cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

AFZAN MEDIA / አፍዛን ሚዲያ

አላህን በደስታህ ጊዜ ተዋወቅ በችግር ጊዜ ያውቅሀልና!!!

Show more
Advertising posts
364
Subscribers
-124 hours
-27 days
-830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የቴሌግራም ባሀቤት የታሰረው ሀማ**ስ ቴሌግራምን በነፃነት በመጠቀሙ ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ሌሎች የተጠቀሱ ማወናጀሊያዎች ሁሉ የውሸት ናቸው። እናም በፈረንሳይ ለቀናት እስር ላይ የቆየው የቴሌግራም ባለቤቱ ፓቨል ዱሮቭ በዋናነት እስር ቤት ያስገባው ነገር ሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ሀማስንና ስለሀማስ እንድሁም ስለፍልስጤማዊያን የሚፃፉ ነገሮች ሲያግዱ እርሱ አለማገዱ መሆኑን የእስራኤሉ Jerusalem post ይዞት የወጣው ዘገባ ያመለክታል። በዚህም መሰረት ፓቨል ዱሮቭ ከእስርቤት ከወጣ በሗላ በርካታ የሀማስ ገፆችን አግዷል። ዋናውን የሀማስ ፔጂንም ቴሌግራም አግዶታል። ለሀሳብ ነፃነት ህይወቴን እሰጣለሁ ሲል የነበረው ፓቨል ዱሮቭም በምእራባውያን ተረቷል። በፊት ላይ የፍልስጤማውያን ድምፆች የሚያስተላልፉ መልእክቶችን ካስተላለፍ የኛን operating system መጠቀም አትችልም በማለት ጉግል ቴሌግራም ላይ እቀባ ጥሎ በነበረበት ሰአት ቴሌግራም በሌላ ሲስተሞች በተወረዱ አፖቹ አማካኝነት ፍልስጤማዊያን ድምፃቸውን እንዲያስተጋቡ ፈቅዶ ነበር። ይህም ባለቤቱን ለእስር ዳርጎታል። እናም ምእራባውያን ለዚህ ውሳኔ እንዲበቃ ማድረግ ተሳክቶላቸዋል።
Show all...
በቀን 8000 ብሎኬት ማምረት የሚችል የብሎኬት ማምረቻ ማሽን በኮልፌ መካነ መቃብር ተተከለ። ባለፈው ረመዳን ወር ላይ ይህንን ማሽን ለመግዛት የማህበረሰብ ትብብር ተጠይቆ የነበረ ሲሆን በተገኘው ፈጣን ምላሽ በአንድ ቀን እስከ 8000 ብሎኬት ማምረት የሚችል ዘመናዊ ማሽን ተገዝቷል። ማምረቻ ማሽኑ 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የፈጀ ሲሆን ይህንን ገንዘብ ከማህበረሰቡ ለማሰባሰብ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ቀዳሚውን ሚና ተወጥተዋል። ይህንን ማሽን ገዝቶ ለማህበረሰቡ ማበርከት ትልቁን ችግራችንን ቀርፈን የተሻለ ስራ ያሰራናል ሲሉ የአዲስ አበባ መጅሊስ የቀብር ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አብዱራህማን ጁሃር ነግረውናል። ማሽኑ ቀሪ ግብዓቶች ተሟልተውለት ወደተሟላ የማምረት ስራ ሲገባ ከቀብር ባሻገር ያሉ የልማት ስራዎቻችንን ይደግፋል ሲሉ ኡስታዝ አብዱራህማን ገልፀዋል። የኮልፌ መቃብር የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳውድ መሐመድ በበኩላቸው የብሎኬት እጥረት ለሥራ እንቅፋት ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ ያገኘነው የማሽን ስጦታ ቀልጣፋ ስራ እንድናከናውን ያስችለናል ብለዋል። ይህ የማሽን ግዢ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፈጸም እኛ ሙስሊሞች ከተባበርን ውጤታማ ስራ መሥራት እንደምንችል አመላካች ነው ያሉት አቶ ዳውድ በሌሎችም ዘርፎች ይህንኑ መልካም ትብብር መቀጠል ይገባናል ብለዋል። ይህ ማሽን በቶሎ ስራ እንዲጀምር የጥሬ ዕቃ አቅርቦቱ መፋጠን እንደሚገባው የተናገሩት አቶ ዳውድ ጥሬ ዕቃውን ለማቅረብና የብሎኬት ምርቶችን ወደ ተለያየ የቀብር ቦታዎች ለማሰራጨት ተሽከርካሪ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። በመሆኑም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለማሽኑ ግዢ ከአራት ብር ጀምሮ ያደረገውን ቀና ትብብር በዚህም ላይ በመድገም በሁሉም የቀብር ቦታዎች ላይ የተሟላ ስራ እንዲሠራ ለማድረግ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። የኮሚቴው ዋና አስተባባሪና የኮልፌ የፋይናንስ ኃላፊው ለማሽኑ ስጦታ ለተደረገው ርብርብ ለመላው ተሳታፊዎች ልባዊ ምስጋና ይድረሳቸው ያሉ ሲሆን በተለይ ለአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ክቡር ዶክተር ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ እና ራሳቸውን ቀብር ውስጥ በማስተኛት ከፍተኛ ቅስቀሳ እና እገዛ ላደረጉት ለኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ከፍተኛ ምስጋና ይድረሳቸው ብለዋል። የብሎኬት ማምረቻ ማሽኑ ባለፈው ሳምንት በሁለት ዙር ገብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ በመግባት በብሎኬት ረገድ ያለውን ከፍተኛ እጥረት ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል።
Show all...
ሀላፊነታችንን ተወጥተናል፤ አማናችሁን አድረሰናል 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በወርሀ ረመዳን በአህመዲን ጀበል አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሙስሊም መቃብሮች የብሎኬት ማምረቻ ማሽን ለመግዛት ከህዝበ ሙስሊሙ ገንዘብ መጠየቃችን ይታወሳል ። በዚህም መሠረት የሚፈለገው ገንዘብ ተሰብስቦ የማሽን ግዢ ከተፈጸመ በኋላ የማሽኑ ከፊል አካል በዛሬው እለት በኮልፌ የሙስሊሞች መቃብር ስፍራ የተተከለ ሲሆን የተቀረው የማሽን አካል ደግሞ በነገው እለት የሚተከል ይሆናል ። በዚህ ኸይር ስራ ላይ የተሳተፋችሁና ላቀረብንላችሁ ጥሪ ምላሽ ለሰጣችሁን በሙሉ አላህን ኽይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁ እያልን ቀሪው የማሽኑ አካል ተተክሎ ሲያልቅ ሙሉ የቪዲዮ መረጃዎችን አያይዘን የምንለቅላችሁ ይሆናል።
Show all...
