cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

የስነ-ልቦና ትምህርቶችን በነፃ ያግኙ ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @biniGirmachew21 ማናገር ይችላሉ

Show more
Advertising posts
115 837
Subscribers
-22824 hours
+9547 days
+7 54730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
እኔ ያቅሜን አስገብቻለሁ እናተም እግዚአብሔር በረዳቹው መጠን እረድው - ይሄንን ጥንታዊና ታሪካዊ ደብር መርዳት ለምትፈልጉ    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000238130631    አቢሲኒያ ባንክ 1674787878 ለበለጠ መረጃ 0921779201                    0946331817                    097415083
Show all...
👍 18 5👏 2🏆 1
- ይሄንን ጥንታዊና ታሪካዊ ደብር መርዳት ለምትፈልጉ    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000238130631    አቢሲኒያ ባንክ 1674787878 ለበለጠ መረጃ 0921779201                    0946331817                    097415083 ተመለከቱት በደንብ   https://youtu.be/qOD4Hi7f05Y?si=ivGpCoNzCFuc1vdO https://youtu.be/qOD4Hi7f05Y?si=ivGpCoNzCFuc1vdO
Show all...
🛑የላቂት መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን አባቶችና ምዕመናንን ይጣራሉ!!!

የላቂት መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን ይጣራሉ!!! - ጥንድ ቦሮቻቸዉን ሸጠዉ የጻድቁን ህንፃ የሚሰሩት ምዕመናን እርዱን ድረሱልን ይላሉ.. - የአቡየ ከተማ የቅዱሳን መፍለቂያ የጻድቁ ደጅ ለምዕመናን ጥሪ አቀረበ.. - ምዕመናንን ያላቸዉን ሁሉ ጨርሰዉ በመላዉ ዓለም የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያንን እየተጣሩ ይገኛሉ። - ይሄንን ጥንታዊና ታሪካዊ ደብር መርዳት ለምትፈልጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000238130631 አቢሲኒያ ባንክ 1674787878 ለበለጠ መረጃ 0921779201 0946331817 0974150839 ንቁ ሚዲያ የተሻለ አገልግሎት እንድንሰጥ ለመርዳት 1000 2975 55549 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :ንቁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ የፀሎትና መርከብ መርዳት ለምትፈልጉ የሂሳብ ቁጥር እና ሰብስክራይብ ፤ላይክ አስተያት በመፃፍ አና የደዎል ምልክቷን በመንካት ቤተሰባችን ይሁኑ ” ምርጫዎ እኛ ስላደረጉ እናመሰግናለን፡፡ ✅join አድርጉ

https://t.me/nikuchannel

