cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ስለ - ህግ - አገልግሎት ⚖

ስለቤተሰብ ሕግ ፣ስለንግድ ሕግ፣ስለወንጀል ሕግ፣ስለውርስ ሕግ፣ስለውል ሕግ ፣የሰበር አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞች የሚያገኙበት ቻናል ነው። ለጥያቄ እና አስተያየት በቴሌግራም አካውንታችን @DesiignerA 📞 0916455355 ☎️

Show more
Advertising posts
548
Subscribers
+124 hours
+217 days
+7330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ቀለብ የመስጠት ግዴታን አለመወጣት ያለውን የወንጀል ተጠያቂነት። የቀለብ ገንዘብ መጠራቀም አይችልም፤ ቀለብ ተቀባዩ ለኑሮ አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ካላቀረበ በስተቀር ቀለቡን መቀበል ካለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሶስት ወራት ውስጥ ቀለቡን ያልተቀበለ ወይም ያልጠየቀ እንደሆነ የተጠራቀመውን ቀለብ መጠየቅ አይችልም፡፡ ቀለብ ተቀባይ የሆነ ሰው በቀለብ ሰጪው ላይ ወይም በቀለብ ሰጪው ወደላይ እና ወደታች በሚቆጠሩ ወላጆች ወይም ተወላጆች ወይም ባል ወይም ሚስት ህይወት ወይም ንብረት ላይ የወንጀል ተግባር የፈጸመ ወይም ለመፈጸም የሞከረ እንደሆነ ቀለብ የማግኘት መብቱን የሚያጣ ይሆናል፡፡ በቂ ምክንያት በህግ መሰረት ሊሰጥ የሚገባውን ቀለብ ለባለመብቶቹ አልሰጥም ያለ ወይም መስጠትን ያስተጓጎለ የወንጀል ተጠያቂነት የሚኖርብት ሲሆን የግል አቤቱ ሲቀርብ ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ ይችላል።
Show all...
ቀለብ_የመስጠት_ግዴታን_አለመወጣት_ተጠያቂነት_የሚያስከትል_ስለመሆን_ያውቃሉ_.pdf1.14 KB
👍 1
አሰሪው ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ ለስራው ተስማሚ አለመሆኑን ሳይመዝን ካሰናበተ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው። ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ ካሳ የሚከፈለው ሲሆን የስንብት እና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች ግን አገልግልትን ታሳቢ ተደርገው የሚሰሉ በመሆኑ አይከፈሉትም። የካሳው መጠን ሰራተኛው የሙከራ ጊዜውን (60 ቀናት) ቢጨርስ ሊያገኝ ይችል የነበረውን የ2 ወር ደመወዝ ብቻ ነው። ለሙከራ ግዜ የተቀጠረ ሰራተኛ ሰ/መ/ቁጥር 212420 https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss
Show all...
