cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

HIVN Tech and Guidlines

Youtube channel 👉 youtube.com/@HIVN Our group 👉t.me/HIVN19 Channel 👉t.me/healthinovation Official website 👉 www.tenajobs.com COC discussion 👉 t.me/HIVN19 WhatsApp 👇 whatsapp.com/channel/0029Va7FNpr4IBhFkrjQ4o02 ማስታወቂያ ለማሰራት @Andualem0 ያግኙን።.

Show more
Advertising posts
11 807
Subscribers
+624 hours
+977 days
+58830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የውጭ ሀገር የስራ ዕድል | የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር (Repost) የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም የሚያስጥብቅ እንዲሁም በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ብቻ ሳይወሰን የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪትን የሚያካትት እና የዘመነ አገለግሎት እንዲሆን ባስቀመጥነው አቅጣጫ መሰረት ወደ አውሮፓ (Sweden and Norway) ገበያ ለመግባት ቀደም ብሎ በተጀመረ ጥረት ተጠናቆ ወደ ተግባር ተገብቷል። በመሆኑም በስምምነቱ መሰረት የተጠየቁ የሞያ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው። 1- ካርዲዬሎጂስት 2- የማርኬቲንግ ባለሙያ 4- ኬሚካል ኢንጅነር 5- ባስ ድራይቨር 6- አርክቴክት 7- አካውንታን 8- አውቶሞቲቭ ቴክኒሽያን ባለሙያ 9- የላብራቶሪ ቴክኒሺያን 10- የአይ ቲ ባለሙያ 11- የፋርማሲ ባለሙያ 12- የሽያጭ ባለሙያ 13- የሶፍትዌር ባለሙያ 14- ሜዲካል ዶክተር 15- የኮምፒተር ጥገና ባለሙያ 16- ነርስ 17- ግራፊክስ ዲዛይነር 18- የፀጉር ባለሙያ 19- የደንበኛ አገልግሎት ባለሞያ ለመመዝገብ: አስፈላጊውን ስልጠና እና ሌሎች መመዛኛዎችን በሟሟላት የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ዜጎች በኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት በመመዝገብ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን። ማሳሰቢያ: ከምዝገባ በኅዋላ አሻራ መስጠት ግዴታ መሆኑንና ዝርዝር ምዝገባ ሂደቱን ከታች ባለው ማብራሪያ ይመልከቱ:: አመዘጋገብ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይህንን ማብራሪያ ይመልከቱ ⬇️ https://youtu.be/e3Q5GziZDuE?si=hHtIVGy-2MyKZzIY 🩵 @healthinovation
Show all...
የውጭ ሀገር የስራ ዕድል ምዝገባ | በአማርኛ

ማስታወቂያ ለሚመለከተው ሁሉ የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ከሃገር ውስጥ እና በሃገር ውጪ ያሉ የስራ ዕድሎችን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ባለው የሪፎርም ስራና በተዘረጋው ቴክኖሎጂ በአምስት ወራት(ወ.ሴ) ከ146,291 በላይ ዜጎች በውጭ ሃገር የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። ሚንስቴር መስሪያቤቱ በውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት የዜጎቻችን ደህንነት እና ጥቅም የሚያስጠብቅ እንዲሁም ብልሹ አሰራርን የሚከላከል ቴክኖሎጂ በውስጥ አቅም አልምቶ እጅግ ፈጣን የሆነ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በመሆኑም ሚንስቴር መስሪያቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በሚያከናውናቸው የሪፎርም ተግባራት እና በዘርፉ በሚሰጠው ፈጣን አገልግሎት እንዲሁም የስምሪት መደረሻዎችን ለማስፋት ከተለያዩ ሃገራት ጋር እየገባናቸው ያሉ አዳዲስ ስምምነቶች የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ በተዘረዘረው የሞያ መስክ ተመዝግበው ስልጠና ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆናቹ ዜጎች በኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት

https://www.lmis.gov.et

ድህረ-ገጽ ላይ ገብታቹ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን። 1. Driver - ሹፌር 2. Cleaner - የጽዳት ባለሞያ 3. Chef - በሼፍ 4. Laborer - በጉልበት ሰራተኝነት 5. Security Guard/ Security Officer - የጥበቃ ባለሞያ 6. Technician - ቴክኒሺያን 7. Carpenter - የእንጨት ባለሞያ 8. Store Keeper - የሱቅ ጠባቂ ተመዝጋቢዎች ድህረ-ገጹ ላይ በሚደረገው ምዝገባ መረጃዎቻችሁን በትክክል የማስገባት ሃላፊነት ያለባችሁ ሲሆን መረጃዎቻችሁን አስገብታችሁ ስትጨርሱ ሲስተሙ በሚሰጠው የባዮሜትሪክስ ቁጥር አቅራቢያችሁ በሚገኙ አንድ ማዕከላት በመሄድ የባዮሜትሪክስ ምዝገባ በማደረግ ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ እናስታውቃለን። ማሳሰቢያ: ለመመዝገብ የፓስፖርት ባለቤት መሆን የማያስፈልግ ሲሆን ፤ የባዮሜትሪክስ ምዝገባ የሚያከናውኑ አንድ ማዕከላትን ዝርዝር

