cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ህጉ ምን ይላል? ፉዓድ መሀመድ (Fuad Mohammed)_ጠበቃ፣ የህግ አማካሪና መምህር

ለማንኛውም የህግ ነክ ጥያቄ፣ምክር እንዲሁም መረጃ ያግኙን። 0922873069 0715873069 [email protected]

Show more
Advertising posts
944
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
+1530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

00:30
Video unavailableShow in Telegram
የህግ አስከባሪነት መነሻው ህግን ማክበር እንጂ ባለጌ*ነት አይደለም❗ የፖሊስ ግዴታዎችና ሰብዓዊ መብትን ፍፁም የማይለያዩ ናቸው። ህዝብ ማገልገል ሰብአዊ በሆነ መልኩ እንዲሆን ህገመንግስታዊ ግዴታና የህግ የማስከበር መርህ ነው። ከስር የሚታዩት የፖሊስ አባል ድርጊት ከሰብአዊነትም፣ ከህገመንግስትም፣ ከሞራልም ፍፁም የሚፃረር የባለ*ጌነት ድርጊት ነው። በዚህ መልኩ በሚደረግ ህግ ማስከበር የህግ የቀላይነትን ማረጋገጥ ከቶ አይቻልም። ህዝቡ በህግና በህግ አስከባሪ ተቋማት ያለውን እምነት የሚሸረሽርና ለፍትህ የህግ ተቋማትን ተስፈ ከማድረግ ይልቅ ህዝቡ ማህበራዊ ፍትህን እንዲጠቀም የሚያስገድዱ በመሆናቸው የሚመለከተው አካል ፈጣን እርምጃ ሊወስድ ይገባል። የዚህችን ምስኪን ሴት ህጋዊ መብት የሚፃረር እርምጃ በወሰደው የፖሊስ አባል ፈጣን ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል። ድርጊቱ አስተዳደራዊ፣ የወንጀልና የፍትሐብሔር ተጠያቂነትን የሚያስከትል ሲሆን በፖሊስ አባሉ አስተማሪ ቅጣት ተጥሎ ሰብአዊ መብቷን በሚፃረር መልኩ የተደበደዘቿ እህታችን የጉዳት ካሳ ሊሰጣት ይገባል❗ የድብ*ደባ ቪዲዮውን ለመመልከት የቴሌግራም ቻናሌ👉https://t.me/attorneyfuad
Show all...
1.40 MB
👍 15
በድጋሚ የተለጠፈ👇 ➡ቼክ ለማስከፈል ስለሚቀርብ ክስ  💦                                                                                  ✴አንድ ሰው በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ ሳይኖር ቼክ የጻፈ ከሆነ በወንጀል ሕግ ቁጥር 693 መሠረት በቼክ ማጭበርበር ወንጀል የሚቀጣ ሲሆን ድርጊቱ ሆን ተብሎ ወይም በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ እንደሌለው እያወቀ የተፈጸመ ከሆነ ቅጣቱ ከአስር አመት የማይበልጥ እስራት ሲሆን ድርጊቱ በቸልተኝነት ከተፈጸመ ደግሞ ከአንድ አመት የማይበልጥ ቀላል እስራት ነው፡፡ ✴በመሆኑም ክፍያ ቼኩን የሰጠው ሰው በወንጀል የሚቀጣ ሲሆን ነገር ግን ቼክ የተሰጠው ሰው በቼኩ ላይ የተገለጸውን ገንዘብ እንዲከፈለው ለመጠየቅ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት የፍትሐ ብሔር ክስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ✴ቼክ ለማስከፈል የሚቀርብ ክስ እንደ ሌሌች መደበኛ ክሶች የመቀርብ ሳይሆን በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርአት ሕጉ መሠረት በአጭር ሥነ-ሥርአት የሚታይ ነው፡፡ ✴ስለዚህ ቼክ ይከፈለኝ በማለት በአጭር ሥነ-ሥርአት የሚቀርብ ሰው ተከሳሹ የተለየ መከራከሪያ እስካላቀረበ ድረስ ቼኩን ባለ ሂሳቡ መጻፉ ተረጋግጦ እንዲከፈለው የሚወሰን ነው። አለኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች የማያያዝ ግዴታ እንደለበት እንደተጠበቀ ሆኖ። ➡ይርጋ💦 እንዲከፈል ==== ቼክ የወጣበት ቀን ከግምት ሳይገባ በቼክ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በሚከተሉት 6 (ስድስት) ወራት ውስጥ እንዲከፈል ባንክ መቅረብ እንዳለበት ህጉ ያስገድዳል። በደረቅ ቼክ ምክንያት ለፍትሐብሄር ክስ ===== በቼክ የሚገደዱ ሰዎች ላይ ቼኩን የተቀበለው ሰው ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩን ለክፍያ ባንክ ለማቅረብ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ ጀምሮ እስከ (6) ስድስት ወር ድረስ ነው፡፡ በመሆኑም ቼክ የተቀበለ ሰው፣ ቼክ ሰጪው ላይ የፍትሀ-ብሄር ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በ 1 (አንድ) ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ለወንጀል ክስ === ስድስት ወር ብቻ
Show all...