ንቁ ሚዲያ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ንቁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የፀሎትና የንስሐ መርከብ የዋትሳፕ ማህበር ✅የማህበሩ አባል መሆን ለምትፈልጉ ስፖንሰር የምታደርጉ የዋሳፕ በዚህ ሊንክ ይግቡ👉

https://chat.whatsapp.com/JJfoncjwiZiLgGT2N6QoFU

ንቁ የፀሎትና የንስሐ መርከብ የዋትሳፕ ማህበር ለበለጠ መረጃ የማህበሩን አድሚኖች በወትሳብና በኢሞ ብቻ ይደውሉልን አልያም በተቀመጠው የወትሳብ ሊንክ join አድርገው ይግቡና ያግኙን +49 1521 37 06 500 +2519 44 274 294 +966 5 37 02 86 64 +966 54 007 9927 +49 1766 68 68 741 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ንቁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የፀሎትና የንስሐ መርከብ የዋትሳፕ ማህበር የFacebook page 👉🏻ንቁ-የወንጌል ትምህርት በፌስቡክ መልስ በኮሜንት።#growth #orthodox

👍 11
በድጋሚ የተለቀቀህ ያሉን አማራጮች ብትወዱም ባትወዱም . . . አንዳንድ ሰዎች በእናንተ ላይ የተለያየ ጤና-ቢስ ነገሮች ሃሳብ ማሰባቸውም ሆነ የተለያዩ ነገሮችን ማውራታቸው አይቀርም። ያላችሁ አማራጭ ፦ ቀድሞውኑ ሰዎች ስለ እናንተ ምን እንዳሰቡና ምን እንዳወሩ ለማወቅ ከመሞከር መቆጠብ ነው። ይህንን ካደረጋችሁ በኋላ ሳትፈልጉት እናንተ ጋር ስለሚደርሰው የሰዎች አሳብና ወሬ ያላችሁ አማራጭ ራሳችሁን ማጠንከር ነው። ብትወዱም ባትወዱም . . . በሚቀጥሉት ቀናት ሕይወት አንዳንድ ደስ የማይሉ ነገሮችንና ገጠመኞችን ማቀበሏ አይቀርም። ያላችሁ አማራጭ ፦ ገና ለገና ምን ይመጣ ይሆን ብላችሁ ከመጨነቅ መጠበቅ ነው። ይህንን ካደረጋችሁ በኋላ ለሚመጣው ነገር ሁሉ ራሳችሁን በማዘጋጀት ብርቱ መሆን ነው። ብትወዱም ባትወዱም . . . አንዳንድ የጀመራችኋቸው ነገሮች እንደጠበቃችኋቸው ላይሄዱ ይችላሉ። ያላችሁ አማራጭ ገና ለገና ባይሳካ ብላችሁ አዳዲስ ነገር ከመጀመር አለመገታት ነው። ይህንን ካደረጋችሁ በኋላ ሁኔታዎች ባልጠበቃችሁት መንገድ ከሄዱ ግን የመጠባበቂያ እቅድ (plan B) ማዘጋጀታችሁን አትርሱ። እውነታው ፦ 1. ሰዎች ስለእናንተ ከሚያስቡትና ከሚያወሩት በላይ ናችሁ! 2. ሁኔታዎች ከሚያቀብሏችሁ መጥፎ ገጠመኞች በላይ ናችሁ! 3. ከተሳካውም ሆነ ካልተሳካው ሁኔታ በላይ ናችሁ! የተለያዩ  ትምህርቶችን  ያዳምጡው https://youtu.be/H0CVvLVVZY4?si=-6vrNVYX2Y_lsWCY subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ቴሌግራም @BiniGirmachew @BiniGirmachew @BiniGirmachew
Show all...
🙏 15👍 11 4🥰 3👏 2👌 2🏆 2🫡 1
