cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

በፌስቡክ ያግኙን፤ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool በድኅረ ገጽ ያግኙን፤ http://www.finotehiwotsundayschool.com

Show more
Advertising posts
11 641
Subscribers
-624 hours
-377 days
+330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#መስከረም 10 ተቀጸል ጸጌ ፤  #ግማደ_መስቀሉ ከእስክንድርያ በንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ቀን  ፨ ተቀጸል ጽጌ የሚለውን ምስጢራዊ  መዝሙር የጀመረው የዜማና የቅኔ መሰራች የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ የመሠረተውም በ6ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን  #በአጼ #ገብረ_መስቀል ዘመነ መንግሥት ነው  የክረምቱና የልምላሜው ጊዜ አልፎ የአበባውና የፍሬው ጊዜ በሚተካበት በመስከረም 25  ቀን ቅዱስ ያሬደ ውደ ንጉሡ  ዙፋን ቀረቦ #ተቀጸል_ጽጌ _ገብረ_መስቀል_አጼጌ በማለት ዘምራል ፡፡  ተቀጸል ጽጌ ብዙ ምስጢር ሲኖረው   ጽጌ (አበባ) የተባለ የንጉሠ ነገሥቱ #ዘውድ ነው ፤ እግዚአበሔር የንጉሡን ዘመን እንዲባርክለት ዘውዱን እንዲቀድስለት ፤ ተቀጸል ጽጌ  አጼጌ ፤ #ንጉሥ_ሆይ_ዘውድን_ተቀዳጅ_እያሉ_ለንጉሡ_ይጸልዩለታል ፡፡ ሌላዉ ትርጓሜ ደግሞ ጽጌ የተባለች #ሃይማኖት ናት  ፡፡ በኦሪት ቤተ መቅድስ #ያቁምና #በለዝ የሚባሉ ሁለት አዕማዶች  በቀኝና በግራ ተተክለው የቅዱስ #ጴጥሮስና  #ጳውሎስ ምሳሌ ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡ በሁለቱ አዕማድ ራስ ላይ አንዲት አባባ ተቀርጻ ትታይ ነበር እሷም #የሃይማኖት ምሳሌ ነበረች፡፡ በዚሁ ዕለት በመዘምራኑ የሚነገረው ቀለም ፤ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በሃይመኖት እልፍ ክርስቲያኖችን ማፍራታቸውን  በጉልህ ያስረዳል፡፡በሃይማኖተ አበው ላይ ፤ አሕዛብ አስተጋብኡ ጽጌ ረዳ ወሦኩሰ ተረፈ በኃበ አይሁድ ( አሕዛብ አበባ ሰበሰቡ እሾህ ግን በአይዱ ዘንድ ቀረ ) ተብሎ ስለተጻፈ ጽጌ የሚለውን ቃል ሃይማኖት ተብሎ እንደሚተረጐም ታሞኖበታል ፡፡ ከዚህም በመነሳት ሊቃውንት መዘምራን ሁል ጊዜ ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ይህን ዝማሬ ለንጉሡ ያቀረባሉ ሊቃነ ጳጳቱም   ከቤቱ መንግሥቱ የቀረበላቸውን የተጐነገጐነ አበባ በመስቀላቸው ባርከው  ያማረውን አበባ  ለንጉሡ #ያድላሉ ከዛም ደግሞ  ለሌሎች አገልጋዮች እንደየ ማዕረጋቸው ይታደላል ፡፡ ይህ ስርዓት #ከአፄ_ገብረ_መስቀል ዘመነ መንግሥት እስከ #አፄ_ዳዊት_ዳግማዊ ድረስ በየዓመቱ መስከረም 25 ሲፈጸም ቆይቶ  በአፄ ዳግማዊ ዳዊት አማካኝነት ግማደ መስቀሉ መስከረም 10 