cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አል-ኢማሙ ነወዊይ መድረሳ የወጣቶች ጀማዓ

☞አላማችን በሸሪዐዊ እውቀት የነቃ እና የበቃ ትውልድ መፍጠር ነው፡፡ ✌ኢኽላስ መነሻችን ተቅዋ መንገዳችን ሰብር ምርኩዛችን ነው! 📡የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችንም በቻናላችን ያገኛሉ። እኛን ብላችሁ ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን።

Show more
Advertising posts
508
Subscribers
No data24 hours
+37 days
+4030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

💐ልብ የሚነካው የመሀኗ ሴት ታሪክ💐 የዛሬው ታሪክ እጅግ በጣም ልብ የሚነካ ነው እህቶቼ ወንድሞቼ በደንብ አንብቡት በተለይ ከአንድ በላይ ሚስት ያላችሁ አንቺም እህቴ ሁለተኛ  ሚስት ከዚያም በላይ የሆንሽው እህቴ ሆይ ኢንተቢሂ ❗❗ 👉 አሁን ወደታሪኩ ባለታሪካችን እንዲህ ስትል ታሪኩዋን ትጀምራለች ባለቤቴ እና እኔ ከተጋባን አምስት አመታችን በጣም እንዋደዳለን በጣም ያከብረኛል ይንከባከበኛል እኔም በምችለው እሱን ለማስደሰት እጥራለሁ ነገር ግን አንድ ነገር አለ እሱም ልጅ እስካሁን አልወለድንም በተደጋጋሚ ሞከርን ግን አላህ አልሰጠንም ።ችግሩ ያለው ከኔ ነው ያው ሀኪም ቤት ሂደን በምርመራው ውጤት ማለት ነው ። ልጅ ባለመውለዴ ቤተሰቦቹ በጣም ይጠሉኛል ይቺን ፍታና ሌላ አግባ የልጅ ልጅ አሳዬኝ እያሉ ሁልጊዜ ይጨቀጭቁታል ። እሱ ግን እኔን እንዳይሰማኝ በጣም ለስሜቴ ይጨነቃል አላህ ሁን ባለው ጊዜ ይሰጠናል እንታገስ ይለኛል ። በእርግጥ አለመውለዴ ቢያስከፋኝም ግን ሁልጊዜ ጌታዬን እንዳመሰግን ከጎኔ ብርታቴ ይሆነኛል ውዱ ባለቤቴ እንዲህ እንዲህ እያልን ስምንት አመት ሆነን እኔም የቤተሰቦቹ ግልምጫው ስድቡም አላስቀመጠኝ እሱም እዬደከመ መጣ አንድ ቀን ቡና አፍልቼ እዬጠጣን ውዱ ባለቤቴ ቤተሰቦችህን ለማስደሰት አንተም አባት መሆን ስላለብህ ለምን ሁለተኛ አታገባም አልኩት ❗እሱም በጣም ስለሚወደኝና ስለምወደው ይህንን ማለቴን በፍፁም ማመን አቃተው ያው በእርግጥ እሱ በጣም የልጅ ጉጉት አለው በጣም አባት መሆን ይፈልጋል ግን ከኔ ሌላ ማግባት የሚለውን አንስቶ አያውቅም ። እኔም ግድ ሆኖብኝጅ በፍፁም ባሌን ሌላ ሴት እንዲትጋራኝ አልፈልግም ሴት አይደለሁ እቀናለሁ ❗ ባለቤቴ ሀሳቤን ለመቀበል ቀናቶች ወሰዱበት እኔም ደጋግሜ ጠዬኩት በመጨረሻም ተስማማ ። የዳርኩትም እኔ ነበርኩ ደግሼ ።