cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office

This is official Telegram Channel of M.o.R Medium Tax payers No 1 Branch office Join the channel.

Show more
Advertising posts
3 493
Subscribers
+1524 hours
+347 days
+13730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በነሃሴ ወር የእቅዱን 102 በመቶ ገቢ ሰብስቧል፡፡ መስከረም 9፣ 2017 ዓ/ም በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር አንድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በነሃሴ ወር የእቅዱን 102 በመቶ ገቢ ሰብስቧል፡፡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ነሃሴ ወር ቀጥተኛ ከሆኑ ታክሶች፣ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክሶች እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ብር 2,818,537,840.02 ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 2,879,136,403.58 በመሰብሰብ የእቅዱን 102 በመቶ ማሳካት መቻሉን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የእቅድና አፈፃፀም ክትትል ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አበባው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት ባካሄዱት የ2017 በጀት ዓመት የነሃሴ ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ወቅት ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ገልፀዋል፡፡ አፈፃፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ክንውን ጋር ሲነፃፀር በብር 1.14 ቢሊዮን ወይም 65.8 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል፡፡ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተቋማዊ አቅምና ድጋፍ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አቡ ብርኪ የ2017 በጀት ዓመት የBSC አስተግባሪ ኮሚቴ የሱፐር ቪዥን ሪፓርት እንዲሁም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሰው ሃይል ሙሌትና የሥራ አፈፃፀም ምዘና ቡድን አስተባባሪ አቶ ያሬድ ሀረገወይን የ2016 በጀት ዓመት የውስጥ ሠራተኞች እርካታ ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በቀረቡት ሪፓርቶች ላይ የሁሉም የስራ ክፍል የሥራ ሂደትና ቡድን አስተባባሪዎች፣ የየዘርፉ ምክትል ሥራ አስኪያጆች በነሃሴ ወር በየስራ ክፍሉ በነበሩ ጠንካራ ጎኖችና በቀጣይ ወር ቢሰሩ የገቢ አፈፃፀሙን ሊያሳድጉ በሚችሉ አንኳር ነጥቦች ዙሪያ ሠፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ታምሩ የነሀሴ ወር ገቢ ከእቅድ በላይ መሰብሰብ መቻሉ እጅግ እንዳስደሰታቸው እና ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም ግብራቸውን በወቅቱ ለሚያስታውቁ ታማኝ ግብር ከፋዮች ምስጋና አቅርበው ለየሥራ ክፍሎች የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ፣ በቀጣይ ሩብ ዓመት ምንም ዓይነት የሚሻገር ስራዎች ሳይኖሩን፤ አመራሩ ጠጋ ብሎ በመምራት እና የተገልጋዮችን እርካታ በማሳደግ ጥንካሬዎቻችንን በማስቀጠልና ክፍተቶቻችንን በመሙላት ከሙስናና ከብልሹ አሠራር የፀዳ አገልግሎት በመስጠት እቅዳችንን ለማሳካት አስፈላጊውን ርብርብ አድርገን የሩብ ዓመት እቅዳችንን ማሳካት ይገባናል ሲሉ አፅንኦት ሠጥተው ተናግረዋል፡፡
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ለተቀላቀሉ የታክስ ኦዲት አመራርና ሠራተኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተካሄደ፡፡ መስከረም 08/2016 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር አንድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከምዕራብ፣ ከሰሜን ምዕራብ፣ ከምስራቅ፣ ከመቀሌ እና ከአዳማ በዝውውር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ለተቀላቀሉ የታክስ ኦዲት አመራርና ሠራተኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አካሄደ፡፡ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ታምሩ ለአዳዲስ የታክስ ኦዲት አመራሮች እና ሠራተኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ሀገርን የመቀየር ተልዕኳችንን መወጣት የምንችለው ገቢ የመሰብሰብ አቅማችንን በማሳደግ በመሆኑ እና እናንተ በ2017 በጀት ዓመት የተሰጠንን የገቢ እቅድ ለማሳካት አቅም ስለምትሆኑን አገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግና በቴክኖሎጂ በመደገፍ እቅዶቻችን ላይ በገንዘብና በሽፋን በእኔነት ስሜት በመስራት ኃላፊነታችሁን መወጣት ይገባል ሲሉ አፅንኦት ሠጥተው ተናግረዋል:: የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ቡድን አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት ጌታቸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከተመሰረተ ጀምሮ ያለውን የገቢ አፈፃፀም እንዲሁም የ2017 የገቢ እቅድ አስመልክቶ የተጠቃለለ ሪፓርት አቅርበዋል፡፡ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ሥርዓት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ እቴነሽ ደሱ በበኩላቸው የ2016 በጀት ዓመት የታክስ አዲት አፈፃፀም ምን እንደሚመስልና በ2017 በጀት ዓመት ለመስራት የተሰጠን እቅድ የተለጠጠ በመሆኑ ስራዎቻችን ላይ ትኩረት በማድረግ እንደ ታክስ ኦዲት የተሰጠንን እቅድ ማሳካት እንድንችል ከወዲሁ አስፈላጊውን ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Show all...
ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሠራተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡ መስከረም 07/2016 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስቴር በመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር አንድ ቅ/ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት በልምድ እና በዜሮ ዓመት ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሠራተኞች በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ሥልጠናውን የሠጡት የቅ/ጽ/ቤቱ የሠው ሃብት ስራ አመራርና ልማት የሥራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሳምሶን መንግስቱ ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሠራተኞች በተቋሙ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች፣ በሠራተኞች አስተዳደር ደንብ ቁጥር 155/2000፣ እንዲሁም በሠራተኞች መብት እና ግዴታዎች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ስልጠና  ሠጥተዋል፡፡ አቶ ሳምሶን አክለውም ሠራተኞቹ ስራቸውን በእውቀትና ክህሎት በተላበሰ መልኩ ለተገልጋዮች ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዳ አገልግሎት በመስጠት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ ለመሰብሰብ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አፅንኦት ሠጥተው ተናግረዋል፡፡
Show all...
ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የኤሌክትሪክ እና ውሀ ፍጆታ መጠን ለመወሰን የወጣ መመርያ ቁጥር 1021/2016 ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.