cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሐድረተል ሐበሻ 💚📖 📚 📖 💚(حضرة الحبشة)

የሐገራችን ቆየት ያሉ እና የቅርብ ጊዜያትን በታላላቅ መሻይሆቻችን ረሱላችንን ያወደሱባቸው # ሀድራዎችን # መንዙማዎች # ተውሰላቶችን # እንጉርጉሮዎችን # ራምሳ #ተራ መንዙማዎችን በድምፅ እና በፅሁፍ የተዘጋጁ የሀድራ እና የተውሒድ ኪታቦችን በዚህ ቻናል ያገኛሉ #https://youtube.com/channel/UCEFBnUIsYzzj_6t7c2Bj5mw#

Show more
Advertising posts
236
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አላህ ከሰጠን ኒዕማ መሀከል መርሳት ነው። የሰው ልጅ ማይረሳ ቢሆን ከ10 አመት በፊት የተፈጠረው እያሰብን ደስታ ከፊታችን ይጠፋ ነበር ህይወታችንም አጭር ይሆናል። ስለሁሉም ነገር አልሀምዱሊላ🥰🤲🤲
Show all...
👍 2
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ እደናችሁ ጀሚአን
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ሶለሏሁ ዓለይሂ ወአሊሂ ወሰለም إِنَّمَا مَثَّلُوا صِفَاتِكَ لِلنَّاسِ كَمَا مَثَّلَ النُّجُومَ الْمَاءُ أَنْتَ مِصْبَاحُ كُلِّ فَضْلٍ فَمَا تَصْدُر ُ إِلاَّعَنْ ضَوْئِكَ الأَضْواءُ لَكَ ذَاتُ الْعُلُومِ مِنْ عَالِمِ الْغَيْبِ وَمِنْهََا لآدَمَ الأَسْمَاءُ الهم صلى وسلم علا وسيدينا ونبينا وحبيبنا محمد 💚💚💚
Show all...
#ተሰናዳሁና   ሀሳቤ: ምኞቴ: ፍቅሬ: ህይወቴ አንቱ ኖት ያረሱለላህ  በቻልኩት ሁሉ ልቤን ለርሷ ከፈትኩ ናፈቁኝ: አሰኙኝ: ፃፍኩኝ: ገጠምኩኝ: አለቀስኩኝ: አዜምኩኝ ግን ይበርዳል ስል ባሰብኝ ቅጥ አሳጣኝ አንቱን ብቻ አስባለሁኝ እንቅልፍ አጣሁኝ ለሊቱን ወዳንቱ ነጓድኩኝ መራቧትን ድንጋይ ማሰረዎትን ስሰማ አቃተኝ ትንሽም ቢገባኝ ብዬ ዘውትር ፆምኩኝ ግን ጨመረ እንጂ አልቀነሰም ከእንግዲህስ በቃ በናፍቆት አልባዝንም ብዬ ሻንጣዬን አዘጋጀሁ ልሄድ ተሰናዳሁ "ሀቢቢ መጣሁኝ የሄደው ቀልቤ አሁን በጀሰዴ" ስል ስንኝ ቆጠርኩ ግን መሄድ አቃተኝ ገናነህ ተባልኩኝ ሳይሳካ ቀረ ሻንጣዬም ከነገ ዛሬ እያለ እንደተዘጋጀ አለ። በአንደበቴ ብቻ ሳይሆን ሀያቴን ሙሉ በአንቱ መንገድ ለመሄድ ተሰናድቻለሁ ፍቀዱልኝ ሰይዲ ከሀድራችሁ አስገቡኝ ከወዳጆቻችሁ አድርጉኝ።        <የንፋሱ_ፖስታ> አላሁመ ሷሊ በዘይኔ ሙሀመድ: በከውኑ ሞገስ ላይ ዳኢመል አበድ: ተሰናዳሁና ወዳንቱ ላቀና ጓዜን አዘጋጀው: ልቤ እንደሄደ ጀሰዴም አንቱን ፈልጎ ነው: ቀን ከሌት አይልም ሙሀባው ሲነሳ: ብቸኝነት አይወድ ልብን የሚያሰሳ: አንቱ የኸልቁ አይነታ ውሰዱኝ አንዳፍታ: ህመሜ ይሻርልኝ ላድርስሎት ሰላምታ።    ሀሳቤም ውጥኔ እቅዴም ህይወቴ: አንቱ ኖት ሀበቢ የኔ ማንነቴ: ባንቱ ነው የላቅኩት ባንቱ ነው ምከብረው: ባንቱ ነው ያለሁት ላንቱ ነው ምኖረው: ወንጀሌ ነው እንጂ እርሷማ ቅርቤ ኖት: ለኔ ብለው አይደል ናፍቀው ያለቀሱት: እንደው ይሄን ሳስብማ ያንገበግበኛል: ምሆነው ጠፍቷኝ ቅጡን ያሳጣኛል: ሰለዋት እያልኩኝ በእጅግ እጓዛለው: አንቱን በማወደስ ደስታን አገኛለው: ጌትዬ እንዳለው በዚክር ነውና ልብ የሚረጋው። ደግሞ ከወረቀት ብዕር አነሳለሁ: የናፍቆት ደብዳቤ ስሜት እከትባለሁ: ፍቅሬን መደሰቴን ሀዘኔን አሳፍራለሁ: እባክሁ ሰይዲ ጥሩኝ እሎታለሁ: ከመጨረሻው ላይ ሰለዋት አሰፍራለሁ: ከቤት እወጣና ዱኣ አደርጋለሁ: ጌትዬ ይሄንን መዲና ውሰድልኝ: እንደ ጀት እበርረህ ከቁባው ጣልልኝ: ከዛም እልካለሁ የናፍቆት ደብዳቤ በንፋሱ ፖስታ: አድርሰህው ይሆን ያንን ሁሉ ፖስታ? እንደው ሙሀባ እንጂ እርሷማ ሁሌም ይሰሙናል: ፖስታም አያስፈልግ ሰለዋት ያደርሰናል: ፍቅራችንን በዚህ ብንገልፅስ ብለናል። አንድ ነው ምኞቴ አንድ ነው አምሮቴ: ላንቱ እያደገደጉ መኖር ነው ሀያቴ: ካንቱ ጋር መሆን ነው የሰርክ ፍላጎቴ: ጥሩኝ ሰይዲ ከዛ ከሀድራችሁ ከአረንጓዴው ቁባ: እኔም በአደቡ ልዘለቅና ልግባ: ነፍሴም ቤተሰቤ ያለኝ የሚኖረኝ ይሁን ላንቱ ይገባ። *አላህ መዲናዬ ጋር ይውሰደን! የመዲናዋስ?
Show all...
#የሰይዲ_ኸድር_ቅዳሜ የአውሊያ ሙርሰሉ የሁሉ ጓደኛ: የኢልምና ኢማን የሀብት መገኛ: ሰይዲና ኸድር የምድሩ ሹመኛ: ባለ ሀይባ ናቸው ንጉስ ፈረሰኛ: ጀሊሉ አጠጥቷቸው የህይወትን ውሀ: በዱንያም አኺራ አወጣቸው ነጃና ፈለሀ: ጠብቀናል አንቱን አመታት በሙሉ: ከኢልምና ሀብት ሰጥተው እንዲያሞሉ: መቼም አዛኝ ኖት ለምስኪን ለደሀ: እኛንም ዘንድሮ አውጡን ፈለሀ: ሰላትና ሰላም በኸድር ኢማሙ: በሚወዱት ሁሉ በሚጠሩት ስሙ። *አላሁመ ሷሊ አላ ሰይዲና ኸድር!
Show all...
የምትወደውን ባል በሞት ያጣች ሴት ምን ያክል እንደምትጎዳና ምን አይነት ስሜት እንደሚስሰማት መገመት አይከብድም በዛ ላይ ልጆች ማሳደጉና የኑሮ ጫና መቋቋሙ እጅግ ፈታኝና ከባድ ነው ✍ሸባቦች አሏህ ፀጋውን የሰጣችሁ ወንድሞች እንዲህ አይነት እህቶችን ብታገቡ  ስብራታቸውን ለመጠገን ብትሞክሩ ልጆቻቸውን ብትንከባከቡ ከአሏህ ትልቅ ምንዳ ታገኛላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ
Show all...
