cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Zeyne Seid (Official channels🇪🇹🇪🇹 )

🔖ይህ የወንድማችሁ Zeyne Seid ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ውስጥ ብዙ አይነት ትምህርቶችን ለማድረስ እሞክራላሁ ። ➜ ከዚህ ቻናል አንብባችሁ በተጠቀማችሁ ቁጥር፤ይህን ደካማ እና ስህተቱ ብዙ የሆነውን ወንድማችሁን በመልካም ዱዓችሁ አስታውሱት! ኢንሻአላህ ስህተቴን በቁርአን በሀዲስ ላረመኝ አላህ ይዘንለት እቀበላለሁ አድርሱኝ ። ለአስተያየት 👇👇👇👇 @zeynu_seid

Show more
Advertising posts
557
Subscribers
-324 hours
No data7 days
-930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሀሰን ቢን አረፍ እንዲህ ይላል "የዚድ ቢን ሀሩንን ዋሲጥ ላይ አየሁት ከሰዎች ሁሉ አይኑ ያማረ ነበር ከዚያም ሌላ ቀን አንድ አይኑ ጠፍቶ አየሁት ከዚያም ሌላ ቀን ደግሞ ሁለቱም አይኖቹ ጠፍተው አየሁት ። ከዛም የኻሊድ አባት ወይ የሚያምሩት አይኖችህ ምን ሆኑ? ብዬ ጠየቅኩት የለሊት ማልቀሴ አጠፍቸው።ብሎ መለሰልኝ  (ተዝኪረቱል ሁፍዝ 3/790) 👉አህመድ ቢን ኢስሀቀል ሀድረሚ እንዲህ ይላል ሳሊሀል መሪ እንዲህ ሲል ሰምቸዋለሁ "ለማልቀስ መድሀኒት አለው። እሱም ወንጀልህን ማስታወስ በዚህ ቀልብ እሺ ብላ ካለቀሰች ነው።ካልሆነ የቂያማ እለት የሚከሰተውን ከባባድ ክስተት አስታውሳት በዚህም ካላለቀሰች በእሳት መሀከል መገላበጥን አስታውሳት አለና ራሱ ማልቀስ ጀመረ (ሂልያ 6/168)
Show all...
👍 1
የወለድ አደጋዎች ~ ዘመናችን በርካታ የቂያማ ምልክቶች የሚታዩበት አስፈሪ ዘመን ነው። ከነዚህ ምልክቶች ውስጥ አንዱ የወለድ መንሰራፋት ነው። ወለድ በቁርኣን፣ በሐዲሥና በምሁራን ኢጅማዕ የተወገዘ እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው። ወንጀሉ ምንም እንኳን አደገኛ ቢሆንም ነገር ግን እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ ነው። ከጥፋቱ መስፋፋት በላይ ይበልጥ የሚያሳስበው በተለያዩ ስልቶች የሐላል ቀሚስ ሊያለብሱት አጉል የሚባዝኑ አካላት መኖራቸው ነው። የወለድን ጥፋት ማቃለል በእሳት መጫወት ነው። ለምን? 1. ወለድ ከሰባት ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ ነው። ነብዩ ﷺ “ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ” ይላሉ። “ምን ምን ናቸው እነሱ?” ሲባሉ፡- (الشرك بالله، والسحر، وقتل النفس التي حرّم اللَّهُ إلا بالحق، وأكل الربا، وأكل مال اليتيم، والتّولّي يوم الزّحف، وقذف المحصنات الغافلات المؤمنات) “በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ ጥብቅ ያደረጋት ነፍስ መግደል - በሐቅ ካልሆነ በስተቀር፣ ወለድን መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ በጦርነት ጊዜ መሸሽ፣ ጥብቅና (ከጥፋት) የዘነጉ አማኝ ሴቶችን በዝሙት መወንጀል።” [አቡኻሪይና ሙስሊም] ወለድ ከምን አይነት ወንጀሎች ጋር እንደተቆጠረ ተመልከቱ። 