cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሙሐመድ አል-ወልቂጢይ ((አቡ ዘከሪያ))

https://t.me/abuzekeryamuhamed ✍ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱ ላሂ ወበረካቱ። ውድ እና የተከበራቹ የዚህ ቻናል ተከታታዮች ይህ ቻናል ረመዳን 29 1442 አ.ሂ የተከፈተ ቻናል ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሀገራችን ሙስሊም ማህበረሰቦችን በተለይም ደግሞ ወልቂጤ ላይ እና ዙሪያዎቿ የሚገኙትን ታሳቢ በማድረግ የተከፈተ ጥርት ያሉ የሰለፊያ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው።

Show more
Advertising posts
7 484
Subscribers
+1024 hours
+737 days
+17830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
አስደሳች የደርስ ዜና ለዲን እውቀት ፈላጊዎች منظومة البيقونية መንዙመቱ'ል በይቁኒየህ በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል በሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ (ሀፊዘሁላህ) ሸርህ ይደረጋል ቀን:- ዘውትር ሐሙስና ጁምዓ ሰኣት:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ደርሱ በአላህ ፈቃድ ነገ ሐሙስ ይጀመራል የኪታቡ መትን የሌላችሁ መርከዝ ይዘጋጃል ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
Show all...
👍 6
📚 اسم الكتاب: صحيح المسلم المؤلف: أبو الحسين مسلم بن الحجاج بن مسلم بن وَرْدٍ النيسابوري (٢٠٦ - ٢٦١)  هجرية باب: باب الدليل على أن من مات على التوحيد دخل الجنة قطعا 🎤  المدرس: د. شيخ حسين بن محمد السلطي تاريخ: ربيع الأول  ١٥، ١٤٤٦ هجرية الموافق سبتمبر ١٨، ٢.٢٤ م في مدرسة الإصلاح https://t.me/medresetulislah
Show all...
صحيح_المسلم_باب_الدليل_على_أن_من_مات_على_التوحيد_دخل_الجنة_18_09.mp311.82 MB
📚 اسم الكتاب: . نزهة النظر في توضيح نخبة الفكر في مصطلح أهل الأثر الدرس الثالث المؤلف : الحافظ ابن حجر العسقلاني رحمه الله (773 - 852هـ) 🎤  المدرس: الشيخ د. حسين بن محمد السلطي تاريخ: ربيع الأول  ١٥، ١٤٤٦ هجرية الموافق سبتمبر ١٨، ٢.٢٤ م في مدرسة الإصلاح https://t.me/medresetulislah
Show all...
نزهة النظر Part-3_18-09-24_13-48-29-459_32_43.mp319.64 MB
በአሏህ ፍቃድ ከዛሬ ጀምረው እነዚህ ኪታቦች በሰዓታቸው ይቀራሉ 1📚الإرشاد إلى صحيح الإعتقاد 2📚روضة الأنوار في سيرة النبي المختار 3📚الداء والدواء 4📚دعائم منهاج النبوة 🗓 ከ4:00 _ 6:20 ከዚህ በፊት ትከታተሉ የነበራችሁ ወንድም እህቶች ኪታባችሁን ይዛችሁ ደርስ ቦታ እንገናኝ وإلى اللقاء السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🕌 ቦታ አዳማ 01 ቀበሌ በኢብኑ ተይሚየህ መስጂድ https://t.me/abuabdurahmen
Show all...
👍 2
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ዘወትር ሮቡዕ እና ሐሙስ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ የኪታብ ደርስ ለምትከታተሉ ተማሪዎች በሙሉ። ሸርሑ ሱናህ ሊልበርበሃሪይ የሸይኽ ሷሊሕ አልፈውዛን ኢብኒ ዓብዲላህ አልፈውዛን ሸርሕ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን። https://t.me/medresetulislah
Show all...
