cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጠበቃ/የህግ አማካሪ⚖️

ማንኛውም አይነት የህግ ምክር ሲፈልጉ @Getsh_bot

Show more
Advertising posts
894
Subscribers
+224 hours
+157 days
+6630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የልጅ_ቀለብ_ልታውቁት_የሚገባ_ነጥቦች በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 113 መሰረት የልጆችን አጠባበቅ እና አያያዝ አስመልክቶ ወላጆች በፍቺ በሚለያዩበት ወቅት ወይም በህግ ከታወቀ ግንኙነት ውጭ ልጆች ሲወለዱ ህፃናቱ ስለትምህርታቸው፣ ስለመኖርያቸው፣ ስለሚለብሱት አልባሳት፣ ስለጤናቸው አጠባበቅ፣ ስለቀለባቸው ባጠቃላይ ስለአኗኗራቸው እንዲሁም ወላጆቻቸውና ልጆቻቸው ለመጠያየቅ ስላላቸው መብት መወሰን እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ የልጅ ቀለብ በሚወሰንበት ወቅት የወላጆችን የገቢ፣ ዕድሜ፣ የጤና እና የአኗኗር ሁኔታ እንዲሁም የልጆቹን ዕድሜ፣ ጥቅማቸውና ፍላጎታቸውን የሚጠብቅበትን ሁኔታ በማገናዘብ የሚወሰን የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን ይህ ድጋፍ በገንዘብም ሆነ በአይነት ሊከፈል የሚችል ነው፡፡ #የልጅ_ቀለብን_የመጠየቅ_መብት_ያለው_ማን_ነው❓ የልጆችን ቀለብ መጠየቅ የሚችለው የህፃኑ/ኗ አሳዳሪነት የተሰጠው ወላጅ እናት ወይም ወላጅ አባት ሲሆን የህፃኑ እናት ወይም አባት በህይወት በማይኖሩበት ወቅት ወይም የህፃኑ/ኗ ሞግዚትነት ለሶስተኛ ወገን የተሰጠ እንደሆነ የህፃኑ ህጋዊ ሞግዚት ለህፃኑ/ኗ ቀለብ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ህፃኑ/ኗን የማሳደግ ሀላፊነትን የወሰደው ወላጅ ወይም ህጋዊ ሞግዚት ሌላኛውን ወላጅ የልጅ ቀለብ እንዲከፍለው የመጠየቅ መብት አለው፡፡ #የልጆች_ቀለብን_የመክፈል_ግዴታ_ያለባቸው_እነማን_ናቸው❓ ማንኛውም ወላጅ የወለዳቸውን ልጆች ፍቅር እና እንክብካቤ እየሰጠ የማሳደግ ሀላፊነት በህግ ተጥሎበታል፡፡ የህፃናቱን ፍላጎት ለሟሟላት ወላጆች በአንድነት በሆነው ልጆቻቸውን ለማሳደግ ያላባቸውን ሀላፊነት ቢወጡ ከህፃናቱ ጥቅምና ደህንነት አንፃር ተመራጭ ቢሆንም ወላጆች በተለያዩ ምክንያቶች በሚለያዩበት ወቅት አሳዳሪነት፣ የልጆች ቀለብ እና የጉብኝት መብት አብረው የሚነሱ ሲሆን አንዱ ወላጅ ልጆቹን የማሳደግ ሀላፊነት ሲወስድ ልጆቹን የማሳደር ሀላፊነትን ያልወሰደው ወላጅ ደግሞ ቀለብ የመቁረጥ ግዴታ ይኖርበታል፡፡ ወላጆች ለህፃናት ልጆቻቸው ቀለብ የመቁረጥ ግዴታ እንዳለባቸው ሁሉ ግዴታው በቀጥታ ወላጆችና ተወላጆች ወይም የቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል እንዲሁም በወንድማማቾች እና በእህትማማቾች መካከልም እንዳለ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 