cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

የኢትዮጵያ ታሪኮች የሚቀርብበትና የሚዳሰስበት ቻናል

Show more
Advertising posts
11 270
Subscribers
+324 hours
+177 days
+12730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

03:26
Video unavailableShow in Telegram
6.81 MB
👍 7 2
የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የህይወት ታሪክ 👇 https://youtu.be/qOTYlUb8iIY
Show all...
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የህይወት ታሪክ

Blatten Geta Herouy WoldeSelassie Biography @TariknWedehuala11 #addisababa #ethiopian #ethiopianhistory #ታሪክን_ወደኋላ #tariknwedehuala #addisababa #movie #BlattenGetaHerouyWoldeSelassie #habesha #ethiopian #ታሪክ #ኢትዮጵያ #ታሪክ

👍 11😡 1
00:24
Video unavailableShow in Telegram
መስከረም 9 ቀን 1931 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከ 86 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ደራሲ ፣ የታሪክ ጸሐፊ ፣ የስነ-ምግባር አስተማሪ እና አንጋፋው የዲፕሎማቱ ሠው ክቡር ብላቴን ጌታ ኃሩይ ወልደ ስላሴ ከዚህ አለም በሞት የተለዩበት ዕለት ነበር። #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala
Show all...
InShot_20240919_183413791.mp418.03 MB
👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
የኦስትሪያ ፕሬዝዳንት ቴዎዶር ኮርነር ለግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴና ልዕልት ሳራ ግዛው በቪየና በፓሌስ አውርስፐርግ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ሲያደርጉላቸው ፤ ኦስትሪያ - እ.ኤ.አ 1954 #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala youtube.com/@TariknWedehuala11
Show all...
👍 14👎 2 2
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ፤ 1943 -- 2017 ነፍስ ሄር 🙏 ገፃችን በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሕልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ፤ ለመላው ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል። #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala
Show all...
💔 27😢 11👍 8 2
Photo unavailableShow in Telegram
መስከረም 5 ቀን 1975 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከዛሬ 42 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በባሌ አጋርፋ የገበሬዎች ሁለገብ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተመርቆ የተከፈተበት ዕለት ነበር። ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማርያም የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተደደር ደርግና (የኢ.ሠ.ፓ.ኮ) ሊቀመንበር የአብዮታዊ የጦር ጠቅላይ አዛዥ... "ትምህርት ለሰፊው ሕዝብ ደረጃ በደረጃ እንዲዳረስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲዳብር የታለመውን ግብ ተግባራዊ ለማድረግ ይህንን የገበሬዎች ሁለገብ ማሰልጠኛ ተቋም መስከረም ፭ ቀን ፲፷፻፸፭ ዓ.ም መርቀው ከፈቱ። #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala youtube.com/@TariknWedehuala11
Show all...
👍 18 5🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
◈ ቀደምት አንጋፋ ጋዜጠኞቻችን..... ➻ አቶ ከበደ አኒሣ ➻ አቶ ነጋሽ ገብረማርያም ➻ አቶ ያእቆብ ወልደማርያም ➻ ? ➻ አቶ በአሉ ግርማ ➻ አቶ ብርሐኑ ዘሪሁን (በስተቀኝ) (ከግራ ወደ ቀኝ) ⨳ በዳግላስ ዲሲ-3 አውሮፕላን #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala youtube.com/@TariknWedehuala11
Show all...
👍 11
01:38
Video unavailableShow in Telegram
ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ለእጩ የፖሊስ ካዴት ተመራቂዎች ሽልማት ሲሰጡ ፤ ሚያዝያ 1969 ዓ.ም #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala youtube.com/@TariknWedehuala11
Show all...
75.00 MB
👍 12 4
00:59
Video unavailableShow in Telegram
መስከረም 3 ቀን 1914 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከ 103 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን እና የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበረው ‹‹ብርሃንና ሰላም›› ማተሚያ ቤት በንጉሥ ተፈሪ መኮንን (በኋላ ላይ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ) መኖሪያ ግቢ ውስጥ ጨው ቤት በሚባለው ባለሁለት ክፍል ቤት ውስጥ የህትመት ስራውን የጀመረበት ዕለት ነበር። #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala youtube.com/@TariknWedehuala11
Show all...
21.92 MB
👍 8 1
Photo unavailableShow in Telegram
የጊዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ምክር ቤት ሊቀመንበር ኮሎኔል መንግስቱ ሃ/ማርያም እና ምክትል ሊቀመንበር (ሌ/ኮ) አጥናፉ አባተ ፤ የጊዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ምክር ቤት ሊቀመንበር ኮሎኔል መንግስቱ ሃ/ማርያም ከኢትዮጵያ ባህር ኃይል ኮሌጅ እና የሐረር ጦር አካዳሚ ለተመረቁት ሰልጣኞች እንደተናገሩት በዚህ ወሳኝ የትግል ወቅት የሚጠብቃቸው ተግባር ሁለንተናዊ አብዮታዊ ግዴታ መሆኑን ተናግረዋል። አብዮታዊውን እናት አገራቸውን በደማቸው ማስጠበቅ የመጀመርያውና ተቀዳሚው ተግባር ሆኖ ሳለ ፣ ሁለተኛው ግን አብዮቱን በሰፊው ሕዝብ ጠላቶች እንዳይቀለበስ መከላከልና ቀጣይነት ያለው ግስጋሴውን እስከ ህዝባዊው ዓለም ድረስ ማረጋገጥ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ኮሌጅ እና የሐረር ጦር አካዳሚ 18ኛ ክፍል የምረቃ ስነስርዓት ላይ ሌ/ኮሎኔል አጥናፉ አባተ ፣ የምክር ቤቱ አባላት ፣ የካቢኔ ሚኒስቴር አቶ አያሌው ማንደፍሮ ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ፣ ሜ/ጄ ግዛው በላይነህ ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ፣ የጦር ኃይሎች ከፍተኛ መኮንኖች ፣ የተለያዩ አምባሳደሮች ፣ የፖሊስና የመከላከያ አባሎች በተገኙበት በብሄራዊ ቤተመንግስት ተካሂዷል። ግንቦት 21 ቀን 1969 ዓ.ም ብሄራዊ ቤተ-መንግስት አዲስ አበባ #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala youtube.com/@TariknWedehuala11
Show all...
👍 9 3
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.