ስለ - ህግ - አገልግሎት ⚖

ስለቤተሰብ ሕግ ፣ስለንግድ ሕግ፣ስለወንጀል ሕግ፣ስለውርስ ሕግ፣ስለውል ሕግ ፣የሰበር አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞች የሚያገኙበት ቻናል ነው። ለጥያቄ እና አስተያየት በቴሌግራም አካውንታችን @DesiignerA 📞 0916455355 ☎️

ብርበራ
ብርበራ የወንጀል ድርጊት ለመፈፀም ጥቅም ላይ የዋሉ መሣሪያዎችን ፣ በወንጀል ድርጊት ምክንያት የተገኙ ቁሳቁሶችን ፣ ምርመራ ለሚደረግበት ጉዳይ ጠቀሜታ ያላቸውን ሌሎች ማናቸውም ማስረጃዎች ለመፈለግ እና ለመያዝ በተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ወይም የተጠቀሱት ነገሮች ተደብቀውባቸዋል በሚባሉ በሌሎች ሰዎች ቤቶች ውስጥ የሚከናወን የወንጀል ምርመራ ተግባር ነው፡፡ ብርበራ ለማድረግና በሚደረግበት ወቅት የሚከተሉትን መርሆች መከተል አስፈላጊ ነው። ✔ ማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ወይም  የፖሊስ አባል በፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ማዘዣ ካልያዘ በቀር የሰዎችን ቤት መበርበር አይችልም። ✔ ብርበራ የሚደረገው ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው። በፍርድ ቤት የተለየ  ትእዛዝ ሲሰጥ ብቻ ከዚ ሰአት ውጭ ሊካሄድ ይችላል። ✔ ማንኛውም የብርበራ ማዘዣ የሚበረበረውን  እና የሚያዘውን ዕቃ ማመልከት ያለበት ሲሆን መርማሪው ፖሊስ ወይም አብሮት ያለ የፖሊስ አባል በማዘዣው ላይ ከተመለከተው ውጭ ሌላው ዕቃ መያዝ አይችልም። ✔ መርማሪው ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በማዘዣ ትዕዛዙ የተመለከተውን ዕቃ በሚይዝበት ጊዜ የተያዘውን ዕቃ ዝርዝር መዝግቦ መያዝ ያለበት ሲሆን ከተቻለ ገለልተኛ የሆነ ሰው ሊስቱ ላይ እንዲፈርምበት ይደረጋል። ✔ ብርበራ የሚያደርገው ብርበራ ከሚደረግበት ሰው ጋር ተመሳሳይ ፆታ ባለው ሰው ነው። ✔ ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ ፖሊስ አስፈላጊውን ሀይል ብቻ ይጠቀማል
Show all...
👍 4
የወራሽነት ምስክር ወረቀት (certificate of heir)     የወራሽነት ምስክር ወረቀት(certificate of heir) ምንድነው?   # የወራሽነት ምስክር ወረቀት በአጭሩ ለመግለጽ ህጋዊ የውርስ ስርዓት ለሟላ የሟች ወራሽ ለሆነው ሰው የሟቹ ወራሽ መሆኑንና ከውርሱ የሚገባውን ድርሻ በተመለከተ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ተረጋግጦ የሚሰጥ የጽሁፍ ማረጋገጫ ነው ለማለት ይቻላል።    ወራሽ የሆነው ሰው ከውርሱ የሚያግኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት ምስክር ወረቀት እንዲሰጡት ዳኞችን ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህግ 996(1) ይደነግጋል።ከፍርድ ቤት የወራሽነት ምስክር ወረቀት መያዝ በወራሹ ሲጠየቅ የሚሰጥ እንጂ ህጉ ሟችን ለመውረስ የግድ ከፍርድ ቤት የወራሽነት ማስረጃ ማውጣት እንዳለበት የሚያስገድድ አይደለም።    