2. ወለድ እንኳን ለአኺራ ለዱንያም አይጠቅምም። ይሄውና አላህ ምን እንደሚል፡- {يَمْحَقُ اللَّهُ الرِّبا وَيُرْبِي الصَّدَقَاتِ} “አላህ አራጣን ያጠፋል። ምፅዋቶችንም ያስፋፋል።” [በቀራህ፡ 276] በየገጠሩ ገበሬውን ባዶውን ያስቀሩት የቁጠባ ተቋማት ናቸው። የወለድ ብድር ውስጥ ገብቶ እንስሶቹ እያለቁ፣ ሰብሉ እየጠፋ፣ ንግዱ እየከሰረ መቀመቅ የገባው እጅግ በርካታ ህዝብ ነው። ወላሂ በአራቱም የሃገሪቱ አቅጣጫዎች የወጣ ከዚህ ጋር የተያያዘ ብዙ ለቅሶ ይሰማል። መሬት ላይ ያለው እውነት በቲቪ እንደሚደሰኮረው አይደለም። ነብዩ ﷺ “አንድ ሰው ከወለድ አያበዛም ፍፃሜው መመናመን ቢሆን እንጂ” ይላሉ። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 5/120] 3. ያለ አስገዳጅ ሁኔታ ከወለድ ጋር የሚነካካ በሁሉም አቅጣጫ የተረገመ ነው። ጃቢር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- ((لعن رسول الله - صلى الله عليه وسلم -: آكل الربا، وموكله، وكاتبه، وشاهديه))، وقال: ((هم سواء)) “የአላህ መልእክተኛ ﷺ ወለድ የሚበላንም፣ የሚያበላውንም፣ ፀሐፊውንም፣ ምስክሮቹንም ተራግመዋል። ‘ሁሉም በወንጀሉ እኩል ናቸው!’ ብለዋል።” [ሙስሊም፡ 1598] “እኔ ቢቸግረኝ ወሰድኩ እንጂ አራጣ አበዳሪ አይደለሁም” ብለህ እንዳትሸወድ። ያለፈውን ሐዲሥ ተመልከት። በተጨማሪም ነብዩ ﷺ “ወሳጅም ሰጪም እኩል ናቸው” ማለታቸውን ያዝ። [ሙስሊም፡ 1584] ስለዚህ ሙስሊም የሆነ ሰው ሌላው ቀርቶ በወለድ ተቋማት ውስጥ ጥበቃና ፅዳት እንኳን ሊሰራ አይገባውም። 4. ወለድ ውስጥ የገባ ሰው ከአላህ ጋር ጦርነት ውስጥ ነው የገባው። አላህ እንዲህ ይላል፡- {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَذَرُوا مَا بَقِيَ مِنَ الرِّبا إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ * فَإِنْ لَمْ تَفْعَلُوا فَأْذَنُوا بِحَرْبٍ مِنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ} “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ። ከአራጣም የቀረውን ተው። አማኞች እንደሆናችሁ (ተጠንቀቁ።) (የታዘዛችሁትን) ባትሰሩም ከአላህና ከመልእክተኛው በሆነች ጦር (መወጋታችሁን) እወቁ።” [አልበቀራ፡ 278-279] ይቺ በነብዩ ﷺ ላይ መጨረሻ ላይ የወረደች አንቀፅ ነች ይላሉ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ። [አቡኻሪይ፡ 2086] 5. ወለድ የሚበላ ሰው ከቀብር የሚነሳው ልክ በጂን እንደተለከፈ ሰው እየተሳከረ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡- {الَّذِينَ يَأْكُلُونَ الرِّبَا لا يَقُومُونَ إِلَّا كَمَا يَقُومُ الَّذِي يَتَخَبَّطُهُ الشَّيْطَانُ مِنَ الْمَسِّ} “እነዚያ አራጣን የሚበሉ ያ ሰይጣን ከመንካቱ የተነሳ የሚጥለው ሰው (ከአውድቁ) እንደሚነሳ ብጤ እንጂ (ከመቃብራቸው) አይነሱም።” [አልበቀራ፡ 275] 6. ወለድ ምህረት የለሸ ወንጀል ነው። ነብዩ ﷺ “ምህረት ከማያገኙ ወንጀሎች ተጠንቀቅ። … ወለድን መብላት። ወለድን የበላ ሰው በቂያማ ቀን ሸይጧን የሚጥለው እብድ ሆኖ ነው የሚነሳው” ካሉ በኋላ የላይኛውን አንቀፅ አነበቡ። ስለዚህ ትክክለኛ ተውበት ካልኖነረ ጥፋቱ አደገኛ ነው። 