cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

ወሳኝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የሚነኩ አገራዊ ጉዳዮችን የውይይት አጀንዳ እንዲሆኑ በማቅረብ አስተያየትና የመፍትሔ ምክረ ዐሳብ ይቀርቡበታል። የሚያወያዩ የቤተክርስቲያንና ስለአገር የሚቆረቆሩ ወገኖች የሚያቀርቡትን ሀሳብ እንጋራታለን። https://www.facebook.com/fwakie Join me also here https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_Fant

Show more
Advertising posts
10 758
Subscribers
-1024 hours
-677 days
-4830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በዐመሓራ የሕልውና ትጋድሎ ውስጥ የሚዋጉት "ብሔሮች" ተብለው በሕወሃትና ኦነግ ሕገ-መንግሥት የተፈጡሩት፣ ቡድኖች ናቸው። እነዚህ "ብሔሮች" የቅኝ ገዥዎች የሤራ ትምህርት ያሳወራቸው ልሂቃን የአእምሮ ውጤት የሆነው ሥርዓት መንጋዎች እንጂ እግዚአብሔር አልፈጠራቸዉም። እግዚአብሔር የፈጠረው ሰውን ነው። ሰው ቤተሰብና ጎሣ ሆነ፤ ጎሣዎች ሰፍተው አገርና መንግሥት ፈጠሩ። ሕወሃትና ኦነግ ግን ሰውን አጥፍተው የሚጠፋፋ ቡድን ፈጠሩ። ቡድኖችን ሁሉ በአማራና ኦርቶዶክስ ላይ አዘመቱት። የብልጽግና ወንጌሉ አብይ አህመድ አሊ የሁለቱ የኢትዮጵያ ካንሰር ድርጅቶች የአስተሳሰብ ድቅል ልጅ የሆነ። ሰውዬው ብልጽግናን መርቶ ወላጆቹን ሳይቀር የሚያጠቃ ተራጋጭ መካን ኢሰብአዊ እንስሳ በቅሎ ሆኖ ተከሰተ። ታላቋ ኦሮሚያ፣ የኩሽ ኢፓየር፣ የቀይባሕ ኢሬቻ፣ የምሥራቅ አፍሪካ ንጉሥ ወዘተ ቅዠቱን ለማሳካት በደም ጎርፍ እየዋኘ ነው። ዐመሓራ ሰውነቱን ለማትረፍ፣ ፍትሕን ለማግኘት፣ እውነትን ከቅዠታም የፖሊተካ-ሥር ብሔርተኝነት ለመከላከል ቆመ። አስገዳጅ የህልውና ጦርነት ውስጥ ገብቷል። ታዲያ ዐመሓራ እንዴት ዐሓራነት ለማጥፋት የተፈጠረ የብሔርተኝነት ጽንሰ ዐሳበን ለመውረሰ ከጅሎ፣ የሚጠላውን ለመሆን "የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም" ወደማለት አዘነበለ? ታዲያ ይህንን "ዐመሓራነት" የተባለ እሤት ሕወሃትና ኦነግ በተጠሩበት ግብሩ የከፋና ከፋሺዝም ሊለይ የማይችል ስም በ"ብሔርተኝነት" የሚሰይሙ የብአዴን እንግዴ ልጆች ብቅ አሉ እና "ዐመሓራነት" ማለትም ክብረ-ሰብእ፣ ክብረ ሀገር፣ ፍትሕ፣ እውነተኝነትን ደፍጥጠው "ያማራ ብሔርተኝነት ይለምልም" ወይንም "ፋሽዝም ይንሥ" አሉ። 50 ዓመት ኢትዮጵያዊነትን፣ ዐመሓራነትን፣ ኦርቶዶክሳወዊ ክርስትናን ለማጥፋት በታተረው "ብሔርተኝነት" ሥር "ዐመሓራነትን" ጭዳ ሊያደርጉ ተነሱ። በእርግጥ ዐውቀዉት አይመስለኝም ይህን ከቅዱስ አስተሳሰብና ማንነት ወደ አጥፊና ርኲስ ፖለቲካ-ሥር ብሔርተኝነት የተንደረደሩት። የዐመሓራ ማኅበረሰብ ስብስብ ብሎ ጠንክሮ በአንድነት ብሔርተኞቹ የደቀኑበትን የህልውና አደጋ መቀልበስ የሚችለው እንደ ሕወሃትና ኦነግ ያለ ድርጅት የሚፈጥራቸው ከሰውነት የወጡ አራጅና አጥፊ መንጋ ፈጥሮ መልሶ ሲዋጋ ነው ከሚል አማራጭን ያለመመልከት እጥረት ይሆናል። ዐመሓራ ሆይ የሰው ልጅ አራዊትን ለመከላከል አራዊት ልሁን ብሎ አያውቅም። እንደዚሁ በተለያዩ ማኅበረሰቦች ስም ራሳቸው ነጻ አውጭና አዲስ አገር አዋላጅ አድርገው ከሰብእና ውጭ በሆኑ ልሂቃን መሪነች ህልውናህን ሊያጠፋ የሚወገህን አካል ለማሸነፍ የግድ ጠላትን መምሰል ከያሻህም። ዐመሓራነት በቂ ነው።
Show all...
💯 4 2
Show all...
ፋ*ሽስት የማይሆን ብሔርተኝነት ምን አይነት ነው? የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም ማለት ምን ማለት ነው? (ክፍል ፩)