በዚህ ጉዳይ  የፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 22 መ/ቁ 130284 ለይ በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የውርስ ሰርተፊኬት አንድ ሰው የራሱን ወራሽነት ለማስረዳት የሚወስደው ማስረጃ እንጂ ሌሎች ወራሾች አለመኖራቸውን የሚያሳይ ሰነድ ስላለመሆኑ፣ እና በግራ ቀኙ የሟች ወራሾች መሆናቸው በማረጋገጥ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከማስረጃነት በዘለለ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ በሚያዘው መሰረት ከሌሎች ሰዎች ክርክር ተደርጎበት ውሳኔ ያገኘና በፍርድ ያለቀ መቃወሚያ የማይቀርብበት ተደርጎ ሊወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ ትርጉም ተሰጥቶበታል።በተመሣሣይ መልኩ በፌ.ጠ.ፍ.ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ14 መ/ቁ 73247 አንድ ወራሽ የወራሽነት መብት በሌለው ንብረት ላይ ከህግ ውጪ የወራሽነት ሠርተፍኬት መያዙ በተረጋገጠ ጊዜ ይኸው ማስረጃ እንዲሰረዝ አቤቱታ ሊቀርብ እንደሚችል  አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።    #በመሠረቱ የመወረስ መብት የሚገኘው በህግ ወይም በኑዛዜ ሲሆን ፍ/ቤት አስቀድሞ ለአመልካቹ ያለውን የውርስ መብቱ አረጋግጦ የሚሰጥ እንጂ ለአመልካቹ የውርስ መብትን የሚስጥ አይደለም።በፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 20 መ/ቁ 113529 ለይ በተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ አንድ ሰው ውርስ ከተከፈተ ቡሃላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባያወጣም ለውርሱ አይገባም እስካልተባለ ድረስ የወራሸነት መብቶች ለእርሱ ወራሾች የሚተላለፍ ስለመሆኑ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።  የወራሽነት ሰርትፍኬት አስገዳጅ የሆነ ህጋዊ ውጤት ይኖረዋል። # የወራሽነት ምስክር ወረቀት የያዘው ወራሽ የምስክር ወረቀቱ እስካልተሰረዘ ድረስ ህጋዊ የውርስ መብት እንዳለውና ከውርሱ ድርሻ የሚገባ እንደሆነ ተደረጎ ይቆጠራል።አሁን በተግባር ባለው ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት አንደ ሰው ከያዘ ቡሃላ ወራሹ በሰርተፍኬቱ መሠረት ህጋዊ ውጤት ያላቸውን(valid juridical acts) ተግባራት መፈጸም ይጀምራል ማለትም ስመ ንብረት የማዞር ከባንክ ገንዘብ የማውጣትና ሌሎች መብቶች ማከናወን ይችላል ማለት ነው።የውርስ ሰርተፍኬት ውርሱ ከመጣራቱ በፊት ነው ወይስ የውርስ መጣራቱ ሂደት ከተጠናቀቀ ቡሃላ ነው ሊሰጥ የሚገባው የሚለው ጥያቄ አከራካሪ ሲሆን ይታያል የውርስ ማጣራት ሂደት ከመጠናቀቁ በፊት የሚሰጠው ምስክር ወረቀት ህጋዊ ወራሾች ከመለየታቸው በፊት እና ከማነኛውም እዳ ነጻ የሆነ የውርስ ንብረት ተጣርቶ ባልተለየበት ሁኔታ የሚሰጥ በመሆኑ አግባብነቱ አጠያያቂ ይሆናል በዚሁ ጉዳይ ለይ የፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ18 መ/ቁ110022  በሰጠው ውሳኔ ፍ/ቤቶች የወራሽነት ማስረጃ ወይም የምስክር ወረቀት ብቻ አንዲሰጡ ማመልከቻ ሲቀርብላቸው ውርስ እንዲጣራ የሚሰጡት ትእዛዝ የማይገባና አላስፈላጊ ስለመሆኑ ትርጉም ሰጥቶት እናግኛለን። https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss
Show all...