ወዳጆቼ! ምን ደከመኝ መሰላችሁ የውሸት ገፆችን፣ የቲክቶክ አካውንቶች እና ልጥፎችን እኔ አይደለሁም እያሉ መዳረቅ 😀 ሰው እንዴት በሰው ምስል ለመነገድ ይሄን ያህል ይደክማል?🤔 ሰሞኑን በቲክቶክ ሲዘዋወር የሰነበተው ይህ ቪዲዮ የኔ ማንነት አይደለም። በደስታዬም በሀዘኔም በዝማሬ አምላኬን የማመሰግን ዘወትር ወደእርሱ የምንበረከክ ሴት ነኝ። "ደስ የሚለዉ ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር" ስለሚል (ያዕ 5፥13)። የሚችሉትን ሁሉ የክፋት ሀሳብ ሞክረው አልሳካ ሲላቸው በ filter እና Al technology በመጠቀም በሰዎች አእምሮ መጥፎ ሀሳብ ለመዝራት የተቀነባበረ ነው። ቴክኖሎጂን ለመልካም ብንጠቀምበት ብዙ እናተርፍበታለን እኛ ጋ ግን በተቃራኒው ነው። ብዙ አንገብጋቢ ጉዳዮች ባሉበት ሀገር ለእንዲህ ያለ ተራ ጉዳይ መልስ መስጠት ቢያሳፍረኝም ይሄን ቪዲዮ ተንተርሰው አንዳንዶች ርትዕት ኦርቶዶክሳዊት ሐይማኖቴን ሲተቹ ስለተመለከትኩ ለመፃፍ ተገደድኩ። በእርግጥ እኔ እንዳልሆንኩ ቢያውቁም አጋጣሚውን ሰብእናዬን እና እምነቴን ለመንቀፍ ሲጠቀሙበት ሳይ እንዲህ ያሉ ቪዲዮች ከተራ ልጥፍነት ባሻገር ሌላ አጀንዳ እንዳላቸው ጥያቄ አጭሮብኛል። ከዚህ በፊትም መሰል ቪዲዮዎችን በማጋራት ብዙዎችን ሲያደናግሩ ነበር። filter እንደሆነ ሰዎች ይረዱታል ብዬ ለመተው ብሞክርም አንዳንድ አስተያየቶች በተለይም እኔን ሮል ሞዴል አድርገው የሚከተሉኝ ወዳጆቼ ቅር እንደተሰኙብኝ ተመልክቻለሁ። እነርሱም የሚፈልጉት ይሄን ነው። እባካችሁ ሴራው ይግባችሁ! ወዳጆቼ እኔ አይደለሁም። ቅሬታችሁ ለኔ ስላላችሁ አክብሮት እንደሆነ ቢገባኝም እንዲህ ያሉ ሰዎችን ማስቆም ስለማልችል ወደፊትም መሰል ቪዲዮዎችን ብታዩ ቅንብር እንደሆነ እንድትረዱኝ እጠይቃለሁ። ከውሸታሞች ጋር ትግል ስለደከመኝ አግዙኝ። እንዲህ ያሉ የውሸት ገፆችን ሪፖርት በማድረግ ወይም የማስመሰል ልጥፋቸውን ባለመከተል እንድትተባበሩኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ። እግዚአብሄር ያክብርልኝ🙏 መሰረት መብራቴ።
Show all...
🥰 29👍 12 4
ትምህርት ተጀመረ! አንዳንድ ወላጅም እንደተለመደው ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት ማድረስ ጀመረ። እኔ 'ምለው ልጆችን ትምህርት ቤት የማድረስ ልማድ መቼ የተጀመረ ነው? እኔ ባደግሁበት ዘመን ከ4 ዓመት ጀምሮ ልጅ ትምህርት ቤት ይገባል። ወላጅ ልጁን የመጀመሪያ ቀን ትምህርት ቤት ለማስገባት ይሄድ ይሆናል። ከዚያ በኋላ ግን ልጅ ከፍ ላሉ ልጆች አደራ ከእናንተ ጋር ይሂድ ተብሎ ከጓደኞቹ ጋር ትምህርት ቤት ይሄዳል። በዚያም ከሌሎች ጋር ተግባብቶ፣ ተስምማቶ፣ አንዳንዴም ተጣልቶ ዘመኑን መስሎ ያድጋል። አሁን ላይ ዓቅም ስላለው ብቻ ልጁን እያሳነፈ ያለ ወላጅ እየበረከተ ይመስለኛል። ልጅን በመኪና ጭኖ ትምህርት ቤት ማድረስ፣ በሰርቪስ መኪና የሚሄድ ከሆነም መሳፈሪያው ድረስ መሸኘት የተለመደ እና ዘወትር የሚታይ ድርጊት ነው። ለልጅ ፍቅርና አቅጣጫ ማሳየት እንጂ እንደ እንቁላል ያለ እንክብካቤ አይጠቅመውም። ሰውን እንጾ የሚሠራው ፈተና ነው - የህይወት ፈተና። ያልተፈተነች ህይወት እርባና ያለው ተግባር መከወን ይሳናታል። ለዚህ ሲባል ልጆች በየዕድሜ ደረጃቸው ከፍ ላለ ፈተና