👍 6
#ቢያስፈልግዎ ሰ_መ_ቁ_96309_ቅጽ_17 አንድ የባንክ ደንበኛ ከባንኩ ጋር በገባው ውል መሰረት የቁጠባ ሂሳቡን በኤቲኤም ካርድ ሲያንቀሳቅስ ቆይቶ ነገር ግን በአጋጣሚ ካርዱ ቢጠፋ እና ይሄንኑ በጽሁፍ ለባንኩ ካሳወቀ ከዚያ ቡሃላ በሂሳቡ ላይ ለሚደርስ ጉድለት ባንኩ ሀላፊነት አለበት።
Show all...
#ጥያቄ:- አንድ አባት በሶስት ሚስት 10 ልጆች አሉት። ነገር ግን ሌሎች ሚስቶችና ልጆች ሳያውቁ ለአንዱ ልጁ ብቻ ከ 2 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ንብረት ሰጥቶታል። በዚህ ሁኔታ በሌሎች ልጆች ጋር ውርስ አብሮ ይካፈላል? ህጉ ምን ይላል? #መልስ ሲጀመር የጋብቻን ንብረት በስጦታ ለማስተላለፍ የተጋቢዎች/ የሚስቶች ስምምነት ያስፈልጋል። ሲቀጥል ልጆችን ወይም ወራሾችን በተመለከተ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1065 መሰረት በውርስ ሃብት ክፍፍል ወቅት ውርሱን የሚቀበለው የሟቹ ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ የሆነ ሰው መመለስ የለበትም ተብሎ ከሟቹ ያገኘው ችሮታ ከሌለ በስተቀር በስጦታ ተቀብሎት የነበረውን ንብረት ከጠቅላላ የሟች ውርስ ውስጥ መልሶ ማስገባት አለበት። በዚህ መሠረት የሟችን የውርስ ሃብት ሁሉም ወራሾች እኩል ይካፈላሉ። በሌላ በኩል በፍ/ብ/ህ/ቁ 1073 መሰረት አንድ ወራሽ ሌሎች ንብረቶች መውረስ አልፈልግም ወይም ውርሱን አልቀበልም ያለ እንደሆነ ከሟች አስቀድሞ በስጦታ የወሰደውን ንብረት ወደ ጠቅላላ ውርሱ እንዲመልስ አይገደድም። ነገር ግን ሌሎች ንብረቶችን ለመውረስ አይችልም።
Show all...
Show all...
Ethiopian Broadcasting Corporation

በወንጀለኞች ላይ የሚሰጡ ቅጣቶች የሕጉን ክፍተት ያሳያል፦ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ******************* በወንጀለኞች ላይ የሚሰጡ ቅጣቶች የሕጉን ክፍተት እንደሚያሳይ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ወ/ሮ አዲስ መሀመድ ገለጹ፡፡ በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሱ አስገድዶ መድፈር እና ጥቃቶች እየተስፋፋ...