👍 1
የወንጀል ክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ የይርጋ ዘመን መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛ የወንጀሉን ድርጊት ከፈፀመበት ቀን አንስቶ ሲሆን የወንጀሉ ድርጊት እየተደጋገመ ተፈፅሞ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ  መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ነው። ሕጉ ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን በሚል ከላይ በየቅጣቶቹ የተቀመጡ የይርጋ ጊዚያት በእጥፍ ጊዜ ካለፈ የወንጀል ክስ ማቅረብ እንደማይቻል ደንግጓል። ለምሳሌ :መደበኛ የይርጋ ዘመኑ አስር አመት ለሆነ ወንጀል ፍፁም ይርጋው ሃያ ዓመት ይሆናል።ነገር ግን የወንጀል ሕጉ ክስ የማቅረቢያ የይርጋ ዘመን ቢደነገግም የኢ.ፊ.ድ.ሪ ሕገ መንግስት በበኩሉ በይርጋ የማይታገዱ ወንጀሎችን አስቀምጧል። በዚህም መሠረት ኢትዮጽያ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በሌሎች የአገሪቱ ሕጎች የሰው ልጅ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ተብለው የተለዩትን፦ 👉⚖️የሰው ዘር ማጥፋት ፣ 👉⚖️ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ መውሰድ ፣ 👉⚖️በአስገዳጅ ሰውን መሰወር ፣ 👉⚖️ አስገድደው የድብደባ ወንጀሎችን በፈፀሙ ሰዋች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም ፣ የወንጀል ክስ አቅራቢነት መደበኛ ክስ የማቅረቢያ  ጊዜን በተመለከተ ሕጉ በየወንጀሎች የቅጣት ጊዜ በመከፋፈል የይርጋ ዘመን አስቀምጧል። በዚህም መሠረት፦ 👉⚖️ከ5 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ለሚያሰቀጣ ወንጀል በ15 ዓመት ውስጥ  ክስ ካልተመሠረተ ጉዳዩ በይርጋ ይታገዳል። 👉⚖️ከ5 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ  ወንጀል በ10 ዓመት ውስጥ ካልተመሠረተ ጉዳዩ በይርጋ ይታገዳል። 👉⚖️ከ10 እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በ20 ዓመት ውስጥ ክስ ካልተመሠረተ ጉዳዩ በይርጋ ይታገዳል። 👉⚖️የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በ25 ዓመት ውስጥ ክስ ካልተመሠረተ ጉዳዩ በይርጋ ይታገዳል። ከዚህም ሌላ ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል አስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አምስት አመት እንዲሁም እስከ አንድ አመት በቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ  ብቻ ለሚያስቀጣ ወንጀል ሶስት አመት የይርጋ ጊዜ ተቀምጧል። https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss
Show all...
👍 4
በይርጋ የማይታገዱ የውርስ ጉዳዮች እና ከኑዛዜ ጋር የተያያዙ ይርጋዎች በ፡ ካሴ መልካም በዚህ ጽሑፍ የሚከተሉትን የሕግ ጉዳዮች ያገኛሉ፡ 1ኛ. የውርስ ይርጋ ማቋረጫ ምክንያቶች እና የውርስን የይርጋ ጊዜ የሚያቋርጡ ምክንያቶች 2ኛ. በይርጋ የማይታገዱ የውርስ ጉዳዮች 1. የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ 2. ከሕገ-ወጥ ተግባር ጋር የተገናኘ የኑዛዜ ሁኔታ 3. የውርስ ሐብቱን ስመ-ሐብት በጋራ ያስመዘገበ ወራሽ 4. የወራሽነት ማስረጃ ይሰጠኝ ክስ የይርጋ ጊዜ 5. በጋራ የውርስ ሃብቱን ይዞ መጠቀም 6. ሟች ሳይሞት ንብረቱን በያዘ ሰው ላይ የሚቀረብ ክስ የይርጋ ጊዜ 7. የወራሽነት የምስክር ወረቀትን በሕጉ የጊዜ ገደብ ያረጋገጠ ከሳሽ 8. በሀሰት የተሰጠን የወራሽነት የምስክር ወረቅ ማሰረዝ 3ኛ. የኑዛዜ ይፍረስልኝ ጥያቄ የይርጋ ጊዜ 1. ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ሰዎች 2. ኑዛዜው ሲነበብ ያልነበሩ ወራሾች 3. በመንፈስ ጫና የተደረገ ኑዛዜ እንዲፈርስ/እንዲቀነስ የመጠየቂያ የይርጋ ጊዜ 4. በሃይል የተደረገ ኑዛዜን የማፍረሻ የይርጋ ጊዜ 5. ከውርስ የተነቀለ ሰው የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ 6. የሟች የኑዛዜ ወራሽ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ ጸሐፊው የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሠረታዊ ሀሳቦች በሚል መጽሐፍ አሳትሞ ለአንባቢ ያበቃ ሲሆን በሕግ የመጀመሪያ ድግሪ እንዲሁም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋና ዳኝነት ከሰባት ዓመት በላይ በማገልገል ይገኛል
Show all...
