cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አቡ ዑመይር

ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ (ሱረቱል ነህል 125) ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Yabekeir ስህተት ባያችሁም ጊዜ አርሙኝ።

Show more
Advertising posts
1 753
Subscribers
No data24 hours
-97 days
-1730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የመውሊድ ማምታቻ ሹብሀዎች ....? ሙብተዲዕ ማለት አይጥ ማለት  ነዉ! 🎙በኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ t.me/Darutewhide
Show all...
መውሊድ.mp33.96 MB
ዳንስና ጭፈራውን "ነብዩን ﷺ ማወደስ" ብሎ ይጠራዋል። ከዚያ "አትጨፍር" ስትለው "ነብዩን ማወደስ አይቻልም ወይ?" ይላል። ማን አታወድስ አለህ? ጭፈራ ዒባዳ አይደለም ነው የተባልከው። =
Show all...
👍 5👏 1
መታወቅያ ወረቀት ✅ ንቦች ወደ ቀፎውአቸው ሲገቡ በቀፎው በመግቢያ በር ላይ ለቆመው ዘበኛ የአባልነት “መታወቂያ” ያሳያሉ፡፡ በአንድ ቀፎ ውስጥ የሚኖሩት ንቦች ሁሉም ተመሣሣይ መታወቂያ አላቸው፡፡ ይህ “መታወቂያ” ከሰውነታችን ውስጥ የሚመነጨው ልዩ ጠረን ነው፡፡ እያንዳንዱ ቀፎ ውስጥ የሚኖር ንብ መለያ ጠረን አንድ ዓይነት ሲሆን ሌላ ቀፎ ውስጥ ካሉት ንቦች ጠረን ይለያል፡፡ በር ጠባቂ ንቦች የቀፎውን አባላት የሚለዩት በዚህ ጠረን ሲሆን ከሌላ መንጋ የመጣ ጠረን ልውጥ ንብ ካለ ጠረኑን ለይተው ያባርሩታል፡፡ ✅ ንብ ለመናደፍ 12 ጡንቻዎችዋን ትጠቀ ማለች፡፡ የዳንስ ቋንቋ ✅ ንቦች እርስ በርሣቸው የሚግባቡት በዳንስ ቋንቋ ነው፡፡ ይህም ዳይሴፈሪንግ ይባላል፡፡ ✅ አንድ የንብ መንጋ ውስጥ 58 000 ንቦች ይገኛሉ፡፡ ✅ ማርን የምታመርተው ሴቷ ንብ ብቻ ናት፡፡ ✅ የወንዱ ንብ ስራው ከንግስቲቷ ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈፀም ንግስቲቷን እንቁላል እንድታፈራ ማድረግ ነው፡፡ ✅ እንቁላል የምታመርተው ወይም የምትጥለው ንግስቲቷ ንብ ብቻ ናት፡፡ ✅ ንግሥቲቱ ንብ በቀን 1500 እንቁላሎችን ትጥላለች፡፡ ✅ንግስቲቷ ንብ በጭራሽ ሰዎችን አትናደፍም፡፡ ሌሎች ንቦችን ግን ትናደፈለች: ✅ አንዲት ንብ በሶስት ወር የሕይወት ዘመና የምታመርተው የማር መጠን የአንድ ማንኪያ 1/12" ነው። ✅ ንቦች 50 ግራም ማር ለመሥራት በአጠቃላይ የሚያደርጉት በረራ ተቀጣጥሎ ቢዘረጋ ከመ ሬት እስከ ጨረቃ ደርሶ ይመለሳል፡፡ ✅ በዓለም ላይ የማይበላሽ፣ የማይሻግት፣ የማይብ ሰብስ እና ጣዕሙ ሳይለወጥ መቆየት የሚችል ብቸኛ ምግብ ማር ነው وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ (ሰዎች) ከሚሠሩትም (ቀፎ) ቤቶችን ያዢ፡፡
Show all...
