cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

AA Airport Customs branch office /አ.አ ኤርፖርት ጉምሩክ

ራዕይ፡- "በ2022 በአገራችን ደረጃዉን የጠበቀ ዘመናዊ የጉምሩክ አስተዳደር ተገንብቶ ማየት"

Show more
Advertising posts
3 535
Subscribers
+224 hours
+117 days
+4830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጉምሩክ ትራንዚት መሠረታዊ ጭብጦች የትራንዚት እቃ ማለት የጉምሩክ ስነ-ስርአት ሳይጠናቀቅ በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆኖ ከአንድ የጉምሩክ ጣቢያ ወደ ሌላ የጉምሩክ ጣቢያ በተፈቀደ መስመር የሚጓዝ እቃ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ከጉምሩክ ጣቢያ ውጭ በተፈቀደ ቦታ የሚጫንና የሚራገፍ እቃን ይጨምራል፡፡ የትራንዚት አይነቶች 1. የገቢ እቃ ትራንዚት (In ward Transit) 2. የተላላፊ እቃ ትራንዚት (Through Transit) 3. የሀገር ውሰጥ ትራንዚት (Interior Transit) 4. የወጭ እቃ ትራንዚት (Out ward Transit) 1. የገቢ እቃ ትራንዚት (In ward Transit) የገቢ እቃዎች ከወደብ ወይም ከመግቢያ በር ወደ ሀገር ውሰጥ ጉምሩክ ጣቢያ/ የተፈቀደ ቦታ/ በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆኖ የሚተላለፍበት ስርአት ነው፡፡ የገቢ እቃ ትራንዚት በዩኒሞዴል ትራንስፖርት ተጓጉዞ ወደ ሀገር ለሚገባ እቃ በሀገር ውስጥ ካሉ የጉምሩክ ጽ/ቤቶች ትራንዚት ፍቃድ ለማግኘት አስመጪው/ወኪሉ ማቅረብ ያለበት፡- ሀ. የትራንዚት ዲክላራሲዮን(IM-8) ለ. ለቀረጥና ታክስ ክፍያ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ወይም የቀረጥ ነፃ መብት ደብዳቤ ሐ. የማጓጓዣ ሰነድ መ. እቃው በኮንቴኔር የሚያጓዝ ከሆነ የኮንቴነር ዋስትና ማቅረብ ይገባል፤ በጎረቤት ሀገር ከሚገኝ የጉምሩክ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለሚሰጥ የትራንዚት ፈቃድ አስመጪው ወይም ወኪሉ የሚከተሉትን ማቅረብ ይኖርበታል፡- ሀ. ኮሜርሻል ኢንቮይስ ለ. የትራንዚት ዲክላራሲዮን(IM-8) ሐ. የማጓጓዣ ሰነድ መ. ለቀረጥና ታክስ ክፍያ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ወይም የቀረጥ ነፃ መብት ደብዳቤ  በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት በትራንዚት ተጓጉዘው ወደ ሀገር ለሚገቡ ዕቃዎች የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ኦፕሬተሩ አጠቃላይ ዋስትና ማስያዝ አለበት  በጎረቤት ሀገር ጉምሩክ የተሰጠ ትራንዚት ዲክላራሲዮን(IM-8) እና የመንገድ ወረቀት T1 በመግቢያ በር ለሚገኙ ጉምሩክ ማቅረብ አለበት 2. የተላላፊ እቃ ትራንዚት (Through Transit) እቃ ከአንድ የጉምሩክ መግቢያ በር ወደ ሌላ የጉምሩክ መውጫ በር በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆኖ የሚተላለፍበት የአለም አቀፍ የአሰራር ስርአት ነው፡፡ አገር አቋርጠው ወደ ሌላ አገር የሚተላለፍ የትራንዚት እቃ ፈቃድ ለማግኘት አስመጪ ወይም ወኪሉ የሚከተሉትን ማቅረብ አለበት፡፡ ሀ.