198 ይደነግጋል፡፡ #የልጅ_ቀለብ_እንዲሻሻል_እንዴት_መጠየቅ_ይቻላል ❓ በፍርድ ቤትም ሆነ በስምምነት የተወሰነ የልጅ ቀለብ መጠን በተለያየ ጊዜ እንዲሻሻል መጠየቅ እንደሚችል በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 203 ላይ ተደንግጓል፡፡ የህፃኑ/ኗ ፍላጎት ከእድሜ ጋር እየጨመረ የሚሄድ መሆኑን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የልጁ ቀለብ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍላጎታቸው ጋር እየጨመረ የሚመጣ ስለሆነ ቀለብ የመክፈል ሀላፊነት ያለበት ወላጅ ገቢው መጨመሩ በተረጋገጠበት ወቅት መጀመርያ ቀለቡን የወሰነውን ፍርድ ቤት የቀለብ መጠን ላይ ማሻሻያ እንዲያደረግ መጠየቅ እንደሚቻል ህጉ ይደነግጋል፡፡ እንዲሁም የቀለብ አከፋፈል ሁኔታ በስምምነት ያለቀ እንደሆነ ወላጆች የህፃኑ/ኗ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት  በየጊዜው እንዲያሻሽሉ ይጠበቅባቸዋል፡፡ #በቀለብ_አወሳሰን_ወቅት_በፍርድ_ቤት_የሚታዩ_ነጥቦች_ምን_ምን_ናችው⁉️ የቀለብ መጠን የሚወሰነው ቀለብ ጠያቂው(ህፃኑ/ኗ) ያለበትን ችግር እና የቀለብ ሰጪውን አቅም በማመዛዘን መሆን እንዳለበት የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ በአንቀፅ 202(2) የተደነገገ ሲሆን በዚህም መሰረት የልጆች ቀለብ ሲወሰን ከግምት ውስጥ የሚገቡ ነጥቦች፦ - የህፃናቱ እድሜ ከግምት ውስጥ በመስገባት ፍላጎታቸውን ማሟላት (መጠለያ፣ ምግብ፣ ትምህርት እና አልባሳት) እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ጥቅማቸው፣ - የህፃናቱ ወላጆች በፍቺ የተለያዩ ከሆነ ከፍቺ በፊት የነበረውን የህፃናት ኑሮ ሁኔታ ከግምት ገብቶ ይህንን ለማስቀጠል ጥረት ይደረጋል፣ - የቀለብ ከፋዩን ወላጅ ገቢ፣ የኑሮ ሁኔታ፣ ጤና እና እድሜን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፍርድ ቤት የቀለብ መጠን የሚወስን ይሆናል፡፡ #የፍርድ_ቤት_የቀለብ_ወሳኔን_እንዴት_ማስፈፀም_ይቻላል ⁉️ በፍርድ ቤት ቀለብ የመክፈል ሀላፊነት የተጣለበት ወላጅ የቀለብ ግዴታውን ያለበቂ ምክንያት አልሰጥም በማለት ወይም በማስተጓጎል በአግባቡ ያልተወጣ እንደሆነ በፍርድ አፈፃጸፀም ችሎት ተገዶ እንዲፈፅም ይደረጋል እንዲሁም በወንጀል ህግ አንቀጽ 658 የልጅ ቀለብ አለመክፈል በቸልተኝነት ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል አስራት ወይም በገንዘብ የሚያስጠይቅ መሆኑን ስለሚደነግግ የልጅ ቀለብ በተገቢው መንገድ ወቅቱን እየጠበቀ እንዲከፈል ወደ ፍርድ አፈፃጸም ችሎት በመሄድ ወይም ወደ ፖሊስ መምሪያ በመሄድ የቀለብ ውሳኔን ማስፈጸም  ይቻላል፡፡ © ሕግ አገልግሎት @Getsh_bot @ethiolawyer1 @ethiopianattorney1
Show all...
