cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Show more
Advertising posts
29 911
Subscribers
-124 hours
-247 days
-22530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል" @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
እኔ_ግን_በእግዚአብሔር_ደስ_ይለኛል_ዘማሪት_አዳነሽ_ምንም_እንኳን_በለስ_ባታፈራ_@Ene_At2rfZ8v.m4a1.16 MB
16
💠የመንፈስ ፍሬዎች💠 ፪. ደስታ ✞ ደስታ በምናየውና በምንሰማው፣ በምንቀምሰው ነገር በተፈጸሙ ክስተቶች የሚሰማን የህሊና እርካታ ነው፡፡ በክርስቲያናዊ ሕይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ከእግዚአብሔር ጋር በመኖር የሚገኝ መንፈሳዊ የርካታ ስሜት ነው፡፡ ደስታችንም የሚፈጸመው በዓለም ከሚገኘው ጊዜያዊ ደስታ በተለየ መልኩ ነው፡፡ ✞ አራት ዓይነት ደስታዎች አሉ። እነዚህም:- ፩) ፍሥሓ መላእክት ፪) ፍሥሓ ኖሎት ፫) ፍሥሓ ቍንጽል (የቀበሮ ደስታ) ፬) ፍሥሓ መስቴማ ናቸው። ◈ ፍሥሓ መስቴማ ማለት የሰይጣን ደስታ ማለት ነው። ሰይጣን ሌሎች ሰዎች ሲሳሳቱ፣ ሲወድቁ፣ ሲሞቱ፣ ሲጎዱ በጣም ይደሰታል። በሌሎች ሰዎች ኀዘን እና ጉዳት የሚደሰቱት ደስታ የሰይጣን ደስታ ይባላል። ◈ ሁለተኛው የደስታ ዓይነት የቀበሮ ደስታ ነው። ቀበሮ የጣዝማ ማር ስታገኝ ከደስታዋ ብዛት የተነሳ ማሩ እስኪጠፋት ትዘላለች። የደስታዋ ምንጭ የሚበላ አገኘሁ ብላ ነው። የሰው ልጅ በሥጋዊ ነገሮች የሚደሰተው ደስታ የቀበሮ ደስታ ይባላል። ✞ ሦስተኛው ደስታ የእረኞች ደስታ ነው። እኒህም ጌታ በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ የተደሰቱት ደስታ ነው። ይህ ደስታ ነፍሳዊ ደስታ ነው። በጌታ መወለድ በሲኦል ተግዞ የነበረ አዳም ወደ ገነት የሚመለስበትን የምሥራች ከመልአኩ የሰሙበት ነውና። እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘይከውን ፍሥሓ ለክሙ እንዲል። ✞ የመላእክት ደስታ የፍጹማን ደስታ ነው። መላእክት አንድ ኃጥእ ንሥሓ በገባ ጊዜ በሰማያት ታላቅ ደስታ ይሆናል ተብሎ የተነገረላቸው ናቸው። የመላእክትደስታ ከግላዊ ጥቅም የተለየ ደስታ ነው። ሌላው ሲጠቀም፣ ሌላው ሲያገኝ፣ ሌላው ሲሾም፣ ሌላው ሲደሰት የሚደሰቱት ደስታ ነው። ✞ እንግዲህ ገላ. ፭፣፳፪ ደስታ የመንፈስ ፍሬ ነው የተባለው በሁለቱ ዓይነት ደስታዎች ነው። እነዚህም ፍሥሓ ኖሎት እና ፍሥሓ መላእክት ናቸው። ትክክለኛው ደስታ የሚገኘው በቁስ አይደለም። በእግዚአብሔር ነው። መዝ. ፺፬፣፩ "ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን" ተብሏል። ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክቱ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ብሏል። በሌላ ቦታ ቅዱስ ዳዊት "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ" ብሏል። ደስታ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ቤት ነውና። ደስታ የራቃችሁ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ። ያን ጊዜ ደስ ይላችኋል። ሰማእታት እየተገደሉ ግን ደስተኞች ነበሩ። ለምንድን ነው ስንል የደስታቸው ምንጭ እግዚአብሔር ስለሆነ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ ሕይወተ ሕይወት ብርሃነ ብርሃን መሠረተ መሠረት ስለሆነ ነው። ደስታችንን በእግዚአብሔር እናድርግ። 👉'ሰላም' ይቀጥላል .............. @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
13
ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ተቃውሞ አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል። ቻናላችን ትግሉን ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር የጀመረው። 👇👇 https://t.me/Ethiopian_Orthodox/490
Show all...
