cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Wolkite University yeselefiyah channel

የዚህ ግሩፕ ዓለማ 1. ከመንሐጅ ጋር በተያያዘ ያሉ ሙሓደረዎች ፣ምክሮችና ሌላም ጠቃሚ መልዕክቶች በማስተላለፍ ለመመካከር 2.ቻነሉ በተለይም WKU ና አከበቢውን በተመለከተ ከሰለፊዮች ጋ ሀቅን የምንማመርበት አጥማሚዎችን የምነስጠነቅቅበት አወዘጋቢዎችን የምናጋልጥበት ግራ የተጋቡትን የምናመለክትበት ይሆነል በአለሀ ፍቃድ እንሸ አላህ 3 WKUተማሪዎችን የሚመለከት መልእክቶችን ለማስተላለፍ ነው

Show more
Advertising posts
1 170
Subscribers
-124 hours
+47 days
+2530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

~
إنتبهوا عند كتابة هذه الكلمات :
~ إنشاء الله ❌ إن شاء الله​ ✔ لأن إنشاء اللَّهَ تعني تأسيس اللَّهَ وَبنيانه لَكِنْ إن شاء اللَّهَ تعني إِذَا أراد اللَّهَ ~ الله وأكبر ❌ الله أكبر ✔ لأن اللَّهَ وأكبر تعني اللَّهَ وَشخص اسمه أكبر لأن الواو حرف عطف لَكِنْ اللَّهَ أكبر تعني ٱلله أكبَر مِنْ كُل شيء . ~~ ����​‏​‏​‏​‏​‏​‏​‏​​​​​​اللهم صلي على محمد ❌ ‏​‏​‏​‏​‏​‏​‏​‏​​​​​​اللهم صلِّ على محمد ✔ لأن صلي فيها الياء والياء ياء تأنيث وَاللَّهَ لَيْسَ مؤنث . ~~ فاعفوا عنا ❌ فاعفُ عنا ✔ لأن الواو واو جماعة ، وَاللَّهَ وَاحِد أحد . ~ ي رب - ي ربي ❌ يَاَ رب -  يَاَ ربي ✔ لأن الياء ياء نداء ، فَإِذَا تم اختصارها لَايصبح هناك نداء ~ جزاك الله ألف خير ❌ جزاك الله خير ✔ لأن جزاك اللَّهَ خير مَنْ قالها فقد أبلغ فِيْ الثناء ، وَالخير يشمل كُل شيء وكلمة ألف فيها تحجير لخير الله .  ~~~~ اللهم أمين يارب ❌ آمين يَاَ رب ✔ مِنْ سلامة الصياغة أَنْ تقول فقَطْ .. آمين يَاَ رب ~ الحمد الله ❌ الحمد لله ✔ لأن الحمد اللَّهَ تعني أَنْ الحمد هُوَ اللَّهَ ، لَكِنْ الحمد لله تعني الحمد وَالشكر لله تعالى . ~~~~ عبارة خطيرة قد تؤدي الى الشرك والعياذ بالله وهي ان  تقول 👈 [ بكرة يحلها ألف حلال ] والصح [ يحلها الله سبحانه ] فقول " ألف حلال "تعني أن هناك ألف رب "لااله الا الله " " انشرها لعل الذكرى تنفع المؤمنين. ( فمن كتم علماً لجمّ بلجام من نآر)
Show all...
- *( لا تقول "صدق الله العظيم" بعد قراءة القرآن )* *قال الشيخ صالح الفوزان:* *لم يرد أن النبيﷺ ولا أحداً من صحابته، أو السلف الصالح كانوا يلتزمون بهذه الكلمة بعد الإنتهاء من تلاوة القرآن، فالتزامها دائماً واعتبارها كأنها من أحكام التلاوة ، ومن لوازم تلاوة القرآن يعتبر بدعة ما أنزل الله بها من سلطان .* [المنتقى (ج1 ص141)].
Show all...
Show all...