አወ ባሌን ቆሜ ደግሼ ዳርኩት ለእኔ የእሱን ደስታ ከማዬት በላይት የሚያስደስተኝ የለም ። ከኔ ያጣውን ልጅ እንዳገኝ ሰበብ መሆን ፈለኩ አልሀምዱሊላህ ተሳካልኝ የራሳችን ቤት አለን እናም እኔ የራሳችን ቤት ሆንኩ እሱ ደሞ እራቅ ወዳለ ሰፈር ነበር የተከራዬው ። ከተጋቡ አልቆዩም አረገዘች ያኔ የነበረን ደስታ በሂወቴ ተደስቼ አላውቅም የባሌ ልጅ የኔም ልጅ ነው የባሌ ደስታ የራሴ ደስታ ነው ። ከባሌ ሚስት ጋ ጥሩ ግንኙነት ነበረን በጣም እንዋደዳለን አማረኝ ያለችውን ሁሉ በቻልኩት እሰራለሁ እሷም እንደኔ እንደምትወደኝ አምናለሁ ። እርግዝናው ውዬገፋ ወደመውለጃዋ ተቃረበች  ስትወልድም እኔ በደንብ እንደማርሳት ብነግራትም እናቴ ቤት ነው የምወልደው ብላ ሄደች ። ወልዳ ከመጣች ወዲህ ግን ተቀዬረች በፊት የማውቃት አልሆንልኝ አለች ። አንዳንደዬማ ጎዶሎነቴን ወጋ ታደርገኝ ጀመር እኔም በጣም ደነገጥኩ እንዴት ሰው በዚህ ልክ ይቀዬራል ብዬ  ልገምት ። ት እኔም ምን ሁነሽ ነው ሳላውቅ ያስከፋሁሽ ነገር ካለ ንገሪኝ ስላት ጥሩም መልስ አትሰጥም ግን ባለቤቴ ይህንን አያውቅም ከእሱጋ ሰላም ነኝ እሱ የልጅ አባት መሆኑ ቢያስደስተውም ግን የእኔ ስሜት እንዳይነካ ይጠነቀቃል በዚህ ሁኔታ እያለን ግን በእሷና በኔ መካከል ክፍተቶች መፈጠር ጀመሩ ። ሁለተኛ ልጇን አረገዘን እንደበፊቱ ባይሆንም የሚያምራትን ማቅረብ ጀመርኩ  ሁለተኛ ልጇንም በሰላም ወለደች አልሀምዱሊላህ ሁለተኛውን ልጅ ከወለደች ቡሀላ ፍፁም የማላውቃት ሴት ሆነች በሆነው ባልሆነው መበሳጨት ጀመረች አለሙውለዴን ትነግረኝ ጀመር አንቺ ያልሰጠሽውን ይሄው እኔ ሶስት አመት ሳይሞላኝ የሁለት ልጆች አባት አደረኩት ትለኛለች ባለቤቴንም ብዙ ነገር ትለዋለች አልፋም እንዲፈታኝ ሁሉ ታግባባዋለች እንዴትስ እኛ ከልጅ  ጋር ኪራይ ቤት አስቀምጠህ እሷን እዛ በራስህ ቤት  ታኖራለህ እያለች ጥዋት ማታ  ትወጋዋለች እኔምጋ መታ በግልፅ እኔ ልጆቼ በኪራይ ቤት እንዳዲጉ አልፈልግም ስለዚህ አንቺ ቤቱን ልቀቂልን ብቻሽን ስለሆንሽ እኛ ያለንበት ኪራይ ቤት ግቢ ብላ በግልፅ ፊቴ ነገረችኝ ማመን አቃተኝ እሱም ስለሞላችው ሀሳቧን -------- منقول ክፍል ሁለት ይቀጥላል ኢንሻ አላህ
Show all...