https://lmis.gov.et/ossc-lists

ከዚህ ላይ ማግኘት ይቻላል። #foreignjobs

👍 23
❤️❤️ youtube.com/@HIVN 17ሺ ሰብስክራይብ እናመሰግናለን 😔
Show all...
👍 3
ነፃ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል #ለሴቶች አክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን ለሴት አመልካቾች ነፃ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል ለመስጠት ዕቅድ ይዟል፡፡ የማመልከቻ ቦታ፦ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ሬጅሰትራር ፅ/ቤት እና ሽረ ግቢ ሬጅስትራር ማስተባበርያ ፅ/ቤት የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ መስከረም 07/2017 ዓ.ም መስፈርቶች፦ ► የተቀመጡ የመግቢያ ነጥብ አሟልተው ሲገኙ፣ ► አመልካቾች ከዚህ በፊት በመንግስት ወጪ የትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው የተማሩ ከሆነ የወጭ መጋራት ክፍያቸውን መፈፀም ይጠበቅበቸዋል፣ ► ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ (Exceptions ይኖራሉ)፣ ► በመንግስት ዕውቅና ከተሰጠው ዩኒቨርሲቲ የተመረቁና የመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታቸው 3.00 እና ከዚያ በላይ (ለአካል ጉዳተኞች 2.75 እና ከዚያ በላይ) የሆነ፣ ► የድኅረ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (GAT) የማለፍያ ውጤት ያገኙ፣ Note: ነፃ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል የተሰጠባቸው የትምህርት ፕሮግራሞች እና ሌሎች መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡ @healthinovation
Show all...
👍 4🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለ2017 ዓም በሰላም በጤና አደረሳችሁ:: ውድ ቤተሰቦች በአዲሱ ዓመት መጥፎውን ሁሉ አርቆ መልካሙን የምናይበትና እቅዳችን የምናሳካበት ያድርግልን::
Show all...
👍 12 3
Photo unavailableShow in Telegram
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ | የፈተና ማብራሪያ ____ ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Public Health, Pharmacy, Anesthesia, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing እና Surgical Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተናው ከመስከረም 8 - 10/ 2017 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን፦ 1. የፈተናው መርሃ-ግብር - 8/1/2017 ዓ.ም…… Medicine, Pharmacy, Anesthesia, Dental Medicine, Environmental Health, Psychiatric Nursing and Surgical Nursing - 9/1/2017 ዓ.ም……… Medical Laboratory Science, Midwifery, Pediatric and Child Health Nursing, Medical Radiology Technology and Public Health - 10/1/2017 ዓ.ም…………… Nursing እያንዳንዱ ተፈታኝ ከሚፈተንበት ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም መስከረም 7/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፤ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል:: 2. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ 3. ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡ 4. በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረማችሁን ማረጋገጥ ይኖርባችኋዋል፣ 5. ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ ▫ የመፈተኛ ጣቢያ ኦንላይን በመረጣችሁት መሰረት ስም ዝርዝራችሁን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ /Link/ በመጫን መመልከት ይኖርባችኋል፡፡ (https://drive.google.com/drive/folders/17QzuVtjm4Uh3yQhA-teNFt7PRDqBc0Ft?usp=sharing) ▫ ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት ተቋም ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ የማትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡ ማሳሰቢያ፦ - ጎንደር ዩኒቨርሲቲ(ቴዎድሮስ ካምፓስ) የመፈተኛ ጣቢያ የመረጣችሁ ተመዛኞች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ(ጤና ሳይንስ ኮሌጂ) የተዘዋወራችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ✔ወቅታዊ የስራ ቅጥር መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት ቻናላችንን ይከታተሉ:: 🩵 t.me/addlist/IWOV6uABAi5lYTA0  🖥 youtube.com/@HIVN 📱 fb.com/healthinovation/
Show all...
👍 11 1
የ COC ተያያዥ መረጃዎች እና ከዚህ በፊት የተሰጡ እና የተሰሩ ጥያቄዎች መመልከት ይችላሉ 👇 https://youtube.com/playlist?list=PLcFcTovEaUnxwyrvfh71jAO8XCkFJHhA1
Show all...
👍 2👎 1
መንግስት ለመንግስት ሰራተኞች እና ለሹመኞች የደመወዝ ማሻሻያ አድርጓል። የተሻሻለው ደመወዝ ይህን ይመስላል። የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ሙሉ ዝርዝር መመሪያ @healthinovation
Show all...
በበ18-6-58-16_New_compressed.pdf14.90 MB
👍 15
አዲሱ የኢትዮጵያ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ስኬል ይፋ ሆኗል:: ክፍያው ከመስከረም 1/2017 አ ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል:: ሙሉ መረጃውን ይመልከቱ 👇 https://youtu.be/w-czLmvjpK0?si=70lKwHZ4sdcWJ9fm
Show all...
👍 5👏 1
የስራ ቦታ ሁኔታና የሠራተኞችን መብት በተመለከተ የተዘጋጀ የኢሰመጉ 156ኛ ልዩ መግለጫ ነሐሴ 29/2016 ዓ/ም
Show all...
156ኛ ልዩ መግለጫ.pdf5.48 KB
👍 5
ለNGAT ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ | ፈተናውን በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ 1️⃣Username እና ፓስዎርድ ከየት እናገኛለን? 2️⃣የፈተና ፕሮግራም ማብራሪያ ⬇️ https://youtu.be/N1RvpBXB9LA
Show all...
👎 4👍 3
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.