مدرسة الإصلاح (አል ኢስላሕ መድረሳ)

ይህ ቻናል “❝ከፉሪ ሕይወት ፋና ወደ የስ ውሃ ፋብሪካ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ ኑሪ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የአል ኢስላሕ መድረሳ ኦፊሺያል የቴሌግራም ቻናል ነው።❞ በአላህ ፍቃድ በመድረሳው የሚሰጡና በተለያዩ የሰለፊያህ ዱዓቶች፣ ኡስታዞችና መሻኢኾች የሚተላለፉ መልዕክቶች (በድምፅም ይሁን በፅሑፍ) ይተላለፉበታል። ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ።

https://t.me/medresetulislah

👍 1
📚 اسم الكتاب: . نزهة النظر في توضيح نخبة الفكر في مصطلح أهل الأثر- الدرس الثاني المؤلف : الحافظ ابن حجر العسقلاني رحمه الله (773 - 852هـ) 🎤  المدرس: د. شيخ حسين بن محمد السلطي تاريخ: ربيع الأول  ١٤، ١٤٤٦ هجرية الموافق سبتمبر ١٧، ٢.٢٤ م في مدرسة الإصلاح https://t.me/medresetulislah
Show all...
نزهة النظر Part-2_17-09-24_13-57-05-341_21_4.mp320.81 MB
✅ ተጨማሪ ቡሽራ ለኢስላም ብርሃን የእውቀት ማእድ ቤተሰቦቻችን በአላህ ፈቃድ በዚሁ ግሩፕ ከዛሬ ጀምሮ የሸይኻችን ሸይኽ አቡ ዘር ደርሶች ቀጥታ ስርጭት የሚጀመር መሆኑን ስናበስራችሁ በደስታ ነው ። https://t.me/YeIslam_brhan_ye_ewket_maed
Show all...
የኢስላም ብርሃን የዕውቀት ማዕድ

በአላህ ፍቃድ በተለያዩ ሀገር ለሚገኙ ሙስሊም ወገኖቻችን ትክክለኛውን የኢስላም አስተምህሮት ከሳምንት እስከ ሳምንት በሚቆይ መልኩ በተለያዩ ውድ ታላላቅ የሱና መሻይኾችና ኡስታዞች ቋሚ ትምህርቶች በonline የሚተላለፍበት ግሩፕ ሲሆን አድ add እያደረግን የኢስላምን ነጸብራቅ ተደራሺነቱን በማስፈን ላይ እንረባረብ!

👍 2
📌መውሊደኞችና የቀን ቅዠታቸው [የሽርክና የተለያዩ ወንጀሎች መናኻሪያ የሆነውን መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎችን፣ “መውሊድ አክባሪ” እያልን ከምንጠራ፣ “መውሊደኛ” ብንላቸው ጥሩ ነው - ቃላት በመቆጠብ በቀላሉ መግባባት እንችላለንና፡፡ “መውሊደኛ” በማለት ከመውሊድ ጋር 'ስላዋሀድናቸው' እነሱም ደስ ሳይላቸው አይቀርም - ቂል “በአሽሙር ሲወጉት ያደነቁት ይመስለዋል” እንዲሉ፡፡] የሐገራችን መውሊደኞች ሸሪአዊ ማስረጃ የሌለውን መውሊድ፣ ኢስላማዊ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ፣ የማይወጡት ተራራ፣ የማይወርዱት ገደል የለም፡፡ ይህን ያህል ኳትነው የሚያቀርቡት ሀሰተኛ የማስረጃ ቡትቶ፣ በአሏህ ዲን ላይ ከመቀጣጠፍ የማይመለሱ ግብዞች መሆናቸውን ከማሳያት አይዘልም፡፡ መስከረም 5 