ለፍትሐብሔር ፍርድ አፈፃፀም ሀብትና ንብረት የማስከበር ሕግ በኢትዮጵያ መግቢያ የፍትሐብሔር አቤቱታ (ክስ) አቅራቢ ወገን ፍርድ ለማስፈፀም ለፍርድ ቤት በመጀመሪያ የክስ አቤቱታዉን ሲያቀርብም ሆነ ካቀረበ በኋላ ለቀረበዉ ክስ ተመጣጣኝ የሆነ ሀብትና ንብረት ማስያዝ ወይም ማስከበር ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ንብረቱ ሳይታገድ ቀርቶ ተከሳሽ (ተጠሪ) ሀብትና ንብረቱን ቢያሸሸዉ ያስፈረደዉ ፍርድ ሳይፈፀም መቅረቱ የፍርድ ባለመብትን  መብትና ጥቅም የሚሳጣ በመሆኑ ነዉ፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ በፍርድ ማስፈፀም ሂደት ሀብትና ንብረት ስለማስከበር እና ስለማይከበሩና በፍርድ ምክንያት ስለማይወሰዱ ሀብትና ንብረቶች እንመለከታለን፡፡ በፍርድ ማስፈፀም ሂደት ሀብትና ንብረት ስለማስከበር ፍርድ የተፈረደበት ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 386 እንደተደነገገዉ እንደ ፍርዱ የማይፈፀምበትን ምክንያት ካላስረዳ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 386 እና 392(1) መሠረት ፍርዱ እንዲፈፀም ወዲያዉኑ ትዕዘዝ ይሰጣል፡፡ ፍርድ የሚፈፀመዉ የፍርድ ባለዕዳዉን ንብረት በማስከበርና በመሸጥ ነዉ፡፡ የፍርድ ባለመብቱም በዚህ አኳኋን ይፈፀምለት ዘንድ ከፍርዱ በፊት ያሳገደዉንም ሆነ ለፍርድ አፈፃፀም ሊዉል ይችላል የሚለዉን የፍርድ ባለዕዳ ሀብትና ንብረት ዝርዝር ያቀርባል፡፡ በፍርድ አፈፃፀም ሂደት መጓተት እንዳያስከትል እንዲያዝና እንዲሸጥ ተብሎ የቀረበዉ የንብረት ዝርዝር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 404 ከተመለከቱት ዉጭ መሆናቸዉንና በእርግጥም በፍርድ ባለዕዳዉ ባለቤትነት የሚገኙ ስለመሆናቸዉ በሚቻለዉ መንገድ ሁሉ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ በፍርድ አፈፃፀም ምክንያት ንብረት እንዲያዝና እንዲከበር የማድረጉ ተግባር አፈፃፀሙን በያዘዉ ፍርድ ቤት ብቻ ሳይሆን በሌሎች ፍርድ ቤቶችም ተይዞ እና ተከብሮ የተገኘ እንደሆነ ጉዳዩ በምን አኳኋን እንደሚታይ በፍ/ብ /ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 413 ተደንግጓል፡፡ ይኸዉም "… ንብረቱ የተያዘዉ በፍርድ ቤት የሆነ እንደሆነ ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ይህንኑ ንብረት አስቀድመን አስይዘናል፣ አስረክበናል በማለት የቀዳሚነት መብት አለን በማለት ክርክር ያነሱ እንደሆነ ክርክሩ የሚወሰነዉ ንብረቱን ይዞ በሚገኘዉ ፍርድ ቤት ነዉ፡፡" የሚል ነዉ፡፡ አንድ ንብረት አስቀድሞ በፍርድ ቤት በመከበሩ ምክንያት የተፈረደ ፍርድ ሳይፈፀም ይቀራል ማለት እንዳልሆነ ይኸዉ ድንጋጌ አስረጅ ቢሆንም ክርክሩ በየትኛዉ ፍርድ ቤት ይታያል ለሚለዉ ግን