አስገድዶ መድፈር ቅጣቱ በኢስላም የኢስላም ሸሪዐ  ከቆመባቸው  አምስቱ ግቦች አንዱ የሰውን ልጅ ዘር መጠበቅ ነው። ለዚህም አላህ ዝሙትን እርምና ፀያፍ ወንጀል አድርጎታል።የወንጀለኛ መቅጫ ህግ (ሐድ)ም ተዘጋጅቶለታል።      ስለሆነም የትኛውም በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ዝሙት አግብተው ለማያውቁ፥ ግርፋትና የአንድ አመት መባረር ሲያስቀጣ አግብተው ለሚያውቁ ደግሞ በመወገር የሚያስገድል እርኩስ ወንጀል ነው። አስገድዶ መድፈር ባንዱ ፆታ አስገዳጅነት የሚፈፀም ዝሙት ነው። ተገዳጁ ፈልጎ ያደረገው ስላልሆነ ጥፋተኛ አይሆንም ። የዱንያም የአኺራም ቅጣት የሚይዘው አይሆንም! አስገድዶ መድፈር ሁለት ወንጀሎችን አብሮ ይይዛል። አንዱ ዝሙትን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የዝርፊያ ወንጀልን ነው። በዐረብኛው «ሒራባህ» ይባላል። ሒራባህ ሀይልና መሳሪያን ተጠቅሞ የሰዎችን ንብረት መቀማት፣ ሽፍትነትንና ግድያን አቅፎ የያዘን ወንጀል የሚገልፅ ቃል ነው። ቁርኣን «በምድር ላይ ጥፋትን የሚያስፋፉ» በማለት በቀጥታ ገልጿቸዋል ። አስገድዶ ደፋሪ ሀይልና ጉልበት የሚጠቀም ዘራፊ መሆኑ ግልፅ ነው።በመሆኑም ቅጣቱ የሚበየነው በሒራባህ አንቀፅ ነው። ስለሆነም ደፋሪ ቅጣቱ፦ 1) በሰይፍ ይገደላል 2) ወይም  ይሰቀላል 3) ወይም እጅና እግሩን በማፈራረቅ ይቆረጣል (ቀኝ እጅ  ከግራ እግሩ ጋር ወይም ግራ እጁን ከቀኝ እግሩ ጋር) 4)  ወይም ከሀገር ይባረራል አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል፦ «የእነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚዋጉ በምድርም ላይ ለማጥፋት የሚተጉ ሰዎች ቅጣት መገደል ወይም መሰቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከአገር መባረር ነው፡፡ ይህ በነሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት ነው፡፡ በመጨረሻይቱም ለእነርሱ ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡»  (አል ማኢዳህ: 33) እነዚህን ቅጣቶች በምርጫ እንዲፈፅም ለኢስላማዊ መንግስቱ መሪ መብት ተሰጥቶታል።ለህዝብና ሀገር አስተማሪ ያለውን ይተገብራል!  በሰሞነኛው የህፃኗ አስገድዶ መደፈር ጉዳይ ላይ አብዛኞች «የገደለ ይገደል»የሚል መፈክር ሲያስተጋቡ ተስተውሏል።ነገር ግን ይህ ኢስላምን ካለማወቅ የመጣ እንጅ ግለሰቡ ህፃኗን መግደሉ ከፈፀማቸው ግፎች ምናልባትም ትንሹ ሊሆን ይችላል። በሸሪዐ ህግ ቢሆን ግለሰቡ በዚና፣በመድፈር፣ሰውነትን በማቁሰል፣እና ነፍስ በማጥፋት ተጠያቂ ይሆን ነበር። አስገድዶ ደፋሪ ግንኙነቱን ሳይፈፅም ራሱ እጅ ከፍንጅ ቢያዝ ስላልፈፀመባት ተብሎ አይተውም።ይልቁንም ሀይል ተጠቅሞ ተደፋሪን ማፈኑ በሒራባ አንቀፅ ያስቀጣዋል ። አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው! 
Show all...
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወደ ሁለት የአውሮፓ ሀገራት ዜጎችን ለስራ ስምሪት ለመላክ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ገለፀ! . የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም የሚያስጥብቅ እንዲሁም በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ብቻ ሳይወሰን የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪትን የሚያካትት እና የዘመነ አገለግሎት እንዲሆን ባስቀመጥነው የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት ወደ አውሮፓ (Sweden and Norway) ገበያ ለመግባት ቀደም ብሎ በተጀመረ ጥረት የዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። በመሆኑም በስምምነቱ መሰረት የተጠየቁ የሞያ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው። 1- ካርዲዬሎጂስት  2- የማርኬቲንግ ባለሙያ  4- ኬሚካል ኢንጅነር  5- ባስ ድራይቨር  6- አርክቴክት 7- አካውንታን 8- አውቶሞቲቭ ቴክኒሽያን ባለሙያ 9- የላብራቶሪ ቴክኒሺያን 10- የአይ ቲ ባለሙያ 11- የፋርማሲ ባለሙያ 12- የሽያጭ ባለሙያ  13- የሶፍትዌር ባለሙያ  14- ሜዲካል ዶክተር  15- የኮምፒተር ጥገና ባለሙያ 16- ነርስ 17- ግራፊክስ ዲዛይነር 18- የፀጉር ባለሙያ   19- የደንበኛ አገልግሎት ባለሞያ በመሆኑም አስፈላጊውን ስልጠና እና ሌሎች መመዛኛዎችን በሟሟላት የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ዜጎች በኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (https://lmis.gov.et) በመመዝገብ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቀርቧል።
Show all...