ወደ ኢትዮጵያ ባስገባበት ቀን እንዲከበር  በሊቃውንት ተወስኖ  የአፄ መስቀል ( መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት )ና የተቀጸል ጽጌ  በዓል እስከ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይል ሥላሴ ድረስ በቤተ መንግሥት እና በቤተ ክህነት ሲከበረ ቆይቶ  ኃላ ደግም በቤተ ክህነት እስከ አሁን ድረስ እየተከበረ ይገኛል ፡፡   ለመጨረሻም ጊዜ ለንጉሠ ነገሥቱ የተዘመረው #ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሲሆን #ተቀጸል_ጽጌ_ኃይለ_ሥላሴ አጼጌ ተብሎ ተዘመሮ ሲያበቃ ለሊቀ ጳጳሳቱ  ድግሞ ጸሎቱን ማቅረብ ቀጥሏል፡፡  በዓሉ በቅድስት ሥላሌ ቤተክርስቲያ አሁን ድረስ ስርዓቱ በዓመት በዓመት መስከረም 10 እየተፈጸመ ይገኛል ፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፨፨፨ ፨፨ #መስቀሉ እንዴት ወደ ኢትዮጵያ እጅ ገባ ?? የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ #አባ ሚካኤል  በአሕዛብ ንጉሥ  በነበረው መርዋን ታሰሩ ይህ ንጉሥም ክርስቲያኖችን ማሰቃየትም ጀመረ  ፡፡  በዘመኑ የነበሩት  ንጉሥ አፄ #ሠይፈ አርዓድ የግብጽ ክርስቲያኖች ላይ መከራ እንዳበዛባቸው በሰሙ ጊዜ ፤ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለው ወደ ግብጽ ዘመቱ ፡፡ ንጉሡ  ከመድረሱም በፊት ደብዳቤ ጻፋ ፤ ሊቀ ጳጳሱን እንዲፈታና ክርስቲያኖችን እንዲተው አስተነቀቁት ፤ ደብዳቤውን ካየ በኃላ  እጅግ ፈርቶ ሊቀ ጳጳሱን ከእስራት  ፈታቸው  ንጉሱም ለበረከት እንዲሆናቸው ከጌታ ወርቅ(የሰበዓ ሰገል ወርቅ ) ጋር እንዲቀመጥ የእጅ መንሻ ወርቅ ለሊቀ ጳጳሱ ላኩላቸው ከዛ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ ፡፡ ከዚህ በኃላ  እርሳቸው ሞተው የእመቤታቸን ወዳጅ የሆነው ልጃቸው ዳግማዊ ዳዊት ነገሠ  ፡ አሕዛቡ  ንጉሥ ሞታቸውን በሰማ ጊዜ አባ ሚካኤልን ዳግመኛ አሰራቸው ፤ ከዚያም የሮም የቁስጥንጥንያ የሶርያ የአርመን ፣ የግብፅ ክርስቲያኖች በአንድ ሆነው ለኢትዮጵያው ንጉሥ ለዓጼ ዳዊት፤ የክርስቶስን ሃይማኖት ለማጥፋት የአህዛብ ነገሥታት ቆመዋል የሚል  መልእክት ላኩ ፡ ዓጼ ዳዊት ይህን በሰሙ  ጊዜ መሃላ በመማፋረሱ ተናደዱ ፡፡መንፈሳዊ  ቅንዓትም አድረባቸው፡፡  ክተት ሠረዊት ብለው  ለጦር ዘምተው ካርቱም ሲደረሱ  #ግዮን (አባይ )ን መልስው ወደ ካሩተም በረሐ ሰደዱት የግብፅ ሰዎች ከእርሱ በቀር የሚጠጡት የለምና ፡፡ የምስሩ ንጉሥ እና መኳኳንንቶች ይህን በሰሙ ጊዜ ያረጉት ስህተት እንደሆነ ተረዱ ደንግጠው ሊቀ ጳጳሱን አባ ሚካኤልን ፈቱዋቸው ከሞት የተረፉትን ምእመናን ነጻ አወጧቸው ፡፡  ለዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ያማልዱት ዘንድ ለመነ። ክርስቲያኖችም ይህንን በሰሙ ጊዜ ነጻ ላወጣቸው ንጉስ  አመላካቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ ፡፡ የግብፁ መኳንንት እጅ መንሻ ወደ ንጉሡ ላኩ   ፡ ንጉሥ ዳዊትም  ሊቀ ጳጳሱ መፈታታቸውን በሰሙ ጊዜ አስዋን ድረስ ወረዱ ይህም በጊዜው ለኢትዮጵያ እና ለግብጽ የወሰን ድካ የነበረው ነው ፡፡ ሰኔ 10 ቀን ከሊቀ ጳጳሳቱ እና ከመኳኳንንቱ ጋር ተገናኙ ፡፡  የአባይን ውሃ እንዲመልሱላቸው እልፍ ወርቅና ይዘው ቢጠይቋቸው ይህ ለኔ ነፍስ ለማዳን  አይጠቅመኝም አሉ   ፡፡ እኔ የምፈልገው የጌታቸንን መስቀል ነው አሉ ፡፡ እነርሱም ከተመካከሩ በኃላ መንፈሳዊ ንጉሥ መሆኑን አይተው ይገባዋል አሉ ፡፡   መስቀሉንም  አስረከቧቸዉ  እርሱን ብቻ ሳይሆን #ሉቃስ የሣላቸውን ሰባቱን #የእመቤታችንን ሥዕሎች ፣ #ዮሐንስ ወንጌላዊ የሣለውን የጌታቸንን #የኵርዓተ ርእሱን ሥዕል ጭምር እንጂ ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው #መስከረም 10 ቀን ነው በዚችም ዕለት በመላው ኢትዮጵያ ብርሃን ሆነ ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦችም መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ  እያሉ ዘመሩ ይህን ልማድ በማድረግ አሁን ድረስ በዓሉ  ይከበራል የበዓሉም ስም #አጼ_መስቀል እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚህ ቦኃላ ወደ ጥንት ላማዱ እንዲሄድ የአባይን ወንዝ መለሰው ለግብጻዊያኑ ለቀቁላቸው ፡፡ ከቅዱስ መስቀሉ ረድኤት በረከት ይክፍለን        አሜን! /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/     #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot      www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 11 4
"ለቅኖች ምስጋና ይገባቸዋል " መዝ 33፥1 #ለታላቁ_ሊቅ_መጋቤ_ሃይማኖት_የኔታ_ዲበኩሉ_ኃየሰ ለቅድስትቤተ ክርስቲያን ከልጅነት እስከ ዕውቀት ከዕውቀት እስከ እርጅና ያለ መሰልቸት ላበረከቱት ታላቅ አገልግሎት ቤተ ክርስቲያን ልታመሰግናቸው #መስከረም_4 ቀን ቀጠሮ ይዛለች እርስዎስ ሊቁን ለማመስገን በዕለቱ ከቀኑ 7:00 ላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋህዶ አዳራሽ እንዲገኙ ተጋብዘዋል ። #መረጃው ለሌሎችም ይደርስ ዘንድ ሼር ማድረግን አይዘንጉ ለበለጠ መረጃ 0913645538 ፤ 0920724765 Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram...  https://t.me/finotehiwott http://tiktok.com/@finotehiwot  .YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w                    www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
Show all...