ሁሉንም ጉዳይ የሸፈነ አይደለም፡፡ በመጀመሪያ ንብረቱን የያዘዉ የከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ሆኖ በተለያየ ምክንያት አፈፃፀሙ በመጓተቱ የተነሣ በወረዳዉ ፍርድ ቤት ዉሳኔ መሠረት እንዲፈፀም የተከበረ መሆኑ ቢታወቅ እንደ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 413 ድንጋጌ ይዘት በባለገንዘቦች መካከል የሚነሳዉ የቀዳሚነት መብት ክርክር በወረዳዉ ፍርድ ቤት ይታያል እንደ ማለት ነዉ፡፡ በእርግጥ ይህ ዓይነቱ ክርክር እንዳይከሰት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378 ( 3 ) ( መ ) መሠረት አፈፃፀሙን ለከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ቢመራዉ የተመረጠ ይሆናል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ድንጋጌዉ ቀጥተኛ ምላሽ አይሰጥም፡፡ ፍርድ ቤቶቹ አቻ ከሆኑ ችግር የሚያስከትል መስሎ አይታይም፡፡ ላይና ታች ከሆኑ ግን ድንጋጌዉ ትርጉም ያሻዋል፡፡ ይኸዉ ድንጋጌ የተወሰደዉ ከህንድ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 63 እንደሆነ ከይዘቱ መረዳት ይቻላል፡፡ በዚሁ የህግ ድንጋጌ የአቻነት ሥልጣን ባላቸዉ ፍርድ ቤቶች ንብረቱ ተከብሮ በሚገኝበት ጊዜ ቀድሞ ንብረቱን ባስከበረዉ ፍርድ ቤት የሥልጣን ደረጃቸዉ እኩል ባልሆነ ፍርድ ቤቶች ንብረቱ ተከብሮ በሚገኝበት ጊዜ ደግሞ ሥልጣኑ ከሁሉም ከፍ ብሎ በሚገኘዉ ፍርድ ቤት ክርክራቸዉ ታይቶ እንደሚወሰን ተመልክቷ፡፡ ስለማይከበሩና በፍርድ ምክንያት ስለማይወሰዱ ሀብትና ንብረቶች ፍርድን ለማስፈፀም ሲባል የማይከበሩና በፍርድ አፈፃፀም ምክንያት ሊወሰዱ ስለማይችሉ ንብረቶች ዓይነትና መጠን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 404 ስር ተዘርዝሯል ከሚከተሉት ሁለቱን ንዑስ አንቀጾች በስተቀር ድንጋጌው በራሱ ግልጽ በመሆኑ ማብራሪያ የሚያስፈልገው አይመስልም፡፤  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 404 (ለ) “ለዕለት ሞያ ስራዎቹ አገልግሎት ለንግድ ስራው ማከናወኛ ተገቢ የሆኑ ዕቃዎች ከሚለው ድንጋጌ “ዕቃዎች“ የሚለው ቃል ሰፊ ትርጉም ሊየሰጥ በሚችል አኳኋን ይጠቀስ እንጂ የዚሁ ግልባጭ ከሆነው የአገልግሎት ንባብ ጋር አጣቅሰን ካየነው ተገቢ የሆኑ የመገልገያ መሳሪያዎች ለማለት ተፈልጎ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 404 ንዑስ ፊደል (ሠ) “ለጡረታው የሚከፈለው ገንዘብ….