👍 1
በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከስቅላት እስከ ብልት ማኮላሸት የሚደርስ እርምጃ የሚወስዱ የዓለማችን ሀገራት August 19, 2024 አሜሪካንን ጨምሮ ስድስት የዓለማችን ሀገራት በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን ብልት እንዲኮላሽ የሚፈቅድ ህግ አላቸው በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከስቅላት እስከ ብልት ማኮላሸት የሚደርስ እርምጃ የሚወስዱ የዓለማችን ሀገራት እንደ ዓለም አቀፉ የስነ ህዝብ ትናት ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ ጠቅላላ ሴቶች መካከል 35 በመቶ ያህሉ ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡ ይሁንና ጥቃቱን ከሚፈጽሙት ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ህግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ በብዙ ምክንያቶች ተገቢውን ፍትህ አያገኙም፡፡ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመላው ዓለም ያለ ክስተት ቢሆንም የተወሰኑ ሀገራት ወንጀሉን ፈጽመዋል በተባሉ ጥፋተኞች ላይ ከባድ ቅጣት እንዲጥሉ የሚፈቅድ ህግ አዘጋጅተዋል፡፡ በሕፃን ሔቨን ጉዳይ የተጀመረው የሚዲያ ዘመቻ እንዲቆም የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ጠየቀ በርካታ ዓለማችን ሀገራት የአስገድዶ መደፈር ወንጀልን ለመከላከል ወንጀለኛ መቅጫ ህጎችን ያዘጋጁ ቢሆንም የተወሰኑ ሀገራት ግን ጥፋተኞች ላይ ከባድ ቅጣትን በመጣል ይታወቃሉ፡፡ ለአብነትም ቻይና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ፓኪስታን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ ጥፋተኞች ላይ የወንድ ብልትን ከማምከን ጀምሮ በስቅላት እና በእሳት በማቃጠል እንዲገድሉ የሚፈቅድ ህግ አላቸው፡፡ አሜሪካ ካሏት ጠቅላላ ግዛቶች መካከል ሰባቱ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን ብልት ማምከን የሚያስችል ህግ ያላቸው ሲሆን በዚሁ ወንጀል እድሜ ልክ የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ቶሎ ከእስር መለቀቅ ከፈለጉ ብልታቸው እንዲመክን መፍቀድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሰሜን ኮሪያ በዚሁ ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን በእሳት በማቃጠል ህይወታቸው እንዲያልፍ የምታደርግ ሲሆን ግብጽ አንቆ በመግደል እንዲሁም ሳውዲ አረቢያ ደግሞ አንገታቸውን በሰይፍ በመቅላት የሞት ፍርድ ትፈጽማለች፡፡ ፓኪስታን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ዩክሬን፣ ቸክ ሪፐብሊክ እና ሌሎችም ሀገራት ዜጎቻቸውን ከወንጀል ለመጠበቅ ጥፋተኛ በተባሉ ዜጎች ላይ ጥብቅ ህግ ካላቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ©አል አይን
Show all...
