cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢትዮ መረጃ - NEWS

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት ማክበር ባትችል አታዋርዳት ማራመድ ባትችል አታዘግያት መጠበቅ ባትችል አትበትናት። ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም። ለአስታየት @ethio_merjabot @biruke_promotion

Show more
Advertising posts
56 748
Subscribers
-2324 hours
+1077 days
-2530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ተፈታለች‼️ ደራሲ እና አርቲስት አዜብ ወርቁ መታሰሯ ከሰዓታት በፊት ተዘግቦ ነበር‼️ ዛሬ በቁጥጥር ስር ውላ የነበረችው አዜብ ወርቁ ለግማሽ ቀን ያህል በእስር ከቆየች በኋላ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተለቃለች። አርቲስቷ ሰሞኑን "ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!" የሚል ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች ካጋራች በኋላ ጽሁፉ ብዙዎች ተጋርተውት እንደነበርና በኋላም ከማህበራዊ ገጿ ጽሁፉን ማንሳቷን ማስታወቋ አይዘነጋም።
Show all...
👍 21 9😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር አርቲስት አዜብ ወርቁ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አርቲስቷ በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደምትገኝ የፖሊስ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመጣለን። አርቲስቷ ሰሞኑን "ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!" የሚል ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች ካጋራች በኋላ ጽሁፉ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበርና በኋላም ከማህበራዊ ገጿ ጽሁፉን ማንሳቷን ማስታወቋ አይዘነጋም። ምንጭ ዘሀበሻ @sheger_press @sheger_press
Show all...
😭 24👍 13 3
Photo unavailableShow in Telegram
ለታጋቾች ማስለቀቂያ ብር ለመክፈል የሄዱ ግለሰቦች እራሳቸው በታጣቂዎች መታገታቸው ተሰማ‼️ ከሳምንት በፊት በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ 38 ሰዎች በጉዞ ላይ እያሉ በሸኔ ታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸው ይታወሳል፡፡ ታጣቂዎቹ ታጋቾችን ለመልቀቅ ከ250ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎም አንዳንድ የታጋች ቤተሰቦች ገንዘቡን ለመክፈል ወደ ተባሉበት ቦታ ማቅናታቸውን የሚገልጹት የመረጃ ምንጮች ገንዘብ አቀባዮቹ በቦታው ሲደርሱ ግን እራሳቸው በታጣቂዎቹ መታገታቸውን ነው የገለጹት ፡፡ ‹‹ካሉበት ቦታ ሆነው ስልክ ደውለው እኛም ታግተናል›› አሉን የሚሉት አንድ ምንጭ የታገቱትን አስፈትተው ይመጣሉ ብለን ተስፋ ስናደርግ እነሱም መያዛቸው ሌላ ጭንቀት ፈጥሮብናል ይላሉ፡፡ ታጋቾችን ለማስለቅ የሚያስችል ገንዘብ አሁን ላይ እንደሌላቸው የሚገልጹት እነዚህ የታጋች ቤተሰቦች የቀደሙትንም ለማስፈታት በገበያ ቦታ፣ በእድርና በመሰል ማህበራዊ አደረጃጀቶች በኩል ጥረት ተደርጎ ገንዘቡ እንደተሰበሰበ ገልጸዋል፡፡ መንቀሳቀስና መስራት ውድ እየሆነ መጥቷል፤ መንግስትም የህግ የበላይነት የሚባለውን መሰረታዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል በማለትም አካባቢው ላይ የሚታይ ስጋት አሁንም እንዳለ ነው ያስታወቁት፡፡ በሌላ በኩል ታግተው ከነበሩ 38 ሰዎች ውስጥ 5 ያህል ታጋቾች ማምለጣቸውንም እነዚህ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ምንጮች አሁን ላይ ያመለጡት ታጋቾች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ግን ተጨማሪ መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ የሸኔ ታጣቂ ቡድኖቹ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ከጎቤሳ ከተማ ወደ ተለያዩ ከተሞች በመጓዝ ላይ የነበሩ አጠቃላይ 8 የህዝብ ማመላለሻዎችን ጋለማ በሚባል ጫካ ውስጥ በማስቆም 38 ሰዎችን በመምረጥ ማገታቸው የሚታወስ ነው። አዲስ ማለዳ
Show all...
