cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

◎የኔ እይታዎች እና ግጥሞች 💁‍♀

ያሰብኩትን ከመፃፍ ና ለናንተ ከማቅረብ ራሴን ማስቆም አልችልም እና ሁሌ አዲስ ነገር ይዘንላችሁ እንቀርባለን እናንተም ማለት ምትፈልጉት ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ @trustmee143ወይም @painkillerrrrrrrrrrr ላይ ጀባ ልትሉን ትችላላችሁ 😘

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ተመልሼ አልመጣም ከወንጌል:ቃል :ሁሉ:እግዜር :ካስተማረው ነብስያዬን :ገዝቶ:ቀልቤን:የማረከው ከልቡ:የሆነ : :ይድናል:የሚለው !! ምክንያቱም :አለሜ : ምክንያቱም :ህመሜ የእውነትን:ካልኖርኩ :እኔ :አልድንም:ፆሜ ፀሎትም:አይሰምር: አይፈይድም:ስግደት ሰደቃም:አያርግ:ይስሙላ: ካለበት እናልሽ:አለሜ : ከወንጌል: ቃል :ሁሉ :እግዜር :ካስተማረው ነብስያዬን:ገዝቶ:ቀልቤን :የማረከው ከልቡ:የሆነ:ይድናል:የሚለው!!! **** ስለዚህ: መሻትሽ:ከልብሽ :ከሆነ በፍቅራችን:ቅጠል:አንቺም:ትድኛለሽ:የኔም ነብስ:ዳነ !! ግና:ነብስያዬን:ፍፁም:ካልወደድሻት ውዴ :ቀረሽብኝ:አንቺም:ቀረሽባት! ደግሞ:ካንቺ :ርቄ: ከሸሸሁኝ:በጣም ውዴ:ካለሽበት:ተመልሼ :አልመጣም
Show all...
Plss hulachum join belu
Show all...
😊አይበልና😂 . . እኔ ፣ ሚስቴ፣ የሚስቴ እህት ተቀምጠን በአንድ ምሽት "አይበልና እና እኔ ብሞት እንደው ሌላ ታገቢያለሽ?" ስል ጠየኳት ውዷ ሚስቴን ልገምታት ... "ምን ሊሆነኝ ካንተ ወዲያ አገባለሁ እስካለልኝ ከእህቴ ዘንድ እኖራለሁ" አለችኝ መልሳ..... "አንተስ ውዴ አይበልና እኔ ብሞት ታገባለህ ሌላ እመቤት?" ጠየቀችኝ በተራዋ ልትገምት እኔም አልኳት••• "ምን ሊሆነኝ ካንቺ ወዲያ አገባለሁ እስካለልኝ ከእህትሽ ጋር እኖራለሁ" 😂😂😂😂😂😂😂 #አንድ_እኩል 😁😁😁😁😁😁😁 እኔ ምለው ይቺን 😂 ብትገጩስ Join @mirakpk1
Show all...
ቀረሽ እንደዋዛ •┈┈•✦•┈┈• ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስ ቆጥር ትመጫለሽ ብዬ ሰዓቱን ስቆጥር ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር ብርድ አቆራመደኝ የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ ውርጩ ቀለደብኝ ጨለማው ሳቀብኝ። አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ መስኮቶች ጨልመው ቤቶች ተቆልፈው ከተማው ሲተኛ አይተዋል ያያሉ አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ። ------------------------------- ©✍ገብረክርስቶስ ደስታ @yegxmrizort @yegxmrizort
Show all...
    #።።።ልማዴ ናፈቀኝ ።።።።   ገና ከመራቅሽ ከአይኔ እይታ ትዝታሽ መጣብኝ በቅፅበት አንዳፍታ በጊዜያት ቆጠራ እብሰለሰላለሁ በህልሞቼ መሀል ሁሌ አንችን አያለሁ ከምኔው በሀሳቤ ስትመጭ ካጠገቤ ላፍታ ትጠፊያለሽ ላቅፍሽ ስል ተስቤ ያበድኩ እስኪመስለኝ ስምሽን ጠራለሁ በሀሳብ ተመስጨ ካንቺ ጋር እውላለሁ ከቶ እውን ላይሆን እኔነቴን ጎዳኝ ፊቴን ቦጭራለሁ ጓደኞቸ እያዪኝ ሀኪም አልሄድ ነገር በሽታ አደለ ልቤ እንዲረጋጋ ከውስጤ እንዲወጣ ኪኒንም አልውጥም መርፌም አልወጋ ወይ እራሴን አልሳትኩ አይወስዱኝ በአልጋ የናፍቆትሽ ልኬት ፍፁም ወሰን የለው ደንበር አልሰጥ ነገር መሀል ሰፋሪ ነው ወይም እንደማትመጭ ወይ ተስፋ አልሰጠኝ ውል እያለው ልቤን እንዳበደ ውሻ ዝም ብሎ ሲያዞረኝ ታዲያ የምን ጉድ ነው ልቤን ያሸከምሽው እባክሽን ውዴ እንደ ፈውስ ፀበል መተሽ ገላግይው          #𝓱𝓪𝓯𝓲𝔃 𝓰𝓪𝓵𝓵𝓮𝓻𝓲𝓮𝓼 ✍️✍️
