cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የአሊ መስጂድ ጀመአ Official

This is Ali Lomi Meda Mesjid Official Channel

Show more
Advertising posts
280
Subscribers
No data24 hours
+137 days
+6930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

08:14
Video unavailableShow in Telegram
IMG_8894.MP486.27 MB
መዉሊድን በተዋቀረ እና በተደራጀ መልኩ ማን ጀመረዉ ? ======================= • መዉሊድ ማለት ሰዪዳችን ﷺ የተወለዱበትን እለት በደስታ ማሳለፍ እንጂ መዉሊድን ዒድ አድርጎ መያዝ  አልያ መዉሊድን እንደ ዒባዳ መቁጠር አይደለም ፡፡ • ዑለሞች ፍቅር ማለት ተፈቃሪን ሁልጊዜ ማሰብ እና ማስታወስ ነዉ ይሉናል ፡፡ የመወሊድ ክብረ በዐል በየአመቱ እንዲሁም ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር ፈር የቀደደዉ የአዩባዊ ሱልጣኔት አካል እና የሰላሁዲን አል-አዩቢ እህት ባል የሆነዉ <መሊክ ሙዘፈር> ነዉ ፡፡ መጠሪያ ስሙ <ኩኩር ኢብን ዐሊይ> ይሰኛል  ኤርቢል በምትባል በዒራቅ ሰሜናዊ ክፍል የምትገኝ ግዛት መሪም እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ ፡፡ • ኢማም ጀላሉዲን አስ-ሲዩጢ <ሁስኑል መቅሲድ ፊ ዐመሊል መዉሊድ> በተሰኘ መጽሀፋቸዉ ላይ መሊክ ሙዘፈር መዉሊድን በተዋቀረ እና በተደራጀ መልኩ እንዳስጀመረዉ አዉስተዋል ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዋቀረ እና በተጀራጀ መልኩ የተከበረዉም በ7ኛዉ ዓ.ሂ መግቢያ አካባቢ ነዉ ፡፡ ( 7ኛ ዓ.ሂ የሚባለዉ ከ600-700 ዓ.ሂ  ድረስ ያለዉ ክ/ዘመን እንደሆነ ልብ ይሏል) • መሊክ ሙዘፈር ዓሊም እና ፈቂህ ነበሩ ይህንን ድርጊት ( መዉሊድን በተደራጀ እና በተዋቀረ መልኩ መጀመሩን) ሲከዉኑ ይሁንታቸዉን ከቸሩ ዑለሞች መሀል <አል-ሀፊዝ ኢብን ሐጀረል አስቀላኒ> የእርሳቸዉ ተማሪ የነበሩት <አል-ሀፊዝ አስ-ሰኻዊ> እንዲሁም<አል-ሀፊዝ አስ-ሲዩጢይ> ይገኙበታል ፡፡  ኢማም ጀላሉዲን አስ-ሲዩጢ 'አልሀዊ ሊል ፈታዋ' በተሰኘዉ ድርሰታቸዉ ላይ በመዉሊድ የተደሳ ሰዉ የሚያገኘዉን ትሩፋት እና ደረጃ ጠቅሰዋል ፡፡ በገፅ 189 ላይ • መዉሊድ በፋጢሚዮች ነዉ የተጀመረዉ ኢብን ከሢር 'አልቢዳያ ወንኒሀያ' ላይ ይህንን ጠቅሰዋል የሚባለዉ ቅጥፈት ነዉ ፡፡ ኪታቡን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ብታገላብጡት  ይህ እንደሌለ ማረጋገጥ ይቻላል በነገራችን መሀል የወሀ^ቢዝም አመለካከት አራማጆች ከሚታወቁበት እኩይ ባህሪያቸዉ ዉስጥ የዉሸት ምንጭን አለቅጥ ለፕሮፓጋንዳ መጠቀማቸዉ ነዉ ፡፡ እጅግ በጣም ብዙ ለቁጥር የሚከብዱ የዉሸት ምንጮችን ይጠቀማሉ ከዛ ዉስጥ አንዱ ከላይ ያሰፈርኩት ኢብን ከሢር ላይ የተቀጠፈዉ ነዉ ፡፡ አላህ ቢፈቅድ በሌላ ጊዜ እና ርዕስ የዉሸት ምንጮቻቸዉ ፣ የቀየሯቸዉን መጽሀፎች ፣ የዋሹባቸዉ ምሁራኖች ፣ በስማቸዉ ኪታብ የሰነዱባቸዉ ልሂቃንን እንዳስሳለን ፡፡ • ምንም እንኳ ኢብን ከሢር 'አልቢዳያ ወንኒሐያ' ላይ መዉሊድ በፋጢሚዮች እንደተጀመረ ባያስቀምጡም ፋጢሚዮች (የሺዐ አስተሳሰብ አራማጅ ) ናቸዉ የጀመሩት የሚሉ አጥኚዎች እንዳሉ ግን አይካድም ፡፡ መዉሊድን ፋጢሚዮች አልጀመሩትም ነገር ግን ፋጢሚዮች  ጀመሩት እንኳ ብንል የመዉሊድ ትክክለኛነት ላይ ምንም ተጽዕኖ አይኖረዉም የሚያመጣዉ ችግርም የለም ፡፡ • ምክንያቱም በዲናችን ብዙ ጠቃሚ የሆኑና በእለት እለት ክንዉናችን የምንፈፅማቸዉ ሀይማኖታዉ ክንዉንች ከሸይ^ጣን ፣ ከአይ^ሁድ ፣ ከዛሊም ወዘተ... ተወስደዋል እንደ ናሙና የተወሰኑትን በግርድፉ እንመልከት ፡፡ የቁርአንን ሀረካ ፣ ቁጥሮች ፣ ስሙኖች ማን ነዉ ያበጀዉ? በዳይ የነበረዉ በዙልም ስሙ የናኘዉ ብዙ ሰሀቦችን የገደለዉ ለቁጥር የሚታክት የነብዩን ሰለላሁ፡ዐለይሂ ወሰለም ባልደረቦች  ያንገላታዉ እና ያሰቃየዉ ሀጃጅ ኢብን ዩሱፍ ነዉ ፡፡  ስለዚህ ቁርአን የምንቀራበትን መንገድ ያቀለለዉ ሀጃጅ ስለሆነ ቁርአን ላይ ያሉ ምልክቶች መጥፎዎች ናቸዉ ፣ አይጠቅሙንም ፣ መወገድ አለባቸዉ የሚል አይተንም ሰምተንም አናዉቅ ፡፡ <ኢማም ዐሊይ ኢብን አቢ ጣሊብ> ከረመላሁ ወጅሐሕ እንዲህ ይሉ ነበር "ላ ዩዘኑል ሀቁ ቢንናስ በል ዩዘኑ-ንናሱ ቢል ሀቅ" "ሰዎች በሀቅ ይለካሉ እንጂ ሀቅ በሰዎች አይለካም" እንደማለት ነዉ ፡፡ • ሰዪዳችን ﷺ መዲና እንደዘለቁ አይሁዶች አንዲትን ቀን ሲፆሙ ተመለከቷቸዉ እናም የሚፆሙበትን ምክንያት ሲጠይቋቸዉ አይሁዶቹ እንዲህ አሉ "አላህ ሙሳን ዐላ ነቢዪና  ወዐለይሂ አፍደሉ ሰላቲ ወስሰላም ከፊርዐዉን