባት ስለሆነች ነው፤ይኽውም ጷጉሜ 5 በዋለችበት ዕለት የክርስቶስ ልደት ዕለት በተመሳሳይ መልኩ ይውላል፡፡😁 ለምሳሌ፦የዚህ ዓመት  ጿጉሜ 5 ዕለተ ማክሰኞ ናት በተመሳሳይ የ2017 የክርስቶስ ልደት ታሕሳስ 29  ማክሰኞ ትውላለች፡፡😀😀😀 በዚ ምክኒያት ነው ዕለተ ምርያ የሚል ስያሜ ሊሰጣት ችሏል፡፡" "❤በተጨማሪ ጷጉሜ አምስት(5) የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የአዲሱ አመት መንደርደሪያ ዕለት እንደ ሆነች የክርስቶስ ልደትም የአመተ ፍዳ ማቆሚያ️ የአመተ ምህረት መጀመሪያ በመሆኑ እለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ መዋሉ እጅጉ ይገርማል፣ይደንቃልም፡፡ "          ምንጭ፦ከመምህር " ሮዳስ ታደሰ "የተወሰደ በመጨረሻ ትንሽ  ነገር ልበላቹ ❤️❤️ይችን ቀን ቀምረው ላስቀመጡልን ሊቃውንት አባቶቻችን ክብር🙏🙏🙏 ክብር ይገባቸዋል!!! በ2016 ያስቀየምኳችሁ ይቅርታ!!!🙏 ዘመኑን በይቅርታ (ይቅር በመባባል እንሸኘው !!!) አዲሱ አመት የሰላም፣የፍቅር እና የአንድነት ያድርግልን !!! "አሜን" "ፍቅር ይስጠን!!! አሜን"❤️❤️❤️ : :   " ሃገራችን ሰላምሽ ብዝት ይበልልን" ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቃት!!!🙏        #Join @natani273
Show all...
👁በ'ነሱ ቤት👁 🌻ክፍል ሠላሳ ሁለት🌻 ❤🌻❤🌻❤🌻❤ ጌታነህ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ እንዳለ ዘርግፎ ለአስተናጋጁ ሰሚር እያስረከበ ወደ እንየው በመዞር እሱም ልክ እንደሱ እንዲያደርግ ነገረው ። እንየው የጌታነህ ሁኔታ የጤና አልመሰለውም ዝምብሎ እያየው ነበር ።ጌታነህ በእንየው መረጋጋትና የጥርጣሬ አስተያየት ተቆጣ ። አስተናጋጁ ሰሚር አረጋጋውና እርዳታው የግድ ዛሬ መሆን እንደሌለበት ነገም ተነገ ወዲያም ይደርሳል ብቻ የእርዳታ እጃችሁን ዘርጉላት እባካቹ አላቸው ። ሁለቱም ተስማሙ  ።ጌታነህ ከሬስቶራንቱ እንደወጣ በቀጥታ ወደቤቱ ነበር የሄደው አይለኛ ድብርት ተጫጭኖታል ።ስለ አብላካት የሰማው ነገር  ምቾት ነስቶታል ቤት ሲገባ ወላጆቹ እናም ወንድሙ ሳሎን ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል ።ሁኔታቸው ግን ያስፈራ ነበር በከባድ ዝምታ ውስጥ ነበሩ ሁኔታቸው ደስ ስላላለው ወደክፍሉ ሊገባ መንገድ ጀመረ  በዚጊዜ እናትየው ሶፋው ላይ እንዲቀመጥ በትህዛዝ ተናገረችው ። ጌታነህ እየደበረው ተቀመጠ በውስጡ ምነው ወደቤት ባልመጣው የሚል አሳብ መጣበት ።እናቱን ቀናብሎ ሲያያት አንድ ነገር ለመናገር ስታምጥ አስተዋለ ።ወደአባቱ ሲያይ  ወደ መስፍን ፊቱን አጨፍግጎ ዞሯል መስፍን በዕንባ የራሱ አይኖቹን እየጠራረገ እና በተደጋጋሚ በአፍንጫው የሚወጣድምፅ እንዳለ አስተዋለ ። ጌታነህ አሁን ይበልጥ ተረበሸ ። ከረጅም ዝምታ በዋላ እናት እያማጠች መናገር ያለባትን ነገር ሁሉ ከስር መሰረቱ አፈረጠረጠችው ። መስፍን ተነፋረቀ ጌታነህ የሚሰማውን ሁሉ ለማመን ከበደው ።  