cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የልብ ፊደል

ለሁሉም ጊዜ አለው... 🙏🙏 ፩) አጫጭር ታሪኮች ፪) ግጥሞች . . .

Show more
Advertising posts
245
Subscribers
-124 hours
-27 days
-530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እርቦኝ ያውቃል !? እህል ብቻ አይደለም ሰውም ሠው ብቻም አይደለም መልካም ነገር ማየት። መልካም አገር ብቻም አይደለም ሰላም ማግኘት። ብቻ አሁን ግን የራበኝ ፍቅር ነው😭 እምነት እና ፍቅር ተስፋም አይዞሽም ጭምር
Show all...
👍 5
ላንተ ስል ተኛለው🥰 ለምትናፍቀኝ😢 የምር ግን እኔ ብቻ ነኝ ሰው ሲናፍቀኝ ተኚ ተኚ ሚለኝ🤭🤭
Show all...
6.18 MB
👏 3
ክፍል-6️⃣ ስለዚህ በሆነ ነገር ልፈትነው አሰብኩ ልክ እንደተገናኘን በመጣደፍ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህማ አልኩት መቼም አንዴ ሲፈጥረኝ እርጋታ ብሎ ነገር አልፈጠረብኝም እሺ ሞልቃቂት አለ እየሳቀ ሲስቅ አንዳች ሰውነትን ስንጥቅ የሚያደርግ ምትሀት ነገርማ አለው ) በቃ ተወው ስንወጣ መኪና ውስጥ እነግርሃለሁ ብቻችንን ስንሆን አልኩት እሺ እንደተመቸሽ አለኝ ደሞኮ ሲያወራ ቃላቶቹ አንቺ ቅደሚ አንቺ የሚባባሉ ነው የሚመስለው አቤት እርጋታቸው ። ልክ መኪና ውስጥ ስንገባ ወደፊት ንዳው አልኩት የት እንደሚሄድ ባያቅም ይነዳዋል ብቻ ዞር ስል ትንሽዬ ቦታ አየሁ አቁመው አቁመው ሳይታወቀኝ አንባረኩበት እሺ ተረጋጊ እንጂ ሰላም አለ ። እሺ ወደ ታች ታጠፍ አልኩት ታጠፈ  ትንሽ ተጉዘን ከመኪናው ወረድን ለሁለታቺንም በደንብ እየተያየን ለማውራት የሚመቸንን ቦታ ከመረጥን ቡሀላ ቁጭ አልን እሱ ትንሽ ከፍ ያለ ድንጋይ ላይ እግሩን ከፍቶ ተቀመጠ እኔ በእግሮቹ መሀል  ገብቼ ቁጭ ልል አልኩና ድፍረት ይሆንብኛል ብዬ ከጎኑ ወደሱ ዞሬ ቁጭ አልኩኝ እሺ አጂሪት ቀጥይ አለ። ለመስማት እንደጓጓ  የሆነ ነገር ሹክ ብሎኛል ። ምን መሰለህ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህ ነበር አልኩ ምን ብዬ እንደምጀምር ግራ እየገባኝ እኮ ነው ። ጠይቂኛ ብቻ አፈቅርሀለሁ እንዳትይኝ እንጂ አለ አነጋገሩ የቀልድ አይመስልም ማለት አልኩት አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ የላቸውም ቀጥይ አለ። እሺ ብዬ የራሴን ጥያቄ ልግባው 😂😂😂😂😂😂 በቃ ለምሳሌ መንገድ ላይ እየሄድክ አንድ የኔ ቢጤና አንድ ሚሊየን ብር ብታገኝ ቀድሞ ልብህ የትኛውን ይከጅላል አልኩት :: መልሱን እስክሰማ   ተጨነኩ እእእ በቃ ለዚህ ነው እዚህ ድረስ ያመጣሺኝ ብሎ አፍንጫዬን ጎተተኝና ወደ መልሱ ስገባ እኔ የኔ ብጤውን እመርጣለሁ ምክንያቱም ይቀጥላል .................... ይቀጥላል     
Show all...
