cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ባይራ |Bayra

ዲጂታል መጽሔት (Digital Magazine) ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/ ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital ለማንኛውም አስተያየት ኢ-ሜይል [email protected]

Show more
Advertising posts
2 951
Subscribers
+124 hours
+147 days
+21630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጥንት ግብጻውያን ሃኪሞች በጥንታዊት ግብጽ ውስጥ ስለ ሃኪሞች መጀመሪያ የተጠቀሰው በ 3533 BC ነው። እሱም Sekhet’enanch, የተባለው ዋና ሃኪም ፈርኦን sahura ን ከ አፍንጫው ህመም ስለ መፈወሱ በሚያትት ጥቅል ላይ ነው። የታሪክ አባቱ ሄሮዶተስ ስለ ጥንታዊት ግብጽ ሃኪሞች የጻፈው ወደ እንግሊዘኛ ተመልሶ እንዲህ ነበር የሚለው። “The art of medicine is divided among them. Each physician applies himself to one disease only and not more. All places abound in physicians; some physicians are for the eye, others for the intestine, and others for the internal disorders. HERODOTUS ሄሮዶተስ ይህንን በተናገረበት ጊዜ ግብጽ በፔርሺያኖች ቁጥጥር ስር የሆነች እና የስልጣኔ ፀሐይዋ ወደ መካተቻዋ ተቃርባ የነበረችበት ወቅት ቢሆንም የጥንት ግብጻውያን የህክምና ጥበባቸው ምን ያህል የጎለበተ እንደንነበር አመላካች ነው። ከጽሑፉ ለመረዳት እንደሚቻለውም ግብጻውያኑ በዚያን ዘመን እንኳ ለአንድ በሽታ አይነት አንድ ሃኪም ብቻ ነበራቸው (ዛሬ ላይ ስፔሻሊስት ዶክተር እንደምንለው አይነት) ። የጥንታዊት ግብጽ ሃኪሞች እንደየደረሱበት ማዕረግ በተለያየ ስም ይጠራሉ። እነርሱም ’swnw’ (ordinary doctor); ’imyr swnw’ (overseer of doctors); ’wr swnw’ (chief of doctors); ’smsw swnw’ (eldest of doctors); and ’shd swnw’ (inspector of doctors). በጥንት ግብጽ ውስጥ ሃኪም ለመሆን የፈለገ ወንድም ሆነ ሴት ሳይለይ ጥበቡን መማር እና መሆን ይቻል እንደነበር የጽሑፍ ማስረጃዎች ይጠቁማሉ። ለሌሎች ዓለማት ባልተለመደ መልኩ ሴት በነጻነት የህክምናን ጥበብ መማር እና ሃኪም መሆን ትችል ነበር። እንደውም አንዳንድ ጽሑፎች እንደሚጠቁሙ ቁጥራቸው በዛ ያሉ የሴት ሃኪሞች፣ አዋላጆች እና ነርሶች ነበሯቸው። ሃውልቶች ላይ በተገኘ የጽሑፍ ማስረጃ መሰረትም “ሜራትፕታህ” የተባለችው በ 2700 BC ትኖር ነበር ተብላ የምትታሰበዋ ሴት ስሟ የሚታወቅ የመጀመሪዋ የሴት ሃኪም ናት። ነገር ግን በ 3000 BC በኔዝ ቤተመቅደስ (ታችኛው ግብጽ) ውስጥ የህክምና ትምህርት ቤት ታስተዳድር የነበረች ሴት ሃኪም እንደነበረች ጠቋሚ ማስረጃዎች አሉ። እንደ አለመታደል ሆኖ ግን ስሟ አይታወቅም። ለአብነት ያህል የጥንታዊት ግብጽን ህክምና ታሪክ ጠቀስን እንጂ በዚህ የምትታወቀው ግብጽ ብቻ ናት ማለት አይደለም። በዘመናቸው በህክምና ጥበብ ተራቅቀው የነበሩ ህዝቦች የሚገኙባቸው ሌሎች ጥንታውያን ስልጣኔዎችም ነበሩ። ጥቂቶቹን ለመግለጽ ያህል፦ ከ 10,000 ዓመታት በፊት የመጀመሪያው የሰው ልጅ ከተማ እንደተመሰረተባት የሚነገርላት፣ በኤፍራጠስ እና ጤግሮስ ወንዞች መካከል ስልጣኔዋ ያበበው ሚሶፖታምያም በዘመኗ የነበራት የህክምና ጥበብ እጹብ የሚያስብል ነበር። ምንም እንኳን ሄሮዶተስ ሜሶፖታምያ በህክምናው ረገድ ያልተደራጀች፣ ሃኪሞች የሌሏት እና ታካሚዎቿም አምላክ ይፍታችሁ ተብለው ሜዳ ላይ እንደሚጣሉ እንዲህ በማለት:- “They have no physicians, but when a man is ill they lay him in the public square, and the passers-by come up to him and, if they have ever had his disease or have known anyone who has suffered from it, they give him advice, recommending him to do whatever they found good in their own case or in the case known to them. And no one is allowed to pass the sick man in silence, but everyone must ask him what ails him.” ቢያትትም ዛሬ ላይ በቁፋሮ ከተገኙ የጡብ ሰሌዳ ላይ ጽሑፎች ለመረዳት እንደተቻለው ሚሶፖታምያም በዘመኗ በእጅጉ ያደገ እና የተራቀቀ ሊባል የሚችል የህክምና ጥበብ እንደነበራት አመላካች ነው። ለምሳሌም ያህል ከጡቦቹ ላይ ከተሰበሰቡት የመድሃኒት ዝርዝሮች 250 የሚሆኑ ከእጽዋት የተቀመሙ መድሃኒቶች፣ 120 ያህል ከተለያዩ ማዕድናት፣ ከአልኮላማ መጠጦች፣ ከስብ እና ዘይት፣ ከእንስሳት ተዋጽኦ፣ ከማር የሚቀመሙ እንደሆነ ያትታል። ከሜሶፖታምያ በተጨማሪ ህንድም በባህላዊ ህክምና ጥበቧ የምትታወቅ ሃገር ናት። ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 8 የተቀነጨበ፡፡ የተዘነጋው ታሪካችን ክፍል 3 (በልዑልሰገድ አስማማው) በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ! ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/ ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ ኢ-ሜይል- [email protected] ኑኒ ባይራክ! ታላላቆች ነን!
Show all...
ባይራ |Bayra