ነፃ ያወጣበት ቀን ስለሆነ ነዉ" ሰይዳችንም "ነህኑ አዉላ ቢሙሳ ሚንኩም" "ለሙሳ ከእናንተ ይልቅ እኛ የተገባን ነን" ብለዉ ያንን ቀን ሙስሊሞች እንዲፆሙ አዘዙ ይህ ቀንም የሙሀረም ወር አስረኛዉ ቀን <ዐሹራእ> ነዉ ፡፡ ከአይ^ሁዶች ስለተኮረጀ እና የነርሱን ተግባር በመመልከት ስለተጀመረ የዐሹራእን ቀን መፆም እንተዉ? አይ^ሁዶች ለሙስሊሞች ዋነኛ ጠላ^ት ስለሆኑ ካሁን በኋላ የዐሹራእን ቀን እንዳትፆሙ ተብሎ ይታወጅ?  ከንቱ ትዉልድ ተመሳሳይ ቦታ ላይ አንድ አይነት ምክንያት እያለ ለአንዱ ጥያቄ ሰንዝሮ ለሌዉ የሚተዉ..... ምፅ • ሰይዱና አባ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንህ <አየተል ኩርሲይን> ከማን የተማሩ ይመስለሀል ከዘይነልዉጁድ ከመሰለህ ተሳስተሀል ከትልልቆቹ ሰሀቦች ነዉ ብለህ ካሰብክም አሁንም መክነሀል ሰይዱና አባ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንህ <አየተል ኩርሲይን> ያወቁት ፣ የቀሰሙት ፣የተማሩት እንዲሁም ለየት ያለ ጠቀሜታ እንዳላት  እና እሷን የቀራ ሰዉ በአላህ ጥበቃ ስር እንደሚሆን የነገራቸዉ አባ ሙራ ነዉ ሊያዉም ከሙሉ ገለፃ እና ማብራሪያ ጋር ፡፡ኅላ ክስተቱን ለሰይዳችን መጥተዉ ሲነግሯቸዉ " እሱ ዉሸታም ነዉ የነገረህ ነገር ግን እዉነት ነዉ" ነበር ያሏቸዉ ፡፡ ነገር ግን ሰይዱና አባ ሂር ከሸይጣን የቀሰምኩት እዉነታ ነዉ ብለዉ <አየተል ኩርሲይን> ለመጠበቅ ብለዉ ከመቅራት አልተወጉዱም ከላይ በከፊል የዘረዘርናቸዉ ናሙናዎች ናቸዉ ደዚህ አይነት ክስተት በዲናችን ዉስጥ ለጉድ ታጭቀዋል የእስልምና መርህ ግን ማን ጀመረዉ? ከማን ተወሰደ? ማን ነዉ አስተማሪዉ? ማን ነዉ ጠንሳሹ? ሳይሆን ስራዉ ልክ ነዉ ወይስ ልክ አይደለም ነዉ ፡፡ • በሀገራችን ወደተደራጀ በዕል የቀየሩት እ.አ.አ በ1798 ጀማ ንጉስ በመባል የሚታወቁት ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ አሽ-ሻፊዒይ መሆናቸዉ ይነገራል ከዚያ ለጥቆ የደረሳቸዉ ደረሳ የነበሩት ጀማሉዲን አል-አኒይ አስቀጠሉት የዳና ከዋክብት የነበሩት ሪጃሎች በይበልጥ አጠነከሩት በሐጅ ሙሀመድ ሣኒ ሀቢቢ ትግል በ1981 ዓ.ል  በደርግ ዘመነ መንግስት ብሔራዊ በዕል ሆኖ ታወጀ ፡፡             *                *                 *
Show all...
