cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🌹 የኢስላም ልጆች 🌻

☝️አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ከረሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም።እሱ እጅግ በጣም እሩህሩህና አዛኝ ነው። . . . . . . . . . . 🖊 ሀሳብ አስተያየት ካሎት @Mahmmud_bot

Show more
Advertising posts
791
Subscribers
-224 hours
-27 days
-2830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ልመናህን መቀበል ባይፈልግ ኑሮ ዱዐውን አያገራልህም ነበር!! hafugraphics
Show all...
00:19
Video unavailableShow in Telegram
2.29 MB
በህይወት ውስጥ የትኛውንም ደረጃ ብትደርስ ከአላህ ቀጥሎ ቤተሰብ ትልቅ ድርሻ ይወስዳል ወጣትነት አያታልህ
Show all...
👍 2
sticker.webp0.49 KB
~አንዲት ሴት አጋጣሚዋን እንዲህ ትናገራለች፤ የሆነ ጊዜ ኒቃብ መልበስ ፈለኩና ቤተሰቦቼን ሳማክራቸዉ አባቴም እናቴም ከለከሉኝ።ፍቃደኛ አልሆኑም ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ኒቃብ ለመልበስ ወስኜ ለበስኩ።ቤተሰቦቼ ኒቃቡን ሲመለከቱ ማንም ለትዳር አይጠይቅሺም፣መማር አትችይም፣መስራት አትችይም…እያሉ መጮህ ጀምሩብኝ።የ አላህ መሻት ሆነና በዛዉ ሳምንት  ዉስጥ የሆነ ወጣት ለትዳር ጠየቀኝ። ኒካህ ታሰረ። ባሌም የሆነ ቀን እንድህ አለኝ«ታውቂያለሽ ከ9 አመታት በፊት ነበር የምወድሽ።ኒቃብ እስከምትለብሺ ነበር የምጠብቀዉ። ልክ እንደለበሽ አንቺን ለማግባት መጣሁ» አለኝ። ከአምስት አመታት ብሃላ  ቁርአን  በ10 አይነት አቀራር  አስሀፈዘኝ  በጣም አጋዤም ነበር። || ☞አላህን ፈርቶ ትዕግስት የሚያደርግ ሁሉ አላህ የተሻለ ነገርን ይወፍቀዋል። ወንድም አቡ ሱፍያን
Show all...
ሚስማር ሲመታ እንደሚጠነክረው ሁሉ አማኞች ✔️ችግር ✔️መከራ ✔️ሀሳብ ✔️ትካዜ ሲያጋጥማቸው የበለጠ ችግሮችን እየተጋፈጡ ጉዟቸውን ይቀጥላሉ ምክንያቱም ወርቅ በእሳት ተፈትኖ ወርቅነቱ እንደሚረጋገጠው ያንተም ኢማን የሚረጋገጠው በአፍህ አምኛለሁ በማለትህ ብቻ ሳይሆን በፈተናዎች አጀብ ነውና ምንግዜም በሶብር ጉዞህን ቀጥል ከችግር በኃላም ምቾት እንዳለ አትዘንጋ aboutalah
Show all...