3
❤️የፍቅር ማእበል❤️      ክፍል8️⃣ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ማብሰልሰል ጀመርኩ ::    ማክቤል   ከኔ የበለጠች ቆንጆ ስለያዘ የሆነች ቅናት ብጤ ተሰምታኛለች እኔምኮ ከሱ የበለጠውን ይዣለሁ ብዬ እራሴን ላፅናና ሞከርኩ ግን ልዑሌ የኔ  እንደሆነ እርግጠኛ አልነበርኩም ።። ትንሽ ቆየሁና ተነስቼ ወደሆስፒታል ሄድኩ ይቅርታ ተራዬ አልፎኛል መሰለኝ ውጤቱ አንቺጋ ስለሆነ ብትነግሪኝ አልኳት ውጤት ለመናገር ስትጣራ የነበረችዋን ዶክተር ኦኦ አንቺ ነሽ ስምሽ ሲጠራ የጠፋሽው ነው ግቢ አለችኝ ። ገባሁ ቁጭ አልኩኝ መጀመሪያ ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቀችኝ ከማንጋ ነው ምትኖሪው ስራ አለሽ ፍቅረኛ አለሽ ወይ የኑሮ ሁኔታሽ እንዴት ነው ብቻ ብዙ ከጠየቀችኝ ከመለስኩላት ቡሀላ ወጤቱን ነገረችኝ ..... የምርመራ ውጤቴን ሳየው እዛው ነበር እራሴን የሳትኩ ስነቃ ዶክተሮቹ ከበው ደህና ነሽ ደህና ነሽ ይሉኛል መልሴን እራሴን ከፍ ዝቅ በማድረግ መልሼላቸው ካላጋ ላይ ወረድኩ እንባዬ ዝም ብሎ ይፈሳል አንዷ ዶክተር ሶፍት ሰታኝ እንድረጋጋ ነገረችኝ መረጋጋት ግን አቃተኝ:: ደና እንደሆንኩኝ ነግሪያቸው ዝም ብዬ ወደቤቴ ሄድኩ እቤት ታናሽ እህቴ ብቻ ነው ያለችው ስታየኝ ደንግጣ  እሮጣ  መታ አቀፈችኝ ዝም እንድትል  አስጠንቅቂያት ወደ ክፍሌ ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ:: ክፍሌ ተጠቅልዬ ሳስብ ሳለቅስ ስገላበጥ አመሻሽ ደረሶ እናቴ ወደ ቤት መጣች እቤት ስትገባ ከሳሎን ስታጣኝ ወደ ክፍሌ መጣች ብታንኳኳ ብታንኳኳ ዝምታ ነበር መልሴ የበሩ ድብደባና ድምጿ በጣም ሲረብሸኝ ተነስቼ ከፈትኩላት ስታየኝ ደነገጠች ምነው ልጄ ምን ሆንሽብኝ እያለች ፊቴን ስታሳሸኝ እንባዬን መቋቋም አቃተኝ ፊቴን አዙሬ ወደ አልጋዬ ሄድኩ ተከትላኝ ገባችና  አልጋዬ ላይ አረፍ ካለች ቡሀላ ወደሷ ጎትታ  ጉልበቷ ላይ አስተኛችኝ በይ አሁን በርጋታ የሆንሽውን ሁሉ ንገሪኝ አለች ከናቴ ምንም ነገር አልደብቃትም ከልጅነቴ ጀምሮ እንደ ልብ ሚስጥረኛ ጓደኛ ሆና ነው ያሳደገችኝ ሌላው ቀርቶ ትምህርት ቤት እንኳን የፍቅር ደብዳቤ ሲሰጠኝ ከናቴጋ ነበር ከፍቼ ማነበው የሚጠቅመኚንና ማይጠቅመኝን ከሷ የተሻለ የሚያውቅ ሰው አለ ብዬ ስለማላስብ ነው ምንም ነገር ማልደብቃት አሁንም ሁሉንም አፍረጥርጬ ልነግራት ነበር ግን እንደማልችል ገባኝ እናቴ ይሄን ብትሰማ ምን ያህል እንደምታፍር ሳስበው ሰቀጠጠኝ እናቴ በቀላሉ እንደማትፋታኝ ስለገባኝ የሆነ ታሪክ ፈጥሬ ልነግራት እያሰብኩ እያለ ድንገት ልኡል አይምሮዬ ውስጥ ብልጭ አለ ። እእእ ....