ጠበቃ/የህግ አማካሪ⚖️

ማንኛውም አይነት የህግ ምክር ሲፈልጉ @Getsh_bot

👍 4
የልጅ_ቀለብ_ማለት_ምን_ማለት_ነው በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 113 መሰረት የልጆችን አጠባበቅ እና አያያዝ አስመልክቶ ወላጆች በፍቺ በሚለያዩበት ወቅት ወይም በህግ ከታወቀ ግንኙነት ውጭ ልጆች ሲወለዱ ህፃናቱ ስለትምህርታቸው፣ ስለመኖርያቸው፣ ስለሚለብሱት አልባሳት፣ ስለጤናቸው አጠባበቅ፣ ስለቀለባቸው ባጠቃላይ ስለአኗኗራቸው እንዲሁም ወላጆቻቸውና ልጆቻቸው ለመጠያየቅ ስላላቸው መብት መወሰን እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ የልጅ ቀለብ በሚወሰንበት ወቅት የወላጆችን የገቢ፣ ዕድሜ፣ የጤና እና የአኗኗር ሁኔታ እንዲሁም የልጆቹን ዕድሜ፣ ጥቅማቸውና ፍላጎታቸውን የሚጠብቅበትን ሁኔታ በማገናዘብ የሚወሰን የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን ይህ ድጋፍ በገንዘብም ሆነ በአይነት ሊከፈል የሚችል ነው፡፡ #የልጅ_ቀለብን_የመጠየቅ_መብት_ያለው_ማን_ነው❓ የልጆችን ቀለብ መጠየቅ የሚችለው የህፃኑ/ኗ አሳዳሪነት የተሰጠው ወላጅ እናት ወይም ወላጅ አባት ሲሆን የህፃኑ እናት ወይም አባት በህይወት በማይኖሩበት ወቅት ወይም የህፃኑ/ኗ ሞግዚትነት ለሶስተኛ ወገን የተሰጠ እንደሆነ የህፃኑ ህጋዊ ሞግዚት ለህፃኑ/ኗ ቀለብ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ህፃኑ/ኗን የማሳደግ ሀላፊነትን የወሰደው ወላጅ ወይም ህጋዊ ሞግዚት ሌላኛውን ወላጅ የልጅ ቀለብ እንዲከፍለው የመጠየቅ መብት አለው፡፡ #የልጆች_ቀለብን_የመክፈል_ግዴታ_ያለባቸው_እነማን_ናቸው❓ ማንኛውም ወላጅ የወለዳቸውን ልጆች ፍቅር እና እንክብካቤ እየሰጠ የማሳደግ ሀላፊነት በህግ ተጥሎበታል፡፡ የህፃናቱን ፍላጎት ለሟሟላት ወላጆች በአንድነት በሆነው ልጆቻቸውን ለማሳደግ ያላባቸውን ሀላፊነት ቢወጡ ከህፃናቱ ጥቅምና ደህንነት አንፃር ተመራጭ ቢሆንም ወላጆች በተለያዩ ምክንያቶች በሚለያዩበት ወቅት አሳዳሪነት፣ የልጆች ቀለብ እና የጉብኝት መብት አብረው የሚነሱ ሲሆን አንዱ ወላጅ ልጆቹን የማሳደግ ሀላፊነት ሲወስድ ልጆቹን የማሳደር ሀላፊነትን ያልወሰደው ወላጅ ደግሞ ቀለብ የመቁረጥ ግዴታ ይኖርበታል፡፡ ወላጆች ለህፃናት ልጆቻቸው ቀለብ የመቁረጥ ግዴታ እንዳለባቸው ሁሉ ግዴታው በቀጥታ ወላጆችና ተወላጆች ወይም የቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል እንዲሁም በወንድማማቾች እና በእህትማማቾች መካከልም እንዳለ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 198 ይደነግጋል፡፡ #የልጅ_ቀለብ_እንዲሻሻል_እንዴት_መጠየቅ_ይቻላል ❓ በፍርድ ቤትም ሆነ በስምምነት የተወሰነ የልጅ ቀለብ መጠን በተለያየ ጊዜ እንዲሻሻል መጠየቅ እንደሚችል በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 203 ላይ ተደንግጓል፡፡ የህፃኑ/ኗ ፍላጎት ከእድሜ ጋር እየጨመረ የሚሄድ መሆኑን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የልጁ ቀለብ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍላጎታቸው ጋር እየጨመረ የሚመጣ ስለሆነ ቀለብ የመክፈል ሀላፊነት ያለበት ወላጅ ገቢው መጨመሩ በተረጋገጠበት ወቅት መጀመርያ ቀለቡን የወሰነውን ፍርድ ቤት የቀለብ መጠን ላይ ማሻሻያ እንዲያደረግ መጠየቅ እንደሚቻል ህጉ ይደነግጋል፡፡ እንዲሁም የቀለብ አከፋፈል ሁኔታ በስምምነት ያለቀ እንደሆነ ወላጆች የህፃኑ/ኗ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት  በየጊዜው እንዲያሻሽሉ ይጠበቅባቸዋል፡፡ #በቀለብ_አወሳሰን_ወቅት_በፍርድ_ቤት_የሚታዩ_ነጥቦች_ምን_ምን_ናችው⁉️ የቀለብ መጠን የሚወሰነው ቀለብ ጠያቂው(ህፃኑ/ኗ) ያለበትን ችግር እና የቀለብ ሰጪውን አቅም በማመዛዘን መሆን እንዳለበት የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ በአንቀፅ 202(2) የተደነገገ ሲሆን በዚህም መሰረት የልጆች ቀለብ ሲወሰን ከግምት ውስጥ የሚገቡ ነጥቦች፦ ~  የህፃናቱ እድሜ ከግምት ውስጥ በመስገባት ፍላጎታቸውን ማሟላት (መጠለያ፣ ምግብ፣ ትምህርት እና አልባሳት) እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ጥቅማቸው፣ ~ የህፃናቱ ወላጆች በፍቺ የተለያዩ ከሆነ ከፍቺ በፊት የነበረውን የህፃናት ኑሮ ሁኔታ ከግምት ገብቶ ይህንን ለማስቀጠል ጥረት ይደረጋል፣ ~  የቀለብ ከፋዩን ወላጅ ገቢ፣ የኑሮ ሁኔታ፣ ጤና እና እድሜን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፍርድ ቤት የቀለብ መጠን የሚወስን ይሆናል፡፡ #የፍርድ_ቤት_የቀለብ_ወሳኔን_እንዴት_ማስፈፀም_ይቻላል ⁉️ በፍርድ ቤት ቀለብ የመክፈል ሀላፊነት የተጣለበት ወላጅ የቀለብ ግዴታውን ያለበቂ ምክንያት አልሰጥም በማለት ወይም በማስተጓጎል በአግባቡ ያልተወጣ እንደሆነ በፍርድ አፈፃጸፀም ችሎት ተገዶ እንዲፈፅም ይደረጋል እንዲሁም በወንጀል ህግ አንቀጽ 658 የልጅ ቀለብ አለመክፈል በቸልተኝነት ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል አስራት ወይም በገንዘብ የሚያስጠይቅ መሆኑን ስለሚደነግግ የልጅ ቀለብ በተገቢው መንገድ ወቅቱን እየጠበቀ እንዲከፈል ወደ ፍርድ አፈፃጸም ችሎት በመሄድ ወይም ወደ ፖሊስ መምሪያ በመሄድ የቀለብ ውሳኔን ማስፈጸም  ይቻላል፡፡ © ሕግ አገልግሎት @Getsh_bot @ethiolawyer1 @ethiopianattorney1
Show all...
ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕

ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2) Ignorance of the law is no excuse. civil code article 2035(2) ነገረ ፈጅ ከፈለጉ አለን @NegereFeji_Bot ወይም [email protected] ይላኩልን።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቻችን እና የጠበቃ/ህግ አማካሪ ቻናል ተከታታዮቻችን በሙሉ እንኳን ለ 1499ኛው የነብዩ መሀመድ መውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ:: መልካም በዓል!! @Getsh_bot @ethiolawyer1 @Ethiopianattorney1
Show all...
