cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር - Ethiopian Federal Bar Association

ይህ በአዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 57 ጥር 15 ቀን 2014 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።

Show more
Advertising posts
5 019
Subscribers
+124 hours
+387 days
+11530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

12👍 3🥰 1
14ኛው የአፍሪካ ጠበቆች ማህበራት ህብረት የጋራ ጉባኤ ዝግጅት መቀጠሉ ተገለጸ፤ *********************** የአፍሪካ ጠበቆች ማህበራት ህብረት PALU 55ቱን የአፍሪካ አገራት የጠበቆች ማኀበራት (National Bar Associations) ፤ 8/ስምንት/ አካባቢያዊ ተቋማትን (SADCLA, ELS..) ጨምሮ 12ዐዐ የሚደርሱ መደበኛና ልዩ ኢንዳውመንት አባላቶችን የያዘ የአህጉሪቱ መሪ የሕግ ተቋምነው፡፡ በዚህም አፍሪካ ሕብረትን ጨምሮ የተባበሩትመንግሥታት ድርጅትና መሰል ግዙፍ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋርበርካታ የስራ ግንኙነትን እያከናወነ የሚገኝ እና {observatory status} ተቋም ነው፡፡ ይህ በእንዲህ ባለበት በተያዘው የፈረንጆች ዓመት የሚደረገውን የተቋሙን ጠቅላላ ጉባዔ እንድታዘጋጅ ተመርጣ የነበረችው የሞሮኮዋ ማራካሽ ከተማ የነበረች ስትሆን፤ የፓሉ የሥራ ፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈው ፌብሩዋሪ ወር 2024 በካሜሮን ያውንዴ ከተማ ባደረገው ስብሰባ የአዘጋጅነት እድሉ ከሞሮኮ ተነጥቆ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ውሳኔ መተላለፉ ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሠረት መጭው 14ኛ የአፍሪካ ጠበቆች ማኀበራት ሕብረት ጉባዔ እ.ኤ.አ. ከኦክቶበር 16 እስከ 19 በአዲስ አበባ ከተማ “Africa as a global power house: Empowering Minds, Enlightening Paths” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ በጉባዔው ከመላውአፍሪካ አገራት የሚገኙት የጠበቆች ማኀበራት ፕሬዚዳንቶችእና የአመራር አባላት፤ ከአካባቢ አህጉራዊ ድርጅቶች፤ ዓለምአቀፍ የጥብቅና ድርጅቶች፤ የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ኤጄንሲ ተወካዮች፤ በመካከለኛ ምስራቅከአውሮፓ፤ ከሰሜንና ደቡብ አሜሪካ፤የሚገኙ የተለያዩ የጥብቅና ድርጅቶች እና 4ዐዐ የሚደርሱ ተወካዮች የሚገኙበት ጉባዔ ነው፡፡ ዝግጁቱን ለማስተባበር የሀገር-ውስጥና አለም አቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴዎች የተደራጁ ሲሆንየሀገር ውስጥ አዘጋጅ ኮሚቴው LOC /Local Organizing Committee/ 17 አባላትን ይዞ በስራ ላይ ይገኛል፡፡ የአለምአቀፍ አዘጋጅ ኮሚቴው አስተባባሪና በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ጠበቆች ማህበር ም/ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው የሀገር ውስጥ አስተባባሪ ኮሚቴው /LoC/ እያከናወናቸው ላሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልፀው በኮሚቴው ቀጣይ ተግባራት እና የትኩረት ነጥቦች ላይ ማብራሪያ በመስጠት አቅጣጫዎች በቅደምተከተል ተቀምጠዋል:: ኮሚቴውም በአስተባባሪ እና ንኡሳን-ኮሚቴዎች ተዋቅሮ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ ዝርዝር መረጃ የሚገልጽ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ በዚህም ሀገርና የሙያ ማህበራችን ጎልተው በሚታዩበት መድረክ የሀገራችን ጠበቆችና የጥብቅና ድርጅቶች እንዲሁም አጋር አካላት የነቃ ተሳተፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡ መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን:: መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ:: ፌስቡክ- https://www.facebook.com/ethiopianbarassociation?mibextid=9R9pXO የቴሌግራም ገፅ- https://t.me/ethiopianfederalbarassociation የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር መስከረም 03 ቀን 2017ዓ.ም አዲስ አበባ ፤
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 10 2👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
Arbitration conference from September 19-20, 2024, Addis Ababa, Ethiopia.
Show all...
10👍 2
የፌደራል ጠበቆች የግብር አከፋፈልን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አመራሮችና የቴክኒክ አባላት ጋር ውይይት ተደረገ የግብር መስተንግድዎን በተመለከተ አቅጣጫ ተቀመጠ ፤ ጠበቆች በቀሩት የመክፈያ ግዜአት የግብር ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ ========================== የፌደራል ጠበቆች የታክስ አከፋፈል ስርአት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ እንደቆዪ እና ቀሪ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች በቅርቡ መፍትሄ እንደተሰጣቸው እንዲሁም መስተንግድዎ ያላገኙ የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮች ደግሞ በቀጣይ ውጤቱን ማህበሩ እንደሚያሳውቅ መግለፁ ይታወሳል:: የ2016 አመት የግብር አከፋፈል ተፈጥረው የነበሩ ችግሮች ግዜአዊና ቋሚ መፍትሄዎች ላይ ማህበሩ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማስተባበር ያደርገው ያላሰለሰ ጥረት መቀመጥ በሚኖርበት የመፍትሄ አቅጣጫ ላይ ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ም/ሀላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ እና ከቢሮ ሀላፊ ከፍተኛ የታክስ አማካሪ ወ/ሮ ሰናይት ፀጋዬ ጋር ዝርዝር ውይይት ተደርጎ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል ፤ በየደረጃው ላሉ አካላትም ሰርኩላር ተላልፏል:: በዚህም መሰረት ፤ 1/ የደረጃ " ሐ" ግብር ከፋዮች የሆናችሁ በታክስ ቅርንጫፍ መ/ቤቶች መስተንግድዎ ማግኘት ያልቻሉ ቀሪ ግብር ከፋዮች አሁንም በቀጥታ መስተንግድዎ እንዲያገኙ ፤ 2/ የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋይ የፌደራል ጠበቆችና የህግ አማካሪዎች ደግሞ ቀድሞ በመመሪያ ቁ. 138 መሰረት ሲስተናገዱበት ከነበረው አሰራር ተከልሶ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁ. 983/2008 አንቀፅ 80 መሰረት የግምት አወሳሰን Ratio ወደ 50/50 ተሻሽሎ እንዲከፍሉ ተወስኗል:: በተደረገው ሰፊ ውይይት ም/ የቢሮ ሃላፊዋ ጉዳዩ ዘላቂ እልባት እንዲያገኝ የጠበቆች ማህበር የበኩሉን ድርሻ መወጣቱን አሁንም እንዲቀጥል ጠይቀው አስተዳደሩ ለዘላቂ መፍትሄው በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል:: የማህበሩ መሪ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው የከተማው የገቢዎች ቢሮ ለወሰደው ሃላፊነት የተሞላው እርምጃ አመስግነው ፤ የሚመለከታቸው አካላት ላለፉት 3 አመታት በነበሩ ከፍተኛ ውጣ ውረዶች አብረውት ድጋፍ ላደረጉት ሁሉ እውቅና ሰጥተዋል:: "የግዜአዊ መፍትሄውን ይዘቶችና ዘላቂው መፍትሄ አሁንም ትኩረት ሊያገኝ እንደሚገባ" በመግለፅም ማህበሩ እንደስካሁኑ ሁሉ ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል:: በእለቱ የተገኙት የግብረሀይሉ አባላትም ለተሰጠው መፍትሄ አመስግነው ዘላቂ መፍትሄው ትኩረት እንደሚፈልግ አፅእኖት ሰጥተዋል:: በማህበሩ መሪነት በሂደቱ በርካታ ተግባራትን ላከናወኑት ለታክስ ግብረ ሀይል አባላት ማህበሩ ምስጋናውን ያቀርባል:: በሂደቱ ድጋፋቸውን ለሰጡት በተለይም ለፍትህ ሚኒስቴር የበላይ አመራር ፤ ለክብርት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፤ ለአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የቀድሞ አመራሮች እንዲሁም እነርሱን ተክተው በቅርብ ወደ ሃላፊነት በመምጣት ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝ ተገቢውን አመራር ለሰጡት ለቢሮ ሃላፊው አቶ ቢኒያም ምክሩ እና ለም/ሃላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ እንዲሁም በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ስር ለተቋቋመው ቴክኒካል ቡድን አባላት ፤ ለገቢዎችና ገንዘብ ሚኒስቴር ሃላፊዎች ፤ በተጨማሪም ለአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች ላደረጉት አስተዋፅኦ ማህበሩ ይፋዊ ምስጋናውን ያቀርባል:: የፌደራል ጠበቆች በየ ቅርንጫፎቻቸው በመቅረብ የታክስ ግዴታቸው በቀሩት ቀናት እንዲወጡ ከተቀመጠው አሰራር ውጭ የሚገጥማቸው ችግር ካለ ለማህበሩ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል:: መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን:: መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ:: ፌስቡክ- https://www.facebook.com/ethiopianbarassociation?mibextid=9R9pXO የቴሌግራም ገፅ- https://t.me/ethiopianfederalbarassociation የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ነሃሴ 28 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ ፤
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 22 4🥰 3👏 2
👍 11 2🤔 2
የኢት/ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ጠበቆችና የህግ አማካሪዎች አዘጋጅቶ የሚያሰራጨውን የስራ/አባልነት መታወቂያ መረጃ ማደራጀት ተግባር ባጠናቀቀባቸው ማሰራጨቱን ቀጥሎአል *********************** የኢት/ ፌደራል ጠበቆች ማህበር በሺዎች ለሚቆጠሩ አባላቱ ከሁሉም ክልሎች መረጃዎቻቸውን በማሰባሰብና በማደራጀት ደረጃውን የጠበቀ መታወቂያ ሲያሰራጭ መቆየቱ የሚታወስ ነው:: በዚህም አስቀድሞ ባሳወቀው መሰረት የመታወቂያ ህትመት በዝርዝሩ መሰረት ከፒያሳ ከፍ ብሎ አራዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍትህ አካላት ህንፃ 9ኛ ፎቅ በሚገኘው በማህበሩ ዋና መ/ቤት ቀርባችሁ እንድትወስዱ የተለጠፈ የስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው:: መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን:: መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ:: ፌስቡክ- https://www.facebook.com/ethiopianbarassociation?mibextid=9R9pXO የቴሌግራም ገፅ- https://t.me/ethiopianfederalbarassociation የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ነሃሴ 20 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ ፤
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 4🙏 2🔥 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.