cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የግጥም ሪዞርት

የግጥም ሪዞርት የተለያዩ ግጥሞች መነባነብ ትረካ እንዲሁም ለሰው ለመላክ የምትፈልጉትን ሀሳብ የምታንፀባርቁበት። እየተዝናኑ ይደሰቱበታል። More information contact wits us 👉 @zemanhatty

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
361
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

።።።።።።።ፍቅር እስከ... """"""""""""""" ሞት አቀረቀረ ዳግም አንገት ደፋ የጌታ ሲገርመው ይህው በኛም ፍቅር ራሱን አጠፋ (ነብስ ይማር ብለናል) እኛ እኮ... ፍቅር እስከ የለውም ፍቅር ጫፍ የለውም ብለን ያወራነው ጫፍ ነው ካሉት ስፍራ ሄደን ስላጣነው ስላላገኘነው! ሄደን አይተነዋል ሄደን አተነዋል እስከ ጫፍ አጥናፉ ጋሽ ሀዲስ ተሳስቷል መቃብር አይደለም የፍቅር ቤት ጫፉ መቃበር አይደለም መቃብርማ እኮ... ሲከፍቱት ሚከፈት ሲዘጉት ሚዘጋ የነበሰቢስ አፀድ የሙታኖች አልጋ መቃብርማ እኮ... የመሬት ውስጥ መሬት የሞት ተቀ'ባይ ቤት እንዴት ይቻለዋል ዘላለሙን ፍቅር ማስቆም በሞት ስሌት ሞት እኮ ጊዜ ነው ሞትእኮ ሞኝ ነው በዘመን ሚታለል በዘላለም ዕድሜ ዕድሜው የሚገታ በዕድሜ ሚዘለል ስለዚህ... ደራሲያን አድቡ ፀሀፊያን አድቡ ዘላለሙን ፍቅር እስከ በምትል ቃል ቀኑን አትገድቡ ዋ!!!..ባለ ብራና ዋልኝ ባለ ቀለም ይቅርና መቃብር ዘላለም ላይ እንኳን ፍቅር ጫፉ የለም ዜማ የግጥም መሰርት @yegxmrizort @yegxmrizort
Show all...
ጎን-እጣ . . . ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት መንሳት ምን ይደንቅ የእግዜር ሴትን መፍጠር ምን ይረቅ በማይመረመር በረቀቀ ስሌት ተፈጠርሽ አንቺ ሴት ረቂቋን አንቺን ያየሁኝ ሲመስለኝ ሚስቴ ናት ምላትን ያገኘሁ ሲመስለኝ ብዙ ነበር ጉዱ ለሰሚው ግራ ነው ማፍቀር ካለመዱ አሁን ለምሳሌ...... ይሄን ግጥም ስፅፍ የጥርስሽን ነገር ጥጥ ይሁን በረዶ ስከራከር ነበር አሁን ለምሳሌ..... አይኔ አንቺን ያየ'ለት የልቤ ሁናቴ ፍቅር ይሁን ግርምት አለየልኝ እቴ አሁን ለምሳሌ...... ግጥሜ ቤት ሲመታ የብዕሬ ቀለም እንደመጀመሪያው ሰማያዊ አይደለም አሁን ለምሳሌ ምሳሌ ነዝናዛ ዋጋ አለው ካንቺ ይህ ልቤ ሲገዛ ከጥርስሽ ጀምሬ ከንፈርሽን ሳልነካ ሚያወነባብደኝ ሳቅሽ ነበር ለካ ምናለ ባትስቂ ጨርሼ እስካይሽ ማለቂያ እንደው የለው ይሄ ሴትነትሽ ማማርሽ ውቅያኖስ ቀረሁኝ ጠልቄ መልክሽ ካይኔ ሆኖ ሄደሽ መኖርሽን እኔ መች አውቄ ውበትሽ ይቀራል ሳቅሽ ሲታከለው ግዴለሽም ላንዴ ከንፈርሽ ግጠሚ ሃሳቤን ልግጠመው ግጥም ግጥምጥም ያኗኗሬ ሙላት የህይወቴ ጣዕም አንቺ ሴት ሙላቴ አንቺ ሴት ውበቴ ገላሽ ከገላዬ-አጥንትሽ ካጥንቴ ሌጣዬን ብኖርም የኖርኩ ቢመስልም አንቺን ሳገኝ ነው ምትሞላው የኔ አለም እናልሽ አካሌ..... ከባዶነት ቅዠት ከብቻነት እንቅልፍ በመምጣትሽ ልንቃ አንድ ሆኜ ልትረፍረፍ (እንዳትቀሪ!!) ✍ቀባጣሪው https://t.me/betmetabetdefa https://t.me/betmetabetdefa https://t.me/betmetabetdefa
Show all...
።።።።።።።።እኔን ብሎ *ጂ በእውቀቱ ስዩም @yegxmrizort @yegxmrizort @yegxmrizort
Show all...
688f51ea43ce2ea30f428d6d0bee1f4e.mp33.71 KB
Photo unavailableShow in Telegram
።።።።።።እኔ ወድሻለው """""""""""""""""" (በእውቄ ስታይል) የታገተን ወንድም ሄዶ እንደማስፈታት ወያኔን ከሸኔ ደርቦ እንደመምታት እኔ ወድሻለው ልክ እንደ ደሞዝ ቀን ልክ እንደ ቅዳሜ ጎል እንደማስቆጠር ከሜሲ ፊት ቆሜ በFollowእንደመብለጥ ከነ khaby ላሜ(🤗) እኔ ወድሻለው እንደ ጀነት አባል እንደ አበው አባባል በጋሽ ፀጋዬ አፍ ሀጠራው እንደመባል እኔ ወድሻለው እኔ ወድሻለው እንደ እናት ምርቃት ካንቺ ጋ እንደማንጋት እንደ ሞውሊድ አፍጥር እንደ ሙሴ በትር እንደ መጀመሪያው እንደ ቢላል ሶላት ከሀይሌ ሪዞርቶች 3ቱን እንደመግዛት እኔ ወድሻለው መውደድ እስኪወደድ ወሰኑን እስኪያጣ ፀጉር እስኪያበቅል የሰይፉ መላጣ እኔ ወደሰሻለው በበጉ ልደት ቀን በቀኙ እንደመቆም የሲዖልን ደጃፍ መከርቸም የሚያስችል ስልጣን ላይ እንደ መሾም እኔ ወድሻለው እወድስሻለው እንደ መንፈስ ቅኔ እንደ ያሬድ ሸማ አንቺ የኔ እውነት እኔ ያንቺ ዜማ ዜማ የግጥም ሪዞርት @yegxmrizort @yegxmrizort