የህለውና ትግል የሌሎችን ህልውና በሚቃረን በዚያው አደጋ በፈጠረ ፍልስፍናና ቅርጽ ቢዋጉት ውጤት አያስገኝም። የእልጽግናንና የጎሣ ፖለቲካ ፓርቲዎችን በዚያው በእነርሱ መርዝ ለማሸነፍ መሞከር አዙራታዊ የህልውና አደጋ ውስጥ የሚያስገባ ስልት ነውና ለበዐሓራነት መሸነፍ አለበት። ዐመሓራነት ብሔርተኝነትና ጸረ-ኢትዮጵያዊነት የማይስማማው በክብረ-ሰብእና ክብረ-ሀገር ላይ የተመሠረተ ቅዱስ፥ እኛና ሌላ የማይል በሁሉም ማኅበረሰቦች ተወዳጅ፥ ከአገር አልፎ ለአፍሪካ ጎረቤት አገራት እረፍት የሚሰጥ የእኩለነት፥ የፍትሕና የእውነት መንገድ ሆኖ ሲቀጥል ድል ያገኛል! ድሉም ማኅበራዊና ቀጠናዊ ጥበቃና እንክብካቤ የሚያገኝ ዘላቂ ይሆናል። ከዚያ ውጭ የሆነው ሁሉ ሌላ ወጥመድ ነውና ይታሰብበት። #amhara #ethiopian #ethinic #ኢትዮጵያን #አማራነት #ፋኖ #ነጻነት #ፍትህ #ፋንታሁን_ዋቄ #ኦርቶዶክሳዊነት