ዲጂታል መጽሔት (Digital Magazine) ድረገጽ (Website)-

https://bayradigital.com/

ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) -

https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ኢ-ሜይል [email protected]

8👍 1
ሰማይ አራሽ ንጉሥ ከሳሽ - ብርሃኑ ድንቄ! በዙፋን ክፍሌ የስመ ጥሩ እንጦጦ ራጉኤልና ወጨጫ ማርያም አለቃ ከነበሩት ሊቀ ጠበብት ድንቄ ይወለዳሉ። ብርሃኑ ድንቄ! አለቃ ገብረሃና ዚቅና አቋቋም ያስተማሩበት መካን ነው- እንጦጦ ራጉኤል። ብርሃኑ ልጅ ሳለ እዚህችው የራጉኤል ሰማይ ስር ዓለም ድንበሯ ይመስለው ነበር። የዓለም ከፍተኛ ባለሥልጣንም በዚያን ወቅት የራጉኤል አለቃ የነበሩት ፀምሩ ይመስሉት ነበር። አንዱ የመስከረም 1 ቀን የራጉኤል ንግሥ የልጅ መስተኀልዩን (mind) ለአንዴና ለመጨረሻ ለወጠው። ለክብረ በዓሉ ልዑል ራስ ተፈሪ(በኋላ አጼ ኃይለሥላሴ) ተገኝተው ነበር። ያኔ ነው ብርሃኑ አለቃ ፀምሩን በሥልጣን የሚበልጥ አካል መኖሩን ያየው። በ'ለቱ እንደሌሎቹ ሳይሽቆጠቆጡ በኩራትና ልበ ሙሉነት ልዑል ራስ ተፈሪን ሲያወሩ የነበሩት አቶ ኅሩይ ወ/ሥላሴ (በኋላ ብላቴን ጌታ) ወደነ ብርሃኑ ቤት ተጋብዘው ይመጣሉ። ኅሩይ የሊቀ ጠበብት ድንቄ የቅኔ ትምህርት ቤት ጓደኛ ኖረዋል። ብርሃኑ በዚህ አጋጣሚ በኅሩይ ወልደሥላሴ ከተጻፉ መጻሕፍት ጋር ተገናኘ። እያለም የብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ያነብ ገባ። ደነቀው ለካ ዓለም ሰፊ ኖራለች! ኋላማ ምኑ ቅጡ?ፈረንሳይኛ አጠናና ከቮልቴይር ጋር ተገናኘ። እነሆ ንጉሥን እስከ መክሰስ ጥብዓት ያለው ድንቁ ብርሃኑ ድንቄ ያኔ ብቅ አለ። በ፯ ዓመቱ ዳዊት ፣ በ 12 ዓመቱ ድጓን ፉት ያላትና በነ ቮልቴይር ባሕር ማዶ መዝለቅ የጀመረው ብርሃኑ፤ በብርሃንና ሰላም ጋዜጣ የመጀመሪያ ጽሑፉን በማሳተም ነው እጅ የፈታው። በአምባሳደርነት ፣ በደራሲነትና ባለቅኔነት የምናውቀው ብርሃኑ ድንቄ በተደጋጋሚ ንጉሡ ስልጣናቸውን በሕግ እንዲገድቡ ፣ የሹሞቻቸውን ንቅዘትና ብልሹ አሰራር ቀርፈው ጊዜውን የሚመጥን አስተዳደር እንዲዘረጉ በደብዳቤ ጠይቋቸው "እምቢ!" ስላሉት ንጉሡን ከስሶና አውግዞ ስልጣኑን በመልቀቅ በአሜሪካ በስደት ተንከራቷል ፣ በንጉሡ የምስጢር ዘቦች ሊገደል እየተፈለገ መከራውን በልቷል። ከርሱ ተርፎ እናቱ በዕድሜያቸው ማምሻ ከገዛ ቤታቸው ወጥተው መንገድ ለመንገድ ፍዳቸውን ጠግበዋል። የወንድ ልጅ እናት! ብርሃኑ ለአገር ከዋለው ብዙ ውለታ ጎን ለጎን ፤ "አልቦ ዘመድ" ፣ "አረሩ" "ኤርትራዊው አስገዶም" ፣ "ቄሳርና አብዮት " ፣ "የአዜብ ንግሥት " ፣ "የኢትዮጵያ አጭር ታሪክ" ፣ "I stand alone" እና ሌሎች ልቦለድና ኢልቦለድ መጻሕፍትን ትቶልናል። ሁሉም እንዲነበቡ ፣ እንዲደገሙ ፣ እንዲሰለሱና እንዲመረመሩ አጥብቄ በመሻት ወደ አልቦ ዘመድ እንለፍ። (ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 8 የተቀነጨበ፡፡ ሙሉውን የቴሌግራም ገጻችንን በመቀላቀል በነጻ ያንብቡ) ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/ ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ ኢ-ሜይል- [email protected] ኑኒ ባይራክ! ታላላቆች ነን!