ጭራሽ እያወሩ ያሉት ስለአብላካት መሆኑን ሲያውቅ አፉን ያዘ የሚሆነው ጠፋው  በተደጋጋሚ ምን አይነት አገሮች ጣሚ ነው ምን አይነት አጋጣሚ ነው .....እያለ ጮኽ እናት ከመስፍን የጌታነህ ባሰባት ... "ተረጋጋ ጌታነህ ምን ሆነሃል መስፍን እንኳ እንዳንተ አላበደም ። ልጅቷ በዚ ሰአት ችግር ውስጥ ናት እናቷን አፈላልገን ልንረዳት ይገባል "አለችው "ማሚ አልገባሽም እኮ ልጅቷን .."ብሎ ጭንቅላቱን ያዘ "ልጅቷን ምን?"አለችው እናት ደንገጥ ብላ "ልልጅቷን አውቃታለው ማለቴ..."ብሎ ሊቀጥል ሲል "አምላኬ የት ነው የምታቃት "ብላ እናት ተነሳች እሷን ተከትሎ አባትየውም ብድግ አለ "ተው ጌታነህ በሌላ መልኩ ነው እንዳትለን ተው !!"አለ አባትየው በድንጋጤ መስፍን የሚገባበት ጠፋው "አይ እንደዛ ነገር አልተፈጠረም ግን ሊሆን ነበር ።ምን እንደሰራቹ ተመልከቱ ልጅቷን በተደጋጋሚ የፍቅር ጥያቄ አቅርቤላት ነበር በእርግጥ አንድ ቀን ነው ያገኘዋት ከዛ በዋላ በስልክ ልቀርባት ሞክሬ አለው ላገኛት ብዙ ቀጠሮ አስዣታለው ነገርግን ፍቃደኛ አልነበረችም እልህ ውስጥ ከታኝ ነበር በአካል ባገኛት ነገር ይበላሽ ነበር ።ወይ ፈጣሪዬ ለካ ለዚነበር የጠበቅከኝ አመሰግናለው አምላኬ "ብሎ ተንበረከከ "ልጅቷእኮ ገና ታዳጊ ናት እንዴት ሌላ ነገር አሰብክ "ብሎ መስፍን ድንገት ጮኽ "ምን ታወራለህ ደሞ አፍ አለኝ ብለህ ዝም በል "አለ አባት በብስጭት ። የጌታነህ እናት ። ጌታነህ ሌላ ግንኙነት አለን የሚላት መስሏት ደንግጣ ነበር ።ያ ባለመፈጨሩ ቅልል አላት ።እናም እርስ በእርስ መነታረካቸውን ትተው ልጅቷን ማዳን እንዳለባቸው አፅኖት ሰጥታ ተናገረች ።ሁሉም በእሷ አሳብ ተስማሙ እናም አብላካትን በፍጥንት ወደ ውጪ ወስደው ማሳከም እንዳለባቸው  እናም የአብላካትን እናት መሳይን  ማግኘት እና ላደረጉት ነገር ይቅርታ ጠይቀው መካስ ያለባትን ሁሉ ለመካስ ቃል ተገባ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ አስተናጋጁ ሰሚር ከጌታነህ ያገኘውን በርካታ ገንዘብ ይዞ ወደነ አብላካት የሄደው ከስራ እንደወጣ ነበር ። አስባልቱን ጨርሶ ቅያስ ውስጥ ሲገባ አንድ አሳብ መጣለት እነገታነህ ይሄን ሁሉ ገንዘብ ከሰጡት ሰመረ ደሞ የተሻለ ነገር እንደሚያደርግ ተማመነ አብላካት እንዳትነገርው ያለችውን ነገር ወደጎን በመተው የሞባይል ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ወደ ሰመረ ደወለ .......... ይቀጥላል......ሰላም እና ፍቅር ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንግዜም ከዘመንህ አይለይ🙏 @natani273 #Share   #Share  #Share     ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
Show all...
