cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethio Psychiatry

Ethio Psychiatry Mental Health services No Health Without Mental Health! ☎️ +251949114685 📩 [email protected]

Show more
Ethiopia4 234The language is not specifiedMedicine4 237
Advertising posts
5 241
Subscribers
+324 hours
+157 days
+3230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

መስከረም-ራስን ስለማጥፋት መከላከል ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር - 2024 ራሱን ለማጥፋት ካሰበ ወይም ከሞከረ ሰው ጋር ሲነጋገሩ፣ ሁኔታውን ከልብ በመነጨ መረዳት እና በጥንቃቄ መቅረብ በጣም አስፈላጊ ነው። አውቀንም ይሁን ሳናውቅ የምንሰጣቸው አስተያየቶች የሰውዬውን የስሜት ጫና በማሳነስ የበለጠ ጉዳት ሊያደርሱ ስለሚችሉ ከታች የተገለጹትን አይነት አስተያየት ከመናገር መቆጠብ የተሻለ መረዳትን ይፈጥራል። ✍️. "ለምን እንዲህ ታደርጋለህ? - ሞኝ ነህ እንዴ?" እነዚህ ጥያቄዎች ፈራጅ ( judgemental ) ከመሆናቸው ባሻገር ሰዎች ስሜታቸው ወይም ድርጊታቸው ተራ እና ምክንያታዊ ያልሆነ በማስመሰል ሰውዬውን እንዲያፍር እና የበለጠ ብቸኝነት እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል። ✍️"የምትኖርለት ብዙ ነገር አለህ!" ወይም ደግሞ “ሕይወትህ በጣም ጥሩ የሚባል ነው!” እነዚህ አስተያየቶች ምንም እንኳን በበጎነት የታሰቡ አስተያየት ቢሆኑም የሰውዬውን የስሜት ሥቃይ ችላ በማለት የበለጠ ሚስአንደርስቱድ የመደረግ ስሜት ይፈጥራል። ራስን ከማጥፋት ስሜት ጋር የሚታገል ሰው በዚያ ቅጽበት የሕይወቱን አወንታዊ ገጽታዎች ማየት ስለሚከብዳቸው የደረሰባቸዉን የስሜት ጫና ማሳነስ የበለጠ ብቸኝነት እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል፤ብዙ ነገር ኖሮት ስንቱ ራሱን ያጠፋ እንዳለ ልብ ይሏል። ✍️"ራስን ማጥፋት ራስ ወዳድነት ነው።" ራሳቸውን ለማጥፋት የሚሞክሩ ሰዎች ከአቅም በላይ በሆነ የስሜት ስቃይ ምክንያት በግልጽ ለማሰብ ሊቸገሩ ይችላሉ። በዙሪያቸው ላሉ ሰዎችም ሸክም እንደሆኑ ሊሰማቸውም ይችላል። እንዲሁም ራስ ወዳድ ስለሆኑ ሳይሆን የሚወዷቸው ሰዎች ያለነሱ ( ቢሞቱ) የተሻለ እንደ ሚኖሩ ሊመስላቸው ይችላል። ስለዚህ እንዲህ አይነት አስተያየት የጥፋተኝነት እና የተስፋ መቁረጥ ስሜትን በመጨመር ችግሩን ሊያባብስ ይችላል ። ✍️ "ስንቱ ካንተ የባሰ አለ አባቴ" ራስን የማጥፋት ስሜት በጣም ውስብስብ ስለሆነ ስቃያቸውን በቀላሉ ከሌሎች ሰዎች ችግር ጋር በማወዳደር የስሜት ስቃያቸውን ማሳነስ ፍፁም ሙያዊ ያልሆነ አስተያየት ሲሆን ግለሰቡ ለተሰማው ትክክለኛ የሰሜት ስቃይ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማው ሊያደርግ ይችላል. ✍️"ትኩረት ፈልገህ ነው!።" ራስን ለማጥፋት መሞከር የአንድ ሰው የእርዳታ ጥሪ ሲሆን ህመሙ ተራ የትኩረት ፍለጋ ነው ብሎ መደምደም የሆነ ቀን እንድናጣቸው ሊያደርግ ይችላል። ✍️" አሁን ከሱ ውጣ እና በጎ በጎውን አስብ አባቴ።" እንደ ራስን የማጥፋት ያሉ ከባድ ሃሳቦች እና ስሜቶችአንድ ሰው በቀላሉ ሊላቀቃቸው ወይም በአዎንታዊ አስተሳሰብ ሊጠግነው የሚችል ነገር ስላልሆኑ እነዚህ አስተያየቶች የሰውየውን የአእምሮ ጤና ትግል አሳሳቢነት በማሳነስ የተስፋ መቁረጥ ስሜትን ሊያባብሱ ይችላሉ። ✍️"ከዚህ የበለጠ ጠንካራ ነህ" ይህ አስተያየት አበረታች ሃሳብ ቢመስልም ሰውዬው የተሰማው ትክክለኛ የስሜት ትግል ራሱ ደካማነት እንደሆነ እንዲሰማው ሊያደርግ ይችላል። ይህም ቀድሞውኑ ደካማ፣ ብቁ እንዳልሆኑ ይሰማቸው ከነበረ ይህ አስተያየት የበለጠ እነዚያን ስሜቶች ያጠናክራል። ✍️" ስትታይ ግን ምንም የተጨነክ አትመስልም።" - ራስን የማጥፋት ሃሳቦችን ጨምሮ አብዛኛዎች የስነ ልቡና ስሜቶች ሁልጊዜም ለሰዎች በግልፅ የሚታዩ ችግሮች አይደሉም ። ታዲያ እንዲህ አይነት አስተያየቶች የተሰማቸዉን እውነተኛ ስሜት በማሳነስ ውጫዊ የጭንቀት ምልክቶች ስላላሳዩ ብቻ ሚስአንደርስቱድ የመደረግ ሁኔታ ይፈጥራል። ✍️ "ዝም ብለህ እንደዛ ስለሰብ ክ ነው " ይህ አስተያየት ሰውዬው እየደረሰበት ያለውን እውነተኛ እና ጥልቅ ህመም በማሳነስ ስቃያቸው ን በተሳሳተ መልኩ ችላ ማለት መቻል መናገር ሌላ ህመም ይሆንባቸዋል ። ከዚህ ይልቅ ምን እንበላቸው?! 🤜" አለሁልህ !" – ምንም ሳንፈርጅ አለሁልህ ማለት ሰውዎች ብቻቸውን እንዳልሆኑ እንዲሰማቸው ያደርጋል። 🥺"እንዲህ እየተሰማህ ስለሆነ በጣም አዝናለሁ -እንዴት ልረዳህ እችላለሁ?” -ይህ ስሜታቸውን ዋጋ በመስጠት እና በማረጋገጥ እና ፍላጎቶቻቸውን እንዲገልጹ በር ይከፍታል። 😥“ስለ አንተ እኮ እጨነቃለሁ ፤ ህይወትህም ለእኔ አስፈላጊ ነው -ሁሌም ዋጋ እንዳላቸው እንዲያውቁ ማድረግ የከንቱነት ስሜትን ለመቋቋም ያግዛል። 🤕"በጣም ከባድ እና አስጨናቂ ስሜት ውስጥ ያለህ ይመስኛል ህመማቸውን በመቀበል በጣም የመረዳት እና የመሰማት ስሜት ለመፍጠር ያግዛል ። 👩‍⚕️ "ወይ የሚረዳህ ሰው እንፈልግ።" ሳንገፋፋ የባለሙያዎችን እገዛ ማበረታታት የመፍትሄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያግዛል። በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩ አስተያየቶችን ከመስጠት በመቆጠብ እነዚህን ተጨማሪ ሙያዊ ስልቶች ብንተግብር የተሻለ ሁኔታ ይፈጥረ ል ። 👉 ያለፍርድ ማድመጥ:- ይችግሩን እዛው ባንድ ጊዜ ለመፍታት ከመሞከር እና አላስፈላጊ ፈራጅ ምክር ከመስጠት ይልቅ ችግራቸውን ልባዊ በሆነ መንገድ ማዳመጥ የበለጠ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። 👉ህመማቸውን ከመቀነስ መቆጠብ -ሰዎች ያሉበት ሁኔታ ምንም እንኳን ለእርስዎ ተራና የማይገባ ቢመስልም ለሰውዬው ግን በጣም እውን መሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው። 👉 ችግሩን በፍጥነት ለመፍታት ከመሞክር መቆጠብ፡- ከሆነ የስሜት ጫና ማገገም ወዲያው የሚዳን አይነት አይደለም እና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ማድረግ መርሳት የለብንም። ሁሌም ቢሆን ርኅራኄን፣ በነሱ ቦታ መሆንን እና ልባዊ መረዳትን ማሳየት ራስን ለማጥፋት በሞከረ ሰው ላይ ከፍተኛ አወንታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል እና ሁሌም ልንለማመዳቸው ይገባል። 💙#ራስን መስለማጥፋት .ግንዛቤ እንፈጠር! #የአእምሮ ጤና ጉዳዮች ላይ ትኩረት እናድረግ እ# .ብቻህንአይደለህም #ሕይወትንምረጥ"💙 ለወዳጅዎ በማጋራት ዘመቻውን ይቀላቀሉ! አብረውን ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! "ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!" ሲደልል አስፋው (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት) Join us:👇👇👇👇👇 Telegram @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ) @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ YouTube https://youtube.com/@Psych_Africa?si=Jr9LJFgLpN4XzPO2 Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61556978168876 LinkedIn https://www.linkedin.com/in/sidelil-asfaw-72a710217?utm_source=share&utm_campaign=share_via&utm_content=profile&utm_medium=android_app
Show all...