"የህፃን ሄቨንን ጉዳይ በተመለከተ ሙሉ የፍርድ ቤት ውሳኔው ይሄ ነው። ምናልባት ጥራት ስለሌው በደንብ ላይታይ ይችላል ነገር ግን ባየሁት ደረጃ ውሳኔው በደንብ በማስረጃ ያልተደገፈ ተብራርቶ ያልቀረበ እና ተከሳሽ እንደተባለውም በይግባኝ ሊያሽረው የሚችል አይነት ደከም ያለ ፍርድ የተሰጠበት ሆኖ አግኝቼዋለሁ። የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በባህሪው ሊረጋገጥ የሚገባው በህክምና ማስረጃ በህክምና ማስረጃ የህፃኗን መደፈርም ሆኖ ከተደፈረችው ህፃን ላይ በሚገኝ የዘር ፈሳሽ ናሙና የደፋሪውንም ማንነት መለየት ይቻላል። ይሄንን አይነት ማስረጃ ደግሞ በምንም ተቃራኒ ማስረጃ ማስተባበል ስለማይቻል ውሳኔውን አስተማማኝ ያደርገዋል። ፍርድ ቤቱ በአሁኑ ውሳኔ ላይ የተጠቀመው አመክንዮ "ሌላ ወንድ በግቢው ሊገባ ስለማይችል" በሚል ነው በእርግጥ በተከሳሹ በኩልም 4 ምስክር አቅርቦ አልፈፀምኩም ብሎ ለማስረዳት ሞክሯል ነገር ግን ምስክሮቹ የመሰከሩት ቃል ክሱን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑንም ፍርድ ቤቱ ገልፆ የ 25 አመት እስራት ፈርዶበታል። ተከሳሹ እና ጠበቃውም በዚህ ፍርድ ላይ ይግባኝ ብለው "ያስቀርባል" ተብሎ ለጥቅምት መቀጠሩን ሰምተናል። "ያስቀርባል" ተባለ ማለት ይግባኝ የቀረበለት ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠው ፍርድ ላይ ክፍተት ወይም ድክመት አይቶበታል ስለዚህ በይግባኝ የተፈረደውን ፍርድ ሊቀነስ የሚችልበት እድል አለ ማለት ነው ትርጉሙ። በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሠረት 25 አመት የእስራት ጣሪያ ነው። ከ 25 አመት በላይ እስራት ፍርጅ አይፈረድም በእስር ደረጃ የእድሜ ልክ እክራት ተፈረደ ሲባል የምንሰማው እንኳን እድሜ ልክ እስራት ማለት በኢትዮጵያ 25 አመት ነው እንጂ ታሳሪው እስኪሞት ድረስ ይታሰራል ማለት አይደለም። ስለዚህ አንዳንድ ወንጀሎች ላይ የሚሰጡ ፍርዶች ምን ያህል የእውነት ፍትሕ የሚባለውን ነገር ያመጣሉ የሚለው በጣም አጠያያቂ ነው። ፍትሕ በራሱ ሁሉንም ሰው የሚያስማማ አንድ ትርጉም ያለው ነገር አይደለም በእርግጥ ለምሳሌ በህፃን ፌቨን ጉዳይ አብዛኛው ሰው ተከሳሹ ሞት ቢፈረድበት ደስ ይለዋል እንዳንዱ ደግሞ ከሞት ፍርድ በላይ ወጣ ባለ አገዳደል ተገድሎ እንዲሞት እንዲፈረድበት የሚፈልግም ሰው መኖሩንም ከብዙ አስተያየት መመልከት ችያለሁ። ስለዚህ እዚህ ጋር እንኳን ፍትህ እንደየሰው ይለያያል ብለን መውሰድ እንችላለን። የህግ የፍርድ ቤት የወንጀል ቅጣቶች የመኖራቸው ዋንኛው አላማ ጥፋተኛውን ለማረም እና ሌሎች ሰዎች እንደዚህ አይነት ድርጊት እንዳይፈፅሙ ለማስተማር ነበር። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ግን የሚሰጡ ፍርዶች ማስተማሪያ እየሆኑ አይደለም በሚያሳዝን ሁኔታ እንደዚህ አይነት የአስገድዶ መድፈር ድርጊቶች በህፃናት ላይ በመላው ሀገራችን ሊባል በሚችል መልኩ በተደጋጋሚ እየሰማን ነው።  