cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አማራ ፋኖ በሸዋ

Show more
Advertising posts
1 897
Subscribers
+124 hours
+207 days
+1130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሁለት ሞት በዳባት ፋኖዎቻችን በዳባት ከተማ ውስጥ በከተመ ጠላት ላይ በድንገት ዘነቡ፤ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ደግሞ ደባርቅ ከተማን ቀጨም በማድረግ ከጠላት አፅድተዋት ነበር። በደባት የሆነው ግን ሌላም አስገራሚ ነገር ነበረው… በዳባት የዘነቡት ፋኖዎቻችን በከተማዋ ውስጥ የነበሩትን የፋሽስቱን ስርዓት ኃይሎች ግንባር መብጣት ሲጀምሩ፣ በርካታ ሁለት የግራ እግር ሚሊሽያዎች ወደ አራዊት ሰራዊቱ ወታደራዊ ካምፕ ይፈረጥጡ ጀመር። ከተማው ውስጥ ከፀዳው አራዊት ሰራዊት የተረፈ ሰራዊት ካምፑ ውስጥ ነበር፤ ይህ ሰራዊትም ሽምጥ እየፈረጠጠ የመጣውን የሚሊሽያ መንጋ ወደ ካምፕ አላስገባም ብሎ አውላላ ሜዳ ላይ በተነው። ሁለት የግራ እግሩ ሚሊሽያ በአንድ ጫፍ ክህደት፣ በሌላ ጫፍ አፈሙዝ ከበበው። አፈሙዙ የፋኖዎቻችን ነበር። አንድ ሚሊሽያ አባት ከእነ 2 ሚሊሽያ ልጆቹ ጨምሮ፣ ከ60 በላይ ሚሊሽያ ግንባር ግንባሩን ተበጣ። አራዊት ሰራዊቱ በር ቢዘጋባቸውም፣ ምድር ግን ሆዷን ከፍታ ሆዳሞቹን ተቀበለቻቸው። የከዱን ፍጡራን ተከዱ፤ ሁለት ሞትም ሞቱ። የእነዚህ ሁለመና ሆዶች የመጨረሻዋ እስትንፋስ፣ ለህይወት ታሪክ ጻህፍት ፈተና ሆኖ አልፏል። ቻው!
Show all...
👍 6
በዱር በገደል በጫካ በዝናብ በውርጭ በበረሀ በፀሀዩ ላይ ያላችሁ የአማራ ሞት ,መፈናቀል, ሰደት ,ጭቆናው መታረዱ ,መደፈሩ መንከራተቱ ይበቃ ብላችሁ ከሞቀ ቤታችሁ ወጥታችሁ ታላቅ ተጋድሎ ,መሥዋዕትነት የምትከፋሉ ፋኖዎቻችን እንኳን አደረሳችሁ ይህ አመት ይህን ጨቋኝ ስረአት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የምንገረስስበት ይህን ታላቅ ህዝብ ወደ ቀድሞ ታላቅነቱ ክብሩ ከፍታው የምንመልስበት አመት ፈጣሪ ያድርግልን በግፍ የታረዱ ,በጅምላ የተገደሉትን ደም የምንመልስበት ያለቀሱትን አንገቱን የደፋውን አባታችንን ቀና እንዲል የእናታችንን እንባ የምናብስበት የድል አመት ይሁንልን .. በመጨረሻም በአገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ ይህን ቅዱስ ትግል የምትደግፉ ሁሉ እነሰኳን አደረሳችሁ ..በስደት በጭንቀት ያለህው ወገናችን አይዞን ልጆችህ እየደረስንልህ ነው..መልካም አዲስ አመት ይሁንልህ አማራው።
Show all...