ከላይ የለጠፍኩትን የዐመሓራነትና የብሔርተኝነት ጉዳይ ማብራራት ይኖርብሃል የሚል ግብረ-መልስ ስላገኘው 2 ክፍል ያለው ቪዲዮ ሠርአቼአለሁ። ከ1፡30 ሰዓት በኋላ አቅርባለሁ https://youtu.be/Vy1T26T2z7U?t=932
Show all...
(ከላይ የቀጠል 👆🏾 “የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም” የሚሉና ኢትዮጵያዊነት ለዐመሓራ መጠቃት ምክንያት ነው የሚሉ ወንድም እኅቶቻችን ዐመሓራን ብሔርተኛ በማድረግ አሁን ሊያጠፉት ለ50 ዓመታት ካጠቁት የሕወሃትና የኦነግ ብሔርተኝነት ጋር እኩል ኢሰብአዊ ውራጅ አስተሳብ ልታደርጉት ነው? ወይስ የዐመሓራ ብሔርተኝነት አሁን በአገራችን ከሚገኘው ኢትዮጵያ-ጠል፥ ጸረ-ሰብእ፥ ጸረ-ውህደትና አንድነት፥ የአውነት ጠላት ሐሰተኛ፥ ገዳይና አሳዳሥ ያልሆነ ሌላ አይነት “አዲስ ብሔርተኝነት” ልትፈጥሩ ነው? “አዲሱ” የዐመሓራ ብሔርተኝነት አሁን ከምናውቀው ዐመሓራነት በምን ይለያል? የጎሣ ልሂቃን “የብሔር ፖለቲካ” ትግል ውስጥ የገቡት በአእምሮ ሕጻንነት፥ በበታችንት ስሜት፥ በተውሶ የባእዳን ትምህርት አእምሮ መታጠብ ላይ በተመሠረተ ጭፍን ግልበጣ (mindless copying) ተመርተው መሆኑ ይታወቃል። የዚህ አይነት ፖለቲካ ሕይወት የሚኖረው ጠላት ሲያገኝ ነው። በዚህ መሠረት የኦነግና የሕወሃት ጠላት ዐመሓራነት፥ ኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክሳዊነት ናቸው። ጠላት ያሉትን በሚያስከትሉት መንጋዎቻቸው አእምሮ ለመቅረጽ የሐሰት ትርክት ማምረትና ጠላት ከጠፋ በኋላ ለየጎሣቸው የሚገኘውን ወተትና ማር የሚያዘንብ መንግሥታዊ ሥርዓትና የለማ አገር፥ ፍጹም ሰላምና ነጻነት በምናብ ስሎ ማሳየት ነው። ይህ ሁሉ ድካም የአእምሮ ድህነት፥ እውነትኛ፥ ፍትሕና ሰብአዊነትን፥ ሁሉ አቀፍነትና ፍቅርን ያገናዘበ ፖለቲካዊ ርእዮተዓለም የመፍጠር አቅም ማጣት፥ የበታችንት ስነ ልቦና፥ የባእዳን አሽከርነትና በቡድን-ዕሳቤ እሥረኝነት የመያዝ እዳዎች ናቸው። ስምንት “የአማራ ብሔርተኝነት ይለምልም” ለሚሉ ለዐመሓራዎች የማቀርበው ጥያቄ፦ 1. የብሔረ-ሰብ ጠላት አበጅተሃል? ካበጀኽ ኢትዮጵያ ውስጥ ጠላቶችህ የትኞቹ ማኅበረሰቦች ናቸው? 2. ኢትዮጵያን ጠላትህ አድርገኻታል? ኢትዮጵያን ካልጠላህ ከኢትዮጵያ ያነሰ በቦታና በቋንቋ ክልል የሚወሰን የብሔር ማንነትና ቦታህ ምንድ ነው? 3. ግፍን፥ ኢፍትሐዊነትን፥ ህልውናህን፥ ሰብአዊ ክብርህን በመከላከል ራስህንና አገርህን ለማዳን የፖለቲካ ፍልስፍና ድህነት አጥቅቶሃል? 4. የበታችነት ስነ-ልቦና ሰለባ ያደረገህ ታሪካዊ ጠባሳና ሌሎችን በመጥላት፥ በመቀማትና ሐሰት በመተረክ የምትታከመው በሽታ አለብህ? 5. ከኦነግ/ብልጽግና እና ከሕወሃት የአፓርታይድ ሕገ-ምንግሥት ፥ አስተሳሰብ፥ የብሔርተኝነት ትርጓሜ ውጭ አገርን፥ ማኅበረሰብእን፥ ሰብአዊነትን፥ መብትና ነጻነት መተርጎም የሚያስችል ታሪካዊ፥ ባህላዊ፥ እምነታዊ መሠረት የለህም? 6. ዐሓራነት እሤት ነው ወይስ የደምና የአጥንት ጉዳይ ነው? ደምና አጥንት ከሆነ ከፋሽዝም በምን ይለያል? በፋሽዝም ውስጥ ነጻነት፥ ሰብአዊነት፥ ፍትሕ፥ እኩልነት እንዴት ይረጋገጣል? 7. “ኢትዮጵያኒሰት ኃይሎች” የሚለው በአሉታዊነት የሚነገረው ንግግር ከዐመሓራ፥ ከኢትዮጵያና ከኦርቶዶክሳዊነት ጠላቶች የመነጨ ነው ወይስ ከዐመሓራ ወዳጆች? 8. የዐመሓራ ብሔርተኝንት (ያለ ጠላት የማይፈጠር ፖለቲካ ሠራሽ ማንነት) ለዐመሓራ ህለውና አደጋን ለማስወገድ አሁን ማኅበረሰቡን ለማጥፋት ተደራጅተው የሚሠሩ አካላትን በትጥቅ ማሸነፍ ብቻ ከሆነ፥ የህለውናውን ዘለቄታዊነት ዋስተና ባለው መዋቅራዊና ሥርዓታዊ አውድ ለማስቀጠል ሁሉም የሚሳተፍበትን አገራዊ ሥርዓት፥ ቀጠናዊ ሰላም ታሳቢ ማድረግ ይኖርበታል፥ ይህ ግድ ከሆነ “ብሔርተኛ” ከሆነ እንዴት ከሌሎች ጋር የሚስማማበት ፖለቲካዊና መንግሥታዊ ሥርዓት ይፈጥራል? ማሳሰቢያ፦ ምላሽ ስንሰጥ ለነፍሰም ለሥጋም፥ ለዐመሓራም፥ ለሌላውም ማኅበረሰብ፥ ለአገርም ለአካባቢም የሚጠቅምና የሕወሃትንና የኦነግን የ50 ዘመናት ሰይጣናዊ ጎዳን የሚቀይር መሆኑ በማረጋገጥ ይሁን። https://t.me/Wakie_EOTCissues
Show all...
ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