እንዲጋለጡ ማድረግ ለልጆቹ ቀጣይ ህይወት ጠቃሚ ነው። ልጆች በሩቅ የዕይታ ጥበቃ ስር ሆነው ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲጫወቱ መልቀቅ፣ ከፍ ሲሉም ከጓደኞቻቸው ጋር ሌላ ሰፈር ሄደው እንዲጫወቱ ማድረግ፣ ዓቅም ከፈቀደም ሌላ ከተማ እና ሀገር እንዲጎበኙ ማድረግ ያስፈልጋል። ከዓመታት በፊት በርካታ የ12 ዓመት ልጆች ከጃፓን ሀገር በአስጎብኚ ስር ሆነው ሮምን ሲጎበኙ አስተውያለሁ። በንጉሡ ዘመን እነ እማሆይ ጽጌ ማርያም ገና 10 ዓመት ሳይሞላቸው በመርከብ ስዊዘርላንድ ተልከው ተምረዋል። የኛዋ ዶ/ር እሌኒ ብቻዋን ናይሮቢ ሄዳ መማር የጀመረችው ገና በ12 ዓመቷ ነው። አንዳንድ ኩባ ሄደው የተማሩ የሀገራችን ልጆች 10 ዓመት ሳይሞላቸው የተላኩ ነበሩ። አንዳንድ ወላጅ ያበዛዋል። የ12 ዓመት ልጅን ትምህርት ቤት ካላደረስኩ፣ ቁርስ ካላጎረስኩ ይላል። ይህ ፍቅር ብቻ አይደለም። ይህ ወላጅ "ልጅ-አዛይ" የሚባል ዓይነት ነው። ልጁን በእግሩ እንዳይቆም እና ሽባ ማድረግ ዓላማ ያለው ይመስላል። እስኪ ጎዳናውን ተመልከት! ጎዳናው ላይ በርካታ የ7 ዓመት ልጆች ራሳቸውን ችለው ሲራመዱ ታያለህ። የወደፊቱ የኢትዮጵያ መሪዎች የሚወጡት ከእነዚያ ውስጥ ነው። መንግስቱ፣ መለስ፣ ዐቢይ እና መሰሎቻቸው በወላጆቻቸው እየታዘሉ ትምህርት ቤት የሚሄዱ አልነበሩም። ብዙዎቹ በ12 ዓመታቸው ከወላጆቻቸው ዕይታ ውጪ ያደጉ ናቸው። ባይሆን ጥሩ ራዕይ ተነግሯቸው ሊሆን ይችላል። ት/ቤት ወላጅ የሚያመላልሳቸው ልጆች ግን አልነበሩም። ወዳጄ :- ልጅህ ከዘመኖቹ ጋር ታግሎና ተመሳስሎ እንዲኖር ልቀቀው። ባይሆን መሠረታዊ የSafety ጉዳዮችን እና የአደጋ ጊዜ ማምለጫ መንገዶችን ቀድመህ አስተምረው። ህይወት የምታብበው እንዲያ ነው! አንድ ሰው ቢራቢሮ ከቅርፊቷ ውስጥ ልትወጣ ስትታገል ዓይቶ አዘነላት እና ቅርፊቷን ቀዶ አወጣት። ቢራቢሮዋ ግን መብረር ሳትችል ቀረች። ምክንያቱም ለቢራቢሮዋ ያ ከቅርፊት የመውጣት ትግል ሰውነቷ ላይ ያለውን እርጥበት ጨምቆ የሚያደርቅላትና የሚያጠነክራት የበረራ ማዘጋጃ ትግል ነበር። አንተም/አንቺም በእንክብካቤ ስም ልጆቻችሁን እንዳይጠነክሩ እና ራሳቸውን እንዳይችሉ አታድርጉ። የጃፓን እና የሲንጋፖር ልጆች ራሳቸውን ችለው እንዴት ብቻቸውን ትምህርት ቤት እንደሚሄዱ ተመልከቱ። እዚህም ያሉ የድሃ ልጆች እንዴት ሰብሰብ ብለው ከሰፈር ተጠባብቀው ወደ ትምህርት ቤት እንደሚሄዱ ተመልከት። እዚያ የልጅነት ጉዞ ውስጥ ብዙ ትምህርት አለ፣ ብዙ ጨዋታ አለ፣ ብዙ ተግባቦት አለ፣ ብዙ ዲፕሎማሲ አለ፣ ብዙ ፍትጊያ/ቻሌንጅ እና ያንን ተቋቁሞ የማለፍ ፈተና አለ። ከዚያ ውስጥ ዘመን የማይሽረው ጓደኝነትና ትዝታ ይፈጠራል። ከዚያ ውስጥ የልጅ በራስ መተማመን ይፈጠራል። ልጅህ በራሱ እግር እንዲቆም በጊዜ አጠንክረው። አለዚያ አይበለውና አንተ አንድ ቀን ያለጊዜህ ብትሰበር ያልጠነከረው ልጅህ የሌሎች መጫወቻ ይሆንና ስብርብሩ ይወጣል። እኔ ባልኖር ልጄ ምን ይሆናል? እያልክ ልጅህ በራሱ እግር እንዲቆም በጊዜ አጠንክረው። አንቺም እናትዋ ጠንክረሽ ልጅሽን ልታጠነክሪ የተገባ ነው።
Show all...