Wolkite University yeselefiyah channel

የዚህ ግሩፕ ዓለማ 1. ከመንሐጅ ጋር በተያያዘ ያሉ ሙሓደረዎች ፣ምክሮችና ሌላም ጠቃሚ መልዕክቶች በማስተላለፍ ለመመካከር 2.ቻነሉ በተለይም WKU ና አከበቢውን በተመለከተ ከሰለፊዮች ጋ ሀቅን የምንማመርበት አጥማሚዎችን የምነስጠነቅቅበት አወዘጋቢዎችን የምናጋልጥበት ግራ የተጋቡትን የምናመለክትበት ይሆነል በአለሀ ፍቃድ እንሸ አላህ 3 WKUተማሪዎችን የሚመለከት መልእክቶችን ለማስተላለፍ ነው

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ እንደሚታወቀው ጤና ተማሪዎች በቀን 3-4መግባተቸው ይተወቃል ስለሆነም ጀማአቺን ባመረ መልኩ ጀመዓ ጁመዓ እና ደርስ እየተሰጠ ይገኛል ስለዚህ ጁማአችን እንዳልተቋረጠ ለመሳወቅ እኖዳለን ከዚህ በመቀጠል በየ ቦታው ብዙ ወንድም እህቶች ለመስጂዳችን ጉዳይ ደፈ ቀና እያሉ ነው አለሀ ይጨምርላቸው ዱአ አድርጉላቸው በመስጂድ ;በገበያ እየሰበሰቡ ይገኛሉ ነገር ግን ትንሽ ናቸው(ትንሽ ቦታ ነው) ስለዚህ ሁላችንም በያለነበት በተለይ ሰፈር(ቤተሰብ) ጋ የሆናቹሁ አደራ አደራ ለአለሀ ብለን የቸልነውን ያህል ጥረት እናድርግ ከተባበርን በጣም ቀላል ነውና በሁሉም ዘርፍ ማለተም ኩፖን በመሸጥ;በጁምአ በመሰብሰብ; በገበያ ; አህለል ከይር በመፈለግ; ለመስጂዳችን እናመጣለን ያልነውን500እና ከዛ በለይ ሁሉም ተማሪ በማምጣት ሀላፍቲናችን እንወጣ በኢክላስ ባረከላሁ ፊኩም
Show all...
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች ————— ① መታጠብና መቀባባት ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል] ② ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል] ③ በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል] ④ መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ) ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል] ⑤ ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ) ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።] ⑥ ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።] ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።] ⑦ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።] ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም። ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Show all...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ እንደሚታወቀው ጤና ተማሪዎች በቀን 3-4መግባተቸው ይተወቃል ስለሆነም ጀማአቺን ባመረ መልኩ ጀመዓ ጁመዓ እና ደርስ እየተሰጠ ይገኛል ስለዚህ ጁማአችን እንዳልተቋረጠ ለመሳወቅ እኖዳለን ከዚህ በመቀጠል በየ ቦታው ብዙ ወንድም እህቶች ለመስጂዳችን ጉዳይ ደፈ ቀና እያሉ ነው አለሀ ይጨምርላቸው ዱአ አድርጉላቸው በመስጂድ ;በገበያ እየሰበሰቡ ይገኛሉ ነገር ግን ትንሽ ናቸው(ትንሽ ቦታ ነው) ስለዚህ ሁላችንም በያለነበት በተለይ ሰፈር(ቤተሰብ) ጋ የሆናቹሁ አደራ አደራ ለአለሀ ብለን የቸልነውን ያህል ጥረት እናድርግ ከተባበርን በጣም ቀላል ነውና በሁሉም ዘርፍ ማለተም ኩፖን በመሸጥ;በጁምአ በመሰብሰብ; በገበያ ; አህለል ከይር በመፈለግ; ለመስጂዳችን እናመጣለን ያልነውን500እና ከዛ በለይ ሁሉም ተማሪ በማምጣት ሀላፍቲናችን እንወጣ በኢክላስ ባረከላሁ ፊኩም
Show all...
