cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ራዕየ ማርያም ✝

በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35

Show more
Advertising posts
1 434
Subscribers
-124 hours
-37 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
          "እመቤቴ ሆይ ከሞት ለዘላዓለሙ ታድኚኝ ዘንድ አድኚኝ አልልም። እንዲህማ እል ዘንድ ለዘለዓለም የሚኖርስ ሞትንም የማያያት ማነው። እኔስ የምለው እንዲህ ነው። ንስሐ  እስክገባ ድረስ እንዲቆይልኝ። የንስሐ ፍሬንም እካቀርብለት ቸርነቱንም ደስ እስካሰን እንዲጠብቀኝ ነው።"                    ❖ አርጋኖን ዘሠሉስ❖ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት ለመላው የራዕየ ማርያም አባላት በሙሉ! በዚህ ልዩ ቀን አዲሱን አመት በተስፋ እና በመታደስ ስንቀበል የሰላም፣ የደስታ እና የተትረፈረፈ ዓመት ይሁንልን ። በጎ ምግባራትን የምንሰራበት ፤ በእምነት የምንለመልምበት ፤በንስሐ  ታጥበን ለቅዱስ ቁርባን የምንበቃበት ያርግልን ። ዓመቱን በሙሉ በእግዚአብሔር ጸጋ እና ስፍር ቁጥር በሌላቸው በረከቶች እንድትሞላ እመኛለሁ!                         🌼🌼🌼          🌼🌼🌼             https://t.me/raiye_mariyam
Show all...
🙏 3 2
Show all...
.m4a6.94 MB
       "እባክህን ከእሳቱ ላይ አትውረድ " አንድ ወንድም አባ ጴሜንን "ምከረኝ" ብሎ ጠየቀው። አባ ጴሜንም "ድስት በእሳት ላይ እያለ ምንም አይነት ተባይ ሊቀርበውና ሊያበላሸው አይችልም። ከእሳት ወጥቶ ሲቀዘቅዝ ግን ነፍሳት ሁሉ ለመግባትና ለማበላሸት ይቻላቸዋል። ክርስቲያንም ከመንፈሳዊ ተግባር ካልራቀ ጠላት የድቀት ምክንያት አያገኝበትም" አለው። ወዳጄ ሆይ ሕይወትህ ቀዝቅዛብሀለችን? ከእሳቱ ወደ መሬት ወርደህ በርደሀልን? የሕያውነትህ ሙቀት እሳት በማጣት ተንዘፍዝፏልን? ድስት የተባለ ሰውነትህ ክረምት የሚያህል ጉድን ተሸክሟልን? ዙሪያ ገባህ ፀሐይ እንደማትወጣበት ምእራብ ጨለማን የሚጠራ ሆኗልን? ማንነትህ እሳት እንዳጣ ምግብ ጥቃቅን ነፍሳት በተባሉ ሀጥያቶች(ቁጣ፣ ቸልተኛነት፣ ስስት፣ አልታዘዝ ባይነት፣ ጭንቀት፣ ሁሉን የመናቅ ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ...) ተወሮ መዓዛ ቅድስና ተለይቶት እጅ እጅ ብሏልን? ሞቅ የሚያደርገው አጥቶ በዓለማዊነት ሻግቷልን? የተባዮች መጫወቻ፣ የተውሳኮች መቀለጃ ሆኗልን? እንግዲያውስ በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡ +ወዳጄ ሆይ ሃይማኖት በተባለችና ከሰማይ በወረደች ልዩ እሳት (ሉቃ.12፡49) ላይ ተቀምጠህ የድስትነትህን ሙቀት መልስ፡፡ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር (1ቆሮ.13፡13) በተባሉ ሦስት ጉልቻዎች ላይ በምቾት ተጥደህ የሕይወትህን የኃጢአት ብርድ አስወግድ፡፡ ንስሐ በተባለች ነበልባል ውበትነት የክረምትህን ጽልመት በምስራቃዊ በጋነት ድል ንሳ፡፡ በሥጋ ወደሙ ፍምነት ድስት የተባለ ሰውነትህን በከዊነ እሳትነት ቀድስ፡፡ እባክህን በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡ ሃይማኖት የተባለ እሳትን ተባይ አይቀርበውም፡፡ እምነት ተስፋና ፍቅር የተሰኙ ጉልቻዎችን ተውሳኮች ሽቅብ አይወጡአቸውም፡፡ የነበልባለ ንስሐን ብርሃንና ሙቀት ነፍሳተ ጽልመት መቋቋም አይችሉም፡፡ ስለዚህ በእሳቱ ላይ እስካለህ ድረስ(በመንፈሳዊ ተግባራት እስከጠነከርክ ድረስ) አንተ ሁሌም ከተባይና ከነፍሳት ብልሽት(ከአጋንንት) የራቅክ ነህ፡፡ ወዳጄ እባክህን ከእሳቱ ላይ አትውረድ፡፡ ወዳጄ ሆይ! እሳቱ በደንብ ይነድ ዘንድ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት የተባሉ እንጨቶችንና ምጽዋት የተባለ ጋዝን መጨመርህን እንዳትዘነጋ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ድስትነት ሁሌም የሞቀ ይሆናል፡፡ እጅ እጅ ከማለት፣ ከመሻገትና የተባይ መጫወቻ ከመሆን ትድናለህ፡፡ ወዳጄ ሆይ እባክህን ከእሳቱ ላይ አይትውረድ፡፡ በኃጢአት እጅ እጅ ከማለትና በበደል ከመሻገት እግዚአብሔር ይሠውረን! አሜን! ©ዘሕሊና                    https://t.me/raiye_mariyam
Show all...
ራዕየ ማርያም ✝

በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35

"ሥላሴን" "ቅድስት ሥላሴ" እያልን በሴት አንቀፅ የመጥራታችን ምስጢር፡- አንድም ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብሎ አይጠረጠሩም፡፡ አንድም ሴት በባህሪዋ ልጅን ታስገኛለች፣ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ፡፡ አንድም ሴት አዛኝ ናት፣ለታናሹም ሆነ ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ፣ ይራራሉ፣ ምህረትን ይሰጣሉ፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ”ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንፃር ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ የምህረት ወንዶች ሥላሴ" በማለት ያመሰጥራል፡፡ ስለእዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው፣ ርህራሄያቸውና፣ ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡ አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም፣ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያቢሎስ እጅ ተይዞ በሐጥያት እንዲታመሙ አይወዱም፣ አይፈቅዱም በመሆኑም “ቅድስት” ይባላሉ፡፡ አንድም ሴት የልጇን ነውር አትፀየፍም ልጄ ቆሽሿል፣ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም፣ ሥላሴም የሰውን በሐጥያት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎብኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንጻር ቅድስት እንላቸዋለን፡፡ አንድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እነደዛው ናቸው በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ፡፡ ስለእዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንፃር ቅድስት ይባላሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን በፍቅር እንጠራለን፡፡ የቅድስት ሥላሴ ረድኤት በረከት አይለየን፡፡         https://t.me/raiye_mariyam
Show all...
ራዕየ ማርያም ✝

በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35

👍 1 1🙏 1
Show all...
new-able.m4a7.34 MB
01:56
Video unavailableShow in Telegram
"ከትውልዱ ማን አስተዋለ" ት. ኢሳ 53÷8 https://t.me/raiye_mariyam
Show all...
5.88 MB
😭 1
00:36
Video unavailableShow in Telegram
Show all...
1.14 MB
2
01:29
Video unavailableShow in Telegram
3.76 MB
03:40
Video unavailableShow in Telegram
12.36 MB
🌿ተስፋ🌿 ‹‹እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ››መዝ 37፡9 ..but those that wait upon the LORD, they shall inherit the earth.Psalms 37:9 ። ልጄ ሆይ ሁል ጊዜም እግዚአብሔርን ተስፋ አድርገው እምነትህ ቢደክም ፍቅር ሲቀዘቅዝ ብታይስ እንኳ ተስፋ ቆርጠህ ወደ ኋላ አትመለስ፡፡ ነገ መለወጥን ተስፋ አድርግ እንጂ ክርስትና ከሥጋና ደም ጋር የምትታገልበት ሕይወት ሳይሆን ትግሉ ከጨለማ ገዥዎች ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር መሆኑን አትዘንጋ፡፡ በሕይወትህ ውስጥ ጠላት ለማጥፋት የሚፈልገው ታላቅ የልብ ሻማ ተስፋ ነው፡፡ የልብህን ተስፋ አጥብቀህ ጠብቅ ተስፋ ካለ ሁሉን መልሰህ ማግኘት ትችላለህ፡፡ ተስፋ ከሌለህ ግን ልታምንም ልታፈቅርም ይከብዳል፡፡ ተስፋ የማታደርግ ከሆነ እንዴት ታምናለህ? ታፈቅራለህስ? ስለዚህ ልጄ ሆይ ዛሬን ብትወድቅ ተስፋ አትቁረጥ ተነስ እንጂ ዛሬ እንደ ቃሉ በፍቅር መኖር ቢያቅትህ መፍትሔው ተስፋ መቁረጥ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ እንጂ ዛሬ በአገልግሎትህ ብትደክም ተስፋ ቆርጠህ ከቤቱ ከቶ አትውጣ፡፡ ከሐዋርያት ጋር ሆነህ ጌታ ሆይ ወደ ማን እሄዳለሁ?  አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ በለው፡፡ ዮሐ 6፡68 ከዳዊት ጋርም ሆነህ አሁንስ ተስፋዬ ማነው አንተ እግዚአብሔር አይደለህምን በለው መዝ 38፡7 ፍሬ ለማፍራትም በእርሱ ተስፋ አድርግ፡፡ በተስፋ ለምትጠባበቀው ለምትሻውም ነፍስ ጌታ ቸር የሚራራም ነውና፡፡ ልጄ ሆይ አዳም ከገነት ቢሰደድ ይዞ የወጣው ሌላ አይደለም ተስፋን ነው፡፡ በጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ እድሜ ልኩን በክፉ ስራ ቢኖርም ተስፋን ግን አልጣለም በመጨረሻ ትንፋሽ ላይ ሳለ ወደ ሕይወት ያደረሰችው ይህች ተስፋ አለመቁረጥ ናት፡፡ በግራ ያለውማ ተስፋ በመቁረጡ የእምነትና የፍቅር ሻማዎቹ ሊበሩለት አልቻሉም፡፡ እንግዲህ ልጄ ሆይ በጊዜውም ያለጊዜውም እርሱን ተስፋ አድርገህ ኑር፡፡ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ https://t.me/raiye_mariyam
Show all...
ራዕየ ማርያም ✝

በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35

👍 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.