👍 17
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ ከ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የተላለፈ የ2017 ዓ.ም የአዲስ ዓመት መልዕክት! *** በቅድሚያ በራሴ እና የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ሥም፡- ለመላው የአማራ ሕዝብ፤ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎና በጎንደር ላላችሁ ለጋራ ዓላማ፤ የጋራ መስዋዕትነት እየከፈልን ላላችሁ ወንድሞቻችን፤ የሕልውና ትግሉ የዲፕሎማሲ ግንባር ተሰላፊ ለሆነው የዲያስፖራ ወገናችን እንኳን ለአዲሱ ዓመት በጀግንነት አደረሳችሁ!! በመቀጠል፡- የአማራ ትግል ወዳጆች፣ በፋሽስቱ የብልጽግና አገዛዝ ጭቆናና ብዝበዛ ውስጥ ላለው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በፅናት አደረሰን፤ አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን አስተላልፋለሁ!! በድል የደመቅንበት 2016 ዓ.ም.፡- እጅግ ፈጣን የመደራጀት፣ የማጥቃትና የጠላትን ኃይል የመበተን አቅም የፈጠርንበት፣ የሕልውና ትግሉ በማይቀበለስ ደረጃ መድረሱ የተረጋገጠበት የድል ዓመት ነበር፡፡ ነፃ ቀጠናዎችን በማስፋት፣ የሕዝባዊ አስተዳደር ልምምዶችን ያሳደግንበት፤ ወታደራዊ፣ የመረጃና አስተዳደራዊ አቅሞችን የፈጠርንበት፤ የትግል ቅርጽና ይዘት ያለው አደረጃጀት እውን ያደረግንበት፤ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለማቀፉ ማኀበረሰብ ዘንድ የአማራ ትግል አጀንዳ የጎላበት፣ በጥቅሉ አማራ ታሪኩን ያደሰበት፣ ትውልዱም የራሱን ደማቅ ታሪክ በደምና አጥንቱ የፃፈበት ታሪካዊ የድል ዓመት ነበር፡፡ ዓመቱ ፋሽስም ወገቡ የተሰበረበት፤ ፋኖነት የአማራ መዳኛ መሆኑ የተረጋገጠበት ሆኗል፡፡ በተለይም የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ተተርከው የማያልቁ ብዙ ጀብዱ፤ እልፍ ገድሎችን ፈጽሟል፡፡ በሰፊ ቀጠና እየተንቀሳቀሰ በደምና አጥንቱ የማይሞት ታሪክ ሰርቷል፡፡ እጅግ አስደናቂ ጀብዱዎች የተፈፀሙባቸው በርካታ ዘመቻዎች በጋራ ታቅደው፤ በጋራ ተተግብረዋል፡፡ በዚህም የጠላት የሰው ኃይል ተራቁቶ ቀፎው ቀርቷል፡፡ በዓለማቀፍ የጦርነት ሕጎች መሠረት ምርኮኞችን በአግባቡ በመያዝ የሞራልና የሕግ ተገዥነታችንን ለዓለም አስመስክረናል፡፡ "አማራን ትጥቅ ብቻ ሳይሆን ቀበቶውንም እናስፈታዋለን" ያሉንን ትጥቃቸውን እያስፈታን፤ ፋሽስታዊ አስተሳብ የተሸከሙበትን አዕምሯቸውን እያጠብን የአማራነትን ልክ አሳይተናቸዋል፡፡"እናፀደዋለን" ያሉንን እየመነጠርን፤ ርቃናቸውን አስቀርተን በድል መራመዳችንን ቀጥለናል!! የትግሉ ባለቤት የሆነው የአማራ ሕዝብ ከአብራኩ ለተገኙ ፋኖ ልጆቹ፣ ስንቅና የመረጃ ምንጭ ሆኖ የተሳተፈበት በመሆኑ ዓመቱን በድል ደምቀን ለማሳለፍ አቅም ሆኖናል፡፡ በሌላ በኩል ዓመቱ የሕልውና ትግሉ አልጋ ባልጋ የሆነበት ሳይሆን የደም ዋጋ እየከፈልን የመጣንበት፤ በርካታ ወንድሞቻችንን የገበርንበት በመሆኑ አዲሱን ዓመት 2017 ዓ.