❤🌻በ'ነሱ ቤት🌻❤ 🍀ክፍል ሠላሳ አንድ🍀 ❤🍀🌻❤🍀🌻❤ የጌታነህ እናት ወይዘሮ ገነት የምትሰራው ነገር ግራ እስኪገባት ድረስ ሆነች። አንዴ በቴሌቭዥን የምታያት የቀድሞ የቤት ሰራተኛዋ መሳይ በዕንባ ታጅባ የምታደርገውን የእርዳታ ጥሪ ልቧ ተሰብሮ ታያለች ቀጥላ ባለቤቷ ከወዲያወዲ እያለ ።'አይ ውርደት አይ መዋረድ ሰሞኑን ያለምክንያት አደለም እዚ ቤት እሳት እየነደደ ያለው ፈጣሪ የሰራነውን ስራ እንድናይ ሊያደርገን ነው ተመልከች አጥያታችን ፈጦ ወጣ "አላት ። ወይዘሮ ገነት ባለቤቷ ከሚናገረው ነገር ይልቅ ። መሳይን ስታባርራት የነበረውን ሁኔታ በአይምሮዋ እያመጣች ማመላለስ ጀመረች ፣በወቅቱ ምን ያክል ጭካኔ እንዳሳየች ሲሰማት በራሷ አፈረች፣የልጇን ብልግና ለመሰወር ብላ አንዲት ቆንጆና ምስኪን ታዳጊ ልጅ ውሻ አድርጋ ከልጇ ዞር እንዳደረገች የታሰባት ዛሬ ነው ። አጠገቧ ባገኘችው ሶፋ ላይ ዘጭ ብላ በመቀመጥ ጭንቅላቷን በሁለት እጆቿ ይዛ በፀፀት ተንገበገበች ፣  ባለቤቷ ቁጣ ቁጣ እያለው"ይሄ የማይረባ ልጅሽ ምን ያክል ወንጀል ሲያሰራን እንደነበር አስተዋልሽ ዛሬ ፣እ ሁሌም ዕፀፁን ለመደበቅ ትታገይለት ነበር ተመልከች እንዳልጠቀምሽው ። በአርባ አመቱ እንኳን ሰው መሆን አቅቶት ዛሬም ጥፋት እያጠፋ ቀሚስሽ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል ።እውነቱን ነው ጌታነህ ዘላለሙን የማያድግ ልጅ ነበር ስታሳድጊ የነበርሽው "ብሎ ጣቱን ወደሷ ቀሰረ። ወይዘሮ ገነት በንዴት ተነስታ ቆመች"ምን እያልክ ነው አንተ እራስህን ነፃ ማውጣትህ ነው።አንተ አይደለህ እንዴ ወንዶች ልጆችህን መክረ ዘክረህ እንደ አባትነትህ ማስተካከል የነበረብህ ፣ ነገር ግን ያንን እያደረክ ነበር ወይ ?በፍፁም ፣ ከዛ ይልቅ ባጠፉ ቁጥር ከመገሰፅ ይልቅ ምን ነበር የምትለኝ 'ልጅሽን ስርሃት አሲዢ 'ልክ ያንተም አላፊነት እንዳልሆኑ ሁሉ !እንግዲ እኔ የጠቀምኳቸው መስሎኝ ራርቼላቸው ይሆናል ፣ አንተ ግን በነሱም ሆነ በኔም ሕይወት ላይ ትልቁን ድርሻ መውሰድ ነቀረብህ !ታውቃለህ እኔም ብሆን አንተን ሳገባ ያን ያክል በዕድሜ የበሰልኩ አልነበርኩም"ብላ ተንጣጣችበት ። ባለቤቷ የራሱን አሳብ በንዴት ሊናገር ሲል ። ልጃቸው መስፍን ድምፅ ሰማው ብሎ ወደሳሎን መጣ "እማዬ ምንድነው ጩኽቱ ሰላም አይደላችሁም?!"ብሎ ጠየቀ "ምን ሰላም አለ አንተ እያለህ"አለው አባቱ ቱግ ብሎ "ስርሃትህን ያዝ አንተ ሰው አትጩኽበት አንዴ የፈሰሰ ውሃ ይታፈስ ይመስል ይልቅ መፍቴሄ ብታመጣ ይሻላል"አለች ወይዘሮ ገነት ለልጇ እየተከላከለች ።መስፍን ድንብርብር ብሎ አባቱን አየው ።ሰሞኑን ደሞ ሁሉም ነገር እኔላይ ነው እንዴ የተነሳው አለ ለራሱ። "ምን አጠፋው ደሞ ሳምንቱን ሙሉ ከቤት አልወጣውም ...."