cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የንባብ ዓለም /Philosophy/

በዚ ቻናል መፅሐፍቶችን እንጋብዛለን ወደ ደራሲያን ማህበር ይቀላቀሉ። ሀሳብ አስተያየት @kaallua11 ላይ ያስቀምጡልን ወይም /[email protected]/

Show more
Advertising posts
3 435
Subscribers
+1324 hours
+407 days
+20430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
ስትመሳሰሉ (1).m4a1.93 MB
👍 4 1👏 1🤣 1
በነገን_ፍለጋ መፅሐፍ ላይ ተስፋአብ ተሾመ እንዲህ ይለናል ነገ  ዘረኝነት በባህላዊነት ይተካ ይሆናል። በቀደመው ጊዜ 'የኛ ዘር የተለየ ነው' ብለው ያመኑቱ ዘራቸውን ለመጠበቅ ዋጋ ከፍለዋል። ሌሎችን ዝቅ አድርገዋል። እስከመገዳደልም ደርሰዋል። አዶልፍ ሂትለር አይሁዳውያንን ለመጨፍጨፍ የዘር ካርድ መዟል። ይህን የእብድ ሃሳብ ፊደል የቆጠሩቱም ደግፈዋል። ትላንት የተማሩ፥ የተመራመሩ ወገኖች የዘራቸውን ምርጥነት በሳይንሳዊ ማስረጃ ለማስደገፍ ታትረዋል። በዚህ ዘመን ግን 'የኔ ዘር የተለየ ተፈጥሮ አለው' ብሎ የሚሟገት ቂል ቢመጣ ሳይንስ በቀላሉ ሙግቱን ፉርሽ ያደርግበታል። ጥቁሮች ከነጭ ያነሰ ተፈጥሮ  እንደሌላቸው ግልፅ ሆናል።  እንዲህ ያለ ጨዋታ ሳይንሳዊ አይደለም። ዛሬ ዛሬ ዘረኝነት በባህላዊነት እየተለወጠ ይመስላል። ካልቸሪዝም ገንግኖ በሬሲዝም መንበር ለመቀመጥ እያደባ ነው። ኹሉም ወገን የራሱን ባህል ልዩ መሆን ይሰብካል። የባሰው ነገር ደግሞ ባህልን ከመጤ ባህል መጠበቅ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነገር ሆኗል። ትላንት "በዘር  የተለየን ነን" ብለው ያሰቡቱ በአመራር ደረጃ የከበረ ዘራቸውን "ከብክለት እንጠብቅ" ብለው ደም አፍስሰዋል። ምናልባት ደግሞ ነገ ምርጡን ባህል ከመጤ ባህል ለመጠበቅ በሚል የሰው ልጅ ደም ይፋሰስ ይሆናል። በእርግጥም የሰው ልጅ ኢምክንያታዊነት የማይናቅ ጉልበት አለው! መልካም የ ንባብ ጊዜ 🙏🙏 ✍✍ ይቀጥላል ✍(3.4k) @yenbabalem1 @yenbabalem1
Show all...
👍 8 2🥰 1👏 1👌 1
🎙🎙🎙ናትናኤል መታሰብያነቱ ለውድ እህቴ ዳናዊት https://t.me/Nothingistruek https://t.me/loveyoumoremm https://t.me/loveyoumoremm
Show all...
ደና ነኝ.m4a1.23 MB
5👍 1
📣job opportunity 📢 Graphics መስራት የምትችል ሴት በጥሩ ደሞዝ እንቀጥራለን፣ 0920248816 0984618973 ደውላችሁ ተመዝገቡ።
Show all...
👍 2🙏 2👏 1
Repost from ስለ እኛ...
ስብሃት ገብረእግዚአብሔር እና በአሉ ግርማ እየተገናኙ አንድ ሁለት የሚሉበት ቤት አለ። ከእለታት በአንዱ መኪና ውስጥ ሆነው የሚፈልጉትን አዘዙ። ትሁቱ እና በአሉን የሚወደው አስተናጋጅ የሚፈልጉትን መኪናው ድረስ አድርሶላቸው እንደተመለሰ አንድ አይና ለማ.ኝ መጣ። "ስለ እግዚአብሔር" አለ። በአሉ ብር ሰጠው። ሰውዬው እንደሄደ "ስማ ስብሃት ይህ ሰው ለማ.ኝ አይደለም። ሰላይ ነው። የመጣው እኔን ለመሰለል ነው። እኔ ባለሁበት ስፍራ ሁሉ እየመጣ ይለምነኛል። እኔም ሰላይነቱን እንዳላወቀ ሆኜ እቸረዋለሁ" አለ። ይሄኔ ስብሃት ተናደደ። "ሰላይ መሆኑን ካወቅህ ለምን ትሰጠዋለህ? ቆሌውን መግፈፍ ነበረብህ" አለው ስብሃት። "አይምሰልህ" አለው በአሉ። "ለሰውዬው የምሰጠው ሆነ ብዬ ነው። ሰላይነቱን እንዳወቅኩኝ ከገባው ተልዕኮው እንደከሸፈበት ይገባዋል። ይሄኔ ያሰማሩት ሰዎች ሌላ ሰላይ ይልኩብኛል። በማላውቀው ሰው ከምሰለል በማውቀው ሰው ብሰለል ለጥንቃቄ ይጠቅመኛል" አለው። ስብሃት "የትረካ ጥበብ" በሚለው መፅሐፉ "የበአሉን መልስ ስሰማ 'አለቻ ጭንቅላት' አልኩ" ብሏል።                 Source-ተስፋኣብ ተሾሞ
Show all...