👍 41 3🥰 3👏 1
"ትንሽ ቦታ" ስሜታዊ ሆኖ ለተናገረን ፣ ሊረዳን ፈልጎ ለሳተ ፣ ኑሮ አስክሮት ለገፋን ፣ ንዴት ገፍቶት ላጠፋ ፣ ግዜ አጣሁ ብሎ ላልጎበኘን ፣ ስናሸንፍ ላላጨበጨበ፣ ስንወድቅ ላላነሳን ፣ ስናስብለት ላልተረዳን ፣ ማደጋችንን ላላየ ፦        "ትንሽ ቦታ ለይቅርታ" አኑረናል አማረልን ብለን ላሳዘንን ፣ አጉል ተስፋ ለሰጠነው ፣ ውድቀት ላይ ለሳቅነው ፣ ብልግናን ላጎላናው ፣ ድድብናን ላነፈስነው ፣ ማድረግ ችለን ላላደረግነው ፣ ችለን ለተጣመምነው ። ለራሳችን ይቅርታ አደርገናል...
Show all...
👏 36👍 12🥰 10👌 4 2
ተማሪው መምህሩን ይጠይቃል 👇🏾 በህይወቴ ምን አይነት ውሳኔዎችን ልወስን? መምህሩ ይመልሳል? 👇🏾 የባርኔጣ: የፀጉር ቁርጥ እና የንቅሳት ውሳኔዎች አሉ አንዳንድ ውሳኔዎች ባርኔጣ ናቸው - ባርኔጣ አንድ ጊዜ ትሞክረውና ካልተስማማህ እና ካላማረብህ አውልቀህ ሌላውን ትቀይረዋለህ: የሚያምርብህን ታደርጋለህ አንዳንድ ውሳኔዎች የፀጉር ቁርጥ ናቸው - ፀጉርህን ትቆረጣለህ ግን አትወደውም: አዲስ ቁርጥ ልትሞክር ትችላለህ ነገር ግን ካልወደድከው እና ከአንተ ስታይል ጋር ካልሄደ እስኪበቅል የመጠበቅ ሁለተኛ እድል አለህ: ፀጉርህ ወደ ቦታው እስኪመለስ ትእግስት ማድረግ ብቻ ነው አንዳንድ ውሳኔዎች ንቅሳት ናቸው - ንቅሳት አንድ ጊዜ ገላህ ላይ ካረፈ የሰውነትህ አካል ነው: አትቆርጠውም አትፍቀውም:: በመስታወት ስታየውም ሆነ ሰዎች ሲያስታውሱህ ያለፈውን ተቀብለህ የወደፊቱን ከመራመድ ውጪ አማራጭ የለህም 👇🏾 ሁላችንም የባርኔጣ: የፀጉር ቁርጥ እና የንቅሳት ውጤቶች ነን
Show all...
🙏 53👍 35👏 7 6🥰 6🫡 1
Photo unavailableShow in Telegram
እጅግ በጣም የማከብራቸው እና የማደንቃቸው የፖለቲካ ሰው ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ እግዚአብሔር ነፍስዎን ይማርልን ።
Show all...