👍 32😁 10 5😭 2👎 1
00:18
Video unavailableShow in Telegram
🏃‍♂️🏃🏃‍♂️በመሃል ፒያሳ ሊሴገብረማርያም ት / ቤት ዘመናዊ ቤት ከ ቴመር ፕሮፐርቲ 👉ስቱዲዮ .....48 and 46 ባለ አንድ መኝታ.....66...64....71...75 ባለ ሁለት መኝታ.....75....78...71....99...92...91 ባለ ሶስት .....111....106 🏠 ተጨማሪ የንግድ ሱቅ ፒያሳ አድዋ ሙዝየም ፊትለፊት በሚኒሊክ አደባባይ ከ12 ካሬ እስከ 22 ካሬ ለወርቅቤት #ቡቲክ #ፋርማሲ #office .....የሚውሉ 💴 483,000 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ!!! ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.me/+33kkNORhQ_JmMDlk ለበለጠ መረጃ ይደውሉ ፡ ☎️0904657777/0902597777 ያግኙን
Show all...
files/Last.mp41.36 MB
👍 11
Call 📞
Join Us
Save Ad
Photo unavailableShow in Telegram
በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን የፋኖ ሀይሎች አምስት ወረዳዎችን መያዛቸውን ተከትሎ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎችና የወረዳና ቀበሌ አመራሮች ወረዳዎቹን ለቀው ከዞኑ ዋና መቀመጫ ደብረታቦር መግባታቸውን ዋዜማ ሬዲዮ ዘግባለች። የፋኖ ሀይሎች ከጳጉሜ መጨረሻ ጀምሮ ባሉት ቀናት በተቆጣጠሯቸው ታች ጋይንት፣ እስቴ፣ አንዳቤት፣ መካነእየሱስ፣ ስማዳ እና ስዴ ሙጃ ወረዳዎች፣ የራሳቸውን አስተዳደራዊ መዋቅሮች የመዘርጋትና ግብር የመሰብሰብ ሙከራ እያደረጉ እንደኾነም በዘገባው ተካቷል። @sheger_press @sheger_press
Show all...
👍 48 6👏 2😁 1
መፈንቅለ መንግሥት‼️ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግብኝ ነው>>የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር‼️ የደብረፅዮን ቡድን ለስልጣኑ ሲል የትግራይ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ክህደት እየፈፀመ ይገኛል ሲል የጌታቸው ረዳ ቡድን ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል። አባላቱ አክለውም የትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ጄኖሳይድ ለስልጣኑ ሲል ወደ መካድ ደርሷል ሲል ከሰዋል።  የጌታቸው ቡድን መግለጫው የደብረፅዮን(ዶ/ር) ቡድን ማንኛውም አካል ላይ ውሳኔ የማሳለፍ ሆነ እርምጃ የመውሰድ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊ እና ህጋዊ ስልጣን እንደሌለው ለህዝባችን እና ለአባላቶቻችን ማሳወቅ እንወዳለን ብሏል። የአቶ ጌታቸው ቡድን ከፌደራል መንግስት ጋር የህወሓት ህጋዊ ሰውነትን ለመመለስ በምናደርገው ፓለቲካዊ ድርድር መላው አባላችን እና ደጋፊ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። @sheger_press @sheger_press
Show all...
👍 42 11😭 6😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአማራ ክልሰ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ በፋኖ ሀይሎች እና በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ውጊያ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ:: በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል ከትላንት በስተያ በነበረው ግጭት ወደ ደባርቅ አጠቃላይ ሆስፒታል ቆስለው ከገቡት ውስጥ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ የሶስት አመት ህፃንን ጨምሮ 28 ሰዎች መቁሰላቸውን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አስታውቀዋል፡፡ ስራ አስኪያጁ አቶ አለ አምላክ ሲናገሩ ከሟቾቹ ውስጥ አንድ ታጣቂና አንድ ሲቪል ናቸው ብለዋል :: ወደ ሆስፒታል ሳይደርሱ የህፃኑን አባት ጨምሮ ከ7 በላይ ስዎች መሞታቸውን አክለው ገልፀዋል፡፡ VOA @sheger_press @sheger_press
Show all...