ብሎ ሊቀጥል ሲል "በመጀመሪያ ደረጃ አንተ ለጥፋት መውጣት አይጠበቅብህም እዚሁ የምታጠፋቸው ስላሉልህ ። ሲቀጥል ደሞ ቀድሞ ያጠፋሃቸው ጥፋቶች ቤትህ ድረስ ሊመጡልህ ስለሚችሉ ውጪ መውጣት አይጠበቅብህም! ችግሩ ያንተን ስእተት ችግር ማስተካከል ያለብን ዛሬም እኛ መሆናችን ነው እንጂ!"ብሎ ተቀመጠ። ወይዘሮ ገነት በባሏ እየተናደደች ።መስፍንን እጁን ይዛ ወደክፍሉ ሄደች እራሴው አረጋግቼ የተፈጠረውን እነግረዋለው ፣ አለዛ ልጄ በሰሞኑ ሁኔታው እራሱን ሊያጠፋም ይችላል አለች.......... ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ መሳይ አስተናጋጁ ሰሚርም የአብላካት ጓደኞችም አሰባስበው አምጥተው የሰጧትን ገንዘብ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆና ደጋግማ ትቆጥራለች ፣ የገንዘቡ አለመሙላት ልጇን በየቀኑ እንደሚገልባት ተሰምቷታል። አብላካትን ዞራ ተመለከተች በፀጥታ ተኝታለች ትንፋሿ እንኳን ጎልቶ አይሰማም ። መሳይ አዘነች ምነው ፈጣሪ ይሄን ሁሉ ነገር በኔ ላይ አመጣህብኝ ? ከልጅነቴ ጀምሮ አንድም ቀን ከአሳብ እና ከችግር ከአዘን እንዳልላቀቅ ማነው የረገመኝ ምንስ ባጠፋ..... አብላካት ተኝታ እያለመች ነው ፍፁም ፀጥ ያለ ና ማንም የማይታይበት አውላላ ሜዳ ላይ ቀስ እያለች እያዘገመች 'ሰው ሁሉ የት ሄዶ ነው ፡እሺ ሰውስ ባይኖር አንዳንድ እንስሳቶች እንኳ አይታዩም እንዴ ኡፍፍፍፍ እንዴት ደክሞኛል ደሞ  'እያለች ትጓዛለች ሄዳ ሄዳ አንድ ወንዝ ጋር ደረስች ለመጠጣት አስባ ዝቅ ስትል በውሃው ውስጥ የሚርመሰመሱ ትላትሎች አይታ በድንጋጤ አፈገፈገች ። እናም በሌላ አቅጣጫ መጓዝ ስትጀምር ደረቅ እና ቢጫ ሰአር የወረረው ስፍራ ደረሰች የሰአሩ መጠውለግ አሳዘናት በቃ እዚ አካባቢ ዝናብ አይጥልም ማለት ነው ብላ አሰበች ። መንገዷን ቀጥላ ወደፊት ስትሄድ ቢጫው ሰአር እየረዘመ እየረዘመ መጣ ለመራመድ ሲያስቸግራት ከፊቷ የተጋረደውን ሳር ገለል ስታደርገው ፊትለፊቷ ሰመረ ቆሞ አገኘችው ። በዚ ጊዜ በደስታ ተፍለቀለቀች ።ሰመረ ግን ምንም አይነት ፈገግታ ሳያሳያት  ወደዋላዋ እየጠቆመ "የት እየሄድሽ ነው ተመለሺ "አላት "እንዴ ወደቤቴ ነዋ" "አይ አይ ቤትሽ ወደዚ አይደለም በይ ተመለሺ" "ግንኮ " "ነገርኩሽ ነይ እኔው እወስድሻለው "ብሎ እጇን እየጎተተ ወደዋላ መለሶ ይዟት መሄድ ጀመረ "እሺ አትጎትተኝ ቀስ እያልን መሄድ አንችልም ?በዛላይ የምነግርህ ነገር ነበረኝ " "ንገሪኝ እሰማሻለው" "እሺ ግን አንዴ መቆም እንችላለን " "እሺ ነይ ብሎ ወደራሱ አስጠጋት" "እ እኔ በጣም በጣም አፈቅርሃለው ይሄንን ሳልነግርህ ሩቅ ቦታ ልሄድ ነበር እኮ" "እንዴ እኔን ጥለሽማ በፍፁም አትሄጂም ።