Show all...
#ትወደዋለች... (ሚካኤል አስጨናቂ) እወደዋለሁ ብላኛለች ፍቅሯን ነግራኛለች። አምናታለሁ ! ደግሞም አላምናትም ብትወደውማ ከሌላ ወንድ ጋር አብራ አትወድቅም! እሷ እንደምትለው ውልደትና እድገቷ ጠባሳው ብዙ ነው የማጣት ቀንበሩ ሸክሙ ከባድ ነው ... ያምራታል መታየት አምሮባት መገኘት እኩል ለመሆን ነው ከጓደኞቿ ጋር  ነፍሷን የምታነደው በቁስ ጥቅም ስካር ለአንድ አልቦ ለአንድ አንባር አንድ አዳር ግድ ነው ከአንዱ ወንድ ጋር። እሷ እንደምትለው.. . ልቧ ታምኖለታል ገላዋ ቢክድም  እንደዛም ሆኖ ግን በሱ ስፍር ልኬት ወንዱን አትመዝንም። ይሄንን አውቃለሁ ! አዎን አምናታለሁ አፍቃሪው ናት ብዬ ከእውነታው ኮብልዬ እሷ እንዳለችው.. . ትውልድና እድገቷ ጠባሳው ብዙ ነው የማጣት ቀንበሩ ሸክሙ ከባድ ነው ገንዘብ ላጣ ድሀ አምሮበት እንዲታይ መፍትሄው ምንድነው? ከወንድ ጋር ማደር ከአንገት በላይ መሳቅ በማስመሰል ስላቅ መጫወት መደነስ  መብነሽነሽ መኩነስነስ ሀጥያት ነው ብዬ ሳልደርስ ለወቀሳ የማዝን መሰለኝ ከጓደኞቿ ዘንድ ብትታይ ተናንሳ ።  አይ አይ አትወደውም ! እላለሁ ለጥቄ ከእውነት ተናንቄ ... የላትም ብትባል ቢንቋት ቢተዋት  ገላዋን ከማርከስ የለም የሚከብዳት ። አይ .. አይ.. አትወደውም ! ብትወደውማ ... ከእምነቱ ሰርቃ ለሌላ ወንድ ወድቃ ... ከሌላ ወንድ ጉያ ውስጡ ተወሽቃ አንድ አዳር አይደለም ለሰከንድ አትቆይም ... እንዲህ ያለ ክህደት ፍቅር አይባልም። ብዬ ከማለቴ ...  ስለሱ ሳወራ ከአንዴም ሁለቴ  የእንባ ውርጅብኝ ጉንጮቿ ላይ ዘርታ ነጉዳ በትዝታ ... በአፍቃሪ ሰው ሲቃ ጠርታዋለች ስሙን አትወደውም ብዬ ይሄን ቃል ባወጣ ... ይሆናል ወይ እሙን ? አይሆንም! አይሆንም ! መውደድማ ትወደዋለች ለፍቅሩ ወድቃለች.. . ሽንፈቱን ደብቃ ሽንፈቷን ደብቃ ... እሷ ጓደኞች ዘንድ  አልቦ ገዝቶልኛል ብላ አውርታለች ሽቶ ገዝቶልኛል ብላ ተናግራለች ። እላለሁ በልቤ በሰው ቁስል እንጨት እንዳልሰድ አስቤ አይ አይ አትወደውም ደግሞ ይለኛል ቀልቤ እንደዚህ ሆኜ ነው እሷን የምሰማት  እንደዚህ ሆኜ ነው እሷን የምቀርባት  ለዚህ መንታ ሀሳቤ  ቁስ ንዋዩ ኖራት  ምናለ ባየኋት ?!... ምናል በመዘንኳት? ብዬም ደግሞ አውቃለው ማጣት ያሸነፈው ፍቅር ግን ምንድነው? አይ አይ... አትወደውም  አይ አይ ...ትወደዋለች ብቻ እንጃ.. . ብቻ እንጃ.. . ይህች ሴት ቅኔ ነች ! @getem @getem @getem
Show all...
#እኔን ፡ ፡ ፡ በመንገድ ስንጓዝ እንቅፋት ሲመታት፣ ሌላ ግዜ ደግሞ ትንታው ሲረታት፣ አላቋርጥ ብሎም ሲብሳት ስርቅታው፣ ገላዋን ሲያግለው መወከል በሽታው፣ የምትወስድ ግዜም ሐኪም ያዘዘውን እንክብል ወይ መርፌ፣ « እኔን የኔ ፍቅር » እንዳልኳት ነበረ ካንጀት ተንሰፍስፌ። ፡ ፡ እንዲያ ስላት ውዬ እንዲያ እያልኩ አድሬ፣ ኖሬ ኖሬ ኖሬ፣ እየው ውረስ ብሎኝ የ አንደበትክን ፍሬ፣ « እኔን » ያልኩት ምኞት ቀን ቆጥሮ ደረሰ፣ ገመምተኛነቴም ውሎ እያደር ባሰ። ህመም ጤና ነስቶኝ ተቆራኘው ካልጋ፣ « እኔን » ያልኳት ፍቅሬ « እግዚአብሔር ይማር » ብላ ጥላኝ ሄደች ጤነኛ ፍለጋ። #ሄኖክ_ብርሃኑ @henockb @getem @getem @getem
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
😐😢
Show all...
😔😭😭ÿənı😔😔
Show all...
Yidnekachew Birahanu - Lemalelesh _ ልማልልሽ.mp312.97 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.