Show all...
ባይራ |Bayra

ዲጂታል መጽሔት (Digital Magazine) ድረገጽ (Website)-

https://bayradigital.com/

ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) -

https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ኢ-ሜይል [email protected]

2🔥 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ውድ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን! ዓመቱን የሰላም ያድርግልን! ኑኒ ባይራክ! ታላላቆች ነን!
Show all...
14👍 7
ባይራ ዲጂታል መጽሔት ባይራ ቅጽ 1 ቁጥር 8 በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ! ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/ ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ ኢ-ሜይል- [email protected] ኑኒ ባይራክ! ታላላቆች ነን!
Show all...
ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 8.pdf5.10 MB
23👍 6👏 3🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 8 ዛሬ ምሽት ይጠብቁን! stay tuned! በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ያገኙናል፡፡ ቴለግራም- https://t.me/Bayradigital ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/ ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) - https://x.com/home ለማንኛውም አስተያየት ኢ-ሜይል [email protected] ኑኒ ባይራክ! ታላላቆች ነን!
Show all...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
5
sticker.webp0.43 KB
ሠላም ጤና ይስጥልን ውድ የባይራ ቤተሰቦች እንደምን ከርማችኋል ። ባይራ ዲጂታል መፅሄት ቅፅ 1 ቁጥር 8 ነገ ይጠብቁን! stay tuned! ኑኒ ባይራክ! ታላላቆች ነን!! ከስር ባለው የቴሌግራም ቻናላችን እንዲሁ በህጋዊ ድህረገጻችን ወዳጅ ይሁኑ።mailto:[email protected] https://t.me/Bayradigital https://bayradigital.com/ https://x.com/BayraDigital
Show all...
ባይራ |Bayra

