cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢብኑ ነጃሽ

نداء الحق

Show more
Advertising posts
189
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
ኢህሳን ስሙን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል:: «أالإحسان ن تعبد الله كأنك تراه»، <<إن الله كتب الإحسان على كل شيء، فإذا قتلتم فأحسنوا القِتلة، وإذا ذبحتم فأحسنوا الذِّبحة، وليُحدَّ أحدكم شفرته، وليرح ذبيحته.>> https://www.facebook.com/share/p/ZSi1ag4m5ENebYh5/?mibextid=oFDknk
Show all...
<<እዱንያ ላይ እስካለህ ድረስ እያሸነፍክም እየተሸነፍክም መኖር ትችላለህ:: ዱንያን ስትለቅ ግን ያለህ አማራጭ አሸናፊ መሆን ብቻ ነው::>> ከአንድ ወንድም #ኢብኑ_ነጃሽ
Show all...
هناك حزن في الحياة هناك ألم في الحزن هناك لذة في الألم ونحن نستمع!! منقول «በህይወት ውስጥ ሀዘን አለ። በሐዘን ውስጥ ህመም አለ በህመም ውስጥ ደስታ አለ ውስጣችን ይህንን ሁላ ስሜት ያዳምጣል!!» ከሌላ ቦታ አንስቼው ወደ አማርኛ ያዞርኩት ነው። #ኢብኑ_ነጃሽ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0vF7nJN12hYhN8Jvzh333YqnE5VnNGR3SG6DxeEkHVSf17AC4xWNotwGAPbu6jko5l&id=100087455954333&mibextid=Nif5oz
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ የታሪክ መነሻ አለው። ያ መነሻው ለእርሱ ልዩ ቀኑ ነው። ለምሳሌ የሳውዲ ነገስታቶች ሳውዲ አረቢያ የምትባል ሀገር የመሰረቱበት ቀን ለእነርሱ ልዩ ቀናቸው ናት። የነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መወለድ ደግሞ ኡማው የተወለደበት አመት ነው። የቁርአን መውረድም ቢሆን፣ ብቸኛና ቁርአናዊ የሱሀባ ትውልድን ያገኘነውም ይሁን የኢስላሚክ ኢንፓየር መመስረት የመጣውም ነብያችን አለይሂ አፍዶሉ ሶለዋቲ ረቢ ወአተመ ተስሊም መገኘታቸውን ተከትሎ ነው። አላህም የነብዩን ወደኛ መላክ እንደ አላህ ውለታ እንድንቆጥረው እንደዚህ እያለ ያስታውሰናል፦ «لقد من الله على المؤمنين إذ بعث فيهم رسولا من أنفسهم يتلو عليهم آياته ويزكيهم ويعلمهم الكتاب والحكمة وإن كانوا من قبل لفي ضلال مبين» «አላህ በምእመናን ላይ ከጎሳቸው የኾነን፤ በእነርሱ ላይ አንቀፆቹን የሚያነብ፣ የሚያጠራቸው፣ መፀሀፍንና ጠበብን የሚያስተምራቸው የኾነን መላክተኛ በውስጣቸው በላከ ጊዜ፤ በእርግጥ ለገሳቸው። እነርሱም ከዚያ በፊት በግልፅ ስህተት ውስጥ ነበሩ።» ሱረቱ አሊ ኢምራን 164 የመዲና ሱሀቦችም ነብያችን ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይሂ ወደ መዲና ሲገቡ ሁሉም በደስታ ተቀበሏቸው። በደስታ ለመቀበልም ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይፈቅዱታል ወይስ አይፈቅዱትም ብለው ማረጋገጫ አልጠየቁም። ምክንያቱም የአንድ ነገር መሰረቱ እንጂ መሰረቱን ተከትሎ የሚመጣው የመሰረቱ ፋና ላይ መረጃ አይጠየቅምና። ለምሳሌ ቁርአንን ማክበር እንዳለብን ከተነገረን የአከባበሩ ጉዳይ ለእኛ የተተወ ነው። ከፈለግን ሽቱ እንቀባው፣ ከፈለግን እንደሱሀቦቹ ተበታትኖ የነበረውን ፅሁፍ በመሰብሰብ በአንድ ላይ በማድረግ እንጠርዘው ለእኛው የተተወ ጉዳይ ነው። ሁለተኛ ምሳሌ፦ እናታችንን ማክበር እንዳለብንና ማስቀየም እንደሌለብን ከተነገረን የአከባበሩ ሁኔታ ለእኛው የተተወ ነው። ከውጭ ወደ ቤት ስንገባ ግንባሯንም ሳምናት ተሸክመንም ሀጅ አስሀጀጅናት ጉዳዩ ለእኛ የተተወ ነው። አንድ የታዘዝነውን ነገር ተከትሎ የምንሰራውን ስራ ለመስራት ሳይሆን መረጃ የሚፈለገው ለመከልከል ነው። ይህም ማለት መረጃ በከለከለው ወይም ጉዳት በሚያመጣ መልኩ አንፈፅመው እንጂ መረጃው ዝም ባለውና ከጉዳቱ ጥቅሙ ባመዘነ መልኩ መፈፀም እንደሚቻል ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት። እንዳውም አንዳንድ መረጃዎችን ከፈተሽናቸው በፍቅር የተነሳ የተጣሰን ሸሪአዊ ትእዛዝ ነብያችን ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይሂ አይተው ሳይቃወሙ እንዳለፉት ሳይ እኛና መረጃው የትና የት ነው ያለነው? ያስብለኛል። መረጃውን ጥቀስና አብረን እንፈትሸው ምክንያቱም የአንተ አረዳድ ተሳስቶ ይሆናል ካላችሁኝ ይሄውላች። 1ኛ/ በሱሉሁል ሁደይቢያ ጊዜ ቁረይሾች «በሙሀመድ የአላህ መላክተኛና… » የምትለዋን ሰርዝ የአላህ መላክተኛ መሆንህን ስላላመን መሰለን መዋጋት የያዝንህ በምትኩ «በሙሀመድ የአብደላህ ልጅና …» ብለህ ፃፍ ባሏቸው ጊዜ አልይን ረዲየላሁ አንሁ ሰርዝላቸው ሲሏቸው አልሰርዝም ብለው መልስ ሰጥተዋል። ይህ አልሰርዝም የምትለዋ እንቢተኝነት ነብያችንን ከማክበርና ከመውደድ የመነጨ ከመሆኑ የተነሳ ጉዳዩ ያለምንም ተቃውሞ ታልፏል። 2ኛ/ ነብያችን ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይሂ በታመሙ ጊዜና አቡበከር ሲዲቅ ረዲየላሁ አንሁ ኢማም ሁነው ባሰገዱ ጊዜ ድንገት ረሱላችን አለይሂ አፍዶሉ ሰላቲ ወአተመ ተስሊም ከህመማቸው ያገግሙና ጀመአውን ተከትለው ሊሰግዱ ሲሉ አቡበከር ሲዲቅም የነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከኋላ መሆን ሲያውቁ ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተከትለው ለመስገድ በማሰብ በሶላቱ መካከል ወደ ኋላ አፈገፈጉ። ነብያችንም ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይሂ ባሉበት እንዲፀኑ በእጃቸው ቢያመላክቷቸውም የእነርሱን ትዛዝ በመተው ወደኋላ በማፈግፈጋቸው ላይ ፀኑ ከሶላቱ በኋላ ሲጠይቋቸው የአቡ ቁሀፋ ልጅ ነብዩ ባሉበት ኢማም መሆን የለበትም ብየ አስቤ ነው ብለው መለሱላቸው። ነብያችንም ለምን የፍቅርህን ዝንባሌ ከእኔ ትግዛዝ አስቀደምክ ብለው አልነቀፏቸውም። አዎ ዛሬ ረቢእ ነው። ረቢእ ማለት ፀደይ ማለት ነው። ዛሬ ላይ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መወለድ ብቻ ሳይሆን የአረብ ኢስላማዊ ሀገራት ህዝቦች ግፍ ይበቃናል ብለው የአረብን የፀደይ አቢዮት ያቀጣጠሉበትና ለፍትህ ሲሉ ብዙ ዋጋ የከፈሉበትን ትግል ሀ ብለው የጀመሩበት ወር ነው። ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ወደ መዲና ሲገቡ ለመደሰት ሱሀቦች ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፍቃድ እንዳልጠየቋቸው ሁሉ እኔም በእዚህ ወር ለመደሰት ፍቃድ አልጠይቅም። ይልቁንም ሰለፍይ ነን ሱሀባንና ሰለፎችን ነው የምንከተለው ካላችሁ ደሊል የማይጠየቅበት ቦታ ላይ ባለመጠየቅ ሱሀቦችን ተከተሏቸው። ምን እያልክ ነው መውሊድ ቀን መደሰትን እኮ ሺአዎች ናቸው የጀመሩት ካላችሁኝ አንድን ነገር ጥሩና መጥፎነቱን ለማረጋገጥ ሰሪው ማነው ብየ ሳይሆን ስራው ምንድን ነው ብየ ነው የምጠይቀው። ሱንዩ አለም ሂጃብን ቢተው ሺአ ሂጃብን ስለለበሰው ሂጃብ መልበስን ልንተው ነውን? የሱንዩ አለም የኡለማ ምክር ቤት በፖለቲከኞች ሲመራ የሺአውን ፖለቲካ የሚመሩት ደግሞ የሺአ ኡለሞች ናቸው ስለዚህ ፖለቲከኞች በኡለማ መመራት የለባቸውም እንበልን? ይህንን በር ዝጋ ምክንያቱም ውሻ በቀደደው ጅብ ስለሚገባ ከሆነ መከራከሪያችው በሩን ልዘጋ ስል በሩ የሚሰበር ቢሆንስ? ማለቴም ደስታውን ተከትለው የሚመጡ ስህተቶችን ለማገድ ሲባል ረቢኡ ዝም ብሎ ይለፍ ትዝም አይበላችሁ ስትሉ ሙሉ በሙሉ በአመት አንድ ጊዜ እንኳ የሚከናወኑ ኢስላማዊ ዳእዋዎች ያሉባቸው ገጠራማ ቀበሌዎች በአመት አንድ ጊዜም ስለ አላህና ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አይስማ ነው እንዴ እያላችኝ ያላችሁት? እረዥም አመት የነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ስም ሲሰማ በለቅሶ ትርትር ሊል የሚደርስ ህብረተሰብ የተፈጠረው በምን እንደሆነ ለምን አንጠይቅም? እረቢእ ለእኔ ሀይማኖታዊ ባእሌ ባይሆንም ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በመወለዳቸው የምደሰትበት "መሷሊሀል ሙርሰላ" ነው። "መሷሊሀል ሙርሰላ" ማለት ደግሞ ጥቅምን የሚያስገኝ ወይም ጉዳትን የሚከላከል ሁኖ ለመፈቀዱም ይሁን ለመከልከሉ መረጃ የሌለበት ጉዳይ ነው። እንደዚህ አይነቱን ጉዳይ በመጠቀም ዲንን መርዳት እንደሚቻል የኢልምን ሽታ ያሸተተ ሁሉ ያውቀዋል። በአጭሩ ይሄንን ሁሉ ፅሁፍ የፃፍኩት በደስታየ ቀን አትረብሹኝ ለማለት ነው። እኔ በመደሰቴም አትመቀኙኝ ምክንያቱም ደስታውን እኔ አልከለከልኳችሁም። ጭፈራም ክልክል ነው እያላችሁኝ ከሆነ ሀበሻ ሱሀቦች በኢድ ቀን እነብዩ መስጂድ እንደጨፈሩ ቡኻሪ ዘግበውልናል። እኛ ደግሞ ሀበሾች ነን። ሱሀቦች እኮ በኢድ ቀን ነው የጨፈሩት ከኢድ ውጭ ሀራም ነው እያላችሁ ከሆነ በኢድ ቀን ሀራም መስራት እንደሚፈቀድ መረጃ አለን እያላችሁኝ ነው። ስለዚህ ገሩን ዲን እናስረዳህ ብላችሁ የበለጠ አታጥኑብኝ ገለል በሉልኝ። «እኔስ አሽቃራለሁ አንተ ባትደለቅ ይሻልህ ነበረ አንተ ባትኸለቅ።» ያሉት ማን ሸይኽ ነበሩ? والسلام عليكم ورحمة الله وبركاته #ኢብኑ_ነጃሽ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid032skhdhe19PD7wCHdXn5eq8DdddzUFuJxpxQ9ju5k8y58zzMNQt8kh73xKynVZU6fl&id=100087455954333&mibextid=Nif5oz