ትራንዚት ዲክላሪሲዮን (IM8) ለ የማጓጓዣ ሰነድ ሐ. ዋስትና መ. ኮሜርሻል ኢንቮይስ ሠ. ዕቃው ከሚደርስበት አግር የተሰጠ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለበት ሆኖም ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የእርዳታ ድርጅቶች ለተላላፊ ዕቃ የትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት የሚከተሉትን ማቅረብ አለባቸው ሀ.ትራንዚት ዲክላሪሲዮን (IM8) ለ. የማጓጓዣ ሰነድ ሐ. ዋስትና 3. የሀገር ውሰጥ ትራንዚት (Interior Transit) ከአንደ ሀገር ውስጥ የጉምሩክ ጣቢያ ( የተፈቀደ ቦታ ) ወደ ሌላ የሀገር ውስጥ የጉምሩክ ጣቢያ (የተፈቀደ ቦታ) እቃ በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆኖ የሚተላለፍበት ስርአት ነው፡፡ ከአንድ የጉምሩ ክ ጣቢያ ወደ ሌላ የጉምሩክ ጣቢያ ለሚተላለፍ እቃ የትራንዚ ት ፍቃድ ለማግኘት አስመጪ ወ ይም ወኪሉ ማቅረብ ያለበት፡- -- ትራንዚት ዲክላሪሲዮን (IM8) -- የማጓጓዣ ሰነድ -- ዋስትና 4. የወጭ እቃ ትራንዚት ( Out Ward Transit) የወጪ እቃዎች ከሀገር ውስጥ መነሻ ቦታ ወደ ውጪ ሀገር በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆኖ የሚተላለፍበት ስርአት ነው፡፡ የወጪ እቃ ትራንዚት ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ አገር ለሚላክ እቃ የትራንዚት እቃ ፍቃድ ለማግኘት ላኪው ወይም ወኪሉ የሚከተሉትን ማቅረብ አለበት፡፡ ሀ. የወጪ እቃ የትራንዚት ዲክላራሲዮን (EX8) ለ. እንደ አስፈለጊነቱ የተቆጣጣሪ መ/ቤት ፍቃድ የደንበኞች ትምህርት ቡድን መስከረም 3/2017 ዓ.ም ምንጭ፡- የጉምሩክ ትራንዚት መመሪያ 168/2012
Show all...
👍 9
የመልቲ ሞዳል እና ዩኒሞዳል የዕቃ ማጓጓዣ መንገዶች በጉምሩክ ትራንዚት መመሪያ 168/2012 መሰረት፤ ዕቃዎች በሁለት አይነት መንገድ ይጓጓዛሉ፤ 1. ዩኒ ሞዳል ✍️ በዩኒ ሞዳል የሚጓጓዙ ዕቃዎች በዕቃ ዲክላሪስዮን አቅራቢ አስመጪ ወይም በወኪሉ (የጉምሩክ አስተላላፊ) ሙሉ እውቅና ቀረጥና ታክስ በመክፈል ወይም በዋስትና መሰረት የሚደረጉ ጉዞዎች ማለት ነው፡፡ 2. መልቲ ሞዳል ✍️ በመልቲ ሞዳል የሚጓጓዙ ዕቃዎች ከዕቃ ዲክላሪስዮን አቅራቢ ወይም ከወኪሉ እውቅና ውጭ በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት(ኢባትሎአድ) ዋስትና መሰረት የሚደረጉ ጉዞዎች ማለት ነው፡፡ “ዓለም አቀፍ መልቲ ሞዳል ትራንስፖርት” ✍️ቢያንስ በሁለት የተለያዩ የማጓጓዣ ዓይነቶች፣ ወጥ በሆነ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ውል መሰረት መልቲሞዳል ትራንስፖርት አከናዋኙ ከአንድ የተወሰነ ቦታ ተረክቦ በማጓጓዝ ሌላ አገር ውስጥ የሚገኝ የማስረከቢያ ቦታ ለማስረከብ የሚደረግ የማጓጓዝ ሂደት ነው፡፡ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ዋና ዋና ባህሪያት  አንድ የኮንትራት ስምምነት  አንድ ሰነድ  አንድ ትራንስፖርት ኦፕሬተር  ሁለትና ከሁለት በላይ የማጓጓዣ አይነቶች የደንበኞች ትምህርት ቡድን መስከረም 3/2017 ዓ.ም ምንጭ፡- የጉምሩክ ትራንዚት መመሪያ 168/2012
Show all...