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
።።።።።።።።በዝምታ!!! """"""""""""" እነሱ... በለኮሱት የሞት ክብሪት፣ ነብስ አምዳ ስትበተን እንደ ጉሊት። ተው' ዝም አትበሉ! በራሳቹ የቤት ውሻ ራሳቹ ስት'በሉ ጎበዝ!!!. ፅድቅ እኮ ነው አንዳንዴም ማሰማት ዋይዋይታ ማደርጀት ውትወታ እንዴት ዜማ ይሰምራል ያለ ቅኝት ያለ ኖታ፣ እንዴትስ ነው ሀገር ሚቆም እያዋሩን በዝምታ። ዜማ የግጥም ሪዞርት @yegxmrizort @yegxmrizort
Show all...
።።።።።።።።ብሉይ ፍቅር """""""" """""" ወድሻለው ማለት አፈቀርኩሽ ማለት ቀሎ' ባይገልፅልኝ የማፍቀሬን እውነት። መሲሁን ሆንኩልሽ.... ከሰማይ ወርጄ በረት በቀልኩልሽ ታውቂለሽ አአአ? ውዴ..... ወንድነት ሞኝ ነው ወንድነት ግብዝ ነው ከጎዶሎ እሚፈስ የኔ ላሉት ሁሉ እሱነቱን ሰቶ የሱን ሴት እሚከስ አየሽ.. ከወንድ አነስኩልሽ ከሰው ኮሰስኩልሽ እንደ ፆመፀሎት ስጋዬን ለፍቅር እየከሰስኩልሽ እኔ እኮ አንቺዬ.... ፍቅሬን እንድታዪ ፍቅሬን እንድታምኚ ልክ እንደ ክርስቶስ እሞትልሻለው አንቺ እንድትድኚ ልክ እንደ ክርስቶስ... እንደ ዝናብ በርኖስ ቀልጦ እንደ ሚበራ እንደ እረኛ ፋኖስ። ላአንቺ ስል ለፍቅር ስል ለፍቅሬ ስል የፍቅርን አምላክ ፍቅሩን ስመስል... ብሉይ በደልሽን በልቤ ተሸከምኩ ከመስዋትሽ ፊት ዋኖስ ሆኜ ሞቼ ለሞትሽ ተቃጠልኩ ደሞም የኔ ፍቅር ልገረፍ ለሀጥያትሽ ልሰቀል ለሞትሽ ፍቅር መሰ'ዋት ነው ጠፍቼ ላቁይሽ ከክብሬ ልቀነስ የሞት ፅዋን ልቅመስ መውደዴ ፅድቅ ሆኖ ከሀዲስ እንዲጠቀስ እቴ የኔ ገላ... ሆኜ ላስደስትሽ ለክረምትሽ ፀሀይ ግብሩ ምን ሆነና የአንድ አፍቃሪ ፀባይ ደሞም ልሁንሽ ለበጋሽ ደመና ወድሻለው ማለት አፈቀርኩሸ ማለት ፍቅርን ለማሳየት ከቶ አይበቃምና ዜማ የግጥም ሪዞርት join & share @yegxmrizort yegxmrizort @yegxmrizort yegxmrizort
Show all...
።።።።።።ለውጥ """""""""" ተገፍተን ተገፍተን ተገፈ'ን ተገፈ'ን ማንነት ስናጣ፣ ይህው እኛኑኑ ለእኛው የሚሸጠን ደግ!! ቡድን መጣ። ዜማ @yegxmrizort ፍትህ እየታገቱ በገንዘብ ለሚለወጡ ወንድም፣እህት፣እናት፣አባት፣ና ዘመዶቻችን!!!።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
።።።።።።ሽንፈት """""""""""" እንደ ፈርዖን ድል እንደ ይሁዳ እድል ባጋደለ'ው ሁሉ ህዝብሽን እንደ ክር ስበሽ ከምትሰፊ፣ እስቲ ለአንድ ጊዜ ባክሽን ኢትዮጵያ ለእግዚያር ተሸነፊ። ዜማ የግጥም ሪዞርት @yegxmrizort @yegxmrizort
Show all...
ቀረሽ እንደዋዛ •┈┈•✦•┈┈• ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስ ቆጥር ትመጫለሽ ብዬ ሰዓቱን ስቆጥር ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር ብርድ አቆራመደኝ የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ ውርጩ ቀለደብኝ ጨለማው ሳቀብኝ። አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ መስኮቶች ጨልመው ቤቶች ተቆልፈው ከተማው ሲተኛ አይተዋል ያያሉ አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ። ------------------------------- ©✍ገብረክርስቶስ ደስታ @yegxmrizort @yegxmrizort
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.