ሰለምቴነት ማሸማቀቂያ አይደለም! ~ አንዳንድ ሰዎች በእምነታዊ ጉዳዮች ላይ ስሜታቸውን ለመከተል፣ ከወረዱበት ለመውረድ ፈቃደኛ ያልሆላቸውን ሙስሊም ወደ ኋላ ታሪኩ በማጠንጠን “አንተ ሰለምቴ አይደለህ? ምን ታውቃለህ?” እያሉ ሊያሸማቅቁ ይጥራሉ። የተለየ አውቀው፣ የተሻሉ ሆነው ሳይሆን እንዲሁ የነሱን ስሜት ተከትሎ ስላላጨበጨበ ብቻ አንድን ሙስሊም በዚህ መልኩ ለማሸማቀቅ መሞከር ጋጠ-ወጥነት ነው። ሰለምቴነት ክብር እንጂ ነውር አይደለም። ሰለምቴነት ገድል እንጂ ማሸማቀቂያ አይደለም። በዚህ ፈተናው በበዛበት፣ የጥፋት ሃይሎች በሚርመሰመሱበት፣ ኢስላምን የሚያጠለሹ አካላት እንደ አሸን በፈሉበት፣ እጅግ ከባባድ ማደናገሪያዎች ያለ ገደብ በሚለቀቁበት ዘመን በምንም ሰበብ ቢሆን ወደ ኢስላም የሚመጡ ሰዎች ሊከበሩ እንጂ ሊነቆሩ አይገባቸውም። ድክመትም ካለባቸው መሸፈ፞ን እንጂ ማጋለጥ አይገባም። ከቻልን ሞራል እንስጥ። ይህን ማድረግ ካቃተን በማሸማቀቅ ገፍተን እንዳናስወጣቸው እንጠንቀቅ። ክርስቲያን ወይም አይሁድ የነበረ ሰውኮ ወደ ኢስላም ቢገባ በእጥፍ እንደሚመነዳ ነብዩ ﷺ ተናግረዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም] አልኢማም አልቡኻሪ ረሒመሁላህ በሶሒሐቸው بَابُ فَضْلِ مَنْ أَسْلَمَ مِنْ أَهْلِ الكِتَابَيْنِ የሚል ርእስ እንዳሰፈሩ እናስተውል። ‘ፈድል’ ማለት ልቅና፣ ብልጫ ማለት ነው። ነብያችን ﷺ ለሮማው ንጉስ ሒረቅል በፃፉት ደብዳቤ ላይ ወደ ኢስላም ሲጠሩት ምን ነበር ያሉት? أَسْلِمْ تَسْلَمْ، يُؤْتِكَ اللَّهُ أَجْرَكَ مَرَّتَيْنِ “ስለም። ትድናለህ። አላህ ምንዳህን #ሁለት_ጊዜ ይሰጥሀል።” [ቡኻሪና ሙስሊም] ይሄ መልእክት በሒረቅል ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። የኢብኑ ሐጀርን ማብራሪያ ይመልከቱ። [ፈትሑል ባሪ፡ 8/221] በነገራችን ላይ አንድ ካ^ፊ^ር ወደ ኢስላም ከገባ ከመስለሙ በፊት ሲፈፅማቸው የነበሩ መልካም ስራዎች ይታሰቡለታል። ሐኪም ብኑ ሒዛም ረዲየላሁ ዐንሁ “በዘመነ ጃ^ሂሊያ ስፈፅማቸው ስለነበሩት ዒባዳዎች፤ ሶደቃ፣ ባሪያ ነፃ ማውጣት፣ ዝምድናን መቀጠል በተመለከተ ንገረኝ እስኪ። ምንዳ ይኖራቸዋልን?” ብለው ነብዩን ﷺ ቢጠይቁ እንዲህ ብለው ነው የመለሱላቸዋል፡- أَسْلَمْتَ عَلَى مَا أَسْلَفْتَ مِنْ خَيْرٍ “ካሳለፍከው መልካም ስራ ጋር ነው የሰለምከው።” [ሶሒሕ ሙስሊም] ልብ በል! ሐኪም ብኑ ሒዛም ከመካ መኳንንት የነበሩ ሲሆን በድር ላይ ከቁረይሾች ጋር ተሰልፈው ጦርነቱን ተካፍለዋል። አላህ ሲያድላቸው እንደ አጋሪ ጓዶቻቸው በድር ላይ ሳይገደሉ በመትረፋቸው ኋላ ላይ ሰልመዋል። ለዚህም ነበር “የበድር ቀን ከመገደል ባተረፈኝ ጌታ ይሁንብኝ” እያሉ ይምሉ የነበሩት። ወንድሜ ሆይ! 1. እስኪ የነዚያን በጀነት የተመሰከረላቸውን ሶሐብዮች ታሪክ እናንብብ። ከነዚያ ታላላቅ የኢስላም ፈርጦች ውስጥ ቀድሞ ጣኦት አምላኪ የነበሩት'ኮ እጅግ በርካታ ናቸው። 