cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Show more
Advertising posts
33 314
Subscribers
+4124 hours
+4567 days
+1 51330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሌባ አጥር ዘሎ ቤት ሰርስሮ ኪስ በርብሮ ምድራዊ ሐብትን፣ ገንዘብን፣ ጥሪትን ይሰርቃል፡፡ መናፍቃን የቤተክርስቲያንን ቅጽር ዘለዉ የሰዉ ህሊናን በጥርጣሬ ሰርስረዉ ከምግባርና ከሃይማኖት አራቁተዉ ነፍሳትን ይዘርፋሉ፤ ሰለዚህ ከኪስ ሌባ ይልቅ የምግባርና የሃይማኖት ዘራፊዎችን ተጠንቀቁ፡፡ (ከአባቶች እንደበት)
Show all...
147👍 24🙏 10
#ትሕትና ልቡ አብዝቶ የጸለየውን ያህል በዚህ መጠን ልብ ትሑት ይሆናል፡፡ ትሑት ቢሆን እንጂ ትሑት ካልሆነ የሚለምን፣ የሚማልድ የለም፡፡ ፈጣሪ ጽኑ፣ ክቡር፣ ትሑት፣ ኅዙን፣ ልቡና የጸለየውን ጸሎት አልቀበልም አይልምና፡፡ ልቡናም በመከራ ትሑት ካልሆነ ትዕቢትን መተው አይቻለውም፡፡ ትሕትና መከራን ያርቃልና፤ ሰው ትሑት በሆነ ጊዜ ይቅርታን ያገኛል፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር እንደተሰጠችው ያውቃል፡፡ ያድነኛል ብሎ በማመን ዕውቀት ገንዘብ ያደርጋል፡፡ ሰው ረድኤተ እግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠችው ያወቀ እንደሆነ ያድነኛል ብሎ ያምናል፡፡ የድኅነት መገኛ እንደሆነች፣ የሃይማኖት መገኛ እንደሆነች፣ ከመከራ ማዕበል ሞገድ ከውስጧ የሚያድን ወደብ እንደሆነች፣ በመከራ ድንቁርና ላሉ ዕውቀታቸው እንደሆነች፣ የድኩማን መጠጊያ በመከራ ጊዜ የሚያርፉባት ክንፍ እንደሆነች፣ በጽኑ ደዌ ጊዜ የሚድኑባት ረድኤት እንደሆነች፣ በጭንቅ ጊዜ የሚያርፉባት የሕይወት ተክል እንደሆነች፣ በጠላት ፊት የተቃጣ ፍላጻ እንሆነች ያውቃል፡፡ (#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ)
Show all...
64🙏 32👍 19
#ለሚመለከተው_ሁሉ - #የበረከት_ጥሪ "...የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ።” 1ኛ ዜና 22፥11 በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በጉባላፍቶ ወረዳ ቤተክህነትን ሥር የሚተዳደረው የበሊለኛ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ሕንፃ ቤተክርስቲያን በግንባታ ላይ መሆኑ ይታወቃል። ቤተክርስቲያኑ ከወልድያ ከተማ 15 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ የሕንፃ ቤተክርስቲያን ግንባታ ሥራ ከመሠረት ቁፋሮ እስከ ኮለን ድረስ ያሉ ሥራዎችን በእግዚአብሔር ፈቃድ በእናንተ ርዳታ ተሠርቷል። ግንባታው አሁን ላይ የደረሰበት የግንባታ ደረጃ በፐርሰንት ሲገለፅ 39.6% የደረሰ ቢሆንም እንኳ ሥራው ከቆመ ከ13 ወራትን በላይ አስቆጥሯል። ከዚህ በኋላ ካሉት ቀሪ ስራዎች መካከል የግድግዳ ግንባታ ሥራ፣ የበርና የመስኮት ሥራ፣ የቆርቆሮ ሥራ፣ የጉልላት ሥራ እና የመሳሰሉት ሥራዎች ሲሆኑ ለእነዚህ ሥራዎች ማጠናቀቂያ የገንዘብ እጥረት ሰለገጠመን እርሰዎ በሚችሉት ሁሉ ዛሬም እንደትናንቱ ድጋፍዎን ያደርጉልን ዘንድ በመድኃኔዓለም ስም እንጠይቃለን። ከበረከቱ ለመሳተፍ /ገቢ ለማድረግ/ የሚከተለውን አካዉንት ይጠቀሙ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአካዉንት ቁጥር፦ ለበሊለኛ ደብረ መ/መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን 1000293049207 ለበለጠ መረጃ፦ 0910516289 0911706980 0913226515 ሼር በማድረግ ይተባበሩ!!
Show all...
👍 39 6🙏 4
በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው። ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ የኤፍራጥስ ወንዝ ገጽ 87
Show all...
218👍 23🙏 19💯 5
“እምነት አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡ ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡ ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡ እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!! #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Show all...
122🙏 17👍 14
#ወንድሞቼ_ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡ መልካም አድርጋችኋል፡፡ ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣ ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡ ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል? ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም? ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን ምን ይረባችኋል? ምንስ ይጠቅማችኋል? #ተወዳጆች_ሆይ! አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡ ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡ #ልብ_በሉ! ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡ #ክርስቶስን_ማክበር_ትወዳላችሁን? እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡ እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡ ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡ በቃሉ “ይህ ሥጋዬ ነው” ያለው ጌታ በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ብሏልና። #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Show all...
124👍 25🙏 18
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.