ዲጂታል መጽሔት (Digital Magazine) ድረገጽ (Website)-

https://bayradigital.com/

ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) -

https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ኢ-ሜይል [email protected]

👍 10
የሰርጓ ትዝታው ሩት ሃብተማርያም “እንዲያ ተሞሽሬ፣ አምሮብኝ ተውቤ አማረብሽ ሲለኝ፣ መላው ቤተሰቤ ዛሬም በዓይን 'ባይኔ፣ ይመጣል ትዝታው እንዴት እንደነበር፣ የሰርጌ ሁኔታው።” ይሄ የአስቴር ዘፈን ከወር በፊት አክስቴ ታማ ቤታችን ከመጣች በኋላ የምንሰማው የቤታችን መዝሙር የሆነ ዘፈን ነው። አክስቴ በሳሎናችን ጥግ ላይ ባለ ሶፋ ላይ ተኝታ ቀኑን ሙሉ ይሄን ሙዚቃ አጠገቧ በተቀመጠ የሙዚቃ ማጫወቻ ስታዘፍን ትውላለች። አስቴር በዘፈኗ ማገባደጃ ላይ “ሰርጌ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው” ስትል ምፅፅ እያለች ራሷን ትነቀንቃለች። ከዛ ዘፈኑን ትደግመዋለች። ይሄን ድርጊቷን ለብዙ ጊዜ አይቸዋለሁ። እዝን ትላለች። የለበሰችውን አርበ ሰፊ ጋቢ ጫፍ ጫፉን ጣቶቿ መሃል እያሽከረከረች ትቋጫለች። የተቋጨውን መላልሳ ትቋጫለች። ከመጣች ጀምሮ የምትደጋግማቸው ተግባራቶቿ፦ ለሰርጓ ድግስ የተቀረጸውን ቪዲዮ ክሊፕ ማየት ፣ የአስቴርን ' የሰርጌ ትዝታ' ዘፈን ማዳመጥ እና ያለማቋረጥ መክሳት ናቸው። በየቀኑ ነበር የምትከሳው። እኛ በየእለቱ የምናደርገውን መብላትና መጠጣት እንኳ እሷ በየቀኑ አታደርገውም ነበር። ምኗን እንዳመማት ግን አልነገሩኝም። የማውቀው ቢኖር ነገር በውበቷ የምትማርከኝ፣ ዘናጯ አክስቴ መታመሟን እና በአስቴር ፍቅር መለከፏን ብቻ ነው። የቤታችንን በሩን ከፍቼ ሳልጨርሰው እጄ ላይ እንዳለ አንገቴን በስተግራ አስረዝሜ ወደተጫችበት ጥግ አማትራለሁ። እንዲሁ ለማረጋገጥ እና ለምዶብኝ እንጂ ለስለስ ብሎ ሲንቆረቆር በሚሰማው የአስቴር ዘፈን ብቻ እቤት ውስጥ መኖሯንም ሆነ አለመተኛቷን አውቃለሁ። ልክ ስታየኝ ፈገግ እልላታለሁ። ፈገግ የምትልልኝ ይመስለኛል። ቀስ ብላ በእጇ ምልክት ትጠራኛለች። ለምን እንደምትጠራኝ አውቃለሁ። ፈጠን ብዬ በሩን መልሼ የሰርጓ ትዕይንት የተጫነበትን ካሴት ወደ ምስል ማጫወቻው አስገባና ከተኛችበት ሶፋ ስር እቀመጣለሁ። ቀስ ብላ ጸጉሬን ታሻሸኛለች። "አቡሽ" "እመት" ምን እንደምትነግረኝ የማውቀው ይመስለኛል። ሁሌ ይሄን ቪዲዮ ባየን ቁጥር ሰርጓ ላይ ከድንኳኑ ጫፍ እስከ ጫፍ ስላሉ ሰዎች ትነግረኛለች። ሁሉንም ታውቃቸዋለች። ስማቸውን ፣ እንዴት ሰርጉ ላይ እንደተጠሩ እና ያመጡትን