✅ የቢዳዓ ባልተቤቶች እንደ ጊንጥ ናቸው አል ኢማሙል በርበሃሪይ – ረሒመሁላሁ — ስለቢዳዓ ባልተቤቶች ሲነግረን እንዲህ ይላል : – يقول البربهاري – رحمه الله – : " مثل أصحاب البدع مثل العقارب ، يدفنون رؤوسهم وأبدانهم في التراب، ويخرجون أبدانهم، فإذا تمكنوا لدغوا. وكذلك أهل البدع، هم مختفون بين الناس، فإذا تمكنوا بلغوا ما يريدون " طبقات الحنابلة ( 2/44 ) " የቢዳዓ ባልተቤቶች እንደ ጊንጥ ናቸው , አንገታቸውና ሰውነታቸውን አፈር ውስጥ ይደብቃሉ , ጅራታቸውን ያወጡና ሲመቻቸው ይነድፋሉ ። የቢዳዓ ባልተቤቶችም ልክ እንደዚሁ በሰዎች ውስጥ ይደበቃሉ ሲመቻችላቸው የሚፈልጉበት ይደርሳሉ " ። 🔹 ይህ ኢማም በሶስተኛው ክ/ዘመን የነበረ ሲሆን አሁን ስላለው ሁኔታ የሚናገር ይመስላል ። የቢዳዓ ሰዎችን ማንነትና ምንነት በመዘርዘር ከገለፁና ከእነርሱ ጋር ሊኖረን የሚገባውን ግብረገብነት የሰለፎችን መርህ በማስቀመጥ ግንባር ቀደሙን ከሚዙ አኢማዎች አንዱ ነው ። አላህ ካለ ሸርሑ ሱና የሚለው ኪታቡን በቅርቡ እንጀምራለን ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉. በኢልያስ ፈረስ የመመይዖችን መንሀጅ - በደንብ ቃኝቶ፤ የደዕዋቸውን አከሄድ - በማስረጃ አጥርቶ፤ የአቋማቸውን መውረድ - አስተውሎ አይቶ፤ የመርከዙን ሰዎች - በይፋ አውስቶ፤ ኢልያስ አህመድን - በስሙ አንስቶ፤ በሚያስገርም ወኔ - በግልፅ አውርቶ፤ ትናንት ወቅሶ ነበር - አውግዞ ተችቶ፤ ዛሬ ማውገዝ ትቷል - የሀቁን መንገድ ስቶ፤ የተምዪዕን መርፌ - (ኦቨር ዶዝ) ተወግቶ፤ ሰላሰዋን ኪኒን - በጥብጦ ጠጥቶ፤ በተመዩዕ ቫይረስ - እጅጉን ተጎድቶ፤ እልም ያለ እንቅልፍ - ለጥ ብሎ ተኝቶ፤ የትናንቱ (ገይራ) - ወኔው ሁሉ ሞቶ፤ ለመጅሊሱ ሰዎች - ትከሻውን አስፍቶ፤ ትናንት የተቻቸውን - ሙመይዖችን ትቶ፤ ሰለፊዮችን ወግቷል - ምላሱን አውጥቶ፤ የረድ ጉረኞች ብሏል - ዛሬ አፉን ከፍቶ፤ ሱሩሪዩ ጀይላን - መረቡን ዘርግቶ፤ ያሴረው ሴራ - እውን ሆነ ዘግይቶ፤ የእነ ሳዳትን - የእውቀት ልክ አይቶ፤ ሴራው እንደሚሳከ - በፊትም ገምቶ፤ ሰብሩ ይመለሳል - ይህን መንገድ ትቶ፤ ብሎ ነግሮን ነበር - እውን ሆነ ሰንብቶ፤ የሱሩሪዩ ጀይላን - ዓላማው ተሳክቶ፤ በኢልያስ ፈረስ - ዛሬ ሳዳት ወጥቶ፤ ወደ ተምዪዕ ሄደ - ቀልጦ ተንሸራትቶ፤ የትናንቱ (ገይራ) - ወኔው ሁሉ ቀርቶ፤ በሰላሰዋ ኪኒን - ኢልያስ ጎትጉቶ፤ ሳዳትን ወሰደው - እንደ በግ ጎትቶ፤ የሱሩሪዩ ጀይላን - ዓላማው ተሳክቶ፤ እሺ ብሎ ሄደ - ሳዳትም ተስማምቶ፤ ከትናንቱ መንሀጅ - ከሀቅ ቶብቶ፤ በኢልያስ ፈረስ - ዛሬ ሳዳት ወጥቶ፤ ወደ ተምዪዕ ሄደ - ሰለፊያን ትቶ፡፡ ✍️ (ኢብኑ ኑሪ) መስከረም 9/2017 ስልጤ (ሳንኩራ) https://t.me/YusufAsselafy https://t.me/YusufAsselafy
Show all...
