cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ባለራዕዮች ቤተ-መጻሕፍት

-አስገራሚ ታሪኮችን -አስተማሪ መልዕክቶችን -አባባሎችን -ትረካዎችንና -በ PDF የተዘጋጁ መጽሐፍቶችእኛ ጋ ያገኛሉ Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100087196406622 Personal contact @samirebel Invite Link t.me/Bale_Raiyoch

Show more
Advertising posts
2 082
Subscribers
+224 hours
+337 days
+11730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"አለማወቅ መነሻ ነው። ማወቅ ባለማወቅ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ከማናውቀው ህይወት፣ ማንነት፣ ኑሮ፣ እውቀት ላይ በትንሽ በትንሹ እየቀነስን ነው የምናውቀው። ስለዚህ የማወቅ ፍላጎት እስካለህ ድረስ ብዙውን የራስህን ጥያቄ መመለስ ትችላለህ። ስለ አንተ ከአንተ በላይ፥ ማንም ሊያውቅ አይችልም" አለማወቅ ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ
Show all...
👍 9
 "የአብዛኛውን ማዕበረሰባችን የአኗኗር ዘይቤ ወረድ ብለን ብናይ ቁርጥ ሥጋ የሚሸጥባቸው ቤቶች ጠጠር መጣያ ቦታ አናገኝም፤ ድራፍት ቤት ብትሄድ ብርጭቆ ይዞ የሚሻማው ስፍር ቁጥር የለውም። ተመልሰህ ላይብረሪ ብትሄድ ቤቱ ባዶ ሆኖ ታገኘዋለህ! አውቶብስ ውስጥ ፣ ታክሲ ውስጥ፣ ወረፋ የሚጠበቅባቸው የአገልግሎት ቦታዎች ውስጥ ስንት ሰዎች ቁጭ ብለው እያነበቡ ነው? ብትል በጣም ጥቂት ሰዎች ነው የምታገኘው!! ... አብዛኛው ህብረተሰብ ልክ ነው ብሎ ድምዳሜ ላይ ከደረሰበት የተሳሳተ አስተሳሰብ ላይ ሥራ ካልሰራን አመለካከት ላይ ፈፅሞ ለውጥ አናመጣም። አብዛኛው ሰው ሆዱን አስቀድሟል፣ የሆድ መቅደም የአስተሳሰብ ድርቀትን ያመጣል። አዕምሮ መቅደም ሲገባው ሆድ ይቀድማል! ብዙ ነገርን ሊሞላልን የሚችለው የአዕምሮ መሙላት እንጂ የሆድ መሙላት አይደለም። የሆድ መሙላት ግሳት ነው.......ለመንቀሳቀስ ነው የሚያገለግለው! ለመኖር ነው የሚያገለግለው!! የአዕምሮ መሙላት ግን ብስለት ነው፣ እውቀት ነው፣ ልምድ ነው! የነገን ችግር የሚፈታበት አስተሳሰብ መቅረፅ ነው። የመጀመሪያው የተሳሳተ አመለካከትና የአብዛኛው የታዳጊ ሀገሮች ችግር ሆድን ማስቀደም ነው። መሰረታዊ ነገር ነው ይሉታል አንዳንድ ሰዎች። መሰረታዊ የሆነውን ሆድን ራሱ ለመሙላት መጀመሪያ መሰረታዊ ያልሆነውን አዕምሮ መሙላት ነው ብዬ አስባለው።" ዶ/ር ምህረት ደበበ
Show all...
🔥 8👍 4👏 1
Emotional Intelligence አንድ ሰው ምንም ያህል በአእምሮ ብልህነት ቢበስል የስሜት ብልህነት መጠኑ አናሳ ከሆነ በውስጡ ያለው እውቀትና ችሎታ የሚወጣበትና የሚገለጥበት “መስኮት” የለውም፡፡ ስሜት ሲወድቅ፣ ሲዘጋ፣ ሲዛባም ሆነ አላግባብ ሲገለጥ በአንድ ሰው ውስጥ ያለውን ብቃት የመጨቆን ወይም ደግሞ ተቀባይነት እንዳያገኝ የማድረግ ተጽእኖ አለው፡፡ ከዚህ እውነታ አንጻር ነው የስሜት ብልህነት በአእምሮ ብልህነት ላይ የበላይነት አለው የሚባለው፡፡ በሕይወታችን የሚገጥመንን ከባድ ጊዜ የምናልፈው በስሜት ብልህነት ልቆ በመገኘት ነው፡፡ ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
Show all...
👍 9 4
የእውቀት ብልጭታ @ETHIO_PDF_BOOK.pdf9.97 MB
ዶክተር ለራሴ.pdf71.60 MB
👍 5
ስህተትን ከመስራት ጋር ተያይዞ ያሉት ምርጫዎች አንደኛው ምርጫህ ራስህን ስህተት-የለሽ አስመስሎ በማቅረብ ከስህተት የመማርንና የይቅርታን ጣእም ሳታጣጥም ማለፍ ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ስህተትን በማመንና ይቅርታን በመጠየቅ ውስጥ የሚገኘውን ነጻነት መጎናጸፍ ነው፡፡ ምንም ስህተት እንደሌለበት የሚያስብ ሰው እንደዚያ በማሰቡ ሌላ ተጨማሪ ስህተት እየሰራ ነው፡፡ ከዚህ የከፋው ደግሞ በስህተቱ መዘዝ ውስጥ ራሱን ሲያገኘው የሰራውን ስህተት ላለማመን የሚታገል ሰው በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህኛው ስህተትን ካለማመን ምርጫ የተሻለው መንገድ ለሰራነው ስህተት ሃላፊነት በመውሰድና ይቅርታን በመጠየቅ ወደፊት መገስገስ ነው፡፡ ሁል ጊዜ ስህተትህን ከማመን ይልቅ የክህደትን ምርጫ የምትከተል ከሆንክ ለብዙ ጠንቆች ራስህን ታጋልጣለህ፡፡ በተጨማሪም ከስህተት ያለመማርና ስህተትን የመደጋገም እንቅፋት ይገጥምሃል፡፡ ይህ ደግሞ ራሱን የቻለ የስሜት እስረኛ ያደርግሃል፡፡ ዛሬ አንድን ያጠፋኸውን ሰው ሰው ይቅርታ ጠይቅና ነጻ ውጣ፡፡
Show all...
8👍 1
“ ሰዎች በልጅነት ጊዜ ይሰለቻቸዋል ለማደግ ይቸኩላሉ፤ ከዚያም እንደገና ልጅ ለመሆን ይናፍቃሉ። ስለ ወደፊቱ ጊዜ በጭንቀት ያስባሉ እና የአሁኑን ይረሳሉ። ስለዚህ በአሁንም ሆነ በወደፊቱ ውስጥ አይኖሩም፤ የማይሞቱ መስለው ይኖራሉ ያልኖሩም ሆነው ይሞታሉ።" ካህሊል ጂብራንን
Show all...
10👏 3
"በእርግጠኝነት አንድ ሰው ማንበብ ይችላል። ነገር ግን የሚያነበውን በጥንቃቄ ይምረጥ እና ያነበበውን በደንብ መረዳቱን ያረጋግጥ። ምክንያቱም በታተመ ቃል ውስጥ ምንም አደጋ የለም፤ ነገር ግን ቃላቶቹ ሊያስከትሉ በሚችሉ ሀሳቦች ውስጥ አደጋ አለ!" Lobsang Rampa!!
Show all...