ደሞ እኔም አፈቅርሻለው እኮ ሚጣ" "ሚጣ አይደለውም !አብላካት ነው ስሜ !ድጋሚ ሚጣ እንዳትለኝ " "እሺ በቃ "ብሎ እቅፍ አድርጎ ሊስማት ጠጋ ጠጋ ሲላት አንዲት አሞራ መጥታ በመሃላቸው ብር ብላ ስትገባ 'ዋይ 'ብላ ብንን አለች   መሳይ በፍጥነት ወደልጇ ተጠግታ ግንባራን እያሻሸችላት "የኔ ውድ አይዞሽ ህልም ነው ፣መጥፎ ህልም አይተሽ ነው እኔን  እኔ ልሳቀቅ ዓለሜ አይዞሽ እስከመጨረሻው አልለይሽም "አለቻት "እማ የኔ ውድ እናት ያን ያክል የሚያሳስብ አይደለም ህልም ህልም እላለው "አለቻት እና ወደ እናቷ አቅጣጫ በመዞር ጥቅልል ብላ ተኛች ።ወዲያው በአሳቧ ወደ ሰመረ ገሰገሰች በህልሟ የተሰማት የተለየ ስሜት ገርሟታል እውነት ከሰመረ ጋር በውንም እንዲ ይሰማኝ ይሆን ?  ልቧ እንደ አዲስ ለሰመረ ሲመታ አዘነች ።ሰመረን እንደፈለገችው ሳታገኘው ስሜቷን ሳታጋራው ወደ ማይቀረው መሄዷን ስታስበው በአልጋዋ ላይ እንዳለች ተቁነጠነጠች ።ሁኔታዋንስትከታተላት የነበረችው መሳይ ይህንን ከማይ ብላ እናም ዕንባዋም ሊመጣ ሲታገላት መጣው ብላት ወጣች። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ጌታነህ በስንት ጊዜው እንየውን አግኝቶ የጦፈ ወሬ ይዘዋል ።ጌታነህ ስላሳለፈው ነገር እየነገረው እንየውን በሚያስቀውም በማያስቀው ያስቀዋል ። ስለሰመረም ትንሽ አሜት መሰል አውርተው ቦጨቁት ።ሰመረ የተቀየረባቸው ያቺን ትንሽ ልጅ አብላካትን ካገኘ ጀምሮ እንደሆነ አወሩ መልሰው ደሞ መራራቃቸው ከዛ ቢጀምርም ።ልጅቷናት ለማለት አይቻልም በሚለው ደሞ ተስማሙ ። በዛውአጋጣሚ  እንየው እሷን ልጅ እጅህ ማስገባቱ አልሆን አለህ አይደል ብሎ ጀመረው ይሄን ጊዜ የጌታነህ በህልህ የተሞላ ልብ ድጋሚ ተነሳሳ እናም የሆነ ያልሆነ ውሸት ከነገረው በዋላ ።ወደ አብላካት ደወለ ይጠራል ብዙ ጊዜ ሞክሮ ስልኳ ዝግ ነበረ ዛሬ ስለሰራለት ደስ አለው 'አንሺው አንቺ ትንሽዬ በቀቀን "አለ ስልኩ ቢጠራም አልተነሳም አቅበጠበጠው  በጣም ስሜታዊ ሆኖ  ሚሴጅ ፃፈላት "አንቺ ፈልፈላ ለምንድነው ስልኬን የማታነሽው ካንቺ ምን ፈልጌ መስሎሽ ነው
Show all...
ይቀጥላል......   ፍቅር፡ሰላምና ጤና ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምን ጊዜም ከዘመንህ አይለይ!!!!!!! ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ☑️ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩት፡ ☑️#Share 👇👇👇👇👇👇👇👇    @natani273
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.