7. ወለድ የከሃዲዎቹ አይሁ.ዳውያን ተግባር ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡- {وَأَخْذِهِمُ الرِّبا وَقَدْ نُهُوا عَنْهُ وَأَكْلِهِمْ أَمْوَالَ النَّاسِ بِالْبَاطِلِ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ مِنْهُمْ عَذَاباً أَلِيماً} “ከርሱ በቁርጥ የተከለከሉ ሲሆኑ አራጣንም በመያዛቸውና የሰዎችን ገንዘቦች ያለ አግባብ በመብላታቸውም ሳቢያ (የተፈቀደላቸውን እርም አደረግንባቸው።) ከነሱም ለከሃ .ዲዎቹ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጀን።” [አኒሳእ፡ 161] 8. የወለድ መብዛት የቂያማ ምልክት ነው። ነብዩ ﷺ “ቂያማ ሲቃረብ ወለድ፣ ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ይበዛል” ይላሉ። [ሶሒሑ ተርጊብ ወተርሂብ፡ 1861] 9. ወለድ የሚበላ ሰው አሰቃቂ ስቃይ አለበት። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “ዛሬ ሌሊት ሁለት ሰዎችን አየሁኝ። ወደተቀደሰች ምድርም ይዘውኝ ወጡ። ደም የሚጎርፍበት ወንዝ እስከምንደርስም ተጓዝን። በውስጡ አንድ የቆመ ሰው አለ። ከወንዙ ዳርቻ አንድ ሰው አለ። ከፊት ለፊቱ ድንጋዮች አሉ። ወንዙ ውስጥ ያለው ሰውየ ሊወጣ ሲያመራ ዳር ላይ ያለው ሰውየ አፍ አፉን በድንጋይ እየመታ ወደነበረበት ይመልሰዋል። ሊወጣ በሞከረ ቁጥር ድንጋይ እየወረወረ አፍ አፉን ይመታዋል። ከዚያም ወደነበረበት ይመለሳል። ‘ማነው ይሄ ወንዙ ውስጥ ያየሁት?’ ስል ‘ወለድ የሚበላ ነው’ ይለኛል።” [አቡኻሪይ፡ 2085] 10. ወለድ ከምናስበው በላይ እጅግ የገዘፈ ወንጀል ነው። ነብዩ ﷺ “ወለድ ሰባ ሶስት አይነት ነው። ከነዚህ ውስጥ ቀላሉ አንድ ሰው እናቱ ላይ ዝሙት እንደመስራት ነው” ይላሉ። [ሶሒሑ ተርጊብ ወተርሂብ፡ 1851] 11. የወለድ መብዛት በምድር ላይ የአላህን ቅጣት ያስከትላል። ነብዩ ﷺ “ዝሙትና ወለድ በአንድ ሃገር ላይ ከበዛ በራሳቸው ላይ የአላህን ቅጣት አስወስነዋል” ይላሉ። [ሶሒሑ ተርጊብ ተርሂብ፡ 1859] ወንድሜ! አላህን ፍራ! እህቴ ሆይ! አላህን ፍሪ! ህይወት ማለት የዱንያ ህይወት ማለት አይደለም። ይቺማ ጤዛ'ኮ ናት። ይልቅ ነብዩ ﷺ ምን እንደሚሉ ተመልከት፡- “አንድ ሰው የሚያገኘው ገንዘብ ከሐላል ይሁን ከሐራም ደንታ የማይኖርበት ዘመን በሰዎች ላይ ይመጣል።” [አቡኻሪይ፡ 2059] ልብህ ካልሞተ ይሄ አስፈሪ መልእክት አለው። ሰው እንዴት ራሱን የቂያማ ምልክት ያደርጋል?! ፍጥጥ ባለ መልኩ ሐራም ላይ መግባት ሲኖርስ? ያውም በአራጣ? አላህ ለሸሪዐዊ ትእዛዝ እጅ የምንሰጥ፣ ከዱንያ ይልቅ ኣኺራን የምናስቀድም ያድርገን። ኣሚን። = (ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 23/2010)
Show all...