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

አንድ ወንድሜ ያጫወተኝን ታሪክ እነሆ ልበላችሁ👇👇 ድሬዳዋ በምኖርበት ሰአት እናቴ የንዋየ ቅዱሳን መሸጫ ሱቅ ነበራት እናም ምትሸጥበት ቤተክርስቲያን መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ነው እና አንድ እናት ሁሌ መሬት መሬት እያዩ ይዞራሉ ታዲያ አንድ ቀን ከ መሬት ቆርኪ እየለቀሙ አየናቸው ጠርተን ለምን እንዲህ እንደሚያደርጉ ጠየቅናቸው መልሳቸውም አባቴ ጊዮርጊስን አረከሱት በስእሉም ተጫወቱበት ብለው እስከዛሬ የሰበሰቡትን የጊዮርጊስ ቢራ ቆርኪ አሳዩን። 😞😞😞😞😞😞😞😞😞 ልብ አድርጉልኝ ክርስቲያኖች እኚህ እናት ምን ያህል የቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕትነትና ቅድስና እንዲሁም ምልጃና በረከቱ ውስጣቸው ዘልቆ እንደገባ ። ቅዱስ ጊዮርጊስ በብዙ ተጋድሎ ያገኘውን ቅድስናና ክብር ለረከሰ ነገር ማዋላችን ምን ያህል እንደሚያስጠይቀን አታውቁምን? ለሰማዕቱ ቤተክርስቲያን ይሰሩለታል፣ ታቦት ይቀርጹለታል እንጂ ቅዱስ ስዕሉን በየቢራው ጠርሙስ ላይ እየለጠፉ እንዴት ለረከሰ ቦታና ለረከሰ ምግባር ያውሉታል? እጅግኑ የሚገርመኝ ደግሞ ተጠቃሚዎቹ እኛው አዋቂዋቹ ማህበረ ክርስቲያን መሆናችን ነው። ወዳጆቼ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለእምነታችን ታግለን ገድል ባናጽፍ እንኳን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ይህን እኩይ ተግባር መቃወም መቻል አለብን። " ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:10) እነሆ እኔ አንድ ብዬ ተነስቻለሁ ይህንን ጽሑፍ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

👍 27 4😢 3🤩 3😇 1
"ፍቅርን ከክርስቶስ" @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
Tewodros_yosef_Ethiopian_Orthodox_mezmur_ፍቅርን_ከክርስቶስ_ትህ_J9YpAhuGg34.m4a5.71 MB
19😍 1
💠የመንፈስ ፍሬዎች💠 ✝️ "የመንፈስ ፍሬ ግን:ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።"ገላ 5÷22 ፩.ፍቅር ✞ በክርስቲያናዊ ሕይወት ከሁሉም የመንፈስ ፍሬዎች የሚቀድመውና የሚበልጠው የመንፈስ ፍሬ ፍቅር ነው።ምክንያቱም፤ ፍቅር የእግዚአብሔር ባሕርይ ስለሆነ ነው 1ዮሐ. 4:16 ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ስለሆነ ነው ሮሜ. 13.8 ማር. 12:28 ✞ የእግዚአብሔር ቃል ይህንን ሲያስረዳ እንዲህም ከሆነ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር፣ እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፡፡ ከነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው ይላል 1ቆሮ.13:13፡፡ በሌላ ክፍል ፍቅርን “የፍጻሜ ማሰሪያ”ብሎታል ቆላ.3:14፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች ከሁሉ የሚበልጠው ይህ የመንፈስ ፍሬ እንዲታይባቸው እግዚአብሔርንም ሰውንም ከልብ ሊያፈቅሩ ይገባቸዋል፡፡ ሌሎቹን የመንፈስ ፍሬዎች ከማሰባችን በፊት ፍቅር ሊኖረን ፍቅርን ልንከታተል ያስፈልጋል 1ቆሮ.14:1፡፡ ✞ ፍቅር የአንዱን ድካም አንዱ ሲሸከም ነው። ሰማዕትነት የሌለበት ፍቅር ፍቅር አይባልም። በአፍ ብቻ እወድሃለሁ እወድሻለሁ ማለት ውሸት ነው። ይህንንስ ባላገሩ "የአፍ ዘመድ ከገበያም አይገድ" ብሎ ተርቶበታል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐ. ፲፭፣፲፫ "ነፍሱን ስለወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" ብሎ የፍቅርን ትርጓሜ አስተማረን። ፍቅር በአፍ የሚናገሩት ብቻ አይደለም በሕይወት የሚኖሩትም ነው እንጂ። ለዚያም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን በቃል ከተናገረ በኋላ በተግባር ደግሞ አዳምን ለማዳን በመስቀል የተሰቀለ። መስቀል ፍቅር በተግባር የተገለጠበት አደባባይ ነው። ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት ብሎ ሊቁ የገለጠው ይህንን ነው። ፍቅር ራሱ እግዚአብሔር ነው። ፩ኛ ዮሐ.፬፣፰-፳ "ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና----ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው" ይላል። ይህ የሚነግረን በፍቅር ጥላቻ እንደሌለ ነው። ፍቅር ሌላውን እንደ ራስ መውደድ ነው። ማቴ. ፯፣፲፪ "ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው" ተብሎ እንደተጻፈ ሰውን መውደድ በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌላውም እንዲደረግ አለመፈለግ ሲሆን እግዚአብሔርን መውደድ ደግሞ ትእዛዙን በመፈጸም ይገለጣል።ዮሐ. ፲፬፣፳፩ "ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው" እንዲል። ✞ ማቴ. ፯፣፳፩-፳፫ "በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ አመፀኞች ከእኔ ራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ" እንዲል የጌታን ስም ብዙ ጊዜ ብትጠራ፣ በስሙ ተአምራትን ብታደርግ፣ በስሙ ትንቢትን ብትናገር፣ በስሙ አጋንንትን ብታወጣ ይህ የፍቅር ምልክት ተደርጎ አይያዝም። እግዚአብሔርን የመውደድ ዋናው ምልክቱ ፈቃዱን መፈጸም ነው። ፈቃዱ ምንድን ነው ከተባለ ዘጸ. ፳፣፩ ጀምሮ ያሉ አስሩን ሕግጋት መፈጸም ነው። ማቴ. ፲፱፣፲፯ "ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ" እንዳለ። ዮሐ. ፲፪፣፶ "ትእዛዙም የዘለዓለም ሕይወት እንደሆነች አውቃለሁ"እንዲል። ✞ ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅርን ጠቅለል አድርጎ ሲያቀርበው እንዲህ ብሎታል። ፩ኛ ቆሮ. ፲፫፣፪-፰ " ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድኾችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለዓመፃ ደስ አይለውም። ሁሉን ይታገሣል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" ብሎ ገልጾታል። 👉'ደስታ' ይቀጥላል ........... @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
22👍 9🥰 3
💠የመንፈስ ፍሬዎች💠
✝️ "የመንፈስ ፍሬ ግን:ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።"ገላ 5÷22
፩.ፍቅር
✞ በክርስቲያናዊ ሕይወት ከሁሉም የመንፈስ ፍሬዎች የሚቀድመውና የሚበልጠው የመንፈስ ፍሬ ፍቅር ነው።ምክንያቱም፤ ፍቅር የእግዚአብሔር ባሕርይ ስለሆነ ነው 1ዮሐ. 4:16 ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ስለሆነ ነው ሮሜ. 13.8 ማር. 12:28 ✞ የእግዚአብሔር ቃል ይህንን ሲያስረዳ እንዲህም ከሆነ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር፣ እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፡፡ ከነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው ይላል 1ቆሮ.13:13፡፡ በሌላ ክፍል ፍቅርን “የፍጻሜ ማሰሪያ”ብሎታል ቆላ.3:14፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች ከሁሉ የሚበልጠው ይህ የመንፈስ ፍሬ እንዲታይባቸው እግዚአብሔርንም ሰውንም ከልብ ሊያፈቅሩ ይገባቸዋል፡፡ ሌሎቹን የመንፈስ ፍሬዎች ከማሰባችን በፊት ፍቅር ሊኖረን ፍቅርን ልንከታተል ያስፈልጋል 1ቆሮ.14:1፡፡ ✞ ፍቅር የአንዱን ድካም አንዱ ሲሸከም ነው። ሰማዕትነት የሌለበት ፍቅር ፍቅር አይባልም። በአፍ ብቻ እወድሃለሁ እወድሻለሁ ማለት ውሸት ነው። ይህንንስ ባላገሩ "የአፍ ዘመድ ከገበያም አይገድ" ብሎ ተርቶበታል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐ. ፲፭፣፲፫ "ነፍሱን ስለወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" ብሎ የፍቅርን ትርጓሜ አስተማረን። ፍቅር በአፍ የሚናገሩት ብቻ አይደለም በሕይወት የሚኖሩትም ነው እንጂ። ለዚያም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን በቃል ከተናገረ በኋላ በተግባር ደግሞ አዳምን ለማዳን በመስቀል የተሰቀለ። መስቀል ፍቅር በተግባር የተገለጠበት አደባባይ ነው። ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት ብሎ ሊቁ የገለጠው ይህንን ነው። ፍቅር ራሱ እግዚአብሔር ነው። ፩ኛ ዮሐ.፬፣፰-፳ "ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና----ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው" ይላል። ይህ የሚነግረን በፍቅር ጥላቻ እንደሌለ ነው። ፍቅር ሌላውን እንደ ራስ መውደድ ነው። ማቴ. ፯፣፲፪ "ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው" ተብሎ እንደተጻፈ ሰውን መውደድ በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌላውም እንዲደረግ አለመፈለግ ሲሆን እግዚአብሔርን መውደድ ደግሞ ትእዛዙን በመፈጸም ይገለጣል።ዮሐ. ፲፬፣፳፩ "ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው" እንዲል። ✞ ማቴ. ፯፣፳፩-፳፫ "በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ አመፀኞች ከእኔ ራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ" እንዲል የጌታን ስም ብዙ ጊዜ ብትጠራ፣ በስሙ ተአምራትን ብታደርግ፣ በስሙ ትንቢትን ብትናገር፣ በስሙ አጋንንትን ብታወጣ ይህ የፍቅር ምልክት ተደርጎ አይያዝም። እግዚአብሔርን የመውደድ ዋናው ምልክቱ ፈቃዱን መፈጸም ነው። ፈቃዱ ምንድን ነው ከተባለ ዘጸ. ፳፣፩ ጀምሮ ያሉ አስሩን ሕግጋት መፈጸም ነው። ማቴ. ፲፱፣፲፯ "ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ" እንዳለ። ዮሐ. ፲፪፣፶ "ትእዛዙም የዘለዓለም ሕይወት እንደሆነች አውቃለሁ"እንዲል። ✞ ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅርን ጠቅለል አድርጎ ሲያቀርበው እንዲህ ብሎታል። ፩ኛ ቆሮ. ፲፫፣፪-፰ " ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድኾችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለዓመፃ ደስ አይለውም። ሁሉን ይታገሣል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" ብሎ ገልጾታል።
👉'ደስታ' ይቀጥላል ...........
@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

እነርሱም በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እየኖሩ እያለ በአንዲት ዕለት የአገረ ገዥው ልጅ ለመታጠብ ወደ ውሽባው ቤት ገባ፡፡ በውሽባ ቤቱም የሰይጣን ኃይል ስለነበረበት የመኰንኑን ልጅ አንቆ ገደለው፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሁሉ ለሞተው የመኰንን ልጅ ሊያለቅሱ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ዮሐንስም አብሮ ቆሞ ሲመለከት ሮምና መጥታ "በጌታዬ ልጅ ሞት ልትደሰት መጣህን" እያለች ረገመችው፡፡ እርሱም "አይዞሽ አትዘኚ" አላትና ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ በመስቀል ምልክት ካማተበበት በኋላ በፊቱ እፍ አለበት፡፡ የሞተውም ልጅ ድኖ ተነሣ፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች እጅግ ደነገጡ፡፡ ሮምናም ደንግጣ "እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን" ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም "በፍጹም እኔ አምላክ አይደለሁም፣ እኔ የእርሱ አገልጋዩና ሐዋርያው ነኝ እንጂ" አላት፡፡ ሮምናም ስለበደለቻቸው በደል ሁሉ መሪር ዕንባን እያለቀሰች ይቅር እንዲሏት ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም አረጋጉዋት፡፡ ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ በጌታችን አመኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ሌሎች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን እየሰበከ ከጣዖት አገልጋዮች በቀር ሁሉንም አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ አገልጋዮችን ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ከሾመላቸው በኋላ ወደ ሌሎች አቅራቢያ አገሮች ሄደ፡፡ በመጨረሻም በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ ድምጥያኖስም ከተገደለ በኋላ ከግዞቱ ተመልሶ ሦስቱን መልእክታቱንና ቅዱስ ወንጌሉን ጽፏል፡፡ ጌታችንም አስቀድሞ ሞትን እንደማይቀምስ ለዮሐንስ ቃል ገብቶለት ነበርና (ዮሐ 21፡22) ጥር 4 ቀን እንደ ኤልያስና ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ወደ ብሔረ ሕያዋን ወስዶታል። ጌታችን ለዮሐንስ ያልነገረው እርሱም ያላስተማረው ምሥጢር የለም፡፡ ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ…" ብሎ የጌታችን ነገር ተመራምሮ ለመድረስ ሲል በመሀል መልአኩን በዮርዳኖስ ባሕር ላይ ሲሄድ አገኘው፡፡ መልአኩም የዮርዳኖስን ባሕር በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ ውጭ ሲያፈስ ተመለከተው፡፡ ዮሐንስም ተገርሞ "ምን ማድረግህ ነው" አለው፡፡ መልአኩም "የዮርዳኖስን ባሕር ቀድቼ እየደፋሁ ልጨርሰው ነው" ሲለው ዮሐንስም መልሶ "ታዲያ በእንቁላል ስባሪ ነውን?" አለው፡፡ መልአኩም "አዎን" አለው፡፡ ዮሐንስም "በከንቱ ደከምክ" አለው፡፡ ይህን ጊዜ መልአኩም መልሶ "አንተስ እንጂ ደግሞ የአምላክን መገኘት፣ አኗኗሩንም ተመራምረህ በጥበብ ለማግኘት ብለህ 'በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ..' ብለህ ጀምረህ የለምን? አንተ ጌታን ተመራምረህ ካገኘህና ከደረስክበት እኔም የዮርዳኖስን ወንዝ በዚህ እንቁላል ቅርፊት ቀድቼ እጨርሰዋለሁ" አለው፡፡ ዮሐንስም ይህን ጊዜ ደንግጦ ዝቅ ብሎ "ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ…" ብሎ ሀሳቡን ለወጠና ሌላ ታሪክ ቀጠለ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ክርስቲያኖችን ሁሉ ወክሎ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ እርሱም ለመቤታችን በአደራ የተሰጠ ሲሆን እመቤታችንን ከወሰዳት በኋላ ለ16 ዓመት እየተንከባከበ ጠብቋታል፡፡ እናቱም በሕፃንነቱ ስለሞተች እመቤታችን ናት እየተንከባከበች ያሳደገችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በመልኩም ከጌታችን ጋር ይመሳል ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ሥዕል የመሳል ተሰጥኦም ነበረው፡፡ ጌታችን በተሰቀለበት ዘመን የነበረው ጢባርዮስ ቄሳር ልጁ በሽተኛ ነበር፡፡ የጌታችንን የማዳን ሥራ እየሰማ እነ ጲላጦስም ስለጌታችን የሚጽፉለትን ይሰማ ስለነበር ልጁን ከጌታችን መቃብር ላይ እንዲያኖሩለት ላከው፡፡ ልጁም ፈጥኖ ተፈወሰለት፡፡ ጢባርዮስ ቄሳርም በልጁ መዳን ምክንያት የጌታችንን ውለታ ማስቀመጥ ፈልጎ የጌታችንን ሥዕሉን የሚሥልለትን ሲያጠያይቅ ዮሐንስን አገናኙት፡፡ ዮሐንስም ጌታችንን ልክ በዕለተ ዓርብ እንደተሰቀለ አድርጎ በመሣል ለጢባርዮስ ቄሳር ሰጠው፡፡ ሲሥለውም በመጀመሪያ ጌታችንን ልክ እንደተሰቀለ አድርጎ ራቁቱን ነበር የሳለው፡፡ ዮሐንስ የሳለው የጌታችን ሥዕልም አፍ አውጥቶ "በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሩሳሌም ራቁቴን ሰቀሉኝ፣ አሁን ደግሞ አንተ ድጋሚ በሮም ራቁቴን ትሰቅለኝን?" ብሎ ተናገረው፡፡ ዮሐንስም እጅግ ደንግጦ "እንዴት አድርጌ ልሳልህ?" ብሎ የሳለውን ሥዕል ቢጠይቀው ሥዕሉም "ከለሜዳ አልብሰህ ሳለኝ" አለው፡፡ ዮሐንስም እንዳለው ከለሜዳ አልብሶ ከሳለው በኋላ ሥዕሉን ትኩር ብሎ ተመልክቶ ቢስመው ከንፈሩ አንድ ቀን ተኩል ያህል ተጣብቆ ቆይቷል፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን የጌታችንን ስነ ስቅለት የሚያሳዩ ሥዕሎች መገኛቸው ይህ ወንጌላዊው ዮሐንስ የሳለው ሥዕል ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፦ 