🥰 2
AUDIO-2024-09-05-22-21-57.m4a2.82 MB
03:27
Video unavailableShow in Telegram
11.81 MB
01:21
Video unavailableShow in Telegram
15.00 MB
የሰይደል ዉጁድ (ﷺ) ታሪክ በዋነኛነት ሁለት እርከኖች አሉት፡፡ ከመወለዳቸዉ በፊትና ከተወለዱ በኋላ፡፡ የመጀመሪያዉ የ‹‹ቡጡን›› /አህመድያ/፣ሁለተኛዉ የ‹‹ዙሁር››/ሙሀመድያ/ ዘመናት ይባላሉ፡፡ የመድሁ ንጉስ በቀጣዩ ስንኝ እነዚህን ሁለት እርከኖች ይጠቅሳሉ፡- አልሀምዱ ሊላሂ በረህመት ላመጣዉ፤ ላለፈዉ ላሁኑ ኋላም ለሚመጣዉ፤ ከሀድረተል ‹‹ቡጡን›› ‹‹ዙሁር›› ላይ ላወጣዉ፤ የታሪክ (ሲራ) ጸሀፊዎች የመጀመሪያዉን እርከን ብዙ አያተኩሩበትም፡፡ ዘራቸዉን በመቁጠር ብቻ በስሱ ያልፉታል፡፡ ተንደርድረዉ እዉልደታቸዉ ይደርሱና የመካ፣የመዲና ዘመን እያሉ ይቀጥላሉ፡፡ ይበልጡኑም ከዘመቻዎች (መጋዚ) ላይ በማተኮር እርሳቸዉን ሳይሆን ልፋትና ስኬታቸዉን ዘርዝረዉ ይፈጽማሉ፡፡ ይህን ያጻጻፍ ስልት ‹‹Horizontal›› ብየ ሰይሜዋለሁ፡፡ ከ‹‹ዐሪፎች›› ዘንድ ግን የመጀመሪያዉ እርከን እንዲህ በዋዛ አይታለፍም፡፡ ለሁለተኛዉ መሠረት ነዉና ልዩ ትኩረት ይሰጡታል፤ በወጉም ይፈትሹታል፤ መርምረዉ ይደመሙበታል፤ በፍቅር ይቀኙበታል፤ ታዳሚን ወደዛ ሩቅ ዘመን በስሜት ይወስዱታል፤ ‹‹ኩንሀቸዉ›› ከ‹‹ዐማዉ ተመንጥቆ፣በጀማል ተንጠቅጥቆ›› እስከ ነቢ አደም መፈጠር እስኪደርስ፣ ከዚያም ‹‹በጡሀራ ማጠን›› እየተረማመደ ከእናታችን አሚነት ሆድ እስኪረጋ ድረስ ያለፉ ሚሊዮኖች ዓመታትን፣በዩኒቨርሱ ሙዳይ ዉስጥ ከትዉልድ ትዉልድ ወላጆች እየተመረጡላቸዉ በክብር የቆዩባቸዉን ዘመናት፣በነዚህ ዘመናት የተፈጸሙ አስደማሚ ነገሮችን በልዩ ቅኝት፣በፍቅር ብዕር እየከተቡ ይመስጡናል፡፡ የ‹‹ዘይኑል ዉጁድ›› (ﷺ) ዕዉነተኛ ክብር፣አቻ የለሽ ዝና፣ ጥልቅ ማንነት እጅግ ሰፊና ምሉዕ፣እጅግ ድንቅና ዉብ፣እጅግ ማራኪ በሆነ ሁኔታ የተገለጸዉ በዘመነ-‹‹ቡጡን›› እንደሆነ በጥልቅ ከማመን የመነጨ ስልት ይመስላል፡፡ ሁለተኛዉን የህይወት እርከን ሲዳስሱም ከዘመቻዎች (መጋዚ) ይልቅ ስብዕናቸዉን /ኸልቀን ወኹሉቃ/ ለመግለጽ የበለጠ ይተጋሉ፤ በ‹‹ወስፋቸዉ›› ይጠበባሉ፡፡ ይህን ያጻጻፍ ስልት ደግሞ ‹‹Vertical›› ብየዋለሁ፡፡ የመጀመሪያዉ አጻጻፍ ይበልጡኑ ከሥራዎቻቸዉና ከስኬቶቻቸዉ፣ሁለተኛዉ ደግሞ ከስብዕናቸዉ ጋር ያቆራኙናል፡፡ የመጀመሪያዉ ዕዉቀትን፣ ሁለተኛዉ ከመረጃ በተጓዳኝ ፍቅርን፣መደመምን፣መመሰጥን፣ በናፍቆት መብሰልሰልን፡፡ የመጀመሪያዎቹ ይበልጡኑ በስድ ንባብ /ነስር/፣ሁለተኛዎቹ በግጥምና ቅኔ ሀሳብ ያመርታሉ፡፡ ሁለቱ ወገኖች የ‹‹ዉጁዱን ሙሽራ›› (ﷺ) የሚስሉበት መንገድ ከሞላ ጎደል በ‹‹Classical›› እና በ‹‹Modern›› ሊትሬቸሮች መካከል ያለዉን ልዩነት ይመስላል፡፡ የሀገራችን መሻኢኾች በአብዛኛዉ በሁለተኛዉ ስልት የተካኑ ናቸዉ፡፡ ሁሉም ወገኖች ወለላዉ ነቢን (ﷺ) በየራሳቸዉ መንገድ አስተዋዉቀዉናልና አላህ ይመንዳቸዉ፤ ገለታ ይድረሰዉ በሌሊትም በቀን፣ አስወድዶ እኒህን እንዳስተዋወቀን፣ የሰይድ ጫሌን ‹‹መላይካ አንቢያ የበለጠዉ›› ድንቅ ሥራ መሠረት አድርገን የወለላወ ነቢን (ﷺ) ከ‹‹ቡጡን›› እስከ ‹‹ዙሁር››፣ የህይወት እርከን አልፎ አልፎ እያነሳን ጭዉዉታችንን እንቀጥላለን-ኢንሻአላህ፡፡ https://t.me/hassentaju
Show all...
👍 1👏 1
02:46
Video unavailableShow in Telegram
32.27 MB
አሏህ ፈቀደ’ና ፍጥረቱን ሊያድሰው፣ ጨለማውን ገፍፎ በኑር ሊፈውሰው፣ መካ ቤቱ ግድም አንዋሩን ለኮሰው፣ ታ’አሚነቱ ማጥንት የተጠነሰሰው፣ ሰጠን ትልቁን ሰው፣ ተ ኢብኑ አድናኔ። በረቢዕ ሆነና የመውሊድ ቢሻራ፣፣ ሊያጅብሁ ታጠቀ የመላዒካ ዙምራ፣ ለ’ናትሁ አዋላጅ ተጀነት ተጠራ፣ አሲያ ደረሱ ሲቲ መርየም ጋራ፣ የጀነት ሙሽራ የሆኑት ለዘይኔ። የረቢዑ ሒላል ሰይድ ሙሐመዱ፣ አምረው ተኳኩለው ሰኞ ተወለዱ፣ የዘለቁ ጊዜ አንጥሰው ሓምመዱ፣ ሪዋየተን ኡኽራ ብሎ አለ ሰጀዱ፣ እሰይ ተወለዱ፥ በየውመል ኢስነይኔ
Show all...
የኣዘል ንጉስ ነው ጌታው የወደደው፣ ሹመትን ጠቅልሎ ብቻውን ወሰደው፣ ሌላውን ተስሩ እንዲሆን ፈረደው፣ ረቢዕ አዝልቆት ነው ከውኑን የኣየደው። ሲቲና አሚነት ሰኞ ብትወልደው፣ ኑሩ ዘለቀ’ና ናሩን አበረደው፣ ኑሩ ነው የኪስራን ጉልላት የናደው፣ ኑሩ ነው ኣغያሩን ከ’ምድር ያስወገደው፣ የዞላሙን አንጃ አርቆ ሰደደው፣ ያንቀላፋን ኹላ ቢሻራው ጀደደው፣ በሃኢሙን ሳይቀር ደስታው አስረገደው፣ ፍቅሩ አያሉን ሰው ምርኮ’ኣርጎ ወሰደው። ረቢዕ ሆነ! ለበይከ ያ ረሱለሏህ!💚
Show all...
🥰 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.