2. እስኪ የነ ዐብደላህ ብኑ ሰላም፣ የነብያችን ﷺ ሚስት ሶፊያን ታሪክ እናገላብጥ። ከነዚያ እንቁ ሶሐብዮች ውስጥ ቀድሞ አይሁድ የነበሩት ብዙ ናቸው። 3. እስኪ የነ ሰልማኑል ፋሪሲ፣ ዐዲይ ብኑ ሓቲምና መሰል ሶሐቦችን ታሪክ እንፈትሽ። አዎ ከነዚያ ወደር የለሽ የኢስላም ጀግኖች ውስጥ ከመስለማቸው በፊት በክርስትና ውስጥ ያለፉ ነበሩ። 4. ከሶሐቦች ጊዜ ወዲህም ታሪክ የሰሩ፣ ለኢስላምና ለሙስሊሞች በዋጋ የማይተመን ውለታን የዋሉ በርካታ ሰለምቴዎች አልፈዋል። ልብ በል ወንድሜ! ልብ በይ እህቴ! ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት እንጂ የማንም ግላዊ ንብረት አይደለም። ኢስላም ለሰው፣ ለጂኑ ባጠቃላይ የቀረበ አምላካዊ መድህን እንጂ ያሰኘንን የምናስገባበት፤ የደበረንን የምናስወጣበት ያ'ባታችን ግቢ አይደለም። ኢስላም ልክ ቄሶች “ውጉዝ ከመ አሪዮስ!” ብለው እንደሚያባርሩት ሸይኾችም እንዳሻቸው የሚፈርዱበት ቀልደኛ ቀኖና የለውም። ስለዚህ ወንድሜ! እስልምናን ከአባት ከአያት የወረስከው አንተ፣ በኢስላም ላይ ከሰለምቴው የተለየ የባለቤትነት መብት የለህም። ከአላህ ዘንድ ያለህ ደረጃ ከፍ የሚለው በተቅዋህ ብቻ ነው። ለሰለምቴው ኢስላምን የሰጠው የፈጠረው ጌታ እንጂ እኔ ወይም አንተ አይደለንም። እኛ ይህን የጌታ ፀጋ አከፋፋዮች አይደለንም። ምናልባት “በሰለመ በማግስቱ ፈትዋ ካልሰጠሁ ብሎ የሚገላገል ሰለምቴስ ዝም ይባል ወይ?” የሚል ሊኖር ይችላል። ይሄ ሌላ ርእስ ነው። እያወራሁ ያለሁት ሰለምቴነትን ለማነወሪያነት ስለሚጠቀሙ አካላት ነው። የነሱን ስሜት ተከትሎ ስላልፈሰሰ ብቻ “እሱ'ኮ ሰለምቴ ነው?” በማለት ለማንጓጠጥ መሞከር ምን ማለት ነው? እስኪ አስቡት! በሚያጋጥሙ አንዳንድ አለመግባባቶች የተነሳ “እሱ'ኮ መስለሙንም እንጃ!”፣ “እሱ'ኮ የሰለመ ጊዜ ቄሶች በደስታ እንኳን ሄደልን ያሉት ነው”፣ “እሱ'ኮ እንደገና ወደ ክርስትና ሳይመለስ አይቀርም”፣ “እሱ'ኮ ሶላት አይሰግድም"፣ "እሱ'ኮ ውዱእ ሲያደርግ ታይቶ አይታወቅም"፣ "እሱ'ኮ ይሰክራል …” ወዘተ በሚሉ እጅግ ሰቅጣጭና ፀያፍ ውንጀላዎች በሃሰት የሚወ፞ነጀል ሰለምቴ ምን እንደሚሰማው አስቡ። በተጨባጭ የተከሰቱ ሃሰተኛ ውንጀላዎችን ነው በምሳሌነት የጠቀስኩት። ተወንጃዮቹ ልፍስፍስ ቢሆኑ በቀላሉ ወደ ኩ^ፍ^ር ተገፍተው ከኢስላም በሸሹ ነበር። ግና ኢስላም ማለት የነዚህ ዋልጌዎች የግል ንብረት እንዳልሆነ ጠንቅቀው ማወቃቸው በጃቸው። ሰዎቹን ከማወቃቸው በፊት ኢስላምን ማወቃቸው ጠቀማቸው። እንጂ እንደዋዛ አኩርፈው በበረገጉ ነበር። ወላሂ! አንድ ስንት ስራ የሰራ ወንድም ፈፅሞ ይዋሻሉ ብለን በማንገምታቸው ሰዎች በተደጋጋሚ በመወ፞ንጀሉ የተነሳ ብዙ ሰዎች እስልምናውን እስከሚጠራጠሩት የደረሱበት ሁኔታ በተጨባጭ አውቃለሁ። መነሻው ግን የእነዚያ ታማኞች የመሰሉን ሰዎች ክፋት ነበር። በተረፈ ሰለምቴ ሆነው ስንቶችን ቁጭ አድርገው እየገሩ ያሉ ኡስታዞች አሉ?! ሰለምቴ ሆነው ለስንቶች መስለም ሰበብ የሆነ ስራ ላይ በሰፊው የዘመቱ አሉ?! ካረገዙ በኋላ በባሎቻቸው ተከድተው ብዙ ፈተና ቢደርስባቸውም ከነ ችግራቸው በኢስላማቸው ላይ እንደፀኑ ያሉ ስንት ሰለምቴዎች አሉ?! ወንድ ወይም ሴት ተከትለው ስንቶች በሚከ^ፍ^ሩበት ዘመን ለኢስላም ሲሉ ከቤተሰብ የተቆራረጡ፣ ትዳራቸውን የበተኑ ስንት ቆራጥ ሰለምቴዎች አሉ?! ነባር ሙስሊሞች በእርዳታ በቆሎ እምነታቸውን በሚቀይሩበት ምድር ለኢስላም ሲሉ ሁለ ነገራቸውን አጥተው ለእለት ጉርስ የተቸገሩ ስንት ፈተና ያልበገራቸው ሰለምቴዎች አሉ?! ደግሞም አላዋቂ ሰለምቴ እውቀት በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ ያላቅሙ ገብቶ ካገኘን ብቃቱ ካለን በአደብ ማስተማር እንጂ ሰለምቴነቱን ለማሸማቀቂያ መጠቀም፣ ሰለምቴነቱን እንደ ነውር በመቁጠር በየደረሱበት ማማት የለየለት ነውር ነው። መሀይም የሆነ ሰው ሰለምቴም ባይሆን ያላቅሙ እንዲያወራ የተሰጠው የተለየ ፍቃድ ወይም መብት የለውም። ስለዚህ ሰለምቴው በተለየ የሚኮነንበት ምክንያት ምንድነው? ሰለምቴ ሆኖ ከብዙዎቻችን የተሻለ ግንዛቤ ያለው ስንት ሰው አለ? ከውልደት እስከ እርጅና እድሜውን ኢስላም ውስጥ አሳልፎ አሊፍ ትቁም ትጋደም የማያውቅ እልፍ አእላፍ ህዝብስ የለም ወይ? እውቀት'ኮ በመማር እንጂ በውልደት የሚገኝ አይደለም። “ሸንበቆ አስር አመት ውሃ ውስጥ ቢቆይ አዞ አይሆንም” ይባላል። ለውጥ ከአላህ እገዛ ጋር በጥረት እንጂ በምኞትም በጉራም አይገኝም። (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 01/2012)
Show all...
👍 1
በጥበቡ አንድን በር ይዘጋና፤በእዝነቱ ሺህ በርን ይከፍትልሃል። የኔ ጌታ…
Show all...
01:10
Video unavailableShow in Telegram
2.86 MB
01:33
Video unavailableShow in Telegram
7.36 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.