“ የሚለውን ድንጋጌ ስለ ጡረታ ጉዳይ ከደነገገው የጡረታ ህግ አዋጅ ቁጥር 1267/14 አንቀጽ 51 ጋር ተገናዝቦ ሊታይ የሚገባው ነው፡፡ ለጡረታው የሚከፈለው ገንዘብ እንደማይከበር በፍርድ አፈፃፀም ምክንያት እንዳይያዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 404 የተገለፀ ቢሆንም በመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1267/14 አንቀጽ 51 ላይ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡ ይኸውም በአንቀጽ 51 ከጡረታ አባል እንዲከፈል የተጠየቀው ዕዳ ለመንግስት ገቢ የሚሆን መቀጮ፣ ግብር ወይም ቀረጥ ለመክፈል ወይም አግባብ ባላቸው የፍትሐብሔር ድንጋጌዎች መሰረት የተወሰነ ቀልብ የመስጠት ግዴታ ለመወጣት በፍ/ቤት የታዘዘ እንደሆነ የጡረታ አባሉ ሊከበር እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ የጡረታ አበል በዕዳ ምክንያት ሊከበርና ሊያዝ የሚችል የመሆኑና የአለመሆኑ ጉዳይ በተለያዩ ህጎች በተለያዩ ሁኔታ ተደንግጎ ከተገኘ በህግ አተረጓጎም ዘዴ መሰረት ስለ ጡረታ ጉዳይ በተለይ የሚደነግገው የጡረታ አዋጅ በመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ ይልቅ ተፈፃሚነት ሊኖረው የሚችል ከመሆኑም በላይ በኋላ የወጣ እንደመሆኑ ተፈፃሚነት የሚኖረው ይኸው የጡረታ ህግ ነው፡፡ (the latest prevails over the previous) ወደሚለው መደምደሚያ ሊያደርሰን ይችላል፡፡ የጡረታ አበል በፍርድ ምክንያት ሊያዝ አይገባውም የተባለው መተዳደሪያው በመሆኑ ነው፡፡ ለመተዳደሪያው ሲል ለህይወቱ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማግኘት ሲል በመጣው ዕዳ ምክንያት ፍርድ አርፎበት ከተገኘ ይህንኑ ዕዳ ለማስፈፀም የጡረታ አበልን ማስከበር ምን ይከለክላል? የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 404 (ሠ) ድንጋጌ ይህን ጉዳይ ሊሸፍን የሚችል አይደለም የሚል ክርክር ሊነሳ ይችላል፡፡ በተለይም ይህንን ጥያቄ ለአብነት ያህል ከተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ አዋጁ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 205 (3) ለቀለብ ተቀባዩ ኑሮ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ለማግኘት ሲባል የወጣ ዕዳ መሆኑ ከተረጋገጠ የቀለብ ገንዘብ ሊተላለፍና ሊያዝ እንደሚችል ከተደነገገው ጋር ተገናዝቦ ከታየ የቀለብ ገንዘብ ማለት ለጡረታ የሚከፈል ገንዘብ እስከሆነ ድረስ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 404 (ሠ) ገዳቢ የሆነ ድንጋጌ መስሎ አይታይም፡፡ በአጠቃላይ በፍትሐብሔር ጉዳይ ክስ መስርቶ እንደመከራከር ሁሉ የከሳሽ ለፍርድ አፈፃፀም የሚሆን ሀብትና ንብረት በፍርድ ቤት ማሳገድ የፍርድ አፈፃፀሙን የተሳለጠ ያደርገዋል፡፡ https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss
Show all...