Psych Africa

ይህ ቻናል ስነ ልቡናዊ ጉዳዮችን በባለሙያዎች ለመዳሰስ የተዘጋጀ ነው። #ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉ። Join Our Channel: Exploring Psychological Issues with Professionals! 🌟 Welcome to our channel dedicated to in-depth discussions about Psychological issues, led by experienced professionals in the field. #SUBSCRIBE now to gain valuable insights 👇👇👇👇👇👇👇 ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን!!

👍 8👌 3
በበዓል ሰሞን፣ ለአእምሮ ጤንነት ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ ነው። ለራስህ ጊዜ ስጥ ፣ ገደበችን አዘጋጅ እና ደስታን እና#የመርሳት ችግር/dementia *** ሰዎች በጊዜ ሂደት በፊት የነበሯቸው የማሰብ፣የማስታወስና የማገናዘብ ብቃት(Cognitive capacity) እየቀነሰ ሲመጣና በህይወታቸው ላይ ችግር መፍጠር ሲጀምር የመርሳት ችግር ተከሰተ እንላለን:: ይህ ህመም: በተለይም እድሜያቸው ከ65 አመት በሆናቸው ሰዎች ላይ በብዛት ቢስተዋልም: በወጣትና ጎልማሶች ላይ ሊከሰት ይችላል:: ምክንያቶቹም:- ▪️አልዛይመር እና ሌሎች የአዕምር ሴሎችን የሚያጃጁ ችግሮች ▪️የጭንቅላት ደም ስር ችግሮች(ስትሮክ..)፣ ▪️የጭንቅላት እጢዎች: ጭንቅላት ላይ የሚደርስ አደጋ: ኢንፌክሽኖች( HIV እና የመሳሰሉ)፣ ▪️የንጥረ ነገሮች መዛባት(ቪታሚን እና የመሳሰሉ) 🔹ምልክቶቹም በሚከተሉት የCognitive domain(የግንዛቤ/ማስመሰል ማእቀፍ) እክሎች ሊገለጡ ይችላሉ:: ▪️ትውስታ/memory (ብዙ ጊዜ የቅርቡን ጊዜ ትውስታዎችን በመርሳት ይጀምርና ቀስ በቀስ የድሮዎቹን መርሳት ይከተላል) ▪️Language: እንደ ልብ ቃላትን አማርጦ ለመጠቀም ይቸገራሉ ▪️ Complex attention- ሃሳባቸውን ሰብስበው ነገሮችን ለመከወን ይሳናቸዋል ▪️Perceptual-motor- በፊት በቀላሉ ሊያደርጓቸው የሚችሏቸውን ነገሮች(ምሳሌ: መኪና መንዳት) ሲያቅታቸው ይስተዋላል: ቅልጥፍናቸው ይቀንሳል:: - Executive function- ነገሮችን በትክክል አቅዶ መፈጸም ያቅታቸዋል:: ስራ ቦታ ያልለመደባቸውን ስህተት መስራት ሊጀምሩ ይችላሉ:: - Social cognition- የሰዎችን ሃሳብና ስሜት አንብቦ መረዳት ያቅታቸዋል:: እንግዳ አይነት ባህርይ(ተሳዳቢነት: የብልግና ቃላትን እንደመጠቀም..) ሊያሳዩ ይችላሉ:: 🔸 ህክምናው ▪️ችግሩን እንዳመጣው መንስኤ ይለያያል:: በጥቅሉ: ▪️ከላይ የተጠቀሱትን ዋንኛ መንስኤዎችን ማከም: ▪️ህመሙ እየተባባሰ እንዳይሄድ የሚያደርጉ መድሃኒቶችን መስጠት ▪️ተጓዳኝ ችግሮችን ማከም- እንደ ድባቴ: የባህርይ መለወጥና ሳይኮሲስ ያሉትን ማከም ▪️ የስነ ልቦና ህክምናዎች( እንደ ትውስታን የሚቀሰቅሱ ክዋኔዎች ያሉ..) ▪️ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ችግር ፈቺ ስራዎች መስራት (የውርስ:ሃብት ማስተዳደርና መሰል ጉዳዮች) *** ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶችን የሚያሳዩ ሰዎች ካጋጠሙን ወደ ህክምና ተቋማት በመውሰድ ህክምናን ማግኘት ይቻላል:: አሻም! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ገጾች ይወዳጁ Telegram @DrEstif Facebook https://www.facebook.com/DrEstif Ethio Psychiatry ✅Join Us @ethiopsychiatry @ethiopsychiatry
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 6🙏 1
ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1499ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት ቀን (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ! Hordoftoonni amantaa Islaamaa hundi baga guyyaa dhaloota Nabi Muhaammad waggaa 1499ffaa nagaan geessan!