1
ታሊባን ድል ያረገበትን ሶስተኛ ዓመት ከአሜሪካኖች የማረካቸውን የጦር መሳሪያዎችና አውሮፕላኖች በትርዒት በማሳየት አክብሯል። ምዕራባውያንም የንብረታቸው በጠላት እጅ መውደቅ ከፍተኛ ቁጭት ፈጥሮባቸዋል። አላህም የኩፍር ሃይሎችን ለማዳከም መጀመሪያ ገንዘባቸውን እንዲያወጡ እንደሚያደርጋቸውና በዚህም ቁጭት ላይ እንደሚጥላቸው ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ «እነዚያ የካዱት ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘቦቻቸውን ያወጣሉ። በእርግጥም ያወጡዋታል። ከዚያም በእነሱ ላይ ጸጸት ትሆንባቸዋለች። ከዚያም ይሸነፋሉ። እነዚያም የካዱት ወደ ገሃነም ይሰበሰባሉ።» (አንፋል 36) አላህ ለእነዚያ ላመኑት ደግሞ ከመከራ በኋላ ሰላምን እንደሚሰጣቸው ሲናገር እንዲህ አለ፡- «ከእናንተ ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን እነዚያን ከእነሱ በፊት የነበሩትን እንደተካ በምድር ለይ በእርግጥ ሊተካቸው፣ ለእነሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፣ ከፍርሃታቸውም በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል።» (አን-ኑር 55) ነገ ይህ አይነት ትርዒት ፍልስጤም ላይ ይታያል። ይህ ተስፋ ሳይሆን የማይቀር የአላህ ውሳኔው ነው።
Show all...
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የታላቁ አንዋር መስጂድን አስመልክቶ 7 አባላት ያሉት ኮሚቴዎችን መሰየሙን አስታውቋል። የአዲስ አበባ መጅሊስ አመራሮች ከተሰየሙ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት በማድረግ በቀጣይ በጋራ በሚሠሩ ጉዳዮች ዙሪያ መነጋገራቸውን ተገልጿል። ኮሚቴዎቹ ተጠሪነታቸው ለአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ክር ቤት ሆኖ የሚቀጥል መሆኑ ከከፍተኛ ምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። የአዲሱ ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው። አቶ ሀይደር ዳውድ..... ሰብሳቢ ሸህ ያሲን ሰልማን.....ም/ሰብሳቢ ሀጂ ሲራጅ ሳሎ.......ዋና ፀሀፊ ዑስታዝ ሙሰማ ከድር....ም/ ፀሀፊ ሀጂ ጁሀር ጀማል..... ገንዘብ ያዥ ሀጂ አብዱሽኩር ሞሳ ..... ሂሳብ ሹም ዑስታዝ ሙሂዲን ጀማል...አባል መሆናቸው ተገልጿል።
Show all...
‏"يا مُحَمَّد : ‏إنَّ فُلانَ ابنَ فُلانٍ يُصلِّي عليكَ ‏. ‏الملائكة لرسولِ اللهِ ﷺ" ❤️ ‏صلُّوا عليه
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.