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

(( «أولئك الذين هدى الله فبهداهم اقتده» (( «እነዚህ (ነብያት)፤ እነዚያ አላህ የመራቸው ናቸው። በመንገዳቸውም ተከተል።» ሱረቱል አንአማ 90 يا الله: إني لا أصلي لك كما يليق بك አላህ ሆይ፦ እኔ ለአንተ የሚገባህን ያህል ልስግድልህ አልችልም፤ ولا أصوم كما كان يفعل داود ነብይህ ዳውድ እንደሚፆሙት አይነት ፆምም አልፆምም፤ ولا أصبر إذا مرضت كما صبر أيوب በምታመምም ጊዜ ነብይህ አዩብ እንደታገሱት አይነት ትግስት ልታገስ አልችልም፤ ولا أسبح بحمدك تسبيح يونس في بطن الحوت ነብይህ ይኑስ በአሳ ሆድ ውስጥ እንዳጠሩህ አይነት ምስጋና ከማጥራት ጋር ቀላቅየ አላጠራህም፤ ولا آخذ ديني بقوة كيحيى እንደነብይህ የህያ ዲኔን በጥንካሬ አልይዝም። (እንደ ያህያ በዲኔ ላይ ጠንካራ አይደለሁም)፤ ولا أغض بصري كما غض يوسف كل جوارحه ነብይህ ዩሱፍ በእዚያ ሁሉ ችግር መሀል (ያልተፈቀዱላቸውን ሴቶች ላለማየት) አይናቸውን እንደሰበሩት እኔ አይኔን አልሰብርም፤ ولست متسامحا لحد القول : إذهبوا وأنتم الطلقاء «ሂዱ እናንተ ነፃ ናችው።» ለምትለው ቃል ተገቢ ሁኜ ይቅርታ የሚገባኝ ሰውም አይደለሁም፤ ولكني مثلهم يا الله أحبك.)) ነገር ግን አላህ ሆይ እኔም እንደ እነርሱ እውደሀለሁ።)) #أدهم_الشرقاوي_رسائل_من_القرآن ፍልስጤናዊው አድሀም አሸርቃው ከቁርአን ምልክቶች በሚለው መፀሀፋቸው ላይ ካሰፈሩት የተወሰደ ሲሆን እኔም ወደ አማርኛ መልሸላችሁ ነው። #ኢብኑ_ነጃሽ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid032MPoDMpf4PaANRacJzGNDPoVcdaCd3oPj5HtAviisHK5A3YW986GLfWgH3Dkiphnl&id=100087455954333&mibextid=Nif5oz
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

إن كلماتنا ستبقى ميتةً لا حراك فيها هامدةً أعراساً من الشموع، فإذا متنا من أجلها انتفضت و عاشت بين الأحياء، كل كلمة قد عاشت كانت قد اقتاتت قلب إنسان حي فعاشت بين الأحياء، والأحياء لا يتبنون الأموات الشهيد #سيد_قطب_رحمه الله «ቃላታችን የሞተ፣ የማይነቃነቅ፣ ህይወት የሌለው፣ (ለብርሀን አገልግሎት እንደማይውሉ) የሰርግ ሻማ ሁነው ይቀራሉ። ለእነርሱ ታምነን ብንሞትላቸው ግን ተነሥተው በሕያዋን መካከል ይኖራሉ። ምክንያቱም ሕያዋን ሙታንን ስለማይቀበሉ።» #ሰመአቱ_ሰይድ_ቁጥብ አላህ ይዘንላቸው #ኢብኑ_ነጃሽ
Show all...
القدس عاصمة قلبنا #ابن_نجاش ቁድስ የልባችን ዋና ከተማ ናት። #ኢብኑ_ነጃሽ
Show all...
Photo unavailable
ይህ ከታች የተሰጠውም ምስክርነትም ይሁን ፎቶ ግራፍ በጀማል አብዱ የአቢዘር ፕሬዝዳንትና በአቢዘር አማካኝነት ሲሆን እኔን እቅዴ ጋር እንድገናኝ በማስብና ለአለሙ ህብረተሰብ ለማስተዋወቅ ታስቦ ጥቅም ላይ የዋለ ስራ ነው። አዎ እቅድህ ላይ ለመድረስ ከአላህ ውጭ ከማንም ጠባቂ መሆን ባይጠበቅብህም አላህ እራሱ እንደ አቢዘር አይነቱን እድል ሲያመቻችልህ አመስጋኝ አለመሆን ደግሞ ሞኝነት ነው። እኛ ባቲዎች ከተማችን ጠባብ ብትሆንም እኛ ግን ጠባብነትና ቀበሌያዊ እሳቤ አይመቸንም። በእዝች ጠባብ መንደር ውስጥ ብዙ ቅኖችና የሰፊ አእምሮ ባለቤቶች ሞልተዋል። ይህንን ሰፊነት ቀጣይነት እንዲኖረው አዲሱን ትውልድ በቁርአን ቤት ከተርቢያ ጋር በተቀናጀ መልኩ የሚማርበትና የሚታነፅበት መአከል ሊኖረው ግድ ይላልም ጊዜም የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም። ዛሬ ላይ በከተማችን ለችግርተኛ ህዝቦቻቸው በአቢዘር፣ በኢህሳንና በላታህዘን ስር በመደራጀት እረፍታቸውን ያጡ ወጣቶች የትላንት ህፃናት አይደሉን? ስለዚህ የዛሬውም ህፃናት የነገ ተስፋዎቻችን ናቸው፤ ግን ደግሞ ተስፋዎቻችን የሚሆኑት ሁሉ ነገሩን ለእነርሱ በመስጠት ዋጋ የሚከፍል ሙረቢ ሲያገኛቸው ነው። አለበለዚያ ከተለቀቁ ሀገር ገንቢ መሆናቸው ቀርቶ ሀገር አጥፊ ሀይልም ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ ይህንን ጉዳይ በመረዳት ሁላችንም የተርቢያን ተቋም የመመስረት አላማን ካነገበ ጎን መቆም ይኖርብናል። #ኢብኑ_ነጃሽ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0Bq3oW8HNtTSM5wLucoQqcNLtrbBiZC7DeqExywEZPFK6YWa2zSiWQve5BAQXMnzRl&id=100087455954333&mibextid=Nif5oz
Show all...
Repost from N/a
መአልሊም ፊጥጦሪቅ (ፍኖተ-ብርሀን) ወይም የጎዳናው መብራት በሚል በአማርኛ ተተርጉሞ የቀረበና አለም እንደት መመራት እንዳለባት አቅጣጫ የጠቆመ ድንቅ የኡስታዝ ሰይድ ቁጥቡ (rehimehullah) መፅሀፍ t.me/seidabdumohamed
Show all...
Copy የኦስታዝ ሸሂድ ሰይድ ቁጥብ.pdf41.07 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.