Show all...
👍 4
It’s okay to set boundaries to protect your mental health. #ethiopsychiatry #mentalhealth #mentalhealthsupport #feelbetter #changeforbetter #health #therapy #therapy #mentalsupport Ethio Psychiatry ✅Join Us @ethiopsychiatry @ethiopsychiatry
Show all...
👍 3👌 1
🌼አድስ ዓመት እና ሥኔ ልቦና!!   አድስ ዓመት ስመጣ የሰው ልጆች ልቦና በብዙ ነገር ይሞላል:: ያሳለፍነው ዓመት ጥሩም ሆነ ክፍ የራሱ የሆኔ ትዝታን በሕይወታችን ላይ ጥሎ አልፎአል  ይህ ያሳለፍነው ዓመት ጥሎብን ባለፈው ክፉ ጠባሳ ልቦናችን ተጠምዶ ቀጣዪን ዓመት በጥሩ ሥኔ ልቦና እንዳንቀበል እንዳያደርገን ከፍተኛ ጥንቃቀ ልናደርግ ይገባናል::  ባለፈው ዓመት ያጣናቼውን ነገሮች ሥኔ ልቦናችንን በሚገባ ካዘጋጄን እንደገና ሠርተን አሸናፍዎች እንደምንሆን አያጠራጥርም:: በየትኛውም ሁነታ ውስጥ ብንሆን ሥኔ ልቦናችን ዝግጅ መሆን አለበት:: 🌼አድስ ዓመት በሥኔ ልቦናችን ላይ ተፅህኖ ፈጣር ሳይሆን ሥኔ ልቦናችን በአድሱ ዓመት ላይ ተፅህኖ ፈጣር መሆን አለበት :: ይሄንን አውቀን ገና ከጥዋቱ ለስከታችን ሥኔ ልቦናችንን ካዘጋጀን አሼናፍዎች እንሆናለን :: በየትኛውም ግዜ እና ቦታ ጠንካራ ሥኔ ልቦና ልኖረን ይገባል ጠንካራ ሥኔ ልቦና ለአዕምሯችን ጤና መሠረት ነው በተለይ ሀገራችን ሠላም ባጣችበት እና የኑሮ ውድነቱ በተጧጧፈበት ዘመን ጠንካራ ሥኔ ልቦና ልንገነባ ያስፈልጋል :: በዓለማችን ላይ ጠንካራ ሥኔ ልቦናን የምገነባ እና ጤናማ አዕምሮን የምገነባ ሀብት ሳይሆን በተፈጥሮ የተቸረን ጠንካራ ሥኔ ልቦና ነው ብዙ ሰዎች በዝህች ዓለም ላይ ብዙ ሀብት አካብተው ጠንካራ ሥኔ ልቦና ስለለላቼው ክፉ ቀን ስገጥማቼው መሸጋገርያ ድልድይ ያጡና ሰምጠው ይቀራሉ እራሳቼውንም ማደስ አይችሉም :: 🌼ስለዝህ በዝህ አድስ ዓመት ጠንካራ ሥኔ ልቦናና ጤናማ አዕምሮን ይዘህ ተነሥ በምትሠራው የሥራ ዘርፍ ያለጥርጥር ሴካታማ ትሆናለህ :: ዛሬ ለራሷ ሠላምን አጥታ ሠላምን በምትነፍገን ዓለም ውስጥ አንቴ ከጭቅጭቋና ንትርኳ ውጣ እግዚሃብሔር በሰጠህ ልቦናና አዕምሮህ ተጠቀም ዘመኑ የሠላም የጤና ይሁንልን 🌼 በአድስ ዓመት አድስ ሥኔ ልቦና ጤናማ አዕምሮን እንመኝላችዋለን መልካም አድስ ዓመት::🌼 ዮርዳኖስ ይሁን  (የስነ-አእምሮ ባለሙያ) Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ) 🌼አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት ዘመን ይሁንልን!!🌼 አብረውን ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! "ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!" Join us:👇👇👇👇👇 Telegram @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ) @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ
Show all...