10👍 4
ከያዕቆብ ብርሀኑ መፅሐፍ ላይ የተወሰደ ተፈጥሮ ህብሯ፣ መገለጫ መልኳ (manifestation) እልፍ ነው፡፡ ውሉን ካገኘኸው፣ ከውሻ ጩኸት፣ ከውኃ እናት እንቅስቃሴ ትማራለህ፡፡ ከቴሌስኮፕና ማይክሮስኮፕ በላይ ደመነፍስህን ታምነዋለህ፡፡ የተፈጥሮን ውል ካገኘኸው ስለሁሉም ነገር ለመማር ዓይኖችህን መጨፈን ብቻ እንደሚበቃህ ይገባሃል፡፡ ዝም ረቂቅ ጸሎት፣ ዝም በመንፈስ መገናኘት እንደሆነ ይገለጥልሃል፡፡ ረቂቁ ነገር ያለው ያልተጻፈው፣ ያልተነገረው ፈጽሞ ሊጻፍ የማይችለው ውስጥ (in the inexplicable) መሆኑን ትቀበላለህ፡፡ ከቀኖና ይልቅ ኅሊና በላጭ መሆኑ ፍንትው ይልልሃል፡፡ ዝሙን መለማመድ፣ የተፈጥሮን ረቂቅ ውል ማሰስ ረቂቅ መንፈሳዊ ፍለጋ (mysticism) ነው፡፡ ሚስቲሲዝምን ከምሥራቁ ዓለም የሐይማኖት እና አስተሳሰብ ጽንፍ ጋር ብቻ አያይዘው የሚያስቡ ሰዎች ያስቁኛል፡፡ አፍሪካዊ የቮዶ (vodooo) አማኞችን ጠይቋቸው.. ‹‹ነጮች ወደ ቤተክስትያን ሄደው ተሰባስበው ስለመለኮት ይጮሃሉ፡፡ እኛ ግን እንዲሁ በመደነስ ብቻ መለኮታዊያን እንሆናለን›› ይሏችኋል፡፡ (The white poeple go to church and speak about God, but we simply dance and become God) ሚስቲዚም የትም አለ፡፡ ስህተተኛው ታናሽ ወንድማችን የሚሉትን ዘመናዊውን የሰው ልጅ ሽሽት በኮሎምቢያ አይደፈሬ የተራራ ሰንሰለቶች የሚኖሩት የኮጊ (Kogi) ጥንታዊ ቅዱስ ሕዝቦችም አኗኗርም ሆነ በእናትህ ዓይኔ ተርገበገበ ማንን ሊያሳየኝ ይሆን? ብሂል ውስጥ ሚስቲሲዝም አለ፡፡ አያቶችህ ወፍ መለሰችኝ፤ ‹ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ፤ እጄን አሳከከኝ ምን ላገኝ ይሆን?› ሲሉ ምን ማድረጋቸው መሰለህ? በስግብግቡ የሰው ልጅ አምሮ ምሪት በምክንያታዊነት ከማይደረስበት ከረቂቁ ተፈጥሮ ጋር ሲመሳጠሩ እኮ ነው! ቢሆንም ዝሙን ጭጩን በምልዓት ለመዋረስ የተዘጋጀን ስላለመሆናች (since we are incapable of being_silent) ከማይነገረው ከዝምታው ጥልቅ ጥቂት ሀቲቶችን ለማፍካት መውተፍተፋችን ጤንነት እንደሆነ ተቀብለን እንቀጥላለን... መጽሐፈ ሥነ ፍጥረት ‹‹እሁድ በመጀመሪያው ሰዓተ ሌሊት ፬ቱን ባህሪያት ውኃ፣ መሬት፣ አየር፣ እሳት) ካለመኖር (እምኅበ አልቦ ሀበቦ) ሰራቸው ይለናል፡፡ እነዚህ የሰው ልጅ አካል የተቀመረባቸው አራት የስጋ ወይም የአካል ባህሪያት እሳት፣ ውኃ፣ መሬት እና አየር የረቂቁ የአልኬሚ ጽንሰ ሀሳብም መሰረታዊ ትዕምርቶች (symbols) መሆናቸውን ልብ ማለት ያሻል፡፡ ውኃ፣ እሳት፣ አየር፣ መሬት በየትኛውም የዓለም ክፍል፣ በየትኛውም ቋንቋ፣ ዘመን፣ መንገድ መንፈሳዊ ሐሰሳ የሚያደርጉ ‌መሰጠቱ ያላቸው ሁሉ የሚጨባበጡባቸው ስጋችን የታነጻባቸው ባህሪያት ስለመሆናቸው በብዙ ታትቷል፡፡ረቂቃዊያን (mystics) ደግሞ መቃተት፣ መቃበዛቸው የቱንም ያህል ሰርቦላ ቢሆን ዞሮ ዞሮ ያው ስሪታቸው የወል (communal) የውኃ፣ አየር፣ የመሬት እና የእሳት ነው... ሕልማቸውም ልዩነት የለውም፡፡በየትኛውም መንገድ ያምልኩ ያመስግኑ ዞሮ ዞሮ ራስን ማብቃት፣ የሰውን መለኮታዊ ማንነት ማንቃት፣ የሰውን ልጅ ከራሱ ደመነፍሳዊ እስራት ነጻ ማውጣት፣ ከስሜት - ከስግብግብነት አዙሪት መንጻት ዓይነት... ሣይንስ በደረሰበት ሰዋዊ አረዳድ መሰረት በማናቸውም ቦታ ሕይወት ይፈጠር ዘንድ እነዚህ አራቱ የስጋ ባህሪያት የግድ ያስፈልጋሉ፡፡ ሆኖም የተሰራንባቸው አራቱ አካለ ባህሪያት መግነጢሳዊ ኃይለ መልኮች (form of energies) እንጂ አንዲያው በሌጣው የሚፈከሩ ቁሳዊ ኢንቲቲስ› አይደሉም፡፡ እነዚህን አራት ስነባህሪያት በቅጡ በማጥናትና በማሰልጠን በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያንቀላፋውን ጉልበት ማንቃት እና የሰውን ልጅ ወደ ቀደመ መለኮታዊ ማንነቱ መመለስ ይቻላል፡፡ መልካም የ ንባብ ጊዜ 🙏🙏 ✍✍ ይቀጥላል ✍(3.3k) @yenbabalem1 @yenbabalem1
Show all...
👍 6 2👏 2
"....ከእንቅልፌ ስነቃ አንድ ሰዓት ከሀያ (1:20pm) ሆኗል፤ በዚህ ከቀጠለ ጥር ላይ ሌላ አዲስ አመት ልናከብር መቻላችን ነው። ልክ እንደ አቦ ሸማኔ ቀልጣፋ ዓመት መሰለኝ የመጣው? ሆኖም ጊዜን ማቆም አይቻልም እና ከጊዜው ጋር መፍጠን ሳይኖርብን አይቀርም" ይለናል አቡበከር። መልካም አዲስ ዓመት🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼Happy new year!!!! በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት!!! 🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌼 @yenbabalem1 @yenbabalem1 @yenbabalem1
Show all...
👍 6🥰 2😍 2🥱 1
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳች እያለ የንባብ ዓለም መልካም ምኞቱን ይገልፃል። በአዲሱ ዓመት ምን ምን መካተት ወይም መቀነስ እንዳለባቸው በመወያያ ግሩፕ ላይ በነፃነት መፃፍ ይቻላል። በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት!!! @yenbabalem1 @yenbabalem1
Show all...
🙏 7 4🥰 2👍 1
🎙🎙🎙ናትናኤል ካህኔ  የኔ መሲ የኔ ረቢ ወዴት ትኖራለህ........ አ......ልምጣ ልከተልህ ድዊዬን አቅፌ ጊዜ አስቆጠርኩኝ ገላዬን አርክሼ ባገሩ ተወኩኝ አውር..... አውር ሰው መሆኔ ምልክት ሆኗቸው ሚቀጣጠሩብኝ ያ ሰው አኮ አኔ ነኝ ልምጣ ልከተልህ.... ወዴት ትኖራለህ..... ለምጣው ለምጣው ውሀ ሰአትን ጠብቄ ልቀዳ ምወጣ ጌታዬ ሆይ የተጠላው እኮ ነኝ አንድ ልጄ አሱም የሞተብኝ ምስኪኗ ባልቴት የተባልኩኝ ያቺ ሴት አኔ ነኝ ጤናዬን አጥቼ ሚፈሰኝን ፈሳሽ ላስቆመው ያልቻኩኝ ጌታዬ ሆይ ደካማው አኔ ነኝ        ተፃፈ በናትናኤል @yenbabalem1 @yenbabalem1
Show all...
ወዴት ትኖራለህ (1).m4a1.48 MB
👍 10 2👏 2🙏 1
Show all...
ወለድኩት.m4a9.93 KB
👍 5❤‍🔥 2😍 2👏 1👌 1🤣 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.