👏 7
የበረራ ህግ ጥሰዋል በተባሉት ስድስት ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱ ተገለጸ የተከሳሾቹ ጠበቃ ዋስትና እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ፍርደ ቤቱ በዋስትና ጉዳይ ብያኔ ለመስጠት ጉዳዩን ለመስከረም 7፣2016 ዓ.ም ቀጥሮታል የበረራ ህግ ጥሰዋል በተባሉት ስድስት ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱ ተገለጸ። በአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ በአውሮፕላን ውስጥ የበራራ ህግ የሚጥስ ተግባር ፈጽመዋል በሚል ታሰረው የነበሩት ስድስት ግለሰቦች ክስ ተመስርቶባቸዋል። ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያው ኢቢሲ እንደዘገባው በእነዮሐንስ ዳንኤል የክስ መዝገብ የተካቱት ስድስት ግለሰቦች በሶስት ነጥቦች ተከሰዋል። የፌደራል ፖሊስ ባለፈው ነሐሴ ወር ከአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መቀሌ ለመሄድ እየተዘጋደ በነበረ አውሮፕላን ውስጥ "ሁከትና ግርግር" ፈጥረዋል በሚል እነዚህን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን መግለጹ ይታወሳል። ፖሊስ በዚሁ መግለጫው እነዚህን ግለሰቦች በሽብር ወንጀል እና ከጸረ-ሰላም ኃይሎች ጋር ግንኙነት ጠርጥሮ ምርመራ እያካሄደባቸው መሆኑን ገልጾ ነበር። አንደዘገባው ከሆነ አቃቤ ህግ አውሮፕላንን አላግባብ በመያዝ፣ በኮምፒውተር በመታገዝ ስም በማጥፋት እና የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን እንዳይፈጽሙ በማወክ በሚሉ ሶስት ነጥቦች ነው የተከሰሱት። በተከሳሽ ግለሰቦች እና በአየርመንገዱ የደህንነት ሰዎች መካከል የተፈጠረውን እሰጣገባ የሚያሳዩ ቪዲዮች በማህበራዊ ሚዲያዎች ተለቀው መነጋገሪያ ሆነው ነበር። በቪዲዮው ውስጥ እነዚህ ግለሰቦች ከአውሮፕላኑ "አንወርድም" ሲሉ እና የደህንነት ሰራተኞቹ ደግሞ "ወረዱ" መሄድ አይቻልም እያሉ ሲጨቃጨቁ ተደምጠዋል።  እሰጣገባው የተፈጠረው የደህንነት ሰራተኞች አውሮፕላኑ መብረር እንደማይችል መግለጻቸውን ተከትሎ ነበር። ክስ የተመሰረባቸው ተጠርጣሪዎች ዮሀንስ ዳንኤል፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤሊያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና ኢሌኒ ክንፈ ናቸው። በቲክቶክ የሚታወቀው እና የመዝበጉ መጠሪያ የሆነው ዮሐንስ በሶስቱ ነጥቦች ሲከሰስ ሌሎቹ አመስቱ ደግሞ በሁለቱ ነጥቦች መከሰሳቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የተከሳሾቹ ጠበቃ ዋስትና እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ፍርደ ቤቱ በዋስትና ጉዳይ ብያኔ ለመስጠት ጉዳዩን ለመስከረም 7፣2016 ዓ.ም ቀጥሮታል። ©Al-Ain @Getsh_bot ለጥያቄዎ @ethiolawyer1 @Ethiopianattorney1
Show all...
👍 4
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 249795 ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 27/1/ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በ 6 ወር ጊዜ ውስጥ 5 ቀን ከስራ የቀረን ሰራተኛ ከስራ ለማሰናበት ሠራተኛው ከስራው በቀረባቸው 5 ቀናት ሙሉ የፅሁፍ ማስጠንቀቅያ መስጠት እንደሚኖርበት ይሄ ማይሆን ከሆነ በዚህ አንቀፅ መሠረት ሠራተኛ ማሠናበት ህገወጥ ስንብት ነው ሲል በሁሉም ፍርድ ቤቶች አስገዳጅ የሚሆነውን ውሳኔ ሰጥቷል። ሙሉ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ። @Getsh_bot ለጥያቄዎ @ethiolawyer1 @Ethiopianattorney1
Show all...