🔥 1
ከዊዝሆልዲንግ ታክስ ነጻ የሆኑ ዕቃዎች ዊዝሆልዲንግ ታክስ ማለት የቅድመ ገቢ ግብር ክፍያ ሲሆን ገቢ በማግኘት የታክስ ግዴታቸውን ሳይወጡ የሚሰወሩትን ግብር ከፋዮች በቀላሉ አነስተኛውን ምጣኔ እንዲከፍሉ ለማድረግ ስለሚያስችል ለግብር አሰባሰቡ የመቆጣጠሪያ ዘዴ (Controlling mechanism) ነው፡፡ ይህ ታክስ ተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀናሽ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዉጪ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ 3% እየተጣለ የሚሰበሰብ የታክስ ዓይነት ነዉ፡፡ የሚከተሉት ዕቃዎች ከዊዝሆልዲንግ ታክስ ነፃ የሆኑ ዕቃዎች፡- ✔️በፌደራል እና በክልል የፋይናስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት ለመንግስት መ/ቤት በተሰጠው ትርጉም ውስጥ የተካተቱ የፌደራል መንግስት መ/ቤቶች እና የክልል መንግስታት መ/ቤቶች የሚያስገቧቸው ዕቃዎች ✔️ለትርፍ ያልተቋቋሙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ማህበራዊ የሚያስገቧቸው እቃዎች /ከተቋቋሙበት አላማ ውጭ በንግድ መልክ የሚያስገቧቸውን ዕቃዎች አይጨምርም ✔️ በዲፕሎማቲክ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት ከንግድ ትርፍ ግብር ነጻ የሆኑ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የውጭ ዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱለር ሚሲዮኖችና የእነዚሁ አባላት የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፡፡ ✔️ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ከቀረጥ ነጻ ወይም ቀረጥና ታክስ ከፍለው እንዲያስገቡ የተፈቀደላቸው ግለሰቦች የሚያስገቧቸው እቃዎች ✔️በጉምሩክ ታሪፍ ደንብ 2ተኛ መደብ (ለ) ተጠቃሚ ሆነው እቃዎችን የሚያስገቡ ግለሰቦችና ድርጅቶች ✔️ በፌዴራልና በክልል ኢንቨስትመንት ባለስልጣን ከገቢ ግብር ነጻ የመሆን መብት/Tax Holiday/ የተፈቀደላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በእፎይታው ጊዜ ውስጥ የሚያስገቧቸው እቃዎች ✔️ የአምራችነት ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች ለሚያመርቷቸው ዕቃዎች በግብአትነት የሚጠቀሙባቸው ጥሬ ዕቃዎች እና ለካፒታል ዕቃዎች የሚያገለግሉ መለዋወጫዎች ✔️ኢንዱስትሪዎችን ለማቋቋም ወይም ለማስፋፋት ወይም ለሃይል ማመንጫ ወይም የመገናኛ አገልግሎት ለመዘርጋት ወዘተ ወደ አገር የሚገቡ የካፒታል ዕቃዎች ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ወይም ጉዳይ ከሚመለከተው አካል የካፒታል ዕቃዎች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከቀረበ ✔️የንግድ ትርኢት ለመሳተፍ የሚመጡ የውጪ አገር ድርጅቶች ምርታቸውን ለማስተዋወቅ ወደ አገር ውስጥ ይዘውት የሚገቡት እቃ ✔️በማዕድን እንዲሁም በፔትሮሊየም ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ለነዚህ ስራዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገቧቸው እቃዎች ✔️ለሰብዓዊ እርዳታ ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች ያካትታል፡፡ የደንበኞች ትምህርት ቡድን መስከረም 3/2017 ዓ.ም ምንጪ፡- የቅድመ ግብር ክፍያ መመሪያ ቁጥር 2/2011
Show all...