5😍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ክታብ ማሰር ~ በአንድ ወቅት አስር ሰዎች ከነብያችን ﷺ ዘንድ መጡ፡፡ ከዘጠኙ ጋር ቃል ኪዳን ገቡና አንዱን ተውት። "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከዘጠኙ ጋር ቃል ኪዳን ገብተህ ይሄኛውን ተውከውሳ?" ሲሏቸው "እሱ ክታብ አለበት" አሉ። ሰውየው እጁን አስገብቶ ቆርጦ ጣለ። በዚህን ጊዜ ከሱም ጋር ቃል ኪዳን ተጋቡ። ቀጥለውም እንዲህ አሉ፦ مَن عَلَّقَ تَميمةً فقد أَشرَكَ "ክታብ /ህርዝ ያሰረ ሰው በርግጥም (በአላህ) አጋርቷል።" [አሶሒሐህ፡ 492] ጥያቄ፦ ይሄ ነገር በአካባቢያችሁ አለ ወይስ የለም? = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
👍 2 1
የሰኞ ፆም እና መውሊድ ~ የመውሊድ አክባሪዎች ለዚህ ቢድዐቸው ከሚያጧቅሷቸው “ማስረጃዎች” ውስጥ አንዱ ነብዩ ﷺ ሰኞን ከሚፆሙባቸው ምክንያቶች አንዱ የተወለዱበት ቀን መሆኑን መግለፃቸው ነው። ይህንን መነሻ በማድረግ “እንዲያውም መውሊድ መከበር የተጀመረው በራሳቸው በነቢዩ ﷺ ነው” ይላሉ። ይሄ ግን ፈፅሞ ማስረጃ ሊሆናቸው አይችልም። ምክንያቱም፦ 1. ፆምና ጭፈራን ምን አገናኘው?! እናንተ'ኮ በጭፈራ እንጂ በፆም አይደለም የምታከብሩት። ተግባራችሁ ባልተመሳሰለበት በምን ስሌት ነው የሰኞን ፆም ለጭፈራ ማስረጃ የምታደርጉት? የልደት ቀናቸውን በጭፈራና በድግስ ማሳለፍ ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ! ደግሞም ነብዩ ﷺ ሰኞን የሚፆሙበትን ምክንያት ሲናገሩ “ስራዎች ሰኞና ሐሙስ ቀን (ወደ አላህ) ይቀርባሉ። እናም ፆመኞ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” ነው ያሉት። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2959] የናንተ ተግባር ግን “ጨፋሪ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” የሚል ነው የሚሰጠው። 2. እናንተ'ኮ ሰኞ ቀን አይደለም የምታከብሩት! ረቢዑል አወል 12 ሁሌ ሰኞ ጋር አይገጥምም። ኧረ እንዲያውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ሆነ ብለው በያመቱ እሁድ ቀን ብቻ የሚያከብሩ አሉ። ሌሎች ደግሞ ህዳር ላይ፣ ሌሎች ጥቅምት ላይ፣ ሌሎች ደግሞ ረጀብ ወር ላይ የሚያከብሩ አሉ። እንኳን ቀኑና ወሩም አይገናኝም። አመት ጠብቆ የልደት ቀናቸውን ማክበር ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ! ስለዚህ እየተፈፀመ ያለው ነገር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን ባህል ማስቀጠል ብቻ ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለሱና የተጨነቃችሁ ይመስል ከናንተ ፀያፍ ተግባር ጋር የማይዛመደውን የነብዩን ﷺ ሳምንታዊ የሰኞ ፆም ማጣቀስ ማጭበርበር አይደለም ወይ? 3. ሰኞን ብትጠብቁም ከጥፋትነት አይወጣም! ሌላው ቀርቶ በየሳምንቱ እየጠበቃችሁ ሰኞን ብታከብሩ እንኳ የናንተ ተግባር በሺርክ የታጨቀ፣ በቢድዐ የተወረረ እና ከስነ ምግባር ያፈነገጠ ነው። አሁንማ ጭራሽ የብልግና መፈፀሚያም ሆኗል። ደግሞስ ነብዩ ﷺ ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራ አላከበሩ? ጭፈራ በምን ስሌት ነው ዒባዳ የሚሆነው? በዚህ ላይ ሺርክ ሲጨመርበት ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል። 4. ከሰኞ ፆም ጋር በቂያስም አይገናኝም! የሰኞን ፆምና የመውሊድን ጭፈራ በቂያስ ማገናኘትም ጭራሽ የሚያዋጣ አይደለም። የሐሙስን የሱና ፆም በጭፈራና በውዝዋዜ ማሳለፍ ይቻላልን? በደስታ እንድናሳልፍ የታዘዝናቸውን ሁለቱን ዒዶች በፆም ማሳለፍ ይቻላል? የምስጋና ሱጁድን በሩኩዕ መቀየር ይቻላል? ዒባዳኮ በታዘዘው መሰረት እንጂ በመሰለኝና በደሳለኝ አይፈፀምም። እውነት ከመውሊድ የሚፈልጉት አላማ ለአላህ ምስጋና መግለፅ ከሆነ ሊከተሉ የሚገባው ነብዩ ﷺ የተከተሉትን እርምጃ ብቻ ነበር። “ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነውና።” [ሙስሊም፡ 2042] እሳቸው ደግሞ የተወለዱበት ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራና በውዝዋዜ ምስጋናቸውን አልገለፁም። እየተፈፀመ ያለው እሳቸው ከሰሩት ተቃራኒ ነው። ታዲያ ለምን ነብዩን ﷺ የበቃቸው አይበቃንም?! ለምንስ ከሳቸው ፊት እንሽቀዳደማለን? አላህ እንዲህ አላለምን? {يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيِ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ} {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልእክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ። አላህንም ፍሩ። አላህ ሰሚ አዋቂ ነው።} [አልሑጁራት፡ 1] ነብዩስ ﷺ “በኔ ላይ መልካም ምሳሌ አይኖርህምን? በአላህ ይሁንብኝ! እኔ ከናንተ ይበልጥ አላህን ፈሪያችሁ ከማናችሁም በበለጠ ድንበሮቹን ጠባቂ ነኝ” አላሉምን? [አሶሒሐህ፡ 1782] 5. ነብዩ ﷺ ስለ ሰኞ ፆም እንጂ ስለ ረቢዑል አወል 12 አልተናገሩም! ነብዩ ﷺ ሰኞ ቀን እንደተወለዱ በግልፅ የተናገሩ ሲሆን ረቢዑል አወል 12 መወለዳቸውን በተመለከተ ግን አስተማማኝና ሶሒሕ ማስረጃ የለም። ጠንካራ ማስረጃ አለመምጣቱ በራሱ ቀኑ ያን ያክል አንገብጋቢ እንዳልሆነ ነው የሚያሳየው። መውሊድ ዛሬ የሚሰጠውን ያክል ክብደት ቢሰጠው ኖሮ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ሰኞ መወለዳቸውን እንደነገሩን ሁሉ ከአመቱ ወራት ውስጥ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ በግልፅ በነገሩንና እንድናከብረውም ባስተማሩን ነበር። 6. የሰኞ ፆም እንጂ የረቢዑል አወል 12 መውሊድ በሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ አይገኝም በሱና ድርሳናት ላይ የሰኞ ፆም ትኩረት ተችሮት የተወሳ ሲሆን ረቢዑል አወል 12ን የሚመለከት ግን አንድም መረጃ የለም። ምክንያቱም ሊቀርብ የሚችል መረጃ የለምና። ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ አራቱ ሱነኖች፣ … ብንፈትሽ ረቢዑል አወል 12ን በደስታ፣ በጭፈራ፣ በተለየ ዒባዳ፣ በሶደቃ እንድናሳልፍ የሚጠቁም አንድም መረጃ አይገኝም። ይህም የሰኞ ፆም ለመውሊድ መረጃ እንደማይሆን ጠቋሚ ነው። ቢሆን ኖሮ ከመውሊድ አጋፋሪዎች በፊት እነ ቡኻሪ ይረዱት ነበርና። 7. ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ቀን ዒድ አይደለም! በኢስላም ዒድ እንዳማይፆም የታወቀ ነው። ሰኞ ቀን መፆም ግን የተወደደ ነው። ከመሆኑም ጋር ይህ መፆሙ የሚወደደው ሰኞ ቀን ከዒድ ቀን ጋር ከገጠመ መፆም አይፈቀድም። ይህም የተወለዱበት ቀን ዒድ እንዳልሆነ በተጨባጭ የሚያሳይ ነው። ነብዩም ﷺ ሰኞን መፆም የሚወደድ እንደሆነ አስተማሩ እንጂ “ቀኑ ዒድ ነው” አላሉም። እለቱ ዒድ ቢሆን ኖሮ በፆም አያሳልፉትም ነበር። የመውሊድ አክባሪዎች ግን ቀኑን ዒድ አድርገውታል። በሚደንቅ ሁኔታ “ቀኑ ዒድ ስለሆነ መፆም አይቻልም” እስከማለት የደረሱ አሉ። "መዋሂቡል ጀሊል ሸርሕ ሙኽተሶሪል ኸሊል" የተሰኘውን ከታብ ገፅ 2/406 ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡ ሙሐመድ ብኑ አሕመድ በኒስ፣ ኢብኑ ዐባድና ሌሎችም እንዲሁ እለቱን ዒድ ነው ይላሉ። የሚያሳፍር! ታዲያ እንደዚያ የሚሉ ከሆነ ለምን ነብዩ ﷺ በፆም ያሳለፉትን ሰኞን ለዚህ ድርጊታቸው መረጃ ያደርጋሉ? ዒድ ይፆማል እንዴ? ቀንደኛ የመውሊድ አቀንቃኝ የሆነው ኢብኑል ዐለዊ ግን መውሊድን መሀይም እንጂ በዒድ አይገልፀውም ይላል። መውሊድ ዒድ (በአል) ነው የምትሉ የዋሀን ሆይ! መሃይማን ባትሆኑ ኖሮ መውሊድን ‘ዒድ ብላችሁ አትገልፁም ነበር’ እየተባላችሁ ነው!! በርግጥ እሱ በዚህ በኩል የሚነሳውን ትችት ለመሸሽ ያክል ነው ይህን የሚለው። እንጂ ዞር ብሎ “ቀኑ ከዒድም በላይ ነው” ይላል። [አልኢዕላም፡ 8] የዞረበት ጉድ! የቢድዐ ፍቅር ሰዎቹን የት እንደሚያደርሳቸው ተመልከቱ። ለዚህ ሙግቱ ከከንቱ ትንተና ባለፈ ከቁርኣንም ከሐዲሥም ከሰለፎች ንግግርም አንድም ሊያቀርበው የሚችለው ነገር የለም። ሲጠቃለል የነብዩ ﷺ የሰኞ ፆም እና አመታዊ የሱፍያ ጭፈራ በየትም አቅጣጭ አይገናኝም። አራምባና ቆቦ ነው። (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2014) የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

👍 1
00:35
Video unavailableShow in Telegram
የባሰ ፊትና የማይከሰት ከሆነ ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ቀብር ላይ የተገነቡ ቤቶችን፣ ግንባታዎችን፣ ዛፎችን፣ ... አፈራርሶ ማስወገድ ይገባል። ይሄ ነው የነብያት ሱና። ይሄ ነው የነብዩላህ ኢብራሂም ተግባር። ለሙሽ .