👍 20😭 13 4
Photo unavailableShow in Telegram
""ወልዲያ"‼️ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑ ተነገረ <<ወረርሽኙ በፍጥነት በመዛመቱ 85 ሰዎች ታመው በሦስት ጤና ተቋማት ሕክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ከታማሚዎቹ መካከል 11 ያህሉ በፅኑ መታከሚያ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።እስከ ትናንት ማክሰኞ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል። የኮሌራ በሸታው ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም. በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ክፍለ ከተማ አድማስ ባሻገር ተክለ ሃይማኖት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የተከሰተው። በሚመለከተው አካል ርብርብ ካልተደረገ ውጤቱ ጥሩ አይሆንም፡፡>> የወልዲያ ከተማ ጤና መምርያ ሜዲካል ኦፊሰር ሲስተር ዘሬ በቀለ ለሪፖርተር ከተናገሩት የተወሰደ
Show all...
👍 23 1
መንገድ መዝጋት   ህዝብን ለመከራና ለስቃይ የሚዳርግ ተቀባይነት የሌለዉ ተግባር ነዉ ሲሉ የመንዝ እና አካባቢዉ ነዋሪዎች ገለፁ አዲስአበባን ከመንዝ የሚያገናኘዉ ዋና መስመር ከተቆረጠ አምስት ቀን እንደሆነ የገለፁት ነዋሪዎች ህዝቡ በከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት ዉስጥ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡ እንደሚታወሰው በአልን አስመልክቶ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ መንዝ እና ሸዋ የተለያዩ ቦታዎች ተወላጆች መግባታቸዉ የሚታዉስ ሲሆን አስቸኮይ የስራ ፍቃድ ያላቸዉ ዉስብስብ የጤና ክትትል ያላቸዉ እና ለህዝቡ መሰረታዊ ፍጆታ የሚያመላልሱ ተሽከርካሪዎች ባሉበት መንገድ መዘጋቱ ህዝብን እያማረረ  መሆኑ ይነሳል ፡፡ ( SNN) @sheger_press @sheger_press
Show all...
👍 24👎 7 5
Photo unavailableShow in Telegram
📍ጎንደር ከተማ ከሌሊት ጀምሮ በጎንደር አንዳንድ የከተማው ክፍል አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መኖሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት በጎንደር ከተማ “ገንፎ ቁጭ”ና ማራኪ በተባሉ አካባቢዎች ከባድ ጦር መሣሪያ ጭምር ከሌሊት ጀምሮ እየተተኮሰ ነው፡፡ አንድ የከተማዋ ነዋሪ እርሳቸው ባሉበት ቀበሌ 18 በሚባለው አካባቢ የቀላል መሣሪያ ድምፅ እንደሚሰማ አመልክተው፣ ራቅ ብሎ ደግሞ የከባድ መሣሪያ ድምፅ ይሰማል ብለዋል፡፡ ሌላ ነዋሪ በተመሳሳይ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተኩስ ልውውጥ የሚመስል ድምጽ ይሰማል ብለዋል፡፡ ትናንትና በአዘዞና በጎንደር ሆስፒታል አካባቢ ተኩስ እንደነበርም ገልጠዋል፡፡ የዛሬው ከባድ እንደሆነ ያመለከቱት እኚሁ ነዋሪ የከባድ መሣሪያው የተኩስ ድምፅ (እርሳቸው እንደገመቱት የመድፍ ድምፅ) መሬት ያንቀጠቅጣል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡ ሱቆችና የከተማ ውስጥ እንቅስቃሴዎች በከተማዋ የተገቱ ቢሆንም ፒያሳ በተባለው የከተማው ክፍል የተወሰኑ ባለሦስት እግር ተሸከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ ማየታቸውን አስረድተዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሐንስ፣ ሽንፋ፣ ኮኪትና ገንዳ ውኃ ዙሪያ ተመሳሳይ ውጊያዎች በመንግስትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ሲካሄዱ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል፡፡(DW-Amharic) @sheger_press @sheger_press
Show all...
👍 58 6
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.