🥰 1
ሞባይሌ የትም ቦታ ብሔድ ኪሴ ያለው ስልኬ፡ አንጡራ ሀብቴ ነው ሞገስና መልኬ፡ አብረን ብዙ ቆየን እሱ ነው ታሪኬ፡ እፅፍበታለሁ በቁመት በመልኬ፡ አንዱ እያወገዘ አንዱ የሚነክሰኝ፡ አንዱ እያገዘፈ አንዱ እሚያሳንሰኝ፡ አንዱ እስደሰተ አንዱ የሚያጨሰኝ፡ እንዱ እያዘናጋ አንዱ እሚያስታውሰኝ፡ ሌላው ሲያበራታኝ ደግሞ ሲያሞግሰኝ፡ ይህኛው ሲያፅናናኝ ያኛው ሆድ ሲያስብሰኝ፡ በስልኬ በኩል ነው ሁሉም የሚደርሰኝ፡ በፌስቡክ በኢሞ ወይ በቴሌ ግራም፡ በዙ ተማርኩበት ሀላልና ሀራም፡ ከሰው አገናኘኝ ብዙ አመት ሰራም፡ ግን ፈሳድም አለው አመፅን አይፈራም፡ ቲክቶክ ላይ ሲሳፈር ይሆናል ሰካራም፡ ብዙ እውቀት አገኘሁ ከስልኬ ላይ ብልም፡ በርግጥ የሰጡትን መርጦ አይቀበልም፡ የቴሌግራም ግን ክፋቱ አያይልም፡ ለደርስ ለፅሁፍ ለመልካም ይሆናል፡ አብዛኛው ኸይር ነው ይህን ሁሉም ያምናል፡ የላይቩ ፕሮግራም በተለይ ያስቀናል፡ ለዚህም ነው ሲሉን እኛ እሱን መርጠናል፡ ክፉና መጥፎውን ተሸክሞ አያሌ፡ ግዛቱ ሰፊ ነው የለውም ምሳሌ፡ የያዘው ብዙ ነው ይሔ ሞባይሌ፡ በኑረዲን አል አረብ
Show all...
👍 1 1
ሞባይሌ የትም ቦታ ብሔድ ኪሴ ያለው ስልኬ፡ አንጡራ ሀብቴ ነው ሞገስና መልኬ፡ አብረን ብዙ ቆየን እሱ ነው ታሪኬ፡ እፅፍበታለሁ በቁመት በመልኬ፡ አንዱ እያወገዘ አንዱ የሚነክሰኝ፡ አንዱ እያገዘፈ አንዱ እሚያሳንሰኝ፡ አንዱ እስደሰተ አንዱ የሚያጨሰኝ፡ እንዱ እያዘናጋ አንዱ እሚያስታውሰኝ፡ ሌላው ሲያበራታኝ ደግሞ ሲያሞግሰኝ፡ ይህኛው ሲያፅናናኝ ያኛው ሆድ ሲያስብሰኝ፡ በስልኬ በኩል ነው ሁሉም የሚደርሰኝ፡ በፌስቡክ በኢሞ ወይ በቴሌ ግራም፡ በዙ ተማርኩበት ሀላልና ሀራም፡ ከሰው አገናኘኝ ብዙ አመት ሰራም፡ ግን ፈሳድም አለው አመፅን አይፈራም፡ ቲክቶክ ላይ ሲሳፈር ይሆናል ሰካራም፡ ብዙ እውቀት አገኘሁ ከስልኬ ላይ ብልም፡ በርግጥ የሰጡትን መርጦ አይቀበልም፡ የቴሌግራም ግን ክፋቱ አያይልም፡ ለደርስ ለፅሁፍ ለመልካም ይሆናል፡ አብዛኛው ኸይር ነው ይህን ሁሉም ያምናል፡ የላይቩ ፕሮግራም በተለይ ያስቀናል፡ ለዚህም ነው ሲሉን እኛ እሱን መርጠናል፡ ክፉና መጥፎውን ተሸክሞ አያሌ፡ ግዛቱ ሰፊ ነው የለውም ምሳሌ፡ የያዘው ብዙ ነው ይሔ ሞባይሌ፡ በኑረዲን አል አረብ
Show all...
شـبـاب السـلــفـــيـــيــن

#ሰለፍያ_ቀጥተኛ_የሀቅ_መንገድ_ብሎም_አይነኬ_ፅኑ_ተራራ_ነው ለአስተያዬትና እርማት

በጣም አስቂኝ ክስተት አንብቡት የመን ውስጥ ዘማር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መስጂድ ውስጥ የተከሰተ በጣጣጣም አስቂኝ ክስተት ነው 👍 አንብበው ሳይጨርሱ በሳቅ ሟቋረጥ ግን አይቻልም ¡¿ ይህ ክስተት እዚያው መስጂዱ ውስጥ ሰፈል አወል(የመጀመሪያው ሰፍ ) ላይ  ቆሞ ሲሰግድ የነበረ አንድ ሰጋጅ ነው የሚያስተላልፍልን እናም ይህ ሰው እንዲህ ይለናል :- አንድ ሰው ይሞትና ተሰግዶበት ተቀበረ ከዚያም ከኢሻ ሶላት በኋላ  ነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው)  ሊመልሱት ይዘውት ወደ መስጂድ ሲመጡ  ሰአት ሄዶ ስለነበር መስጂዱ ተዘግቷል ስለዚህ ኻዲሞች ለፈጅር ሶላት ሲመጡ እንዲያነሱት በሚል ጀናዛ መሸከሚያው ከመስጂዱ በር ከደረጃ ላይ ያስቀምጡታል ነገር ግን ሌሊት 9:30 ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደ መስጂድ ሲመጣ መስጂዱ ዝግ ሆኖ እና በረንዳው ተከፍቶ አገኘው  የተወሰነ ቢጠብቅም  መስጂዱን የሚከፍተው አጣ ብርዱ በጣም ሲበረታበት ዞር ብሎ ሲያይ ጀናዛ መሸከሚያው ከአጠገቡ አገኘ በውስጡም ብርድልብስ ነገር አለ እና ይህ ሰው አገኘሁ  ብሎ ጀናዛ መሸከሚያው ውስጥ ብርድልብሱን ለብሶ ለጥ ብሎ እንቅልፉን ተኛ  አባቴ ! በብርድ ደንዝዞ የነበረው ሰውነቱ ትንሽ ምቾት ሲያገኝ ነፍሱንም አያውቅ ለጥ ብሎ ተኝቶልሀል ክክክ ትንሽ እንደቆየ የመስጂዱ ኻዲም መጥቶ መሲጂዱ ሊከፍት ሲል  በረንዳ ላይ ከነእሹ(ጀናዛ መሸከሚያው) ላይ የተኛ ሰውዬ  ይመለከታል ከፈጅር በኋላ ሊሰገድበት ያመጡት  ጀናዛ መሰለው  ከኋላውም ሌሎች ሰዎች መጥቶ ግማሹ ሽንት ቤት ሌላው ውዱእ ሊያደርግ ይሄዳሉ  ይህ  በረንዳ ላይ ተኝቶ የሚያዩት ሰውዬ ( ጀናዛ) ደግሞ ሁሉም ቀድሞኝ የመጡ ሰዎች ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ ነው ብሎ ያስባል በውስጡ በዚያ ላይ ፈጅር ነው ሰው  ከእንቅልፉ ተነስቶ እየመጣ ነው ያለው  ገና በደንብ ያልነቃ ህዝብ  ነው ሊሰገድበት የመጣ ጀናዛ ይሆናል በማለት ተጋግዘው ወደ መስጂድ ኢማሙ ጋር ወደ ሚህራብ አስገቡት  ክክክ ይህ ብርድ የቀጠቀጠው ሰውዬ ሲሸከሙት አያውቅ ተኝቷል   ሰዎቹም የማን ይሁን ብለው አይጠይቁ ገና ከእንቅልፋቸው  በደንብ አልነቁም  እና ተሸክመው  መስጂድ ውስጥ አስገቡት ፈጅር አዛን ብሎ ለመስገድ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተሰበሰቡ 👌 ይህንን ታሪክ የሚያስተላልፍልን ሰው  እኔም ከሰጋጆቹ አንዱ ነኝ የመጀመሪያው ሰፍ ላይ ነበርኩ ይላል ከፈርድ በኋላ ልንሰግድበት ጀናዛው ከፊት ተደርጎ  የፈጅር  ሶላት እየሰገድን ነው