👍 15 8
#በዓለ_ርዕሰ_ዐውደ_ዓመት_ዮሐንስ_ወቅዱስ_ራጉኤል #እንኳን_አደረሳቹ #ዐዲስ_ዓመት ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ የመሸጋገሪያው ዕለት በየዓመቱ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ የዘመን መለወጫ፣ እንቁጣጣሽ፣ ሌላም መጠሪያ ስሞቹ ናቸው፡፡ በግእዝ ርእሰ ዐውደ ዓመትም ይባላል፡፡ ይህ በዓል የዓመት መጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን በየዓመቱ ወሮች በመጀመሪያ ቀን ይከበራል፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል 12 ሰዓት ይሆናል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ሲቆጥሩ 364 ቀናት ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ለዘመን መታወቂያው ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትንም ፈጠረ” ይላልና /ሔኖክ. 21፥49/፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ በፍል ውኃ አጥለቅልቆ በኃጢአት ሕይወት ይኖሩ የነበሩት የኖኅ ዘመን ሰዎች ቀጥቶ ካጠፋ በኋላ ከንፍር ውኃ ምድር የተገለጠችበት ወር ነው /ኩፋሌ. 7፥1/፡፡ “በመጀመሪያው ወር ምድር ታየች የንፍር ውኃም ከምድር ደረቀ” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት አድርገው የአቡሻኸር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስቀምጣሉ፡፡ ✞ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናዊ ሥርዐት ያጠኑ ሊቃውንት ደግሞ አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን መሆኑን አስመልክተው በክታባቸው እንዳስቀመጡት በአራቱ ወንጌላውያን ዘመኑን ይከፍሉታል፡፡ ምክንያቱም በዘመነ ዮሐንስ ተፀንሶ በዘመነ ማቴዎስ ተወልዶአል፡፡ በዘመነ ማርቆስ ተጠምቋል፡፡ በዘመነ ሉቃስ ተሰቅሎ ዓለምን ከፍዳና ከመርገም ነጻ አውጥቷል፤ እያሉ ታሪካዊ ሐረጋቸውን ጠብቆ አራቱ ወንጌላውያን ተከትለው ያለ እንቅፋት እንደሚጓዙ ያስረዳሉ:: #እንቁጣጣሽ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሳባ የጠቢቡ ሰሎሞንን ዝና ሰምታ ኢየሩሳሌም ተጉዛ ስትመለስ “እንቁ ለጣትሽ /ለጣትሽ እንቁ/ በማለት ከእንቁ የተሠራ የጣት ቀለበት ንጉሥ ሰሎሞን እጅ መንሻ እንዲሆናት አበርክቶላት ነበርና ይህን ታሪክ መነሻ አድርገው “እንቁጣጣሽ” የሚለው ስያሜ ከዚያ እንደመጣ የታሪክ ድርሳናት ያስረዱናል ፡፡ በኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ዕለት ምድሪቱ በክረምቱ ዝናብ ረስርሳ ድርቀቷ ተወግዶ በአርንጓዴ እጸዋት ተውባ ሜዳው፣ ሸለቆውና ተራራው በአደይ አበባ ተንቆጥቁጠው የሚታዩበት ወቅት በመሆኑ ዕለቱ “እንቁጣጣሽ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ ወቅት ሕፃናትና ልጃገረዶች ነጭ ባሕላዊ ልብስ በመልበስ ለምለም ቄጤማና አደይ አበባ በመያዝ በአካባቢያቸው በመዞር አዲስ ዘመን መበሠሩን “እንኳን አደረሳችሁ” በማለት በቸርነቱ ዓመታትን የሚያፈራርቀውን እግዚአብሔርን በዝማሬ ያመሰግናሉ፡፡ መልካም_አዲስ_ዓመት #ራጉኤል ሊቀ መላእክት:- ራጉኤል ማለት የብርሃናት አለቃ ማለት ነው። የብርሃናት አለቃ ሲባል ፀሐይን፣ ጨረቃን እና ከዋክብትን በማመላለስና ለሰው ልጆች፣ ለአዝርዕት፣ ለእንስሳት፣ ለአራዊት ሁሉ ብርሃንን የሚመግብ ነው ማለት ነው። አንድም ራጉኤል ማለት የሚበቀል ማለት ነው። የሚበቀል ነው ማለት በቀል የሚገባው ለጠላት ነው የሰው ልጅ ጠላት ደግሞ ዲያብሎስ ነው፤ ስለሆነም ቅዱስ ራጉኤል እግዚአብሔርን አምነው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው በፍርሐተ እግዚአብሔር አምልኮቱን ለሚፈጽሙ ሁሉ ጠላት ዲያብሎስን የሚያርቅላቸው ወደ እነርሱም ፈጥኖ በመድረስ የሚታደጋቸው ነው ማለት ነው። ሔኖክ 6:4፡፡ አንድም ራጉኤል ማለት የኃያላን ኃያል እግዚአብሔር ማለት ነው። የኃያላን ኃያል ያለው የእግዚአብሔርን ኃያልነት ከምድር ፍጥረታት ዘንድ ኃያል ከሚባሉት ሁሉ ሊገለጽ የማይችል ኃያልነቱን ለመግለጽ ኃያልነቱም ከ እስከ የሌለው መሆኑን ለመግለጽ የተቀመጠ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ኃያል የኃያላን ኃያል መሆኑን የሚገልጽ ትርጉም አለው። አንድም ራጉኤል ማለት ጽኑ እግዚአብሔር ማለት ነው። የእግዚአብሔር አምላክን ጽኑነት ለማጉላት ሲል ጽኑ አለው። እግዚአብሔር የማይወላውል የማይዋዥቅ የማይከዳ ነው ለማለትም ሲል ይህ ስያሜ ተሰጠው። የእግዚአብሔርን ጽናት የሚያሳይ ትርጉም ያለው ስያሜ ነው። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ራጉኤል አገልግሎት እና ስልጣን፡- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዚህ ዓለም በ64 ዓመቷ ካረፈች በኋላ ሥጋዋ ወደ ዕፀ ሕይወት ሲነጠቅ (ሲያርፍ) አብሮ ለሔደው እና ስጋዋን በእጣን ሲያጥን ለነበረው ለፍቁረ እግዚ ለቅዱስ ዮሐንስ ኅብስትን የመገበ መልአክ ነው። በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክ ነው። ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ የሆነ በእግዚአብሔር ፊት ግሩም ያማረ ሥራው የሰመረ እስከዛሬ የሞት ወጥመድ ያልያዘው የሞት ጥላ ያላረፈበት ነብዩ ሔኖክ "ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው" ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡ እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና ቅዱስ መልአክ ነው። (ድርሳነ ራጉኤል ዘ ጥቅምት ገጽ 23) አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ለመተካት ዓለምን የመለወጥ ሥልጣን የተሰጠው ቅዱስ መልአክ ነው። ከእግዚአብሔር የጌትነቱ አዳራሽ ይገባና ይወጣ ዘንድ ስልጣን ያለው ከኪሩቤልና ከሱራፌል ጋር ከፈጣሪ የጌትነት ዙፋን ፊት የሚቆም ነው። ሎጥን ሚስቱንና ልጆቹን ከእሳተ ጎመራ ያዳነ የበለአምን እርግማን ወደ በረከት የለወጠ እርሱ ነው። በቅዱስ ራጉኤል ስነ ሥዕል ላይ የምናየው ይህ ባለ አራት እራስ ንስር ከአርባእቱ ኪሩቤል አንዱ ገጸ ንስር ነው። የሥላሴን የጌትነት ዙፋን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳት ናቸው። የሚሸከሙት ሲባል ጫማ የሰውን ልጅ እንደሚሸከመው እንጂ ችለውትስ አይደለም። እነርሱም የሰው ገጽ፣ የእንስሳ ገጽ፣ የንስር ገጽ እና የአንበሳ ገጽ ያላቸው ናቸው። ይህንንም ነብዩ ሕዝቅኤል "ለእያንዳንዱ እንስሳትም የተለያዩ አራት ገጾች ነበሩት። ይህውም በስተቀኝ በኩል የእንስሳ መልክ፣ በስተ ግራ የላም ገጽ፣ በበስተ ኋላም የንስር ገጽ የሚመስሉ ነበሩ" ብሏል ሕዝ 1፡6-13፡፡ ከዚህ የምንገነዘበው ነገር ቢኖር አራት ገጽ ካላቸው ኪሩቤል መካከል አንዱ ንስር መሆኑን ነው። ቅዱስ ራጉኤል ደግሞ የእነዚህ ኪሩቤል አለቃቸው (የጌትነቱ ዙፋን ጠባቂ) በመሆኑ በዚህ ምክንያት ማለትም እነርሱ ዙፋኑን ተሸካሚ እርሱ ደግሞ አጠገባቸው መቆሙ መንበሩን ጠባቂ በመሆኑ በዚህ አይነት የአገልግሎት ድርሻ አብረው ሊሳሉ ችለዋል። ቅዱስ ያሬድም በድጓው "አርባእቱ እንስሳ አልቄንጥሩ እንደሚባለው ንስር ፊት ለፊት አይታዩም አንዱም በመራቸው ይሔዳሉ እነርሱም እያንዳንዳቸው አራት ገጽ ሲኖራቸው ሳያርፉና ሳይደክሙ የሚያመሰግኑ ናቸው" በማለት ጽፏል። https://t.me/finotehiwott http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like
Show all...