ም. በጀግንነት ስንቀበል የጀግኖች ሰማዕታትን የትግል አደራ ከግብ ለማድረስ የትግል ቃል-ኪዳናችንን በማደስ ነው፡፡ አማራነት በጀግኖች ደም ደመቆና ተከብሮ ይኖራል! በትግላችን ውስጥ ያረጋገጥነው እውነት፣ አማራነት በእሳት ተፈትኖ ራሱን እንደንሥር አድሶ ከፍ ብሎ በመብረር ላይ ነው፡፡ ዛሬ የአማራ ሕዝብ አምጦ የወለደው ፋኖ የሕዝብ ልጅ ስለመሆኑ በተግባር ታይቷል፡፡ ፋሽስምን ብቻ ሳይሆን በፋሽስም ጥላ ስር ያሉ ሌባ፣ ቀማኛ፣ አጋችና ዘራፊዎችን በመቅጣት የሕዝብ ወገንተኝነቱን አሳይቷል፡፡ ያለፈው የትግል ዓመት፣ ፋኖ በአስተሳሰብና በተግባር ከአማራ ሕዝብ የተገኘ፤ ጠንካራ ማህበረሰባዊ ግንኙነት እና የትግል ሥነ-ምግባር ያለው እውነተኛ ታጋይ መሆኑን ያሳየበት የድል ዓመት ነበር፡፡ ይህ ያስጨነቀው ጠላት የትግል ስልቱን በመቀያየር የሕልውና ትግሉን የድጋፍ መሰረት ለመሸርሸር፤ ሕዝባችንን ለማማረር፤ የትግል ትኩረት አቅጣጫ ለማሳት፤… የተለያዩ የቀውስ ታክቲኮች፣ የተደራጁ ወንጀሎች፣ የሐሰት ፕሮፖጋንዳዎች፣ ከፋፋይ አጀንዳዎች ቢረጩም አማራ የብረት አጥር ሆኖ መክቶታል፡፡ በዚህ ድል ኩራት የሚሰማን ሆኖ፣ አሁንም ጠላት በባከነ ሰዓት በእኩይ ሴራዎቹ የቀጠለ በመሆኑ እንደአማራ በአዲሱ ዓመት የትግሉን ፍፃሜ ለማሳመር ኳሷን በአግባቡ መቆጣጠር፣ የመጨረሻውን ሳቅ ለመሳቅ ኳሷን የድል መረቡ ላይ ለማሳረፍ በብርቱ ጥንቃቄ ማጥቃት አለብን! የትግል ሜዳው ላይ ዋጋ እየከፈልን ያለነውን የአማራ ፋኖ መስዋትነት ማክበር የሚቻለው፣ የሕልውና ትግሉን ከጠላት ሴራ በመጠበቅ፤ አማራዊ የብረት አጥሩን በማጥበቅ ነው!! እንደአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ፣ በአዲሱ የትግል ዓመት አማራነት በፈተናዎች የሚፀና እንጂ የሚበተን ማንነት አንዳልሆነ ለወዳጅ ጠላት እናረጋግጣለን! ትግላችን የቱንም ያህል ፈታኝና መራራ ቢሆንም በሞት ሸለቆ ሳይታለፍ ታሪክ አይቀየርምና ለአማራ ሕዝብ ዘላቂ አሸናፊነት የማይተካ ሕይወታችንን ዋጋ እየከፈልን አዲሱን ዓመት ዘላቂ ድል የሚመጣበት የድል ዘመን እንደምናደርገው አንጠራጠርም፡፡ ለዚህም ‹አማራዊ ሕብረት፤ ለአማራ ሕልውና!› በሚል ከፍታችን አስጠብቀን በድል እንበራለን፡፡ በአዲሱ ዓመት 2017 ዓ.ም የሕልውና ትግሉ ዘመኑን ወደዋጀ ሁለገብ ትግል ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ለዚህም ከሥጋና የትግል ወንድሞቻችን ጋር በአንድነት በመቆም፣ በጋራ አመራር ስትራቴጂካዊ ድል እንደምናረጋግጥ እናበስራለን፡፡ በመጨረሻም፡- የአማራ ሕዝብ ትግል በፈተና የተሞላ፤ መራራና ዋጋ የሚከፈልበት እንደሆነ በመጣንበት የትግል መንገድ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን ዋጋ የምንከፍለው ለአማራ ሕልውና መረጋገጥ፤ አማራ አንገቱን ቀና አደርጎ እንዲሄድ፤ ለዘላቂ ጥቅሞቹ መከበር ነው፡፡ ፈተናና መከራው የቱንም ያህል ቢበረታ ድሉ አይቀሬ ነው፡፡ 2017 የትግል ዘመን የአማራ ሕዝብ የዘላቂ አሸናፊነትና የነጻነት ዓመት ይሆናል! አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ ጎንደር-አማራ-ኢትዮጵያ ጷግሜ 5/2016 ዓ.ም.