🎤 Ibn Muzayan ~ ኢብን ሙዘይን! ሁለንተናዊ ከፍታ የሚገኘው በቁርዓንና ሐዲስ ብቻ ነው።

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ ደዕዋ ሰለፊያ ማሰራጫ ይሆናል ኢንሻ አላህ!! አላህ መልካም የሻለትን~ ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል ።

https://t.me/YusufAsselafy

👉  የኸድርና የነብዩላሂ ሙሳ ታሪክ                 ክፍል አንድ      ቁርኣን ላይ ትኩረት ከተሰጣቸው አስተማሪ ታሪኮች ውስጥ የነብዩላሂ ሙሳና የኸድር ታሪክ ነው ። በዚህ ታሪክ ውስጥ ትልቁ አስተማሪ ነገር ማንም ቢሆን በእውቀት ጥግ ደርሻለሁ ማለት እንደሌለበት አላህ ከባሮቹ ውስጥ ለሚሻው ሰው ጥበቡ ባስፈረደው የእውቀት አይነት ለየት እንደሚያደርገው ።      በዚህ ታሪክ ውስጥ ነብዩላሂ ሙሳ ረሱልና ከዛም ከፍ ባለ ደረጃ ዑሉል ዐዝም ከሚባሉት ውስጥ ናቸው ። ኸድር ደግሞ በቀደምት የኢስላም ሊቃውንቶችና እስካለንበት ዘመን ባሉ ተከታይ የኢስላም ሙሁራኖች እንደተረጋገጠው ነብይ መሆናቸው ነው ። በመሆኑም ኸድር ማለት ከነብያቶች ውስጥ አንዱ ናቸው ። ይህ ማለት በደረጃ ነብዩላሂ ሙሳ ይበልጣሉ ማለት ነው ። ምክንያቱም የረሱልነት ደረጃ ከነብይነት ደረጃ የሚበልጥ መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ ። ነብዩላሂ ሙሳ ደግሞ ከረሱልም በላይ አምስቱ ዑሉል ዐዝም የተባሉት ውስጥ ናቸው ።        ነገር ግን የጥመት አንጃ የሆኑት ሱፍዮችና ሺዓዎች ይህን አስተምሮ በማስተባበል ኸድር ወልይ ነው አሉ ። እዚህ ጋር ቢቆሙ አንድ ነገር  ነበር ነገር ግን ከዚህም አልፈው ሄዱ ። ወልይ ከነብይም ከረሱልም ከዑሉል ዐዝም ይበልጣል አሉ ።‼ ለዚህህ ስህተታቸው መነሻው ደግሞ አላህ ነብዩላሂ ሙሳን ኸድር ጋር ሄደህ ተማር ማለቱ ነው ። ይህ ማለት ኸድር አላህ ዘንድ በደረጃ ከሙሳ ከፍ ያለ ስለሆነ ነው ልዩ እውቀት ሰጥቶት ከሱ ተማር ያለው አሉ ። በመሆኑም የኸድር እውቀት የውስጥ እውቀት ( ዒልመል  ባጢን) ነው የሙሳ እውቀት ደግሞ የውጭ እውቀት ( ዒልመ ዛሂር ) ነው  የሚል ፍልስፍና ውስጥ ገቡ ።          ከዚህ በመነሳት በእነርሱ እምነት የነብያት ተከታዮች የውጪውን እውቀት ነው የሚያውቁት የወልይ ተከታዮች ደግሞ የውስጡን ነው የሚያውቁት በመሆኑም የነብያት ተከታዮች የሸሪዓን ሚስጥር አያውቁም ላዩን ነው የሚከተሉት እኛ ደግሞ የሸሪዓን የውስጥ ሚስጥር ስለምናውቅ የውስጡን ነው ምንከተለው አሉ ። በዚህም ነብዩን ጨምሮ ሶሓቦችንና አጠቃላይ ቁርኣንና ሐዲስን የሚከተሉ የኢስላም ሊቃውንቶችን አላዋቂ መሀይማን አደረጉ ።      ይህ እምነታቸው ነው ዛሬ ላይ እየታየ ያለውን የኩፍርና የሽርክ ተግባር እንዲፈፅሙ ያደረጋቸው ። ምነው ሲባሉ እናንተ ስለማታውቁ ነው ኩፍር የሚመስላችሁ ነገር ግን የሙታን መንፈስ ማምለክ ፣ በቀብር ላይ ጠዋፍ ማድረግ ፣ ወደ እነርሱ የተለያዩ ቁሩባን በማቅረብ እነርሱን መለማመን ፣ እርዱኝ ፣ አክብሩኝ ፣ ድረሱልኝ ፣ አሽሩኝ … ወዘተ ማለት ተውሒድ ነው አሉ ።‼      ይህ በተሳሳተ መነሻ ላይ የተመሰረተ የተሳሳተ እምነት ነው ። የዚህ ማሳያው እንደሚከተለው ነው : – 1ኛ – ኸድር ነብይ እንጂ ወልይ አይደለም ።          የነብይነትና የወልይነት ደረጃ አይገናኝም ። የነብይነት ደረጃ በጣም የላቀ ነው ። 2ኛ – አንድ ሰው ሄደህ ከእገሌ ተማር መባሉ ያ           አካል ከሱ መብለጡን አያሳይም ። ይበልጣል ቢባልም በዛ በሚያስተምረው ጉዳይ ነው ሊሆን የሚችለው ። ይህን ወደ ታሪኩ ስንገባ በግልፅ የምናየው ይሆናል ። 3ኛ – የነብዩላሂ ኸድር እውቀት ለራሱ የተሰጠው           እንጂ ሸሪዓ ሆኖ ሊሰራበት አይደለም ። ሸሪዓ ቢሆን እንኳን ለነብዩ ተከታዮች ከዛ በፊት የነበሩ ነብያቶች ሸሪዓ ከቁርኣንና ሐዲስ ወይም ከነብዩ ሸሪዓ ጋር ከተጋጨ አይሰራበትም ሸሪዓም አይሆንም ።        ሱፍዮችና አሕባሾች እያጨማለቁት ላለው ኩፍርና ሽርክ የነብዩላሂ ሙሳና የኸድር ታሪክ በፍፁም መረጃ ሊሆን አይችልም ። ምክንያቱም በባጢል ላይ የተመሰረተ ነገር ባጢል ነውና ።       አላህ ለነብዩላሂ ሙሳ ከኸድር እንዲማሩ የፈለገው እሱ ዘንድ ካለው እውቀት ለሳቸውም ይሁን ለኸድር የተሰጠው በጣም ኢምንት መሆኑን ለማሳየት ነው ። ለዚህ ማሳያ በታሪኩ ላይ ከባህር ላይ የምትጠጣዋን ወፍ ምሳሌ እንዳደረገው ሁሉ ።         የነብዩን ሸሪዓ በፍልስፍና ውድቅ ያደረጉና ኩፍርና ሽርክ ያነገሱ ሱፍዮችና አሕባሾች ታሪኩ በእነርሱ ላይ እንጂ ለእነርሱ መረጃ አይሆናቸውምና በደንብ እንወቀው ። አላህ ካለ ሠዒድ ኢብኑ ጁበይር ከዐብዱላሂ ኢብኑ ዓባስ ዐብዱላሂ ከኡበይ ኢብኑ ካዕብ ይዘው ባስተላለፉትና ኢማሙል ቡኻሪይ በዘገቡት ሐዲስ  ላይ እንደተዘገበው ሙሉ ታሪኩን የምናይ ይሆናል ። በሱረቱል ካህፍ ላይ ይህ ታሪክ ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ሲሆን በአቀማመጥ ሐዲሱ ላይ የመጣው ይበልጥ ቀለል ስለሚል የሐዲሱን እናያለን ።       አላህ ካለ ይቀጥላል ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🟢“ቀጥኜ ቢያዩኝ ጅማት ለመኑኝ ” ለነሲሃ ቲቪ ተፃፈው የተባለው “በመውሊድ ስንጨፍር በካሜራ ቅረፁን” አይነት ደብዳቤ አሳዛኝም አስተማሪም ነው። 