ኢማም አሽ-ሻፊዒይ ሰይዳችንን ﷺ ሲያልቁ "አር'ሪሳላህ" ኪታባቸው ላይ  ከተጠቀሟቸው አገላለፆች ውስጥ አንዱ : «..በዲንም በዱንያም ምርጥ እድያን ያገኘንባት ግልፅም ሆነ ድብቅ ችሮታ በኛ ላይ አልዘወተረችም ልክ እንደዛውም መጥፎ የተባለ ነገር በዲንም በዱንያም ወይም በአንዳቸው ከኛ አልተመለሰም ሰይዳችን ሙሐመድ ﷺ የዛ ሰበብ ቢሆኑ እንጂ !  ወደ ኸይሯም መሪ ወደ ትክክለኛውም አመላካች ቢሆኑ እንጂ ! ከጥፋትም ሆነ ከቀናው ተቃራኒ ከሆኑ ክፉ መንገዶች ከልካይ ፤ ወደ መጥፋት ከሚያደርሱ ምክንያቶች ሁሉ አስጠንቃቂ ፤ በማስጠንቀቅና ቅኑን በማመላከት ደግሞ መካሪ ቢሆኑ እንጂ..!  የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸውም በቤተሰባቸውም ላይ ይስፈን..» «فلم تمس ﺑﻨﺎ ﻧﻌﻤﺔ ﻇﻬﺮﺕ ﻭﻻ ﺑﻄﻨﺖ، ﻧﻠﻨﺎ ﺑﻬﺎ ﺣﻈﺎ ﻓﻲ ﺩﻳﻦ ﻭﺩﻧﻴﺎ ﺃﻭ ﺩﻓﻊ ﺑﻬﺎ ﻋﻨﺎ ﻣﻜﺮﻭﻩ ﻓﻴﻬﻤﺎ، ﻭﻓﻲ ﻭاﺣﺪ ﻣﻨﻬﻤﺎ: ﺇﻻ ﻭﻣﺤﻤﺪ ﺻﻠﻰ اﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﺳﺒﺒﻬﺎ، اﻟﻘﺎﺋﺪ ﺇﻟﻰ ﺧﻴﺮﻫﺎ، ﻭاﻟﻬﺎﺩﻱ ﺇﻟﻰ ﺭﺷﺪﻫﺎ، اﻟﺬاﺋﺪ ﻋﻦ اﻟﻬﻠﻜﺔ ﻭﻣﻮاﺭﺩ اﻟﺴﻮء ﻓﻲ ﺧﻼﻑ اﻟﺮﺷﺪ، اﻟﻤﻨﺒﻪ ﻟﻷﺳﺒﺎﺏ اﻟﺘﻲ ﺗﻮﺭﺩ اﻟﻬﻠﻜﺔ، اﻟﻘﺎﺋﻢ ﺑﺎﻟﻨﺼﻴﺤﺔ ﻓﻲ اﻹﺭﺷﺎﺩ ﻭاﻹﻧﺬاﺭ ﻓﻴﻬﺎ. ﻓﺼﻠﻰ اﻟﻠﻪ ﻋﻠﻰ ﻣﺤﻤﺪ ﻭﻋﻠﻰ ﺁﻝ ﻣﺤﻤﺪ ﻛﻤﺎ ﺻﻠﻰ ﻋﻠﻰ ﺇﺑﺮاﻫﻴﻢ ﻭﺁﻝ ﺇﺑﺮاﻫﻴﻢ ﺇﻧﻪ ﺣﻤﻴﺪ ﻣﺠﻴﺪ» 📗 الرسالة : 13 የችሮታ የደስታችን ሁሉ ምንጫችን ናቸው .. ልባችን ውስጥ ፍቅራቸውን በማጎልበት እሳቸው ላይ ሰለዋት በማብዛት ከአላህ ለሚገኘው ስጦታ ተገቢ እንሁን☺️
Show all...
"መውደቅ ቀላል ነው: ትነሳለህ። አላህ ብቻ አይጣልህ።"   "ልብስ ስለቀየርክ ማንነትህ አይቀየርም: ልብህ እስካልፀዳ ድረስ።"             *ይሄን ጉዞ ትወደዋለህ ልብህን ይከፍታል ኩራትህን ምቀኝነትና ትቢእትህን ያራግፍልሀል ከደጁም ያደርስሀል። ና ወደ አላህ እንጓዝ! እንግዲያውስ             መልካም ኸሚስ ምሽት
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ምድርን ከረገጡ ሰማየ ሰማያትን ከወጡ ሁላ የበላይ በሆኑት ነቢይ ላይ ምርጡን የሰለዋት አባባል በማለት ሰለዋት አውርዱ ﷺ 🌹الصلاة الإبراهيميه 🌹 اللَّهُمَّ صلِّ عَلى مُحَمَّدٍ وَعَلَى ءالِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلى إِبْرَاهيمَ وعلى ءالِ إِبْرَاهيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلى مُحَمَّدٍ وعلى ءالِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهيمَ وعلى ءالِ إبْرَاهيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجيدٌ.
Show all...
አፍቃሪዎች ልቦቻቸው ከማራኪ ነገራቶች በተፈቃሪያቸው ይጠመዳል የኔ የፍቅር ነብይ😍😍😍😍 ቁጥር ስፍር የሌለው ሰላት እና ሰላም ቁንጅናቸው ቁንጅናን በበለጠው ውድ ነብይ ላይ ሳይቋረጥ ይውረድ ኸሚስ . . .🦋🦋🦋🦋🦋🦋 اللهم صلي وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.