😢 1
በሊባኖስ በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች (AR-924” ) ስለተፈጸመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው “AR-924” ምንድን ነው? አምራቹ ኩባንያስ? 💀የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) መረጃ ለመለዋወጥ የሚውሉ “ፔጀር” የተባሉ መሳሪያዎች ወደ ሊባኖስ ከመግባታቸው በፊት ፈንጂ ቀብሮባቸው ነበር ተብሏል 💀በሊባኖስ “ፔጀር” የተሰኙ የመረጃ መለዋወጫ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ፍንዳታ የዘጠኝ ሰዎችን ህይወት ቀጥፎ ከ2 ሺህ 800 በላይ ሰዎችን አቁስሏል ℹ️ ሬውተርስ ያነጋገራቸው የሊባኖስ የደህንነት ባለስልጣን የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) የመረጃ መለዋወጫ መሳሪያዎቹ ለሊባኖሱ ሄዝቦላህ እንዲደርሰው ማድረጉን ይገልጻሉ። ℹ️ 5 ሺህ የሚደርሱት “AR-924” የተሰኙት መልዕክት መለዋወጫ መሳሪያዎች ወደ ሊባኖስ ከመግባታቸው ከወራት በፊትም የሚፈነዱ መሳሪያዎች ተቀብሮባቸዋል ነው ያሉት። “AR-924” ምንድን ነው? አምራቹ ኩባንያስ? ℹ️ አነስተኛ መጠን ያላቸው የግንኙነት መሳሪያዎቹ በድጋሚ ሃይል በሚሞሉ ሊቲየም ባትሪዎች የሚሰሩ መሆናቸውንና ባትሪያቸው እስከ 85 ቀናት የመቆየት አቅም እንዳለው አምራቹ ያወጣው መረጃ ያሳያል። ℹ️ ይህም እንደ ሊባኖስ ባሉ የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ በስፋት በሚታይባቸው ሀገራት ተመራጭ መረጃ መለዋወጫ መሳሪያ አድርጎታል። ℹ️ “ፔጀርስ” ከስልኮች በተሻለ በተለያዩ ገመድ አልባ ኔትወርኮች መስራታቸውም በአለማቀፍ ደረጃ በርካታ ሆስፒታሎች አሁንም ድረስ ዋነኛ መልዕክት ለመለዋወጥ ተመራጭ እንዲያደርጓቸው ምክንያት ሆኗል። ℹ️ የታይዋን የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ከነሃሴ 2022 እስከ ነሃሴ 2024 ድረስ 260 ሺህ ”AR-924” ፔጀርስ ወደተለያዩ የአውሮፓና አሜሪካ ሀገራት መላካቸውን ገልጿል። ይሁን እንጂ አምርቹ “ጎልድ አፖሎ” ወደ ሊባኖስ በቀጥታ ምርቶቹን እንዳላከ ነው ባወጣው መግለጫ የጠቆመው። በሊባኖስ የፈነዱት መሳሪያዎች በሃንጋሪ መዲና ቡዳፔስት የተመረቱ መሆናቸውንም ጎልድ አፖሎ ይፋ አድርጓል። የቡዳቤስቱ “ባክ ኮንሰልቲንግ” የተባለው ኩባንያ የጎልድ አፖሎ የምርት ስያሜ ለመጠቀም ፈቃድ ቢያገኝም የሚያመርታቸው “ፔጀርስ” ዲዛይንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የተለዩ በመሆናቸው ሃላፊነቱን አልወስድም ብሏል የታይዋኑ ኩባንያ። ምንጭ:- አል ዐይን
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ዕለቱ ረቡዕ ነው ጦርነቱ 348ኛ ቀኑን አስቆጥሯል 41,252 ሹሃዳኦች (ነህተሲቡሁም ከዛሊክ) ከ95,497 በላይ ከባድና ቀላል ጉዳት እና ከ10,000 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም የወራሪዋ ጦረኞች በጋዛ ሰርጥ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በተፈናቃዮች መጠለያ ማዕከላት የየብስ፣ የአየርና የባህር ጥቃታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። በረፈህ በተደረገው ትንቅንቅ 4 የወራሪዋ ወታደሮች መገደላቸውንና ሰባት ሌሎች መቁሰላቸውን የጦራቸው ቃል አቀባይ ይፋ አድርጓል። የታይዋን ኩባንያ ጎልድ አፖሎ በሂዝቦላህ ወታደሮች እጅ የነበሩ የራዲዮ ፍንዳታዎች ድርጅቱ ሆን ብሎ ያቀነባበረው ነው የሚለውን ዘገባ ፍፁም ሐሰት ሲል አስተባብሏል። ይህን ተከትሎ  እንደ ሮይተርስ ዘገባ የፈነዳው መገናኛ ራዲዮ በአውሮፓ የሚገኝ የታይዋን ኩባንያ የንግድ ምልክት ነው ብሏል። ሞሳድ የሂዝቦላህ የመገናኛ መሳሪያዎችን ማግኘት በመቻሉ የተፈጠረ ወጥመድ ነው ተብሏል። ትላንት በሊባኖስ ወራሪዋ ለፈፀመችው ድብደባ ሂዝቦላህ ምላሽ በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቴልአቪቭ እና በወራሪዋ እስራኤል አዋሳኝ አካባቢዎች የማስጠንቀቂያ ሳይረን ድምፅ ደጋግሞ በመሰማት ላይ ይገኛል
Show all...