DocScanner Aug 30, 2024 4-30 PM(1).pdf3.89 MB
👏 4👍 2
የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 1334/2016 ሆኖ በሥራ ላይ ዋለ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣው አዋጅ በሥራ ላይ ውሏል። በአዋጁ ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት በሚል የተቀመጡ 1. መስከረም አንድ ቀን የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል፣ 2. የካቲት ሃያ ሶስት ቀን የአድዋ ድል በዓል፣ 3. ሚያዚያ ሃያ ሶስት ቀን የዓለም የሠራተኞች (የላብአደሮች) ቀን፣ 4. ሚያዚያ ሃያ ሰባት ቀን የአርበኞች (የድል) ቀን በዓል በአዋጁ ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት ተብለው የተቀመጡ፦ በዚህ አዋጅ እና በሌሎች ሕጎች እውቅና የተሰጣቸው ታስበው የሚውሉ በዓላት እንደተጠበቁ ሆነው የሚከተሉት በዓላት በሀገር አቀፍ ደረጃ ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት እንደሆኑ ያስቀምጣል። 1. የካቲት አስራ ሁለት ቀን የሰማዕታት ቀን፣ 2. ሕዳር ሃያ ዘጠኝ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን፣ ኃይማኖታዊ በዓላት በተመለከተ፦ የሚከተሉት በዓላት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ኃይማኖታዊ በዓላት እንደሆኑ ተጠቅሷል፦ 1. መስከረም አስራ ሰባት ቀን የመስቀል በዓል፣ 2. በየአራት አመቱ የሚመጣው ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ ታህሳስ ሃያ ዘጠኝ ቀን የሚውለው የገና ወይም የልደት በዓል፣ 3. ጥር አስራ አንድ ቀን የጥምቀት በዓል፣ 4. የስቅለት በዓል፣ 5. የትንሳኤ(ፋሲካ) በዓል፣ 6. የመውሊድ በዓል፣ 7. የኢድ-አልፈጥር፣ 8. የኢድ-አልአድሃ(አረፋ) በዓል ናቸው። አዋጁ በህዝብ በዓላት ሊሰጡ ወይም ሊሰሩ ስለሚችሉ አገልግሎቶችና ሥራዎች ይደነግጋል። አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ነሐሴ 8 ጀምሮ የጸና ይሆናል ተብሏል፡: @Getsh_bot t.me/ethiopianattorney1
Show all...
Public Holidays Proclamation No.1334_2024.pdf7.11 KB
👍 9
የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ዋጋን እስከ 500 ፐርሰንት የሚያስወድደው መመርያ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ሆነ - የሶስተኛ ወገን የሀላፊነት ገደብ ክፍያዎች ላይም የገንዘብ ጭማሪ ተደርጓል (መሠረት ሚድያ)- ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን የወጣው የሶስተኛ ወገን የሀላፊነት ገደብን ተከትሎ የፕሪሚየም ዋጋ እስከ 500 ፐርሰንት በአንድ ቀን ውስጥ እንደጨመረ መሠረት ሚድያ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል። በአዲሱ የሶስተኛ ወገን የሀላፊነት መመርያ መሰረት ለአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት በፊት ተቀምጦ የነበረው 2,000 ብር ወደ 15,000 ብር አድጓል። በተመሳሳይ ለሞት እስከ 40,000 ብር የነበረው ክፍያ አሁን እስከ 250,000 ብር ከፍ ተደርጓል እንዲሁም ለአካል ጉዳት እስከ 40,000 ብር ይከፈል የነበረው አሁን እስከ 250,000 ብር ጣርያ ተቀምጦለታል። ይህን ተከትሎ የኢንሹራንስ ፕሪሚየም ዋጋዎች እስከ 500 ፐርሰንት ጭማሪ እንዳሳዩ የመሠረት ሚድያ ምንጮች ጠቁመዋል። "በፊት 500 እና 600 ብር የነበረ የሶስተኛ ወገን ክፍያ አሁን 3,000 ብር እና ከዛ በላይ ሆኗል" ያለ አንድ የኢንሹራንስ ባለሙያ ይህን የሶስተኛ ወገን የሀላፊነት ገደብ ክፍያዎች ላይ ጭማሪ በመቀመጡ እንደሆነ ተናግሯል። ©መሠረት ሚዲያ @Getsh_bot @Ethiopianattorney1 @ethiolawyer1
Show all...
😢 2👍 1
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት የቀለብ አወሳሰን ላይ ዳኞች የቀለብ ክርክሮችን ወጥ፣ተገማች እንዲሁም ቀልጣፋ እንዲያደርጉ ለማስቻል ይረዳ ዘንድ የህፃናት የቀለብ አወሳሰን መመሪያን አፅድቆ ወደ ስራ አስገብቷል። ዳኞችም በመመሪያው መሠረት የቀለብ ክርክሮችን ወጥ ተገማች እንዲሁም ባነሰ ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ ለወሰን ስለሚረዳ በዛ መሠረት ተግባራዊ እንደሚደረግ ይፋ ሆኗል።
Show all...
👍 5
የህጻናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያ.pdf2.67 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.