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

በፌስቡክ ያግኙን፤

https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

በድኅረ ገጽ ያግኙን፤ http://www.finotehiwotsundayschool.com

👍 8 5
Photo unavailableShow in Telegram
ደብተራው ደራሲ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም.) የጻፋቸው መጻሕፍት -ለኢትዮጵያ ቤ/ን ብዙ የደከመና ያገለገለ የዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ዕረፍት ጳጉሜን 3 1460 ዓ.ም ነበር፡፡ -ደብተራ ዘርዓ ያዕቆብ(1400-1460 ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ታሪክ ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ መጽሐፍ የጻፈ ንጉሥ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከጻፋቸው መጻሕፍት መካከል የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. መጽሐፈ ብርሃን 2. መጽሐፈ ሚላድ 3. መጽሐፈ ሥላሴ 4. መጽሐፈ ባሕርይ 5. ተዓቅቦ ምሥጢር 6. ጦማረ ትስብእት 7. ስብሐተ ፍቁር 8. እግዚአብሔር ነግሠ 9. ድርሳነ መላእክት (ጌታቸው ኃይሌ፣ ባሕረ ሐሳብ፣ገጽ 236) 10. ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ በቅርቡ ባሳተሙት “ከግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ጋር ብዙ አፍታ ቆይታ” መጽሐፍ ላይ ደግሞ ድርሳን ወገድለ ያሬድን የጻፈው ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ እንደሆነ ነግረውናል፡፡ -ፕ/ር ጌታቸው በመጽሐፋቸው እንደሚነግሩን “ዘርዓ ያዕቆብና ደብተራዎቹ ለዘመኑ ችግር መፍትሔ ለመስጠት ብዙ ድርሳናት ደርሰዋል፡፡ የሚታወቁት መጽሐፈ ብርሃን፣ መጽሐፈ ሥላሴ ወመጽሐፈ ሚላድ፣ እግዚአብሄር ነግሠ፣ ጦማረ ትስብእት፣ መጽሐፈ ባሕርይ፣ ስብሐተ ፍቁር፣ ተዓቅቦ ምሥጢር፣ ድርሳነ መላእክት፣ መልክአ ፍልሰታ እና ጥቂት ተአምራተ ማርያም ናቸው፡፡” (ጌታቸው ኃይሌ፣ ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስታወሻዎች፣ ገጽ-38) -የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብን ዕረፍት ጳጉሜን 3 ይታሰባል፡፡ ከዲ/ን ዮሴፍ ፍሥሐ ገጽ
Show all...
21👍 4👏 2
#ጳጕሜን_3 #ሩፋኤል_ሊቀ_መላእክት_ወመልከጼዴቅ_ካህን ‹‹#ርኅወተ_ሰማይ_/ሰማይ የሚከፍትባት እለት››፤:: #እንኳን_ለቅዱስ_ሩፋኤል_በዓለ_ሢመትና_ለቅዳሴ_ቤቱ_በ4ኛው_መቶ_ክ_ዘመን_በቅዱስ_ቴዎፍሎስ_ዘእስክንድርያ_አማካኝነት_በሚደንቅ_ተዓምራት_በአሣ_አንበሪ_ጀርባ_ደሴት_ላይ_ለታነጸው_ቅዳሴ_ቤት #እንዲሁም_ለካህኑ_መልከጼዴቅ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ_አደረሰን_፡፡ # ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው። ሣልሳይ ሊቀ መላእክት ነው። (“ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ” እናዳለ /ጦቢ ፲፪፥፲፭/፡፡ ✤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3):: ✤ ለሄኖክ ወልደ ያሬድ 6 ዓመት በእግረ ገነት ወድቆ ሳለ ኅበዓቱን ክሡታቱን አሳይቶታል። መ.