Show all...
👍 6
ሰበር ዜና! የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለ ጦር    በቅርቡ ወደ አማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ውስጥ የተካተተው በፋኖ ጥላሁን የሚመራው  ራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ ሻለቃወች ከአገዛዙ የብልፅግና ሰራዊት በሁለት ቦታ አንገት ለአንገት ተያይዞ ሲደመስሰው ውሏል። የመጀመረሚያው በመርሃቤቴ ወረዳ ገረን ቀበሌ ፋኖን እደመስሳለሁ በሚል የህልም ቅዠት ጨዋታ ወደ ቦታው ያመራው ወንበዴው ሰራዊት ያሰበበት ቦታ ሳይደርስ ልዩ ስሙ ቀርጫ ቀርጫ የሚባል ቦታ ላይ በአናብስቶቹ የፋኖ አባላት በደፈጣ ውጊያ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ብዛት ያለው የአገዛዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። ይህ ወንበዴ ሰራዊት በደረሰበት ክፉኛ ምት ብስጭት ውስጥ የገባው የአገዛዙ ሰራዊት ወደ ከተማው ሲመለሱ ምንም የማያውቁ  በየመንገዱ ያገኛቸውን ሲቪል ሰወች እየደበደበ እና በሰብል ጥበቃና በእንስሳት ጥበቃ ላይ የነበሩ ህፃናትን ማለትም የ10 አመት ሴት ልጅ የ11እና የ12አመት ወንድ ልጆችን   በጥይት በመምታት ሶስቱም ህፃናት በህክምና ላይ እንዳሉ ለማወቆ ችለናል። ሁለተኛው ሬሽን በመጫን ወደ መርሀቤቴ አለምከተማ ለመቀባበል ከለሚ የወረደ እና ከአለም ከተማ የወረደ የጠለት ሃይል በጀማ ድልድይ አቅራቢያ ወደ የጎፍ ለመሻገር ሲሞክር የነበረው የአገዛዙ ጥምር ጦር በክንደ ነበልባሎች የራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ የፋኖ አባለት በበርሲና ወንዝ ላይ ሙትና ቁስለኛ ሲሆን ሌላኛው እድል ቀንቶት ከፋኖ ጥይት ያመለጠው  የጠላት ሃይል እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ መጣበት ፈርጥጧል።    ይህ በእንዲህ እንዳለ ሽንፈቱን የተከናነበው የአገዛዙ ቡድን ጀማ በረሃ ላይ በግል ሰራ ተሰማርቶ ግሮሰሪ የሚሰራን ግለሰብ የፋኖ ሃብት ነው በማለት ለብዙ ጊዜ ሲሰራበት የነበረውን የግሮሰሪ እና ማለትም ፍሪጅ ብዛት 2፤ ጀነሬተር፤ ባዶ እና ያለበት የቢራ ካሳ፤ በዛት ያለቸው የምግብ ቤት ዕቃወችን ብረት ድስት እንጀራ እና ያልተጋገረ ሊጥ ጭልፋ ሳይቀር ጠራርጎ በመጫን ወደየመጣበት የሄደ ሲሆን ይህ ዘራፊ ሰራዊት የወንበዴነት  ተግባሩን በግልፅ ያሳየበት ዕለት ነው።                          ከሸዋ የትግል ሜዳ                        ጳጉሜ 3/2016ዓ.ም ክብር ለተሰውት    ሪፖርተር ግራ አዝማች ፈለቀ ታደሰ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር የሚዲያና ኮምንኬሽን ተጠሪ ክፍል
Show all...
👍 12
የደጋዳሞቱን ደፈጣ የሚያስታውስ ግዙፍ ኦፕሬሽን በጎንደር ምድር ላይ ተፈጽሟል። በሺህ የሚቆጠር የብርሐኑ ጁላ ጦር ወደ አዲሱ ዓመት ሳይሸጋገር ቀርቷል። ክብር ለጎንደር አማራ ፋኖ✊
Show all...
👍 4
00:59
Video unavailableShow in Telegram
ይህ ሰው ከስድቡ በላይ ቁምነገር ያወራል በእውነት ስሙት .. "ግብፅ ልትረን ነው ይላል ወረሞ ..እና እኛ አማሮች ምን አገባን " "..ትክክል ነው
Show all...