ክክክ ልክ ለሁለተኛው ረከአ ስንነሳ ጂናዛው ሲንቀሳቀስ አየሁ  እንዴዴዴ አይኔ ነው ወይስ ምንድ ነው  ብዬ አይኔን አበስኩ  ጨፍኜም ገለጥኩ መንቀሳቀሱ ግን አልተወም በቃ እንቅልፍ አለቀቀኝም ይሆናል ብዬ አሰብኩ ነገር ግን ነእሹ በደንብ መንቀሳቀስ ጀመረ  ያኔ መረባበሽና መፍራት ጀመርኩ ይህ የተኛው ሰውዬ  ከብርድልብሱ ውስጥ ድንገት አንገቱ  አውጥቶ ሰገዳችሁ ❓ ብሎ ጠየቀ ወ ያኔ  ሁሉም ሰጋጆች ደንግጦ  መተረማመስና መሮጥ ጀመሩ  እኔም አጠገቤ ከነበረው በር ወጥቼ በባዶ እግሬ  ሮጥኩኝ ወደ 1 ኪ.ሜ ያክል የሚርቀው ቤቴ በትንሽ ደቂቃዎች ደረስኩ ደግሞ ባዶ እግሬ መሆኔም የማውቀው ነገር የለም ኢማሙ( አሰጋጁንም ) ሳየው ደንግጦ መሬት ላይ ወድቋል ሌሎች ሰዎች  ግማሹ  ከግድግዳ ጋር ይጋጫል ሌላው ደግሞ  ልክ እንደኔው  በባዶ እግሩ  ይሮጣል መስጂድ ውስጥ አንድ ሰው አልቀረም አሁንም ሌላኛው  በጣጣጣም የሚያስቀው ክስተት ተከሰተ ያ ከሬሳ መሸከሚያ(ከነእሹ) ላይ ተኝቶ የነበረው ሰውዬ ሲነሳ ሰዎች ሲሸሹ ሲሮጡ ሲያይ ከኋላቸው ተከትሎ መሮጥ ጀመረ እናንተ ምን ሆናችሁ ነው ? ቂያማ ቆሞ ነው እንዴ ❓ እያለ ከኋላ ኋላቸው መሮጥ ጀመረ ክክክ ሰዎቹ ደግሞ  ወደ  ኋላቸው  ሲዞሩ ይህ ሰውዬ እየተከተላቸው  መሆኑ ያያሉ  ያኔ ይብስባቸዋል  ባለ በሌለ ሀይላቸው ይሮጣሉ በዚህ መልኩ ሁሉም  ሰላታቸውን አቋርጠው ሮጡ ይለናል ቦታው ላይ የነበረ አንዱ ሰጋጅ መቼስ ይህንን አንብቦ በሳቅ ያልደከመ ይኖራል ?  እኔ እንጃ በድጋሜ  የተፖሰተ (®) ✅ ለማንኛውም ሼር ማድረግ ይቻላል
Show all...
👍 1🥰 1
02:08
Video unavailableShow in Telegram
📚ትምህርት ሊጀመር ነው! 🎙ኡስታዝ ሑሴን አለሙ ……………………………………………     ሊንክ በመንካት ቻናሉን ጆይን ብለው      ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናል:  || ጀይን👇👇👇 https://t.me/zeyneseid
Show all...
9.75 MB
👍 1
• ቀልብ .... 🎙ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጁ     ሊንክ በመንካት ቻናሉን ጆይን ብለው      ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናል:  || ጀይን👇👇👇 https://t.me/zeyneseid
Show all...
ቀልብ (1).mp32.34 MB
🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጀግና አባት ልጁን  ሲመክር‼️     ሊንክ በመንካት ቻናሉን ጆይን ብለው      ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናል:  || ጀይን👇👇👇 https://t.me/zeyneseid
Show all...
1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.