ሄኖክ 8፡5 ቅዱስ ሩፋኤል ሰማያውያን መዛግብትን በእጁ የሚጠበቁ በመሆናቸው "ዐቃቤ ኖኅቱ ለአምላክ" ይባላል፡፡ እግዘአብሔር እንዳዘዘው የሚዘጋቸው የሚከፍታችው እርሱ ነው፡፡ ✤✤✤ ቅዱስ ሩፋኤል ሰውን በመርዳት ሲኖር የነበረውን የጦቢትን ዓይን ያበራና፤ ሣራ ወለተ ራጕኤልን ተቆራኝቷት ከነበረው አስማንድዮስ ጋኔን (ያገባችውን ባል የሚገድል) አላቅቆ የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት ያደረገ በመኾኑ “ፈታሔ ማሕፀን (መወልድ/አዋላጅ፥ ምጥን የሚያቀል) ይባላል:: ” ና ‹‹መልአከ ከብካብ›› ተብሏል (ዛሬም ድረስ የእናቶች ሐኪም ነው)፤ በኋላም ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት ቤቱንም በበረከት ሞልቶታል፤ በዚህም ፈዋሴ ቊስል (ድውያን)፥ ዐቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ) ተብሎ ይጠራል፡፡ #ጦቢት ልጁን ወደ ሜዶን ክፍል ወደ ምትሆነውና ራጌስ ወደ ምትባለው ሀገር ወደ ገባኤል ቤት ሲልከው መንገዱን የመራው አዛርያስ /ቅዱስ ሩፋኤል/ ነው፤ በዚህም ቅዱስ ሩፋኤል ‹መራኄ ፍኖት› /መንገድ መሪ/ ይባላል፡፡ #ቅዱስ ሩፋኤል በራማ ሰማይ ሁለተኛ ክፍል ላይ የሰፈሩትንና መናብርት በመባል የሚጠሩትን 10ሩን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ነው፤ በዚህም ‹‹ሊቀ መናብርት›› ተብሎ ይጠራል፤ መናብርት የሚባሉት መላእክት ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ፥ የእሳት ጦር ይዘው፤ ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ፤ ከእነዚኽ 10ር ነገደ መላእክት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡ በኢትዮጵያ በቅዱስ #ሩፋኤል ስም ከተሰየሙት ቤተ ክርስቲያን መካከል፤ 1,ጎንደር ደብረ ሣሕል ቅዱስ ሩፋኤል ወአቡነ ሐራ ድንግል ወቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን (ጐንደር)፤ በአፄ በካፋ የተመሠረተና ዚቅ እንደተጀመረባቸው ከሚነገርላቸው ቦታዎች አንዱና ታላቁ ደብር፡፡ 2,አዲስ አበባ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል፤ በ1878 ዓ.ም. በዳግማዊ አፄ ምኒልክ የተመሠረተና ባላ አንድ ጣሪያ ያለው ቀደምት የአዲስ አበባ ደብር፡፡ 3,ደብረ ዘይት (አየር ኃይል) ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ. 4,ወላይታ ዳሞት ፑላስ ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ. #በብዙኃን_ዘንድ_ለሚነሱ_ጥያቄዎች_መልስ_፡፡ #መልከ ጼዴቅ ማነው? #አባትና እናትስ የሉትምን!?፤ #የሰው ዘር አይደለምን!!?፤ #እውን መልከ ጼዴቅ ክርስቶስ ነውን?!!!! ✤✤ #መልከ_ጼዴቅ_ማነው_? መልከ ጼዴቅ በዘመነ አብርሃም የነበረ የሳሌም ንጉሥ እንዲሁም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነው /ዘፍጥ.14፤ ዕብ. 7/፡፡ ይህ ሰው አብርሃም ጠላቶቹን ነገሥተ ኮሎዶጎሞርን ድል አድርጎ ዮርዳኖስን ተሻግሮ በተመለሰ ጊዜ አብርሃምን ሊቀበለውና ሊባርከው ኅብስትና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ ባረከውም አብርሃምም ደግሞ ለመልከ ጼዴቅ ከምርኮው ዐሥራት አወጣ፡፡ (ኅብስትና ወይኑ የቅዱስ ቊርባን፣ መልከ ጼዴቅ የካህናት፣ አብርሃም የምእመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት ምሳሌዎች ናቸው)፡፡ ካህኑ መልከ ጼዴቅን ‎ቅዱስ ዻውሎስ "የትውልድ ቊጥር የለውም፤ ለዘመኑም ጥንትና ፍጻሜ የለውም" ብሎ ያስቀመጠው /ዕብ.7፥3/፤ ለወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ ሲያደርገው እንጂ ትውልዱ ከነገደ ‎ካም ነው፡፡ ወላጆቹም ‹‹#ሚልኪና #ሰሊማ ›› ይባላሉ፡፡ በፋሬስ ደግሞ፤ ፋሬስ የኦሪት ዛራ ደግሞ የወንጌል ምሳሌዎች ናቸው፤ ዛራ እጁን አውጥቶ መመለሱ ወንጌል በመልከ ጼዴቅ ታይታ የመጥፋቷ ምሳሌ፤ ፋሬስ ጥሶ እንደወጣ በመሀል ኦሪት ተሠርታለች፤ ዛራ ሁለተኛ እንደመወለዱ ወንጌልም ቆይታ ተሠርታለች፡፡ #መልከ ጼዴቅ ክርስቶስን በአራት ነገሮች ይመስለዋል፤ #1. መልከ ጼዴቅ ማለት የጽድቅ ንጉሥ የሰላም ንጉሥ ማለት ነው፤ ክርስቶስም ደግሞ አምላከ ጽድቅ አምላከ ሰላም ነው፣ #2. መልከ ጼዴቅ በኅብስትና በወይን ያስታኵት /ያመሰግን/ ነበር፤ ክርስቶስም ሥጋና ደሙን በኅብስትና በወይን ሰጥቶናል፣ #3. መልከ ጼዴቅ በመጽሐፍ ቅዱስ እናቱና አባቱ አልተጠቀሱም ክርስቶስ ደግሞ ለሰማያዊ ልደቱ እናት ለምድራዊ ልደቱ አባት የለውም፣ በዓለማችን በመልከ ጼዴቅ ስም የተሰየመው ብቸኛው ቤተ ክርስቲያን፡፡ ደብረ ዘይት ሂዲ መልከጼዴቅ፡፡ ‹‹#ርኅወተ_ሰማይ_/ሰማይ የሚከፍትባት እለት››፤ የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግበት፥ አራተኛው መጋቤ ኮከብ (ሕልመልመሌክ) የሚያልፍባት፤ ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ሰማይ የሚከፈትባት ቀን፤ በቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ጸሎት የሚያርግባት፤ በዚህም ‹‹መዝገበ ጸሎት›› /የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው/ ይባላል፡፡ የጌታችን ዳግም ምጽአት የሚታሰብባት ዕለት፤ በዚህም ምክንያ አባቶቻችን በዚህች እለት 365 አቡነ ዘበሰማያት ሲጸልዩ ያድራሉ፡፡ ፎቶ 1) በዓለማችን በመልክ ጼዴቅ ስም የተሰየመው ብቸኛው ቤተ ክርስቲያን፡፡ ደብረ ዘይት ሂዲ መልከጼዴቅ፡፡ #በኢትዮጵያ በቅዱስ ሩፋኤል ስም ከተሰየሙት ቤተ ክርስቲያን መካከል፤ ፎተ 2) ጎንደር ደብረ ሣሕል ቅዱስ ሩፋኤል ወአቡነ ሐራ ድንግል ወቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን (ጐንደር)፤ በአፄ በካፋ የተመሠረተና ዚቅ እንደተዠመረባቸው ከሚነገርላቸው ቦታዎች አንዱና ታላቁ ደብር፡፡ ፎቶ 3) አዲስ አበባ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል፤ በ1878 ዓ.ም. በዳግማዊ አፄ ምኒልክ የተመሠረተና ባላ አንድ ጣሪያ ያለው ቀደምት የአዲስ አበባ ደብር፡፡ ፎቶ 4) ደብረ ዘይት (አየር ኃይል) ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ. ፎቶ 5) ወላይታ ዳሞት ፑላስ ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ. ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ ፠፠፠ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 8 4🔥 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.