👉በሕይወቱና በኑሮው ሁሉ ጌታችንን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታችንም እጅግ ይወደው ስለነበር "ፍቁረ እግዚእ" ተባለ፣ 👉 የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ስለሆነና አባቱም ዘብድዮስ ስለሚባል "ዮሐንስ ወልደ ዘብድዮስ" ተባለ፣ 👉ለጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ እንዲሁም የጌታችንን አምላክነት በመግለጡ "ቦአኔርጌስ ወይም ወልደ ነጎድጓድ" ተብሏል: 👉ነገረ መለኮትን ከሌሎቹ በበለጠ ሁኔታ አስፍቶና አምልቶ በማስተማሩ "ነባቤ መነኮት ወይም ታዖሎጎስ" ተብሏል። 👉ኃላፊውንና መጻዒውን ጊዜ በራእዩ ስለገለጠ "አቡቀለምሲስ" ተባለ፣ ይህም በግሪክኛ ባለራእይ ማለት ነው፡፡ 👉የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያስታወሰ ፸ ዘመን ሙሉ እያለቀሰ ስለኖረና ፊቱም በሀዘን ስለተቋጠረ "ቁጹረ ገጽ" ተብሏል፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ አይለየን! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
20👍 13😇 2
Photo unavailableShow in Telegram
መስከረም ፬ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ መስከረም አራት በዚህች ዕለት ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ከእናቱ ማርያም ባውፍልያ ከአባቱ ዘብዴዎስ የተወለደበት ዕለት እንደሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ ዕጣ የደረሰው እስያ ስለነበር ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን አስከትሎ ሄደ፡፡ ይኽችውም ኤፌሶን በጥንቱ በታናሽ እስያ በዛሬው የቱርክ ግዛት ውስጥ ከተማ ናት፡፡ ዛሬ ኢያዞሎክ ተብላ የጥንት ታሪኳ ጠፍቷል፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ሰብኮባታል፡፡ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ጢሞቴዎስንም በከተማዋ ላይ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ እርሱም በግፍ እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ቅዱስ ዮሐንስን እየረዳው በከተማዋ ብዙ አገልግሏል፡፡ በኋላ ግን በግፍ ገድለውታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ለመሄድ በመርከብ ሲሳፈር መርከቡ በማዕበል ተሰበረ፡፡ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን መዕበሉ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በመርከቡ ስባሪ ተንጠልጥሎ በባሕሩ ማዕበል መካከል 40 ቀንና 40 ሌሊት ከኖረ በኋላ ማዕበሉ ተፍቶ አብሮኮሮስ ካለበት ደሴት አደረሰውና ተያይዘው ኤፌሶን ከተማ ገቡ፡፡ የከተማይቱም ሰዎች እጅግ ክፉዎች ስለነበሩ መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አልቻሉም ነበር፡፡ እነርሱም እጅግ ክፉዎች መሆናቸውን ስላወቀ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ዕጣው ሲደርሰው በሀዘን አልቅሶ ነበር፡፡ አሁንም ከተማው በገቡ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመፍጠር ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤቷ እሳት አንዳጅ ሆኖ አብሮኮሮስም ዕቃ አጣቢ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ የቀጠረቻቸው ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ጀመር፡፡ ባሮቿ እንደሆኑ ተስማምተው ስለጻፉላት ትደበድባቸውም ነበር፡፡
Show all...
9👍 6
ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
NEW_ethiopia_orthodox_tewahedo_mezemur_FEKURE_EGZIHE_by_cgLqd96YLoM.ogg2.30 MB
14👍 1😇 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.