4.93 MB
👍 14
የ ሸዋ አማራ ሸዋ የ ንጉስ ሚኒሊክ የ ፕሮፌሰር አስራት ሀገር፡፡ሸዋ የ አክሊሉ ሀብተወልድ ሀገር ድንበር እና ካርታ ስሎ ኢትዮጵያን የ ፈጠረ ምጡቁ የ ሸዋ ህዝብ የ ራሱን መሪ ማዉጣት መቻል እንዴት አቃተዉ ፡፡ ሁሉም አማራ በ የሰፈሩ የ ራሱን መሪ ይዞ ሲወጣ ሸዋ ግን እራሱን በራሱ እንዳይቆም ለምን ተፈለገ ? ሸዋ ተሸካሚ፣መራጭ እንጂ ተመራጭ እንዳይሆን ለምን ተሰራበት ይህንን ሁሉ ስትመረምሩ የ ሸዋ አማራን ደግመን አናነግስም ከ ሸዋ አማራ ትግሬ ይግዛን ብለዉ አማራን አንገቱን አስደፍተዉ እነሱም መሬታቸዉን ተቀምተዉ ሲማቅቁ የኖሩት ወደጭንቅላቴ ይመጣሉ አሁንም በዚህ ህልዉና ትግል ዉስጥ የ ሸዋ አማራ ላይ ሴራ እየጎነጎኑ ያሉ እነኚህ ሆዳም ሀይሎች ናቸዉ፡፡ ሸዋ የ አማራ መዳኛ !!!
Show all...
👍 11
Photo unavailableShow in Telegram
ሼር ከደራ በረኸኞች ለአርበኛ ሽመልስ ንጉሴ(ዳግማዊ ምንሊክ ) እና ለቀስተንህብ ብርጌድ ጓዶቹ የተላለፈ ጥሪ                                      21''12''16 አ.ም     ወንድማችን በቅድሚያ እንደምን አለህ ?   ከከበረው ኑሮ ያስመነነህ የግፉአን ትግል እንዴት ይዞሃል ?           እኛ ደህና ነን አምክ ይመስገን።   ጠላት በወረረው ግዛት ከንደ ብርቱ ሆነን የገፋንን አረመኔ ስርዓት እንዳመጣጡ አየሸኘነው አለን ። ፈለጋቸውን ተከትላችሁ የወጣችሁህችለው የነ በፍቃዱ በላይ የነ ባልፈው አበይ የነ ማሙሽ ያዘው የነ ሽፈራው ደም  በወኔ ላይ ወኔ በድፍረት ላይ ድፍረት አስታጥቆን ሃሞታቸውን እንደውሃ ጠጥተን ከአላማችን ውልፍት ሳንል የዚህን መከረኛ ህዝብ እንባ በብረት ለማበስ ቆርጠን ተነስተናል ።  ትግሉንና የናንተን ናፍቆት እንኳን አታንሱት መንታ ናቸው ። ክንዳለም ሽሜ እኛማ ------ አምስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የቱቲ አውደ ውጊያ ላይ ሆነን ከወደ ወለቃ ተኩስ በሰማን ቁጥር ጀግናው ጦሩን ይዞ ከተተ እያልን ብናማትርም የለህም  ።   ነጋ ጠባ የናንተን  መምጣት እየጠበቅን እንገኛለን  ። አስችሏችሁ  ይሆን ? ወይስ የትግል ጓዶቻችሁ ወገኔ ተደፍሯል እንዝመትለት ስትለበቸው ለገሙ? ጀግኖቼ ቢሆን ይከተሏችሁ ታልሆነ ግን እናንተ ብቻ ኑ!    ተቃላችን ከወጣችሁ ብረቱን አምጡ ያሉ እንደሆን ወርውሩላቸውና ኑ ። በማይመስሏችሁ  ስብስብ ውስጥ በይሉኝታ ሰንሰለት ታጥራችሁ እሰከመቼ ? እኛ ወንድሞቻችሁ ከጠላት የማረክነው ክላሽ  ያጥር መገርገሪያ ሆኗል  ኑልን ።   ስትሏቸው ግን ★ በሉ ደህና ሁኑ እኛ ለወጣንለት ህዝብ ሄደናል ብንሰዋ ተሰዋልን የሚለን ህዝብ አለን ። ብንኖርም በርታ የምንለው ከአለት የፀና ወታደር አለን ።  ሳንኖር በስማችን ይዋጋሉ ስለዚህ አናስፈልጋቸዋለን በሏቸውና ኑ ቶሎ ክንዶቼ ።   እኔ አርማዬ ወለቃ ወንዝን ተሻግሬ እቀበልሃሁ ።  ጀግናው ስለሺ ደግሞ እንዳለህ★ [ ሽሜዋ ጓዶችህን ይዘህ ናልኝ ቀኝ እጄ ሌሎቹ የሽዋን ትግል የመሰረተችውን ደራን ረስተው ለይፋት ሆኗል የሚዋጉት ናና ጠላትን እንደቀድሟችን እንቅጣው ]  ብሎሃል ።    አርማዬ ነኝ ወለቃ ወንዝ ስር ።  💪
Show all...