<==========> ጀግኖችን እንተዋወቅ <===========> إشتهر كثير من العلماء بغير اسمهم الأول، ولايعرف كثير من الناس اسمهم الصريح، ومنهم  አብዛኞቹ የኢስላም ዑለማወች እና  ሊቆች ከመጀመሪያ ስማቸው ውጭ በሆነ መጠሪያቸው ነው የሚታወቁት አብዛኛው ሰው ትክክለኛ ስማቸውን አያውቀውም። <======================> ከነዚህ የኢስላም ፈርጦች መካከል የተወሰኑትን እነሆ ላስተዋውቃችሁ፡–   (١)‏➖ابن تيمية :  أحمد بن عبدالحليم  . ①➖ኢብኑ ተይምያ=> አህመድ ኢብኑ አብደል ሀሊም (٢)‏ا➖بن القيم  :  محمد بن أبي بكر  . ②➖ኢብኑል ቀይም=> ሙሀመድ ኢብኑ አቢ በክር (٣)‏➖ابن رجب   :  عبدالرحمن بن أحمد. ③➖ኢብኑ ረጀብ =>አብደረህማን ኢብኑ አህመድ (٤)‏➖ابن حزم   :  علي بن أحمد. ④➖ኢብኑ ሀዝም=> አልይ ኢብኑ አህመድ (٥)‏➖ابن حجر   :  أحمد بن علي. ⑤➖ኢብኑ ሀጀር => አህመድ ኢብኑ አልይ (٦)‏➖ابن كثير   :  إسماعيل بن عمر  . ⑥➖ኢብኑ ከሲር =>ኢስማዒል ኢብኑ ዑመር (٧)‏➖ابن الجوزي:  عبدالرحمن بن علي  . ⑦➖ኢብኑል ጀውዚ=> አብደረህማን ኢብኑ አልይ (٨)➖البخاري     :  محمد بن إسماعيل  . ⑧➖ቡኻሪ => ሙሀመድ ኢብኑ ኢስማዒል (٩)‏➖أبو داود     :  سليمان بن الأشعث  . ⑨➖አቡ ዳውድ=> ሱለይማን ኢብኑ አሽዐስ (١٠)‏➖الترمذي    :  محمد بن عيسى  . (①⁰)➖ቲርሚዚይ=> ሙሀመድ ኢብኑ ዒሳ (١١)‏➖النسائي    :  أحمد بن شعيب  . (11)➖ነሳዒይ => አህመድ ኢብኑ ሹዐይብ (١٢)‏➖ابن ماجه  :  محمد بن يزيد  . (12)➖ኢብኑ ማጀህ=> ሙሀመድ ዒብኑ የዚድ (١٣)‏➖أبوحنيفة :  النعمان بن ثابت  . (13)➖አቡ ሀኒፋ => ኑዕማን ኢብን ሣቢት (١٤)‏➖الشافعي    :  محمد بن إدريس  . (14)➖ሻፍዕይ=> ሙሀመድ ኢብኑ ኢድሪስ (١٥)‏➖الذهبي     :  محمد بن أحمد  . (15)➖ዘሀቢይ=> ሙሀመድ ዒብኑ አህመድ (١٦)‏➖القرطبي   :  محمد بن أحمد  . (16)➖ቁርጡብይ=> ሙሀመድ ኢብኑ አህመድ  (١٧)➖الصنعاني  :محمد بن اسماعيل (17)➖ሶነዐኒይ=> ሙሀመድ ኢብኑ ኢስማዒል (١٨)➖الشوكاني  :محمد بن علي ‏ (18)➖ሸውካኒይ=> ሙሀመድ ኢብኑ አልይ (١٩)➖السيوطي  :  عبدالرحمن بن أبي بكر (19)➖ሲዩጥይ=> አብደረህማን ኢብን አቢ በክር <===========================> رحمهم الله جميعا ورضي عنهم ሁላቸውንም አላህ ይዘንላቸው አላህ ይውደዳቸው ጀነትንም ያጎናፅፋቸው አሚን። copied