ስጦታ ሳይቀር ታስታውሳለች። "እየው! እዛ የድንኳኑ ምሰሶ ጋ ያለው ሰውዬ ይታይሃል? እየጎረሰ እጁን ሰሃኑ ላይ የሚያራግፈው?" "አዎ" ሁለታችንም እኩል እያየነው እሷ ስትነግረኝ በጣም አተኩራለሁ። "እሱ ሰውዬ የዓለሜ አለቃ ነው። ዓለሜ ለሱፍ መግዣ ጎሎት ከእሱ ትንሽ ብር ተበድሮ፣ ጨምሮ ነበር የገዛው።" ዓለሜ የምትለው ባሏ ነው። ቅድም ከነገርኳችሁ ያጎደልኩት የእለት ተእለት ተግባሯ የእሱን ኮቴ በንቃት መከታተሏን ነው። ዓለሜ አክስቴ እኛ ጋር ታማ ከመጣች በኋላ ሁሌ ማታ ማታ ከስራ ሲወጣ እኛ ጋ ይመጣል። ረጅም ፣ ጺሙ የሞላ ፣ ኮስታራ ፣ ጠይም እና ረጋ ያለ ነው። በርግጥ ረጋ የማለቱ ሁኔታ በአክስቴ አጠገቡ መኖር እና አለመኖር ይወሰናል። አሁን ለምሳሌ እኔ ሰፈር ውስጥ ኳስ እየተጫወትኩ እሱ ደሞ ከስራ ሲመለስ ሳየው ረጋ ብሎ የሚራመድ ፤ ኮስታራነቱ እንኳን የማያውቁትን የሚያውቁትን የሚያሸሽ ነው። ከዚያ ከተል ብዬው ቤት ስገባ አክስቴ የተኛችበት ጋ እኔ እንደምቀመጠው ተቀምጦ ጸጉሩን ስታሻሸው አልያም ሲደንስላት ካልሆነ እንኳ በጣም በፍጥነት በውሎው ያደረገውን ሁሉ ሲናዘዝላት ደግሞ ቅብቅጥብጥ ነው። እሷ ጋ ረጋ አይልም። እንደሚለያዩ ታውቆት ነው የሚቸኩለው መሰለኝ? ግን በጣም ይዋደዳሉ። ሲገናኙ ከሌላ ሰው ቤት እየኖሩ ያሉ ወይም ሊታዘባቸው የሚችል ሰው ያለ አይመስላቸውም። ጸጉሯንም ገላዋንም የሚያጥባት እሱ ነው። ቀስና ለስለስ አድርጎ ያሻታል፤ ልክ እንደ አስቴር ዘፈን። ዓይኗን ፣ ጸጉሯን ፣ እግሯን ፣ ጉንጯን እና ሁሉንም ቦታዋን ይስማታል። (ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ አንድ ቁጥር 7 የተቀነጨበ) ሙሉውን የቴሌግራም ገጻችንን በመቀላቀል ወይም በድረ ገጻችን ላይ በነጻ ያንብቡ። ይራ ዲጂታል መጽሔት ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/ ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital ለማንኛውም አስተያየት እንዲሁም ጽሑፍ ለመላክ ኢ-ሜይል [email protected] ኑኒ ባይራክ! ታላላቆች ነን!
Show all...
ባይራ |Bayra

ዲጂታል መጽሔት (Digital Magazine) ድረገጽ (Website)-

https://bayradigital.com/

ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) -

https://x.com/BayraDigital

ለማንኛውም አስተያየት ኢ-ሜይል [email protected]

19👍 4🥰 2👏 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.