👍 17
በእነዋሪው ውጊያ 387 የገዢው ቡድን ወታደሮች መገደላቸው ተገለፀ! የሞረትና ጅሩ ወረዳ ዋና መቀመጫ በሆነችው እነዋሪ ከተማ ላይ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ እስከ አመሻሹ በተደረገ ውጊያ በቁጥር 387 የገዢው ቡድን ወታደሮች ሲገደሉ ከዘጠኝ ተሽከርካሪ በላይ ቁስለኛ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝ በላከው መግለጫ አስታውቋል። የአገዛዙ ጦር የፋኖ አባላትን ገደልኩ በሚል ከባሕልና ከእሴት ባፈነገጠ መልኩ የሟቾችን አስከሬን አውራ ጎዳና ላይ እየጎተተ ተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረፅ በሚዲያ ማሰራጨቱ ይታወቃል። ለዚህ ምላሽ የሰጠው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ አገዛዙ የደረሰበትን ከባድ የሆነ የሰውና የንብረት ኪሳራን ለማካካስ በሚል በማሕበረሰቡ ላይ የግፍ በትሩን በጭካኔ እያሳረፈ ነው ያለ ሲሆን፡ ሰራዊታችንም ዘመቻ ሰማዕታት በማወጅ ይሄንን ወራሪ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ከባድ ትንቅንቅ እያደረገ ነው ብሏል። ነሐሴ 11/2016 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ እስከ አመሻሹ በተደረገ ውጊያ 336 የኮማንዶ አባላት፣ ሁለት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሦስት የፖሊስ አባላት፣ 48 ሚኒሻ፡ በድምሩ 387 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ ከዘጠኝ ተሽከርካሪ በላይ ቁስለኛ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ዕዙ በላከው መግለጫው ገልጿል። እኛ ብንወድቅ፣ ብንሰዋ እንኳን እልፍ ጠላት ይዘን ነው ሲል በመግለጫው የጠቀሰው ዕዙ፡ ስለዚህ ሕዝቡ በውጊያ በሚሰው ጀግኖች ስነ ልቦናው እንዳይጎዳና ማዘንም እንደለለበት አሳስቧል። ሰራዊታችን ከትናንት የተሻለ ቁመና ላይ የሚገኝ ሲሆን ለቀጣይ ግዳጅ የተዘጋጀ አስተማማኝ አቅም ያለው ነው ሲል የጠቀሰው መግለጫው፡ በማሕበረሰባችን ላይ የበቀል ዱላ ያነሳውን የገዢው ቡድን ወታደርን በዘመቻ ሰማዕታት አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ነው ብሏል። በመጨረሻም ዕዙ በመግለጫው፡ የሰማዕታቱን ሞት የግል ፖለቲካ ፍላጎታቸው ማሟያ ለማድረግ ከፋፋይ ሃሳቦችን ሚያናፍሱ አካላትን ተመልክተናል ያለ ሲሆን፡ እነዚህ ከፋፋይ ያላቸውና በሰማዕት ጓዶቻችን ነፍስ ላይ ቁማር ለመጫዎች ሙከራ እያደረጉ ነው ላላቸው አካላት በአስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
Show all...
👍 17👎 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.