ምሽት ላይ አሚኮ በትእይተን ዜና ፕሮግራሙ፣ “መውሊድና አሰተምህሮቱ” በሚል ርእስ ያቀረበው ዝግጅት፣ መውሊደኞች ምን ያህል በቀን ቅዠት የተለከፉ ከንቱዎች ለመሆናቸው አንድ ጥሩ አብነት ሆኖ አልፏል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ድርሳናት መምህር ከሆነው ከዶ/ር እንድሪስ ሙሀመድ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ቀርቧል፡፡ ይህ ሰው የአህባሽ ዋና አቀንቃኝ የሆነው የሀሰን ታጁ የቀኝ እጅና የቀድሞው መጅሊስ የህዝብ ግንኙነት ባልደረባ የነበረ ነው፡፡ ዶ/ር እንድሪስ “ከቃል ፍች አኳያ ስለውልድት ነው የምናወራው፡፡ ውልደቱ ግን የስተዋልዶ ውልደት ላይ ያተኮረ አይደልም” ካለ በኋላ  የነብዩን (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) “የውልደት ትኩረት” በሚከተለው መንገድይገልፃል፡-  “የስልጣኔ ውልደት፣ የስነመለኮት    ትምህርት ውልደት፣ የስነ ምግባር ውልደት፣ የአኗኗር ዘይቤ ውልደት፣ የህግና ስርአት ውልደት፣ የሰላም ውልደት፣ የአብሮነት ውልደት፣ የእዝነትና የፍቅር ውልደት በአጠቃላይ ለሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት የሚጠቅሙ የህይወት አስተምህሮቶችና ትግበራዎችን የምንዳስስበት፣ የምናይበት፣ ውልደቱ ከሪሳላ ወይም ከተልእኮ ጋር የተያያዘ ነገር ነው፡፡ የላክንህ ለአለም እዝነትን፣ መተዘዘንን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን ልታጎናፅፍ ነው የተላከው ይላል፡፡” ሆኖም ዶ/ር እንድሪስ እዚህ ላይ የዘረዘራቸው ጉዳዮች፣ የአሏህ መልእክተኛ (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) የተወለዱበት ትኩረትም ሆኑ አላማዎች አይደሉም፡፡ ነብዩ ሙሀመድ፣ ነብይም ሆነ መልእክተኛ የሆኑት በውልደታቸው አይደልም፡፡ እንደተወለዱ ብቻ ሳይሆን እስከ 40 አመታቸው ድረስ ነብይ አልሆኑም፡፡ መውሊደኛው ዶ/ር እንድሪስ እዚህ የዘረዘራቸው ጉዳዮችም፣ ከነብይነት በኋላ እንጂ ስለተወለዱ የተገኙ ትሩፋቶች አይደሉም፡፡ የሀገራችንን መውሊደኞች የቀን ቅዠታቸው እንዲህ ነው የሚያደርጋቸው፤ እንዲህ ነው የሚያሰክራቸው፡፡ መውሊደኛው ዶ/ር እድሪስ፣ መውሊድን ገበያ እንደምትወጣ ሴት አዳሪ ኳኩሎ ለማቅረብ ሲል፣ የነብይነት ትሩፋቶችን የውልደት ቱሩፋቶች አድርጎ አቀረባቸው፡፡ የመውሊድ ፍቅር ሰዎቹን እንዴት በቀን ቅዠት እያሰከራቸው አንደሆነ ልብ በሉ፡፡  ማንም እንደሚያውቀው፣ የአሏህ መልእክተኛን (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) አሏህ ነብይ አድርጎ የላካቸው እድሜያቸው 40 አመት እንደ ሞላ ነው፡፡ አሏህ በተከበረው ቁርአኑ፣ “ለአለማት እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም” (አል-አንቢያ፣ 107) ያላቸው፣ እድሜያቸው 