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ከዕለታት በአንዱ ቀን የሳዑዲው ንጉስ ኻሊድ ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ ታላቁን ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚንን ሊዘይሩ ወደቤታቸው አቀኑ፤ ሲደርሱም በቤታቸው ውስጥ ዓይን ውስጥ የሚገባ ውብ ነገር ቢያጡ ተገርመው "እርሶን የሚያክል ሸይኽ እንዴት በዚህ በከረከሰ ቤት ውስጥ ይኖራሉ?" ከደረጃዎ ጋር የሚስማማ አዲስ ቤት እንዲገነባልዎ አዛለሁ" አላቸው። ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚንም "ለመልካም እሳቤህ መልካም ምንዳህን አላህ ይክፈልህ ሷሊሂያ ሰፈር የተዘጋጀልን አንድ ቤት አለ። በቅርብ ጊዜ ወደሱ እንዘዋወራለን" በማለት ሸኙት። ንጉስ ኻሊድ ከሄደ በኋላ ተማሪዎቻቸው ሸይኻቸውን በመገረም ጠየቁ " ያ'ሸይኽ ሷሊሂያ አካባቢ ቤት እንደሰሩ አላወቅንም ነበር እንድናግዝዎ ለምን አልነገሩንም?" አሏቸው። አላህ ይዘንላቸውና ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "የመቃብር ሥፍራው የሚገኘው ሷሊሂያ አካባቢ አይደለምን? ሊገነባ የሚገባው ያ የቀብር ቤት እንጂ የዱንያው ቤት አይደለም"
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
እ.ኤ.አ በ 2003 በኢራቅ ውስጥ በነጀፍ አቅራቢያ ከሚገኝ የአሜሪካ የእስር ካምፕ የተነሳ አሳዛኝ ፎቶ ነው። ፎቶው ኢራቃዊው እስረኛ የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ሰንሰለቱን ከፈቱለት በኋላ የ 4 ዓመት ህጻን ልጁን ከሚያቃጥለው የበረሃ ፀሐይ ሊከልለው  ሲሞክር የሚያሳይ ነው ። ልጁን እንዳያይና የበለጠ እንዲሰቃይ ደግሞ  በራሱ ላይ ጥቁር ፌስታል አልብሰውታል ። ልጁ በእቅፉ እያለ ማየት ግን አይችልም! በልቡ ውስጥ የሚኖረውን የጭቆናና የቁጭት መጠን አስቡት እንግዲህ ... ይህ ምስል በኢራቃውያን አህሉሱናዎች ዘንድ ሁሌም የማይረሱትና  አሜሪካ  በየቦታው በሙስሊሞች ላይ የምትፈፅመውን ሽብር የሚያሳይ  ለመሆኑ ምስክር ነው!  (መንቁል)
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.