👍 2 1
በወንጀል አለመቀጣት ከውል ውጪ ኃላፊነት ይርጋን ያስቀረዋልን? በከውል ውጪ ኃላፊነት ህግ ተበዳይ የሆነ ሰው ክስ ማቅረብ ሚችለው ካሳ የሚጠይቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ ሁለት አመት ድረስ እንደሆነ በፍ/ህ/ቁ 2143(1) ላይ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ጉዳቱ በወንጀልም ጭምር የሚያስቀጣ ሆኖ የይርጋ ዘመኑ ርዝመት የበለጠ እንደሆነ የካሳው ጉዳት ክስ የይርጋ ዘመን ልክ በወንጀሉ መሰረት እንደሚሆን ተገልጧል፡፡ታዲያ አንድ በከውል ውጪ ኃላፊነት ህግ መሠረት ጉዳት ያደረሰ ሰው ያደረሰው ጉዳት በወንጀልም ጭምር የሚያስቀጣ ሲሆን እና ጉዳት አድራሹ በወንጀል ባይቀጣ በአንቀፅ 2143(2) ስር የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚነት አይኖረውም?የሚለው ጉዳይ የቀረበለት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 11 በሰ/መ/ቁ 58920 ላይ የከውል ውጪ ኃላፊነቱ ድርጊት ወይም ጉዳት በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የየይርጋ ዘመኑ ርዝመት በወንጀል ህጉ በተደነገገው መሠረት እንደሚሆን የተደነገገው የሚያስገነዝበው ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑ ከሚታይ በቀር የድርጊቱ ፈፃሚ ተከሶ መቀጣት እግምት ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡በመሆኑም በወንጀል አልተከሰስኩም ወይም አልተቀጣሁም በማለት የሚቀርበው መከራከሪያ ተቀባይነት ያለው መከራከሪያ አይደለም ሲል ትረጉም ሰጥቶበታል፡፡ https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss
Show all...
በወንጀል አለመቀጣት ከውል ውጪ ኃላፊነት ይርጋን ያስቀረዋልን? በከውል ውጪ ኃላፊነት ህግ ተበዳይ የሆነ ሰው ክስ ማቅረብ ሚችለው ካሳ የሚጠይቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ ሁለት አመት ድረስ እንደሆነ በፍ/ህ/ቁ 2143(1) ላይ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ጉዳቱ በወንጀልም ጭምር የሚያስቀጣ ሆኖ የይርጋ ዘመኑ ርዝመት የበለጠ እንደሆነ የካሳው ጉዳት ክስ የይርጋ ዘመን ልክ በወንጀሉ መሰረት እንደሚሆን ተገልጧል፡፡ታዲያ አንድ በከውል ውጪ ኃላፊነት ህግ መሠረት ጉዳት ያደረሰ ሰው ያደረሰው ጉዳት በወንጀልም ጭምር የሚያስቀጣ ሲሆን እና ጉዳት አድራሹ በወንጀል ባይቀጣ በአንቀፅ 2143(2) ስር የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚነት አይኖረውም?የሚለው ጉዳይ የቀረበለት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 11 በሰ/መ/ቁ 58920 ላይ የከውል ውጪ ኃላፊነቱ ድርጊት ወይም ጉዳት በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የየይርጋ ዘመኑ ርዝመት በወንጀል ህጉ በተደነገገው መሠረት እንደሚሆን የተደነገገው የሚያስገነዝበው ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑ ከሚታይ በቀር የድርጊቱ ፈፃሚ ተከሶ መቀጣት እግምት ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡በመሆኑም በወንጀል አልተከሰስኩም ወይም አልተቀጣሁም በማለት የሚቀርበው መከራከሪያ ተቀባይነት ያለው መከራከሪያ አይደለም ሲል ትረጉም ሰጥቶበታል፡፡
Show all...
Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

@lawyerhenoktaye (LL.B LL.M) 0953758395 ☎️ Youtube👇

https://youtu.be/5cnK4gX2Mrg

Tiktok👇

https://www.tiktok.com/@lawyer_henok.t?_t=8iQ7AEnkz4v&_r=1

Facebook 👇

https://www.facebook.com/profile.php?id=100071372553654&mibextid=ZbWKwL

ተጋቢዎች በፍርድ ቤት ባልፀደቀ የስምምነት ፍቺ ተለያይተው ይኖሩ በነበረበት ወቅት የሚያፈሩትን ንብረት ውጤት አስመክቶ የተሰጠ ውሳኔ.pdf 👇👇👇👇 https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss https://t.me/aboutlawsss
Show all...
ተጋቢዎች_በፍርድ_ቤት_ባልፀደቀ_የስምምነት_ፍቺ_ተለያይተው_ይኖሩ_በነበረበት_ወቅት_የሚያፈሩትን_ንብረት.pdf9.13 KB
👍 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.