40 አመት ሞልቶ በነብይነት ከላካቸው በኋላ ነው፡፡  ከዚህም በላይ መውሊደኛው ዶ/ር እድሪስ በከፍተኛ ድፍርት ተሞልቶ፣ እንዲህ ይላል፡- “በውልደታች የተከሰቱት፣ ከውልደትም እስከ አርባ አመታቸው ድረስ በምን ሁኔታ ነበር ነብዩ ሙሀመድ የኖሩት - በጣም አስፈላጊው ዘመን እስከ አርባ አመት የኖሩበት ዘመን ነው፡፡ እንደ ሰው የኖሩበት ዘመን ስለሆነ” ይላል፡፡ ይህን የሚለን ግን፣ ከላይ ከፍ ሲል ነብይ ሆነው በመላካቸው የተገኙትን ቱሩፋቶች የመወዳቸው ቱሩፋቶች አስመስሎ ካቀረበልን በኋላ ነው፡፡ በሌላ በኩል “በጣም አስፈላጊው ዘመን እስከ አርባ አመት የኖሩበት ዘመን ነው” ብሎ ለወሸከተው፣ አንዲትም ማስረጃ ወይም ቱረፋት አልነገረንም፡፡ ወይ ቅዠት! ከሁሉ ክፉው ቅዠት ደግሞ የቀን ቅዠት ነው፡፡ የሌሊትን ቅዠት በመባነን ወይም በንጋት ይገላገሉታል፡፡ የቀን ቅዥትን ግን ምን ያደርጉታል? ሲቃዡ መኖር ብቻ! የመውሊድ ፍቅር እንዲህ ነው የሚያስቃዥ! ቢድአ እንደዚህ ነው - በስሜት አረቄ በማስከር፣ በማይጨበጥ የቅዠት አለም ውስጥ እንድትኖር ያደርግሀል፡፡  መውሊደኛው ዶ/ር እንዲህ በማለት ይቀጥላል፡-      “የነብይነት ማእረግ ከተሰጡ በኋላ ያለው ወቅት፣ መለኮታዊ እገዛም አለ፤ ተልእኮም ተሰጥቷቸዋል፤ አድናቆትህን የምትቸረው ቢሆንም፣ ከአርባ አመት በፊት ግን የነብዩ ሙሀመድ ስብእናና ማንነት በራሱ በዚህ የውልደት በአል የምናስተውለው ነው፡፡ ከአርባ አመት በፊት የነበራቸው ማንነት ነው ለነብይነትም እንዲታጩ ያደረገው፡፡” ከዚህ የቀን ቅዠት ንግግር ውስጥ ሁለት አደገኛ ነጥቦችን እናገኛለን፡፡ አንደኛ ነገር፡- መውሊደኛው ዶ/ር እድሪስ ከልደታቸውም ቀን አልፎ እስከ አርባ አመት ያለውን የእድሜያቸው ጊዜ ክፉኛ ከፍ-ከፍ አድርጎታል፤ ክፉኛ ሰቃቅሎታል፡፡ በዚህ አያያዙ ነገ ከነገ ወዲያ “የነብዩ አስረኛ አመት የመውሊድ በአል”፣ “የነብዩ ሀያኛ አመት የመውሊድ በአል”፣ “የነብዩ ሰላሳኛ አመት የመውሊድ በአል”… የሚል ተጨማሪ፤ ቢድአ ይዞ ብቅ እንደማይል ምን ዋስትና አለ? መውሊደኞቹ መጅሊሶች “የኡለሞች መውሊድ” በማለት ተጨማሪ ቢድአ መስርተው ማክበራቸውን አትርሱት እንጂ! ሁለተኛ ነገር፡- በተማኙ ጅብሪል አማካኝነት ቁርአን ከሰባቱ ሰማያት በላይ ወደ መልእክተኛው (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) የወረደበትን፣ የተውሂድ ፓውዛ የተንቦገቦገበትን፣ የጃህልያ ስርአትና ስፍር ቁጥር የሌላቸው የአረቡ ምድር ጣኦታት የተንኮታኮቱበትን፣ የኢስላም ብርሀን ከመካ መንደር በአራቱም አቅጣጫ ወደ አለም የተሰራጨበትን፣ የአሏህ በብቸነት ተመላኪነት የበላይ የሆነበትን፣ የከሀድያኑ የሮምና የፋርስ ግዛቶች ለኢስላም እጅ የሰጡበትን… ባጭሩ ከአርባ አመት በኋላ ያለውን የነብይነት ጊዜ፣ “አድናቆትህን የምትቸረው ቢሆንም” በማለት ከነብይነት በፊት ካለው ስኬታቸው ዝቅ ተደርጎ እንዲታይ ለማድረግ ሞክሯል - መውሊደኛው ዶ/ር እድሪስ፡፡ አሁን ይሄ ምን ይባላል? ይህን