ንገሪኛ.. ልጄ አለች በለሆሳስ ድምፅ ጠየቀችኝ ምን መሰለሽ ማም ፍቅር ያዘኝ አልኳት እየተቅለሰለስኩ :: አላመነቺኝም 💀ፍቅር ስለያዘሽማ እንዲህ አትሆኚም ።ደሞስ ዛሬ ነው እንዴ ፍቅር የያዘሽ እእእ ይሄን ያህል ጊዜ ከማክቤልጋ ስትቆይ ፍቅር እንደያዘሽ ነበር ማቀው እኔ እናትሽ ስታይኝ ህፃን ልጅ ነው እንዴ ምመስልሽ በይ አሁኑኑ እውነቱን ተናገሪ ብትዋሽኝ አውቅብሻለሁ እሺ አፋጠጠችኝ።   እኔም ድርቅ ብዬ እማዬ ከማክቤልጋ ተለያይተናል ከሌላ ሰው ነው ፍቅር የያዘኝ ....      .... ይቀጥላል     
Show all...
💔 3
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻 💙  የፍቅር  ማዕበል🔸 ❤️  ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️                        #ክፍል_ 7️⃣ ምክንያቱም እኔ የብር ችግር የለብኝም ይሄንን ጥያቄ ለ1 የኔ ቢጢ ብታቀርቢለት መልሱ ገንዘቡን ይልሻል እኔን ስጠይቂኝ ደሞ ሰውዬውን አልኩሽ ሰው የሌለውን ነገር ነው የሚመኘው እኔ ገንዘብ አለኝ ፍቅር ግን የለኝም ባሁን ሰአት ከገንዘቡ ይልቅ አንድ የልቤን ማማክረው እውነተኛ ሰው ባገኝ ነው ምመርጠው እኔ ሚስት ማግባት ብፈልግ ገንዘቧን አይቼ አይደለም ማገባት ለምን መሰለሽ በቤት ላይ ቤት በመኪና ላይ መኪና በገንዘብ ላይ ገንዘብ እንጂ ፍቅርን አትሰጠኝም አንዲት ሴትን ሳፈቅራታ ክፍተቴን እንድትሞላልኝ እፈልጋለሁ የኔ ክፍተት ገንዘብ አይደለም የኔ ክፍተት እውነተኛ ፍቅር ነው ገንዘብ ሳላጣ ጤነኛ ሆኖ በሚኖረው ሰው እቀናለሁ :ሁሌ እየሳቀ በሚኖረው እቀናለሁ :የልቡን ሁሉ ዝርግፍ እያደረገ ለልብ ጓደኛው ሲያማክር ሳይ እቀናለሁ: ምክንያቱም አሁን የጠቀስኩልሽ ነገሮች ሁሉ የለኝም እነዚህ ነገሮች ያሏቸው ሰዎች ግን ለነሱ እንደተራ ነገር ናቸው እነሱ በእጃቸው የሌለውን እሩቅ አሻግረው ሲያዩ የተሰጣቸው ነገር ሳያመሰግኑበት  ሳይጠቀሙበት ያልፍበታል ተመለሰልሽ ብሎ ጉንጬን ነካ ነካ እስኪያደርገኝ ድረስ አፌን ከፍቼ ነበር ምሰማው አንዳንድ ጥያቅዎችን ተፈጥረውብኛል ግን ዝም አልኩኝ ። ልኡሌ አነጋገሩ ውስጤ ነበር የገባው እውነት ፈልጎ ያጣውን ክፍተቱን እኔ  ብሞላለት ብዬ ተመኘሁ ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እሱን ለማስደሰት ለራሴ ቃል ገባሁ  ። ሳየው ሁሉ ነገሩ ነው የሚያሳሳኝ ከንፈሩ አይኑ ብቻ አላቅም ወደሱ የሚጎትተኝ ብዙ ነገር አለ በጭራሽ መቋቋም የማልችለው ። አንዳንዴ በጣም ያመኛል ምግብ እራሱ አይረጋልኝም በልቼው ወዲያው ይወጣል ያጥወለውለኛል ብቻ ሀኪም ቤት ለመሄድ እነሳና ምን እንዳስቀረኝ ሳላቅ እቀራለሁ። ዛሬ ግን በጣም ሲብስብኝ ሄድኩ ምርመራ አድርጌ ጨርሼ ልወጣ ስል  ማክቤል ደወለ ግራ እየተጋባሁ አነሳሁት ሄሎ የኔ ውድ አለኝ አቤት አልኩ በመኮሳተር ድምፅ🙄😡😡 ፈልጌሽ ነበር ከቻልሽ አስቸኳይ ነው እባክሽ አለ። እኔም ምን ሊለኝ ነው ብዬ እያሰብኩ  እዛው ከግሮሰሪያችሁ   ፊት ለፊት ያለው ሆስፒታል ነኝ አልኩት ትንሽ እንኳን አልደነገጠም አስቸኳይ ነው ትመለሻለሸ ቶሎ ነይ አለኝ  እኔም ውጤት ለመስማት ተራዬን እየጠበኩ ስለነበር ዝም ብዬ ወጥቼ ሄድኩ ። ውጤቱን እስክሰማም ጨንቆኛል ግን ለምን ወጥቼ እንደሄድኩ እንጃልኝ። ልክ  አስፋልቱን ተሻግሬ  በር ላይ ስደርስ ማክቤል በር ላይ ቆሞ በፈገግታ ተቀበለኝ የኔ ፊት ግን ጭራሽ አልተፈታም። አቤት ምንድነው አልኩት ከፊት ለፊቱ ቆሜ: አትኮሳተሪ እንጂ ጉዳዩን ደግሞ ግቢና እነግርሻለሁ በናትሽ አልገባም እንዳትይኝ ብቻ መቼም እዚህጋ ቆመን እናውራ አትይኝማ አለ የመማፀን ፊት እያሳየኝ እሺ ብዬ አልፌው ገባሁ ከፊቴ ቀደመና የሆነ ወንበር ስቦልኝ ተቀመጥኩ ምን ልታዘዝ አለችኝ አስተናጋጇ ነበረች አይ ምንም አልፈልግም በቃኝ ስል.. ማኪያቶ አምጭላት አለ ማክቤል :: እሺ ምን ፈልገህ ነው ንገረኝ አሁን እቸኩላለሁ አልኩት። ተረጋጊ እንጂ እስቲ የሆነ ነገር ቅመሺ አለኝ እየሳቀ ነበር ወዲያው አስተናጋጇ ማኪያቶውን ይዛ መጣች እንደዛ የምወደው ማኪያቶ ገና ሲሸተኝ አቅለሸለሸኝ ፉት ለማለት ወደ አፌ  እንኳን ማስጠጋት አቃተኝ አጎንብሼ ልውጣ አልውጣ እያለ የሚታገለኝ ነገር እየከበደኝ  አፌን በሶፍት አፍኜ ስጠባበቅ ትንሽ መለስ ሲልልኝ በቃ ንገረኝ ልሄድ ነው ብዬ ቀና ስል በጣም የምታምር የደም ግባት ያላት ልጅ የማክቤልን ትከሻ ተደግፋ ቆማለች ተዋወቁ ፍቅረኛዬ ነች አለ በማፌዝ አስተያየት እያየኝ ልጅቷ ፈገግ ብላ እጇን ዘረጋችልኝና መርሀዊት እባላለሁ አለች ስትስቅ ድፕሏ ጎላ ብሎ ይታያል ውበቷንም በእጥፍ ይጨምርላታል ውስጤ ቅጥል እያለ ሰላም እባላለሁ ብዬ ጨበጥኳት እጇን ለቀኳትና በጣም እንደምታምር ነግሪያት ተነስቼ ወጣሁ ማክቤል መጣሁ ብሏት ተከተለኝ በህይወቴ እንደሱ ወራዳ ሰው አይቼ አላቅም በጣም ጠላሁት ከኋላዬ መጥቶ እየሳቀ ቆንጆ ናት እንዴት አየሻት ሲለኝ ድምፁ ሊያስታውከኝ ምንም አልቀረውም ነበር ዝም ብዬ ወደፊቴ ሄድኩ እሱ እየተከተለኝ ይለፈልፋል እንዴት ነው ፍቅረኛሽ ሸመጠጠሽ እንዴ አብራችሁ አትታዩም  ወይስ ተከራይተሽው ነበር ብቻ ምላሱን ብቆርጠው በምን እድሌ መጨረሻ ላይ ትግስቴ ሲሟጠጥ በርጋታ ወደሱ ዞርኩና ፍቅረኛህ በጣም ቆንጆ ናት በጣም ደስ ትላለች ግን ደሞ ታሳዝናለች እንዳተ አይነት ሰው ላይ ስለጣላት ለማንኛውም ያዝልቅላቺሁ እኔን ግን ተወኝ እኔኮ በቃ እርግፍ አድርጌ ትቼሀለሁ እኔ የራሴን ህይወት ጀምሬሀለሁ አንተን ከሰው እኩል እንኳን መቁጠር ካቆምኩ ሳምንታቶች አልፈዋል ሰርግህን እንዳትረሳኝ ከቀደምኩህ አረሳህም ብዬው በቆመበት ጥዬው ሄድኩ ልክ ልኩን ስለነገርኩት አልተከተለኝም ብቸኝነት ሲሰማኝ የምሄድበት የሆነ ቦታ አለ እዛ ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ የምርመራ ውጤቱም አለ ለካ ..... ይቀጥላል
Show all...
❤‍🔥 2 2
ሌላ ይጨመር ወይስ??
Show all...
🥰 5
ዝም🤫🤫 በ...
Show all...
3.88 MB
❤‍🔥 2👍 2
ነገ🥹🥹
Show all...
😢 1
ግጥም በvoice ?🥺
Show all...
🥰 5
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ . እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ መንገድ ጥረጊልኝ ይህቺን ብቻ አርጊልኝ! . ስምሽን እያነሱ እንዳያስታውሱኝ በሞተው ትዝታ እንዳይቀሰቅሱኝ ያንቺ አለመሆኔን ዛሬ እንዳሳያቸው ጨረቃን ፀሐይን ምድር አውርጂያቸው ውቅያኖስ ባህሩን ሰማይ ስቀያቸው . እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ የረገጥነው አስፋልት የሄድንበት መንገድ ያ ያለፈው ፍቅር ያ ያለፈው መውደድ ፍፁም ውሸት ብዬ እንድሸመጥጠው ተፈጥሮን አዛቢ መውደዴን እንድተው . እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ ገደሉን ሙዪና ተራራውን ናጂው ደመናን አውርደሽ አፈሩን ውሰጂው የረገጥሽው መሬት አምሮ እንድታይበት በአበባው ፋንታ ሳማ ትከይበት . እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ ያ ሁላ ቃል ኪዳን ተበትኖ እንዲቀር አይጥ ሀይቅ ትዋኝ ዓሳ ሰማይ ይብረር በህይወት ባሉት ምትክ ሙታኖች ይነሱ ነገስታት ይውረዱ ባርያዎች ይንገሱ . ይሄን ካረግሽልኝ መውደዴን ይቅርና መኖር አቆማለሁ በመኖር ብረሳሽ ባለመኖርም ውስጥ አስታውስሻለሁ 🦁🦁🦁🦁
Show all...
🥰 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.