👉አሳዛኙ በሱና ማማ ከፍ ካሉ በኋላ ወድቆ ለሙብተዲዕ መሳለቂያ መሆን እጀግ ያሳዝናል። እነ አጅሬ "ነሲሃዎች" ከዚህ በፊትም በርካታ የተጠለፉባቸው ወጥመዶች በደብዳቤ የጀመሩ ናቸው። ከሱፊዮችና መሰሎቻቸው ጋር በተለያዩ የሙጃመላ መድረኮች ላይ ስለሚተዋወቁ ነው የተናቁት ። “ ቀጥኜ ቢያዩኝ ጅማት ለመኑኝ ” እንደሚባለው ነው። በሱና ላይ የነበራቸው አቋም እንደቀለጠ ከጀይላን ጀምሮ ወዳጅም ጠላትም ነገራቸው ። ከዚህም በከፋ ጉዳይ እንደለመዱት እንተባበር ይሉ ይሆናል። 👉አስተማሪው 1️⃣አቋም በወረደ ልክ በጠላት መደፈርና ውርደት ይመጣል ።የአላህ እርዳታም ይርቃል። عَنْ ثَوْبَانَ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " يُوشِكُ الْأُمَمُ أَنْ تَدَاعَى عَلَيْكُمْ كَمَا تَدَاعَى الْأَكَلَةُ إِلَى قَصْعَتِهَا ". فَقَالَ قَائِلٌ : وَمِنْ قِلَّةٍ نَحْنُ يَوْمَئِذٍ ؟ قَالَ : " بَلْ أَنْتُمْ يَوْمَئِذٍ كَثِيرٌ، وَلَكِنَّكُمْ غُثَاءٌ كَغُثَاءِ السَّيْلِ، وَلَيَنْزِعَنَّ اللَّهُ مِنْ صُدُورِ عَدُوِّكُمُ الْمَهَابَةَ مِنْكُمْ، وَلَيَقْذِفَنَّ اللَّهُ فِي قُلُوبِكُمُ الْوَهْنَ ". فَقَالَ قَائِلٌ : يَا رَسُولَ اللَّهِ، وَمَا الْوَهْنُ ؟ قَالَ : " حُبُّ الدُّنْيَا وَكَرَاهِيَةُ الْمَوْتِ ". أخرجه أبو داود (4297) وصححه الألباني ሰውባን አሉ ፥ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ)አሉ፦" የጥመት ህዝቦች (ለጥቃት) ሊጠራሩባችሁ ይቀርባሉ ፤ ልክ በላተኞች ተሻምተው ወደ ሚበሉት ማዕድ እንደሚጠራሩት ።" ጠያቂ እንዲህ አለ ፥ ያኔ በቁጥር አናሳ በመሆናችን ነውን ? ነቢዩ (ﷺ) አሉ ፦ " እንዲያውም የኔ ብዙ ናችሁ ፤ ነገር ግን እንደ ጎርፍ ግሳንግስ ደካማ ናችሁ ፤ አላህም በእርግጥ ከጠላቶቻችሁ ልብ ውስጥ ለእናንተ የነበራቸውን ክብር ነቅሎ ያስወጣል ፤ አላህም በእርግጥ በልባችሁ ውስጥ ውርደትን ይጥልበታል ።" ጠያቂ እንዲህ አለ ፥ ከምን የመጣ ውርደት ነው ? ነቢዩም (ﷺ) አሉ ፦ "የዱንያ ውዴታ እና ሞትን መጥላት (አኺራን መርሳት) ።” 2️⃣ለጠላት ማባበያና ማቀራረቢያ አንዴ በር የከፈተ ዲኑን እና ክብሩን ለአደጋ አጋልጧል። ከዕብ ኢብኑ ማሊክ ከገሳን ንጉስ የመጣለትን ማባበያ ደብዳቤ ምን ነበር ያደረገው ⁉️ ✍  ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ) http://t.me/Abuhemewiya
Show all...
🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍

የጠራ እውቀት ከተቃና አቐምና ተግባር ጋር የተረዘቀ ታድሏል !!

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.