መሰሉ የቀን ቅዠት በምን ይገለፃል? በቁርአንም ሆነ በሀዲስ ምንም ማስረጃ በሌለው የመውሊድ ቢድአ ከንቱ ፍቅር ተለክፈው፤ በቀን ቅዠት የሚሰቃዩት እነዚህ የሀገራችን መውሊደኞች፤ ቆሻሻ የሆኑ የሽርክ ተግባራት መናገሻ የሆነውን መውሊድን ጥሩ አስመስሎ ለማሳየት የማይፈነቅሉት የሀሰት ድንጋይ፣ ፀያፍ የሆኑ ወንጀሎች መናኻሪያ የሆነውን መውሊድ ለማቆንጀት የማይጠቀሙበት የውሸት ኮስሞቲክስ የለም፡፡ ቢድአን አምልኮ አድርጎ ከያዘ ሰው የበለጠ እውር፣ ስሜቱን አምላክ አድርጎ ከያዘው የበለጠ ጠማማ ማን አለ? “ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን፣ አላህም ከዕውቀት ጋር ያጠመመውን፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን፣ በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን! ታዲያ ከአሏህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሠጹምን?” (አል-ጃሲያህ፣ 23)  መውሊደኛው ዶ/ር እድሪስ ስለመውሊድ የቦተለከው የቀን ቅዠት ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በፕሮግራሙ የተላለፈውን “ክሊፕ” እያስፈለኩ ነው፡፡ ከተገኘ በጋራ የምናየው ይሆናል፡፡ ዝግጅት/በዶክተር ጀማል ሙሐመድ - ሀፊዞሁሏህ - https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Show all...
👍 1
ሐያእ (አይናፋርነት) ለሴት ልጅ ትልቁ ሀብቷና ውበቷ ነው!! ————— ሐያእ በመሰረቱ ወንዱም ሴቱም ጋር ሊኖር የሚገባው ተወዳጅ ምርጥ ባህሪ ነው። በተለየ መልኩ ግን ሴቶች ዘንድ ወሳኝነት አለው። ይሁን እንጂ ሐያእ (አይናፋርነት) የሚባለው ነገር አላህ ካዘነላቸው ጥቂት እንስቶች በስተቀር "ብን!" ብሎ የጠፋ ይመስላል። ሴት ልጅ አይናፋርነት ከሌላት እንዲሁ ባህሪዋ ለባሏ እንኳ አይማርከውም፣ ምክንያቱም አይናፋርነት ለሴት ልጅ ከፈጣሪዋ ከአላህ የተሰጣት ልዩ ውበትና ግርማ ሞገሷ፣ ተፈጥሯአዊ የሆነ ስጦታዋ ነውና። ሀያእ (አይናፋርነት) የሚባለው ነገር ከብዙ ሴቶች ልብ ድራሹ ጠፍቶ በስመ ስልጣኔ ጋጠ-ወጥ ሴቶች አስባልቱን ከሞሉት ሰነባብቷል። እንዲያውም አንዳንዴ በተቃራኒው ሀያእ የሚባለው ነገር ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ዘንድ ይስተዋላል። በተለያዩ ዝግጅቶች፣በተለይ በሰርግና የተለያዩ የሺርክ ስንኞች የተሞሉበት መንዙማና ነሺዳ በሚደለቅበት መውሊድ ላይ ከወንዶች ጋር ለመዝለልና ለዚና ሀያእ የሚባል ነገር አሽቀንጥረው ጥለውት ይወጣሉ። " እህቴ ሆይ! ቁርኣን አንድን ነገር ሲጠቅስ ያለ ምክንያት አይደለም!። ይልቅ ከእኛ መተገበሩ ወይም መጠንቀቁ ተፈልጓል ማለት ነው። ለምሳሌ አላህ ስለ ነቢዩላህ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ስደት ላይ ሆነው የገጠማቸውን