8🔥 1
....አንድሪው ካርኒጌ ከስኮትላንድ ጠፍቶ ወደ አሜሪካ ሊመጣ አፍላ ወጣት ነበር፡፡ ዝቅተኛ ሥራዎችን በመሥራት የጀመረው የአሜሪካ ሕይወቱ አሁን በአሜሪካ ውስጥ ካሉት ግዙፍ ብረት አምራቾች ሁሉ ቁንጮ ለመሆን አብቅቶታል፡፡ በአንድ ወቅት አብረውት የሚሠሩ አርባ ሶስት ሚሊየነሮች ነበሩት፡፡ በአሁኑ ዘመን አንድ ሚሊየን ዶላር ብዙ ነው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ በ1920ዎቹ አንድ ሚሊየን ምን ያህል ብዙ ገንዘብ አንደነበር መገመት አይከብዳችሁም። ባንድ ወቅት አንድ ሰው ሚስተር ካርኒጌን ከስዎች ጋር እንዴት እንደሚግባባ ጠይቆት ያገኘው ምላሽ የሚከተለው ነበር፤ ከስዎች ጋር ተግባብቶ መሥራት ወርቅን ለማግኘት መሬት ከመቆፈር ጋር ይመሳሰላል። አንዲት ግራም ወርቅ ለማግኘት በሚልዮን ቶኖች ከብደት ያለው : አፈር ዝቀን እናወጣለን፡፡ ሆኖም የቁፋሮው ግብ ወርቁ እንጂ አፈሩ ስላልሆነ የአፈር ከምሩን ሳናስተውል ወርቁን ፍለጋ እንቀጥላለን፡፡" የአንድሪው ካርኒጌ ምላሽ ጠቃሚ መልዕክቶችን ያዘለ ነው፡፡ በሁሉም ሰው ላይ በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ በጐ ነገሮች አሉ - ጐልተው ስለማይታዩ አናስተውላቸውም እንጂ፡፡ ስለዚህ እነዚህ በጐ ነገሮች ጐልተው እስኪታዩን ድረስ ቁፋራችንን ማቆም አይገባንም፡፡ የእናንተስ ግብ ምንድነው? ወርቁን ማግኘት አይደለምን? ከሰዎች ስህተትን የምትፈልጉ ከሆነ የትየለሌ ስህተቶችን ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡ ግን እኮ ግባችሁ ወርቄን ማግኘት እንጂ የአፈር ከምሩን አይደለም፡፡ ስህተት ነቃሾች ከገነት ውስጥ እንኳን ስህተት እንደማያጡ መወራረድ እንችላለን፡፡ ደግሞም ማንኛውም ሰው መጨረሻ ላይ የሚያገኘው አጥብቆ የፈሰገውን፤ ትኩረት የሰጠውን ነገር ነው፡፡
Show all...
10👍 5
ያገዘፍከውና ያሳነስከው የዛሬዋ ሕይወት በትናንትናውና በነገው መካከል እንደ ሳንዱዊች የተጣበቀች ሂደት ነች፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሕይወት ገጽታዎች በዛሬው የሕይወትህ ሂደት ላይ ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከእነዚህ ሁለት ገጽታዎች መካከል ያገዘፈው ህይወትህን የማንቀሳቀስ አቅም አለው፡፡ የትናንትናውን ስታገዝፈው፣ የነገው ይደበዝዛል፤ የነገውን ስታገዝፈው ደግሞ የትናንትናው ይደበዝዛል፡፡ በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች መካከል የመወሰን መብቱም አቅሙም አለህ፡፡ ብዙ የተሳካላቸው ሰዎች የትናንትናውን ልምምዳቸው “መልካምም” ሆነ “መጥፎ” ያንን ሳይክዱና ፈጽመው ሳይጥሉት ነገር ግን ከትናንትናው ይልቅ የነጋቸውን በማግዘፍ እንደሚያምኑ ይናገራሉ፡፡ የትናንትናውን በማግዘፍና የነገውን በማግዘፍ መካከል መምረጥ ማለት በመቃብር ውስጥ ባለውና በመሕጸን ውስጥ ባለው መካከል እንደመምረጥ ነው፡፡ የትናንትናህ መቃብር ውስጥ ነው - ሞቷል! በተቃራኒው፣ የነገህ ደግሞ በማህጸን ውስጥ ነው - ሊወለድ ተዘጋጅቷል! የትኛውን ትመርጣለህ? ለየጥኛው ትኖራለህ? የትናውን ስታሰላስል ታሳልፋለህ? ወደየትኛው አቅጣጫ መሄድ ትፈልጋለህ? ያለፈው ታሪክ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ካለፈው ታሪክ ይልቅ የነገው ራእይህ ሲገዝፍ ሕይወት ወደፊት ትሄዳለች፡፡ ከመጣህበት ይልቅ የምትሄድበት ሲገዝፍ! ካለፈው ስቃይ ይልቅ ከዚያ በመማር የያዝከው የመለወጥ ሂደት ሲልቅ! ካለፈው ስኬት ይልቅ የነገው የላቀ ደረጃ ሲተልቅ! አስገራሚ ሕይወት!!! አስገራሚ የወደፊት!!! ዶ/ር እዮብ ማሞ
Show all...
👍 11
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.