👍 1🔥 1
የዕቃዎች የሥሪት አገርን ለመወሰን ግምት ውስጥ የማይገቡ ሁኔታዎች 1. የዕቃው የሥሪት አገር ሲወሰን ዕቃውን ለማምረት ጥቅም ላይ የዋሉ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ነዳጅ፣ የማምረቻ ህንጻና መሳሪያ፣ የደህንነት መጠበቂያ መሣሪያዎችን ጨምሮ፣ ማሽኖች እና የዕጅ መሳሪያዎች መጨረሻ ላይ የዕቃው አካል የማይሆኑ በመሆኑ የስሪት አገር ለመወሰን ከግምት ውስጥ አይገቡም፡፡ 2. የሚከተሉት የስራ ሂደቶች የታሪፍ አመዳደብ ለውጥ የሚያስከትሉ ሆኑም አልሆኑም ወደ አገር ውስጥ የገቡ ዕቃዎች የሥሪት አገር ለመወሰን ከግምት ውስጥ አይገቡም ✔️ በምርት ማጓጓዝ ወይም ክምችት ወቅት ምርቱን ባለበት ሁኔታ ለማቆየት የሚከናወኑ ተግባራት ✔️ የዕቃዎችን የማጓጓዝ ሂደት ለማቀላጠፍ ሲባል የሚከናወኑ ተግባራት ✔️ ዕቃዎችን ለማሸግ ወይም ለሽያጭ ለማዘጋጀት ሲባል የሚከናወኑ ተግባራት ✔️ ዕቃዎችን በአየር የማናፈስ፣ የማስጣት፣ የማድረቅ፣ የማቀዝቀዝ፣ የተበላሹ ክፍሎችን የመቀየር፣ ማለስለሻ የመቀባት ወይም ዝገት የማስወገድ ተፈጥሮአዊ ሁኔታዎች በዕቃው ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ቀለም የመቀባት፣ የማጠብ፣ የማጽዳት፣ የማበጠር፣ የመፈተግ፣ የመለየት፣ የመመዘን፣የመሞከር፣ የመለካት፣ የማሸግ፣ እሽጎችን የመፍታትና መልሶ የማሸግ የመከፋፈል ምልክት የማድረግ በውሃ ወይም በሌላ ፈሳሽ ነገር አያያዝ ማድረግ በጨው የመንከር የመላጥ የመከካት የመውቃት እና የእንስሳት እርድ የመሳሰሉት ቀላል ሂደቶች ክንውን፤ ✔️የተሟላ የምርት ውጤት ለማስገኘት የሚከናወን ቀላል የመገጣጠም ሥራ ያካትታል፡፡ ……………….//…………….. የደንበኞች ትምህርት ቡድን ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም ምንጭ፡- የዕቃዎች የስሪት ሀገር አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 134/2010
Show all...
👍 3 1
ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ለአገር ውስጥ ፍጆታ የምርት ሂደታቸውን እንዲያጠናቅቁ ስለሚደረግበት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ……………………………………………………………………………………………….. 1. ወደ አገር ውስጥ የገቡ ዕቃዎች ለአገር ውስጥ ፍጆታ ከመለቀቃቸው በፊት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ሆነው የምርት ሂደታቸውን እንዲያጠናቅቁ ኮሚሽኑ ሊፈቅድ የሚችለው፡- ✔️ የሂደቱ ውጤት የሆኑትን ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ከተደረጉት ዕቃዎች የተገኙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሲሆን ✔️ የምርት ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ዕቃዎቹን ቀድሞ ወደ ነበሩበት ሁኔታ መልሶ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲሰጡ ለማድረግ የማይቻል ሲሆን፤ 2. ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች ለአገር ውስጥ ፍጆታ ከመለቀቃቸው በፊት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ሆነው የምርት ሂደታቸውን እንዲያጠናቅቁ በማድረግ ተግባር ላይ በመደበኛነት ለሚሠማራ ሰው ሂደቱን የሚሸፍን አጠቃላይ ፈቃድ ኮሚሽኑ ሊሰጥ ይችላል። 3. ከላይ በተራ ቁጥር (1) እና (2) ድንጋጌ ተፈጻሚ ሊደረግ የሚችሉ ዕቃዎች ዓይነት ፈቃድ ለመስጠት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እና የጉምሩክ ቁጥጥሩን የሚመለከቱ እርምጃዎች ኮሚሽኑ በሚያወጣው መመሪያ ይወስናሉ፡፡ 4. ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች ለአገር ውስጥ ፍጆታ ከመለቀቃቸው በፊት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ሆነው የምርት ሂደታቸውን እንዲያጠናቅቁ የማድረግ ተግባር የዕቃዎቹ አስመጪ ከሆነው ሰው ውጪ በሌላ ሰው እንዲከናወን የሚፈቀድበት ሁኔታ ኮሚሽኑ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡ የቀረጥና ታክሱ አከፋፈል ወደ አገር ውስጥ የገቡ ዕቃዎች ለአገር ውስጥ ፍጆታ ከመለቀቃቸው በፊት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ሆነው የምርት ሂደታቸውን እንዲያጠናቅቁ ሲደረግ እነዚህ ዕቃዎች ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሊለቀቁ የሚችሉት ምርቶቹን ለማምረት ወደ አገር ውስጥ በገቡት ጥሬ ዕቃዎች ላይ ሊከፈል በሚገባው ታሪፍ መሠረት ቀረጥና ታክስ ከተከፈለ በኋላ ይሆናል፡፡ ሥነ-ሥርዓቱ ስለሚቋረጥበት ሁኔታ 1. ወደ አገር ውስጥ የገቡ ዕቃዎች ለአገር ውስጥ ፍጆታ ከመለቀቃቸው በፊት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ሆነው የምርት ሂደታቸውን እንዲያጠናቅቁ የሚደረግበት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ወደ አገር የገቡት ጥሬ ዕቃዎች ቀረጥና ታክሱ ተከፍሎባቸው ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሲለቀቁ የተፈቀደው የጉምሩክ ሥነ -ሥርዓት ይቋረጣል፡፡ 2. ከላይ በተራ ቁጥር (1) ላይ ድንጋጌ ቢኖርም ተቀባይነት ሊሰጠው የሚችል ምክንያት ኖሮ ወደ አገር የገቡት ጥሬ ዕቃዎች ሌላ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት እንዲፈጸምባቸው በኮሚሽኑ ሲፈቀድ የቀረጥና ታክሱ አከፋፈል የተፈቀደው የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ይቋረጣል፡፡ ሆኖም ተፈጻሚ እንዲሆን የሚፈቀደውን ሌላውን የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት የሚመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎችና ገደቦች መከበር ይኖርባቸዋል፡፡ የደንበኞች ትምህርት ቡድን ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም ምንጪ፡- የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006
Show all...