ሲተርክ እንዲህ በማለት የአንዲትን እንስት አካሄድ አውስቷል:- فَجَاءَتْهُ إِحْدَاهُمَا تَمْشِي عَلَى اسْتِحْيَاءٍ «ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሐፍረት ጋር የምትሄድ ሆና መጣችው፡፡» አል-ቀሰስ 25 ሸይኽ ናሲሩ ሰዕዲ (ረሂመሁላህ) ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ ተፍሲራቸው ላይ እንዲህ አሉ:- “ይህ የሚያመላክተው የመልካም ስነ-ምግባር ባለቤት መሆኗን ነው፣ ምክንያቱም አይናፋርነት በላጭ ከሆነው ከመልካም ስነ-ምግባር ነው!፣ በተለይ በሴቶች ላይ።” [ተፍሲሩ ሰዕዲ] "ከሀፍረት ጋር የምትሄድ ሆነ…" በማለት አካሄዷን አውስቷል፣ አላህ ይህን አካሄድ አንቺም ከቤት የሚያስወጣሽ አስገዳጅ ነገር ሲኖር ተግባራዊ እንድታደርጊው ፈልጓል ማለት ነው። አለባበስሽ ሸሪዐው የሚፈልገው አይነት ሆኖ በጅልባብና ኒቃብ የተሰተርሽ ሆነሽ ብትወጪ እንኳን ይህ አይናፋርነት ፈፅሞ ሊለይሽ አይገባም!። ምክንያቱም ሀያእ ከፈጣሪሽ ዘንድ የተቸረሽ ትልቁ ሀብትሽና ውበትሽ ነው!። " ነቢዩ እንዲህ ብለዋል:- “ኢማን ከሰባ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፣ ሐያእ ከኢማን ቅርንጫፍ ነው።” ቡኻሪይ ዘግበውታል " የነዚያ ጋጠ-ወጦች ጩሃት ሸንግሎሽ በስመ-ስልጣኔና ግልፀኝነት ሀያእሽን አትልቀቂው የአንቺ የሙስሊሟ እንስት የፈጣሪዋ ትልቅ ችሮታ ነው!!። ሀያእ የሚባለውን የተፈጥሮ ስጦታሽንና ሀብትሽን ለማቆየት ምናምንቴዎችን ትተሽ ጓደኝነትሽን ሀያእ ካላቸው እህቶችሽ ጋር አድርጊው!። ጓደኛሽ ሀያእ ከሌላት ሙተነቂብ መሆኗ አለያም ከአንቺ በላይ እውቀት ስላላት አትሸንግልሽ!፣ ከቻልሽ ሀያእ እንዲኖራት ምከሪያት! ካልተስተካከለች ግን ራቂያትና ሀያእ ያላቸውንና ዲናቸው ጠንካራ የሆኑ እህቶችሽን ጓደኛ አድርጊ!። " ወንድሜ ሆይ! ልታገባ ስታስብ ሀያእ ያላትን ሴት መምረጥ እንዳለብህ አትዘንጋ!። ልታገባት ያሰብካት ሴት ምናልባት ማሻ አላህ አለባበሷ ሸሪዐዊ የዲን እውቀቷም እንደዛው ሊሆን ይችላል፣ ግን ሀያእዋ እንዴት ነው?!። ምክንያቱም ሀያእ ትልቅ ዋጋ አለው! በዚህ አስቸጋሪ ማህበረሰብ በበዛበት ዘመን ሀያእ የሌላት እንስት ከራሷ የባሰ ሀያእ የሌለውን ትውልድ ቢሆን እንጂ ሀያእ ያለውን ትውልድ ልታፈራ አትችልም!!። ሀያእ እየጠፋ የመጣ የሙስሊም እንስቶች ትልቅ ሀብት ነው!! እህቴ ሆይ! ትልቁን ሀብትሽን ውበትሽን፣ የፈጣሪሽን ስጦታ ፈልገሽ አጥብቀሽ ያዢው!! ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) #join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Show all...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

👍 8
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.