ሪኮች ምን ነበር ያሏቸው? { وَتَٱللَّهِ لَأَكِیدَنَّ أَصۡنَـٰمَكُم بَعۡدَ أَن تُوَلُّوا۟ مُدۡبِرِینَ (57)} እነሱ ዞር ሲሉ ሊያፈራርሱላቸው በመሀላ አስረግጠው ነገሯቸው። አውርተው አልቀሩም። ይሄውና፡ فَجَعَلَهُمۡ جُذَ ٰ⁠ذًا إِلَّا كَبِیرࣰا لَّهُمۡ لَعَلَّهُمۡ إِلَیۡهِ یَرۡجِعُونَ (58)} "(ዘወር ሲሉ) ስብርባሪዎች አደረጋቸው፡፡ ለእነሱ የሆነ አንድ ታላቅ (ጣዖት) ብቻ ሲቀር ወደርሱ ይመለሱ ዘንድ (እርሱን ተወው)፡፡" [አልአንቢያእ፡ 57 - 58] የነብያችን ﷺ አስተምሮትም እንዲሁ ነበር። የሰልፎቻችንም ተግባር እንዲሁ ነበር። አቡል ሀያጅ አል አሰዲይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ قَالَ لِي عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ : أَلَا أَبْعَثُكَ عَلَى مَا بَعَثَنِي عَلَيْهِ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ؟ ( ... وَلَا قَبْرًا مُشْرِفًا إِلَّا سَوَّيْتَهُ) "0ሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ እንዲህ ብሎኛል፦ ' የአላህ መልእክተኛ ﷺ በላኩብኝ አምሳያ አልክህምን? { ...ከፍ ያለ ቀብር አይተህ (ከሌሎች ቀብሮች ጋር እኩል) ሳታስተካክለው እንዳታልፍ!}' " [ሙስሊም፡ 969] ባይሆን በደመ ነፍስ መወሰን አይገባም። እርምጃ ከመውሰድ በፊት ጉዳዩ ምን ሊያስከትል እንደሚችል በጥልቀት መመርመር ይገባል። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
10.11 KB
3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ውጤት በሚንስትሩ ድህረገፅ ላይ ለሊት 6 ሰዓት የሚለቀቅ ይሆናል። @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የ2016 የ12ተኛ ክፍል ውጤት ሲለቀቀ ውጤት ማያ ሊንኮች ይፋ ሁነዋል ! 1.በዌብሳይት - http://result.neaea.gov.et 2. በ6284 - SMS 3. በቴሌግራም - @eaesbot እንዴት ማያት እንችላለን ካላቹ ቪዲዮ ጎል ቻናል ላይ አሰቀምጠናላቹዋል። 4-3-3 😍 @Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
Show all...
👍 1
{የጁሙአ ቀን ሱናዎች} 1,ሻወር መውሰድ 2,ሽቶ መቀባት(ለወንድ) 3,ጥርስ መፋቂያ መጠቀም 4,የክት ልብስ መልበስ ለወንድ(ነጭ ልብስ) 5,በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ 6,በእግር ወደ መስጂድ መሄድ 7,መስጂድ ውስጥ ሰዎችን አለማስቸገር 8,ኹጥባ እየተደረገም ቢሆን ተህየቱ መስጂድ መስገድ 9,ኹጥባ ወደ ሚያደርገው ኢማም መዞር እና ኢማሙን እያዩ ኹጥባን ማዳመጥ 10,ኹጥባ በሚደረግበት ወቅት ፀጥታን መላበስ 11,ሰደቃ ማብዛት 12,ሱረቱል ካዐፍ መቅራት 13,ዱአ ማድረግ 14,በአላህ መልክተኛ(ሰ.አ.ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድاللَّهُمَّ صَلِّ وَ سَلِّمْ وَ بَارِكْ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ መልካም ጁመዓ ይሁንላችሁ 🥰
Show all...
8🥰 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.