👍 2
👍 2🔥 2
የውጤት ተኮር ስርአትን እና የለዉጥ ትግበራን አስመልክቶ ስልጠና ተሰጠ። በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ የስልጠና አዳራሽ የቢ ኤስ ሲ(BSC) እቅድ አስተቃቀድና የውጤት ተኮር ስርአትን እንዲሁም የለዉጥ ትግበራን የተመለከተ ስልጠና ከነሐሴ 21 ቀን ጀምሮ በአራት ዙሮች ለ200 አመራሮችና ሰራተኞች ተሰጠ፡፡ የቅ/ጽ/ቤቱ የአቅምና ድጋፍ ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ዘራኤል ለዓ አለሙ ስልጠናውን ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት በቅ/ጽ/ቤቱ የቢ.ኤስ.ሲ ስልጠና መሰጠቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ስራን በትክክል ቆጥሮ ከመስጠት አንስቶ ትክክለኛ የምዘና ስርዓት እንዲኖር ከማስቻሉም በላይ ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት ከአመራርና ሰራተኛው የሚጠበቁ ውጤቶችን ከማምጣት አንጻር ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ በተጨማሪም አመራሩና ሠራተኛው የተሰጠውን ግብ ከየዕለት ስራውና አፈጻጸም ጋር አስተሳስሮ የሚያይበት፣ የሚከታተልበት፣ የሚደግፍበት እንዲሁም የሚገመግምበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መረሃ-ግብሩን የማዘጋጀት አስፈላጊነትን ተናግረዋል፡፡ ስልጠናዉን የሰጡት የፕላኒንግ እና የለዉጥ ስራዎች ስራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ አየለች ጡምዶሎ በበኩላቸዉ ስልጠናው ቢ ኤስ ሲ(BSC) እቅድ አስተቃቀድ፣ የውጤት ተኮር ስርአትን እና ከባለፈው በጀት አመት የመጡ መልካም አፈፃፀሞችን ይዘን ለአዲሱ 2017 በጀት አመት የታቀደዉን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የአገልግሎት አሰጣጥን የምናሳልጥበትና የሚታዩ የአፈጻጸም ክፍተቶችን የምንፈታበት መደላድል የሚፈጥር ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ አየለች አያይዘዉም ተቋሙ የውጤት ተኮር ሥርዓትን በመዘርጋት፣ አፈፃፀምን ሚዛናዊ በሆነ ዕይታ አስተሳስሮ ለመምራት፣ የሚፈለገውን ውጤት ከበጀት ጋር አጣጥሞ ለመተግበር፣ ስትራቴጂያዊ ግቦችን ወደ አፈፃፀምና ተግባራት ለመቀየርና የቅድሚያ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን ስራዎችን ለይቶ በማውጣት ስትራቴጂን የዕለት ተዕለት ሥራ ለማድረግ የባላንስድ ስኮር ካርድ (ዉጤትተኮር)እቅድ የአፈፃፀም ማዕቀፍ ተመራጭ በመሆኑ የቅ/ጽ/ቤቱን እስትራቴጂ በዚሁ አግባብ በመቅረፅ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን የቅ/ጽ/ቤቱ ሰራተኞች እና አመራሮች በቢ ኤስ ሲ(BSC) ፅንሰ ሀሳብ ላይ ስልጠና እንዲወስዱ እና በስራቸው ያሉ ሰራተኞችን በማሰልጠን የጋራ መግባባት ተደርሶ ወደ ትግበራ እንዲገቡ የሚያስችል በመሆኑ ሁሉም አመራርና ፈጻሚ የተሰጠዉን ተልዕኮ በብቃት በመወጣት ቅ/ጽ/ቤቱ የሚጠበቀዉን የገቢ እቅድ እና የፊዚካል ስራዎችን በሙሉ ኃላፊነትና ባለቤትነት እንዲወጣ አደራ ብለዋል፡፡ በተያያዘ ዜና የለዉጥ ስራዎችን አስመልክቶ ስልጠና የሰጡት የለዉጥ ስራዎች ቡድን አስተባባሪ አቶ አብርሃም አብተው እንደተናገሩት፤ የተሻሻሉ ደንብና መመሪያዎችን መገንዘብ፣ ከይስሙላ የወጣ እቅድ አቅዶ በአግባቡ መፈፀም እና የመሳሰሉ ተግባራትን መሬት ማስነካት ስለሚገባ ቀጣይነት ያለዉ ድጋፍና ክትትል ይደርጋል ብለዋል። በስልጠናዉ ዘጠኙን የቢ ኤስ ሲ(BSC) ደረጃዎች በየደረጃው በማሳየት የተቋሙ እቅድ ይህን መሰረት አድርጎ በመዘጋጀቱ እና ይህም እቅድ ደረጃ በደረጃ ወደ ሰራተኛው ሲወርድ ሰራተኞች እንዴት የግል ዕቅድ ማዘጋጀት እንደሚችሉ ለማሳዬት በተግባር የተደገፈ ሰፊ ገለፃ እና ውይይት ተደርጓል፡፡ …………//…………. የደንበኞች ትምህርት ቡድን ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም
Show all...
👍 2
ወደ ተፈቀደ የጉምሩክ መጋዘን የገቡ ዕቃዎችን የማቆያ የጊዜ ገዳብ 1. በኮሚሽኑ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል ውሳኔ መሠረት ወደ ቦንድድ መጋዘን ፣ቦንድድ ኤክስፖርት ፋብሪካ፣ የቦንድድ ኤክስፖርት ማምረቻ መጋዘን እና የቦንድድ ግብአት አቅርቦት መጋዘን የገቡ እቃዎችን በሚከተሉት ምክንያቶች የጊዜ ገደቡን ለተጨማሪ ጊዜ ሊራዘም ይችላል፡- ሀ/ ከኢንዱስትሪው የሚገለገልበት ማሽን በመሰበሩ ወይም በሰራተኞች የሥራ ማቆም እድሜ እና ሌሎች አሳማኝ ምክንያት ድርጅቱ ከአንድ ወር ላላነሰ ጊዜ ሥራ ማቆሙን የሚያረጋግጥ መረጃ ሲቀርብ፣ ለ/ ጥሬ ዕቃው በዓለም ገበያ ላይ እጥረት ያለበት በመሆኑ ወይም ከፍተኛ የግዢ ትዕዛዝ በመኖሩ ምክንያት የተያዘ ስቶክ ሲኖር፣ ሐ/ ምርቱን የሚገዛው የውጭ ድርጅት ውሉን ማፍረሱ ሲረጋገጥ ወይም ሌላ ገበያ ለማግኘት ተጨማሪ ጊዜ የሚያስፈልግ ሆኖ ሲገኝ፣ መ/ በሌሎች ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች፣ ሠ/ በዚህ ንዑስ አንቀጽ /ሀ/ ፣/ለ/፣ /ሐ/ እና /መ/ ከተመለከተው በተጨማሪ ስልጣን ከተሰጠው አካል የድጋፍ ደብዳቤ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ 2. ባለፈቃዱ በአንድ በጀት ዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ የማራዘሚያ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም፡፡ 3. የጊዜ ገደብ ማራዘሚያ ጥያቄ የሚቀርበው የጊዜ ገደቡ ከማለፉ በፊት መሆን አለበት 4. የማራዘሚያው ጥያቄ በኮሚሽነሩ ወይም ኮሚሽነሩ በሚወክለው አካል ሲፈቅድ ብቻ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ………..//……….. የደንበኞች ትምህርት ቡድን ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም ምንጭ :-የጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 154/2011
Show all...
👍 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.