4👏 2👍 1🙏 1
"ሴንቴምበር 10 አለም ራስን ማጥፋት መከላከል ቀን" እንደ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሪፖርት ራስን ማጥፋት በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከ700 000 የሚበልጡ ሰዎች የሚሞቱበት ትልቅ የህዝብ ጤና ፈተና ነው። ከ2024-2026 የአለም ራስን ማጥፋት መከላከል ቀን የሶስት አመት ጭብጥ "Change the narrative on Sucide" የሚል ሲሆን "Start the conversation" የሚል የተግባር ጥሪም አስተቀምጧል። ይህ መሪ ሃሳብ ራስን ማጥፋትን ለመከላከል መገለልን መቀነስ እና ግልጽ ውይይቶችን ማበረታታት ስላለው ጠቀሜታ ግንዛቤን ማሳደግ ነው። ይህም ይህን ውስብስብ ጉዳይ እንዴት እንደምንገነዘበው እረዳዳችን መለወጥ እንዳለበት እና ከዝምታ እና መገለል ባህል ወደ ግልጽነት፣ መረዳት እና መደጋገፍ መቀየር ነው። የተግባር ጥሪውም ሁሉም ሰው ስለ ራስን ማጥፋት እና ራስን ማጥፋት መከላከል ላይ ውይይት እንዲጀምር ጥሪ ያቀርባል። ማንኛውም ውይይት ምንም ያህል ትንሽ እንኳን ቢሆን ደጋፊ ፣ የማይፈርጅ እና ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር አስተዋፅዖ ያደርጋል። ይህ መሪ ሃሳብ ራስን ማጥፋትን ለመከላከል እና ለአዕምሮ ጤንነት በፖሊሲ አወጣጥ ላይ ቅድሚያ የመስጠት አስፈላጊነትን በሞጉላት መንግስት ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስድም ጥሪ ያቀርባል ። ታዲያ እኛም በዚህ ቀን እያንዳንዱ ሕይወት ዋጋ አለው እንላለን! ሁሉም የህይወት ትግል ልዩ ነው እንላለን! እርስዎም ህይወት ድክም ካላችዎ፣ ከመጠን በላይ ከተጨናነቁ፣ ባዶነት ከተሰማዋ እና ከፍተኛ የብቸኝነት ስሜት ከተሰማዎ ራስዎን ለመጉዳት ከማሰብዎ፣ ከመወስንዎ፣ ከማቀድዎ ወይም ከመሞከርዎ በፊት ይህንን ከባድ ስሜት በመጋራት ሊያግዝዎ የሚችል አንድ ሰው እንዳለ ያስቡ! ለወዳጅዎ ፣ ለቤተሰብዎ፣ ለሃይማኖት መሪዎች ወይም ለስነ -ልቡና እና ስነ አዕምሮ ባለሙያዎች ይተንፍሱት፤መፍትሔም ይኖራል! ህይወትዎም እርስዎ ከሚሰማዎ በላይ ለሚወድዎት ሰው ዋጋ አላት! ታሪክዎ ገና አልተቋጨም እና ሁልጊዜም ሌላ ተስፋ፣ ሌላ አማራጭ፣ ሌላ መዳን እና ዳግሞ መነሳት እንዳለ አይርሱ! ከተባበርን ማንም ወደ ኋላ የማይቀርበት እና የማይረሳበት ዓለም መፍጠር እንችላለን እና እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው በዚህ ስሜት ዉስጥ እየታገለ ከሆነ ጊዜ ሳይጠብቁ ዛሬውኑ ከአንድ ሰው ጋር ይነጋገሩ ፤ መፍትሄም ይኖራል። የአለም ራስን ማጥፋት መከላከል ቀን (World Sucide Prevention Day) የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ2003 ዓ.ም ሲሆን የተጀመረውም በአለም አቀፍ ራስን ማጥፋት መከላከል ማህበር ከአለም ጤና ድርጅት (WHO) ጋር በመተባበር ነው። ሴፕቴምበር 10 በየዓመቱ በጉዳዩ ላይ ትኩረት ለማድረግ ያለመ እና መገለልን በመቀነስ በድርጅቶች፣ በመንግስታት እና በህብረተሰቡ ውስጥ ግንዛቤን በመፍጠር ራስን ማጥፋት መከላከል እንደሚቻል መልእክት ለማስተላለፍ ያለመ ቀን ነው። 💙 #ራስን ስለ ማጥፋት ግንዛቤ እንፈጠር #የአእምሮ ጤና ጉዳዮች ላይ ትኩረት እናድረግ# ብቻህን አይደለህም #ሕይወትን ምረጥ"💙 💥መልካም አዲስ አመት - 2017 ዓ.ም!💥 "ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!" ሲደልል አስፋው (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት) Join us:👇👇👇👇👇 Telegram @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ) @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ YouTube https://youtube.com/@Psych_Africa?si=Jr9LJFgLpN4XzPO2 Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61556978168876 LinkedIn https://www.linkedin.com/in/sidelil-asfaw-72a710217?utm_source=share&utm_campaign=share_via&utm_content=profile&utm_medium=android_app
Show all...