አስገድዶ መድፈሩም በተለያየ መልኩ በዚህም ሳይቆም ግድያም ለዛውም በሚዘገንን መልኩ ምንም በማያውቁ ህፃናት ላይ አስከትሎ መምጣቱንም እየሰማን እንገኛለን። ድርጊቶቹ ሳይፈፀሙ የህፃናቱን አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ሁኔታን ህመም እና ስቃይ ውስጥ ሳይከትቱ መከላከል መቻል ነው የመጀመሪያውም ግብ ሊሆን የሚገባው ድርጊቶቹ ከተፈፀሙ በኋላ ፈፃሚው ላይ እድሜ ልክም ተፈረደ ሞትም ተፈረደ የህፃናቶቹን የሴቶቹን ህይወት አይመልስም አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳታቸውንም ይጠግናል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። ስለዚህ ፍርድ ቤቶች ዳኞች በእጆቻቸው መዶሻ ይዘው የሚሰጡት ፍርድ አስተማሪ እና ሌሎችንም በዚህ አይነት ድርጊት ውስጥ እንዳይሳተፉ ሊያደርግ የሚችል መሆን ይኖርበታል። ዳኞች ጋር ህግ እንዳለ ሁሉ ህብረተሰቡ ጋር Social justice /ማህበረሰባዊ ፍትሕ/ የሚባለው እሳቤ አለ። ይሄ ነው ሰውን የሚገዛው አንዳንዴ ከህግም በላይ። የፌቨን ደፋሪ እና ገዳይ 25 አመት ተፈርዶበት በህዝቡ ዘንድ ይሄ አነስተኛ ነው የሚል አስተያየት ተሰጠበት ማለት የህብረተሰቡን ማህበራዊ ፍትሕ አላሟላም ማለት ነው። 25 አመት ትንሽ ነው ከተባለ ነገ ከነገወዲያ 25 አመት ምን አላት እያሉ ይሄንን አይነት ድርጊት ሊፈፅም የሚችል ሰውም አብሮ ማህበረሰቡ ውስጥ እየተፈጠረ ነው የሚሄደው ስለዚህ ነው ይሄንን በትኩረት ታይቶ በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች ላይ የሚሰጡ ፍርዶች የእውነትም አስተማሪ እና ሌሎችን ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዳፈፅሙ ሊያደርግ የሚገባ መሆን ይኖርበታል የምለው እንደ ህብረተሰቡ አባል ሚስት እናት እህት እንዳለው ሰው በተጨማሪም እንደ ህግ ባለሙያ ፍርዶች ለውጥ እያመጡ እና ሌሎችንም እያስተማሩ ስላልሆነ ነው ይሄንን ፅሁፍ ለመፃፍ የተገደድኩት ስለዚህ በዚህ ላይ ትኩረት ትኩረት ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ ጉዳይ ነው። #ፍትህ_ለፌቨን እያለ ህብረተሰባችን የሚጠይቀው አንድም ለተደፈረችው እና ለተገደለችው ህፃን ትክክለኛ ፍርድ ስላልተሰጠ ነው አንድም ለራሱ ለልጁ ለእህቱ ወደፊት ምን ሊገጥማቸው እንደሚችል ስጋት ውስጥ በመውደቁ ነው ዋናው የህግ እና ፍትሕ አላማ ህብረተሰቡን መጠበቅ እስከሆነ ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ለውጥ እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለሁ ነብስ ይማር ለህፃን ፌቨን ለእናት እና አባቷም መፅናናትን ይስጥልን። @ethiopianatorney1
Show all...
👍 6 1
በህፃን #ፌቨን ጉዳይ ፍ/ቤቱ የሰነው ውሳኔ
Show all...
አክሲዮን ድርሻ የሌለው ሰው የቦርድ አባል መሆን ይችላል❓ ➖➖➖➖➖ 🔥 የአክሲዮን ማህበር አባል ያልሆኑ ሰዎች የአክሲዮን ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆነው ሊመረጡ እንደሚችሉ አዲሱ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 በአንቀፅ 196/2 ፈቅዷል ። ነገር ግን ባለአክሲዮን ያልሆኑት የቦርድ አባላት ቁጥር ከጠቅላላው የቦርድ አባላት ቁጥር 1/3ኛ መብለጥ የለበትም። እንዲሁም ባለአክሲዮን ያልሆነ ሰው የቦርድ አባል መሆን ቢችልም የቦርዱ ሰብሳቢ መሆን አይችልም።
Show all...
👍 1
25:34
Video unavailableShow in Telegram
የሀገሪቱ ባንኪንግ ህጎች ከእስላማዊ ባንክ መርሆዎችና ልዩ ባህሪያች የሚጣጣሙ መሆን አለባቸው።
Show all...
1344.41 MB
11👍 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.