👍 26🙏 12 6
ዘወር ብላችሁ አልቅሳችሁ ታውቃላችሁ ...ወይ ደግሞ ለሊት ተነስታችሁ በእንባ ታጥባችሁ ...ሲቃችሁን ሰው እንዳይሰማው አፋችሁን በእጃችሁ አፍናችሁ ስትንሰቀሰቁ ያደራችሁ....ነግቶ ለጠየቃችሁ እንዲሁ አይኔን አሞኛል ምን እንደሆነ እንጃ ብላችሁ ላለቀሰው አይናችሁ ሰበብ የደረደራችሁ...ብሶተኛ ላለመባል በሆነው ባልሆነው የገለፈጣችሁ.... የፊታችሁ እና የሰውነታችሁ ከለር አራምባና ቆቦ ሆኖ መጎሳቆላችሁን ያሳበቀባችሁ የላችሁም....ልብሳችሁ እስኪሰፋችሁ ድረስ ከስታችሁ መክሳቱን ፈልጌው ነው ብላችሁ የዋሻችሁም...አልያም "ስጋ ለበሬ ነው...እንደ እኔ አትሸናቀጡና..."....የሚል  ውስጠ ወይራው ብሶት የሆነ ቀልድ ቀልዳችሁ ለብቻችሁ የሳቃችሁም ትኖራላችሁ...ዘመድ እንደ ሰውነት የሆነባችሁስ...ሲኖራችሁ የሚቀርብ ስታጡ ደግሞ የሚርቅ....መቼ ነው አልፎልኝ እኔም እንደ ሰዎቹ, "ሂሳብ እኔ ነኝ የምዘጋው...."...ብዬ ምከራከረው ብላችሁ የምትተክዙ....ማጣት...መንጣት የአማርኛ ፊልም ላይ እንደሚታየው  ኮሜዲ እንዳልሆነ የምታውቁ..ለተራበው ሆዳችሁ ስትሉ ውሻ የሆናችሁ.... ተስፋ ያደረጋችሁት ጉም የሆነባችሁ...እኮ እናንተ እንዲህ ሆንኩ ብላችሁ ማስረዳት የሰለቻችሁ...ልባችሁ የሰለለባችሁ...."ለበጎ ነው"..የሚለው ቃል ተራ ዲስኩር የመሰላችሁ..."ደህና ነህ"...ለሚለው ጥያቄ እንዲሁ ስለሚባል ብቻ "ደህና ነኝ" የምትሉ....የደከመው ልባችሁ ደልዳላውን መሬት የተራራን ያህል አግዝፎ ላሳያችሁ ...ለዶፍ ዝናብ የማትበገሩ የነበራችሁና አሁን ካፊያ ድንኳን ለሚያስደኩናችሁ እናንተ.... ማን ያውቃል ገና አፍ ላልፈቱ ልጆቻችሁ  ስትሉ ክብራችሁን የዘነጋችሁም ትኖራላችሁ...እኔስ መቼ ነው "ተደላደለልኝ ህይወቴ.."..ብዬ የምዘምረው ብላችሁ የሰው ደስታ አጃቢ ብቻ ሆናችሁ የቀራችሁ ለመሰላችሁ እናንተ...በሰው ደስታ ግርግር መሀል  ፊታችሁ መጨለሙን የምታስተውሉት "ምነው ፊትህን ጣልከው..."...በሚል የተመልካች ጥሪ የሆነ...ምቀኝነት እንዳችመስልብኝ ብላችሁ በደረቅ ሳቅ መከፋታችሁን የምትደብቁ ....ቁጭ ብላችሁ ለሚነጋባችሁ...እንቅልፍ እንኳን የሸሻችሁ እናንተ.... አይዞአችሁ ትዕግስታችሁ ፍሬ ያፈራል...ከልባችሁ የምትስቁበት ጊዜ ይመጣል...ወዴትም መሄድ አይሻልም...ፈተናው ፀና ብላችሁ ካልተጠራችሁበት አትሂዱ...የሰርግ ድንኳን ሰባሪ የቤተሰብ ፎቶ ላይ ሲገባ አይታችሁ ታውቃላችሁ....?...ያልተጠራችሁበት ለምን ትሄዳላችሁ...አይዟችሁ ይሄ የመጨረሻ ትግላችሁ ይሆናል....ይሄን ሩጫ ለየት የሚያደርገው አበረታች መድሀኒት ብትጠቀሙ የማትከለከሉበት መሆኑ ነው...አበረታች መድሀኒቱ ፀሎት ይባላል...dose በጨመራችሁ ቁጥር ሩጫችሁ እያጠረ ይመጣል.... የትም አትሂዱ...ፈተናውን ያሳለፋችሁ ፈጣሪ ለሽልማት በመጣ ጊዜ በድናችሁን አያግኘው...አሸነፋችሁ እኮ ኧረ ተሸለሙ.... በርቱ...ተሸለሙ።
Show all...
81👍 29🙏 13🥰 11🫡 5👌 4👏 2🏆 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.