Psych Africa

ይህ ቻናል ስነ ልቡናዊ ጉዳዮችን በባለሙያዎች ለመዳሰስ የተዘጋጀ ነው። #ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉ። Join Our Channel: Exploring Psychological Issues with Professionals! 🌟 Welcome to our channel dedicated to in-depth discussions about Psychological issues, led by experienced professionals in the field. #SUBSCRIBE now to gain valuable insights 👇👇👇👇👇👇👇 ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን!!

6👍 1
🌼Bara haaraa fi Xiin-sammuu cimaa fayyaa sammuutif ••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• Barri haaraan gaafa gahu Xiin- sammuun namootaa waan baay'eedhaan guutama.  Barri darbe gaariis ta’ee hamaa ta’us, yaadannoo mataa isaa jireenya keenya keessatti dhiisee darba. 🌼Wantoota bara darbe dhabneef  Xiin-sammuu keenya akka gaariitti yoo qopheessine kaarorsine, hojjennee akka injifannu shakkii hin qabu. Haala kamiinuu haa ta'u Xiin-sammuu keenya qophaa'uu qaba. 🌼Barri haaraan Xiin-sammuu keenya irratti dhiibbaa uumuu hin qabu, garuu Xiin-sammuun keenya bara haaraa irratti dhiibbaa uumuu qaba.  Kana beeknee ganamarraa kaasee Xiin-sammuu keenya mo'umsaf yoo qopheessine mo'ataa taana. Yeroo fi bakka kamittuu Xiin-sammuu cimaa qabaachuu qabna. Xiin-sammuu cimaan fayyaa sammuu keenyaaf bu'uura ta'a. Keessumaa bara biyyi keenya nagaa dhabde fi qaala'iinsi jireenyaa dabale kanatti Xiin-sammuu cimaa fayyaa sammuu keenyaf ijaaruu qabna. Addunyaa kana irratti Xiin-sammuu cimaa fi sammuu fayyaa kan ijaaru qabeenya osoo hin taane Xiin-sammuu cimaa uumamaan ittiin eebbifamnedha.  Namootni baay'een addunyaa kanarratti qabeenya hedduu kuufatanii Xiin-sammuu cimaa waan hin qabnef guyyaa hamaan gaafa isaan mudatu daandii dhabanii  liqimfamani hafu. Ofis dammaqsuu hin danda'ani! 🌼Egaa, bara haaraa kana keessatti Xiin-sammuu cimaa fi sammuu fayyaa qabaadhuuti kaa'i damee hojii hojjechaa jirtu irratti namaa milkaa'a taatatti!! Hara'a addunyaa ofiif nagaa dhabdee nagaa nu dhowwu keessa ba'i.  Waaqayyo sammuu fi Xiin-sammuu siif kenneti itti fayyadami. Bari haaraan kun kan nagaa fi fayyaa nuf haa ta'u. Fayyaa Sammuu fi  Xiin-sammuu cimaa,haaraa  isiniif hawwa.🌼 Yordanos Yihun (Oggessa Fayyaa Sammuu) “FAYYAA SAMMUU MALEE FAYYAAN HIN JIRU”!! Ethio Psychiatry ✅Join Us @ethiopsychiatry @ethiopsychiatry
Show all...
👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
🌼የበዓል ወቅት እና የአእምሮ ጤና     ============ 🌼በበዓላት ወቅት ውጥረት እና ጭንቀት በአእምሮ ጤና ላይ ተጽእኖ ሊያመጡ ይችላሉ። ይህ ውጥረት እንደ ጭንቀት፣ ብስጭት ወይም ድባቴ ሆኖ ሊታይ ይችላል። በዓል በራሱ ይዞ የሚመጣው የገንዘብ ችግር ሸክሙን ሊጨምር ይችላል፤ ይህም የጭንቀት ስሜትን ይፈጥራል። በዙራያችን ካሉ ሰዎች ለመታየትና ከአቅማችን በላይ ዝግጅቶችን ለሟሟላት የምናደርገው ትንቅንቅ ድካምና መሰልቸት ሊያስከትል ይችላል። 🌼በሌላ በኩል በዓል አንዳንዴ የብቸኝነት እና የመንፈስ ጭንቀት ስሜትን ያባብሳል። በርቀት ወይም በግላዊ ሁኔታዎች ምክንያት ከሚወዷቸው ጋር መገናኘት የማይችሉ ሰዎች ከፍ ያለ የብቸኝነት ስሜት ሊሰማቸው ይችላል። ይህ አሉታዊ ስሜቶችን ያጠናክራል እና ለአእምሮ ጤና መቃወስ አስተዋጽኦ ያደርጋል። 🌼እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ዋነኛው ለራስ እንክብካቤ ቅድሚያ መስጠት ነው። አስቀድሞ ማቀድ እና በጀት ማውጣት የገንዘብ ጫናን ሊቀንስ ይችላል። በበዓል ትርምስ መካከል የተለመዱ የእለት እለት ተግባራት ለማከናወን እና ለመዝናናት ጊዜ መመደብ አስፈላጊ ነው። 🌼የብቸኝነት ስሜት ለሚሰማቸው በማህበረሰብ ዝግጅቶች ወይም የድጋፍ ቡድኖች ግንኙነት መፈለግ ብቸኝነትን ለመቀነስ ይረዳል። በመደበኛነት ከጓደኞች ወይም ከቤተሰብ ጋር መገናኘት፣ በአጭር መልዕክቶች ወይም ጥሪዎችም ቢሆን ስሜታዊ ድጋፍ ሊሰጥ ይችላል። ደስታን በሚያመጡ ተግባራት ውስጥ መሳተፍ የአእምሮን ደህንነት የበለጠ ሊደግፍ ይችላል። 🌼🌼አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት ዘመን ይሁንልን!!🌼🌼 አብረውን ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! "ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!" Join us:👇👇👇👇👇 Telegram @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ) @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ
Show all...
👍 8 2
የስቶይስም ፍልስፍና እና የስነ-አዕምሮ ጤና ስቶይሲዝም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በጥንዊቷ ግሪክ የተፈጠረ የፍልስፍና ትምህርት ቤት ነው። የተመሰረተው በዜኖ ሲቲየም ሲሆን በኋላም እንደ ኤፒክቴተስ፣ ሴኔካ እና ማርከስ አውሬሊየስ ባሉ ፈላስፎች የበለፀገ የህይወት ፍልስፍና ነው። ስቶይሲዝም ወደ ጥሩ እና የተረጋጋ ሕይወት የሚወስደው መንገድ የአሁኑን ጊዜ እንዳለ በመቀበል፣ ዓለምን ለመረዳት ምክንያትን በመጠቀም እና በጎነትን በጥልቀት በመለማመድ እንደሆነ ያስተምራል። የ Stoicism ቁልፍ መርሆዎች የሚከተሉትን ያካትታል :- 1. በጎነትን በጥልቅት መለማመድ:- እስቶይኮች እውነተኛው ህይወት በጎነትን በጥልቀት መለማመድ እንደሆነ ያስረዳሉ። ይህም በተፈጥሮ እና በምክንያት መኖርን፣ ፍትህን ፣ እና እውነተኛ ፍቅር መሻትን ያካትታል። እንደ ሀብት እና ዝና ያሉ ውጫዊ ሁኔታዎችም ጥሩም መጥፎም ባይሆኑም የደስታ መሰረት መሆን እንደ ሌለባቸው ይሞግታሉ። 2. የምትችለውን ተቆጣጠር፡- ሌላው በስቶይሲዝም ውስጥ ያለው ዋና ሃሳብ በእኛ ቁጥጥር ውስጥ ያሉትን እና ያልሆኑትን ሁኔታዎች መለየት ነው። ስቶይኮች እኛ ልንቆጣጠረው በምንችለው ነገር ላይ ብቻ እንድናተኩር ( ማለትም:- የራሳችንን ሀሳቦች፣ ድርጊቶቻችን እና ለነገሮች የምንሰጣቸውን ምላሾች) እና መቆጣጠር የማንችለውን ( ማለትም:- ውጫዊ ክስተቶችን እና የሌሎችን ሰዎችን ድርጊት) መቀበልን ይመክራሉ። 3. ስሜትን መቋቋም፡- ስቶይሲዝም የሚያስተምረው እንደ ቁጣ፣ ፍርሃት እና ቅናት ያሉ አሉታዊ ስሜቶች የሚመነጩት ከተሳሳቱ የራሳችን ፍርዶች እንደሆነ ይሞግታሉ ። ታዲያ እነዚህን የተሳሳቱ የራሳችንን አመለካከቶች እና ፍርዶቻችንን በመለወጥ የስሜት መረጋጋትን ማግኘት እንችላለን ብለው ያስረዳሉ ። 4. ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር መስማማት፡- እንደ ስቶይኮች ፍልስፍና ጥሩ ህይወት ለመኖር ራስን በሚገባ ማወቅ እና ከአለም የተፈጥሮ ስርአት ጋር ማስማማትን ያስፈልጋል። ይህም ሞት የማይቀር ነገር መሆኑን እና ዓለም ላይ ቋሚ (Permanent) የሚባል ነገረ አለመኖሩን እና ነገሮች ተለዋዋጭ መሆናችዉን መቀበልን ይጨምራል። 5. ተግባራዊ ጥበብን መለማመድ፡- ስቶይሲዝም የተግባር ጥበብን መለማመድ አስፈላጊነትም ላይ ያተኩራል ። ይህም ምክንያታዊነትን ውሳኔዎችን ለማድረግ እና የህይወት ፈተናዎችን ለመመርመር መጠቀም እንዳለብን ያስተምራሉ። ይህም ጥበብ ሰዎች በችግር ጊዜ ተረጋግተው እንደቆዩ እና እንዳይሸበሩ ይረዳቸዋል። ከስቶይሲዝም ጋር የተያያዙ ዝነኛ ስራዎች በማርከስ ኦሬሊየስ የተፃፈው "ሜዲቴሽን"፣ በሴኔካ የተፃፈው "letter from Stoic" እና "Enchiridion" በ Epictetus ይገኙበታል። ስቶይሲዝም በብዙ የምዕራባውያን አስተሳሰቦች ላይ ተጽዕኖ በማሳደር ዛሬም ፅናትን፣ ምክንያታዊነትን እና ውስጣዊ ሰላምን የሚያበረታታ ጠቃሚ ስነ-ልቡናዊ የህይወት ፍልስፍና ሆኖ ቀጥሏል። አብረውን ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! "ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!" ሲደልል አስፋው (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት) Join us:👇👇👇👇👇 Telegram @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ) @Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ YouTube https://youtube.com/@Psych_Africa?si=Jr9LJFgLpN4XzPO2 Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61556978168876
Show all...
Psych Africa

ይህ ቻናል ስነ ልቡናዊ ጉዳዮችን በባለሙያዎች ለመዳሰስ የተዘጋጀ ነው። #ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉ። Join Our Channel: Exploring Psychological Issues with Professionals! 🌟 Welcome to our channel dedicated to in-depth discussions about Psychological issues, led by experienced professionals in the field. #SUBSCRIBE now to gain valuable insights 👇👇👇👇👇👇👇 ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን!!

👍 4
ኢትዮ ሳይካትሪ የአዕምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና የማማከር አገልግሎት የምንሰጣቸው አገልግሎቶች: 🌀 አጠቃላይ የአዕምሮ ጤና ምርመራ እና አጠቃላይ የጤና ምርመራ 🌀ለሱስ ማገገምያ የማማከር አገልግሎት 🌀የሳይኮቴራፒ/ የንግግር ህክምና 🌀በሃኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶች አጠቃቀም ማስተማርና መስጠት ለበለጠ መረጃና ቀጠሮ ለማሥያዝ ይደውሉልን ስልክ ቁጥር/WhatsApp ☎️ +251949114685 ☎️ +251925801544       0714266756 ✅Join Us @ethiopsychiatry @ethiopsychiatry
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.