ይህ ገጽ " Fantahun Wakie ዋቄ" የሚለው ቻነል ጓደኞቼ እና ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን እድገትና ከሁለገብ ጥቃት በላይ መሆን የሚገዳቸው ክርስቲያኖች ምክረ ዐሳባቸውን የሚለጥፉበት ነው። በዩቲዩብ እንገናኝ

https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_FantahunWakie/videos

💯 17🤣 2🏆 1
(ከላይ የቀጠል 👆🏾 “የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም” የሚሉና ኢትዮጵያዊነት ለዐመሓራ መጠቃት ምክንያት ነው የሚሉ ወንድም እኅቶቻችን ዐመሓራን ብሔርተኛ በማድረግ አሁን ሊያጠፉት ለ50 ዓመታት ካጠቁት የሕወሃትና የኦነግ ብሔርተኝነት ጋር እኩል ኢሰብአዊ ውራጅ አስተሳብ ልታደርጉት ነው? ወይስ የዐመሓራ ብሔርተኝነት አሁን በአገራችን ከሚገኘው ኢትዮጵያ-ጠል፥ ጸረ-ሰብእ፥ ጸረ-ውህደትና አንድነት፥ የአውነት ጠላት ሐሰተኛ፥ ገዳይና አሳዳሥ ያልሆነ ሌላ አይነት “አዲስ ብሔርተኝነት” ልትፈጥሩ ነው? “አዲሱ” የዐመሓራ ብሔርተኝነት አሁን ከምናውቀው ዐመሓራነት በምን ይለያል? የጎሣ ልሂቃን “የብሔር ፖለቲካ” ትግል ውስጥ የገቡት በአእምሮ ሕጻንነት፥ በበታችንት ስሜት፥ በተውሶ የባእዳን ትምህርት አእምሮ መታጠብ ላይ በተመሠረተ ጭፍን ግልበጣ (mindless copying) ተመርተው መሆኑ ይታወቃል። የዚህ አይነት ፖለቲካ ሕይወት የሚኖረው ጠላት ሲያገኝ ነው። በዚህ መሠረት የኦነግና የሕወሃት ጠላት ዐመሓራነት፥ ኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክሳዊነት ናቸው። ጠላት ያሉትን በሚያስከትሉት መንጋዎቻቸው አእምሮ ለመቅረጽ የሐሰት ትርክት ማምረትና ጠላት ከጠፋ በኋላ ለየጎሣቸው የሚገኘውን ወተትና ማር የሚያዘንብ መንግሥታዊ ሥርዓትና የለማ አገር፥ ፍጹም ሰላምና ነጻነት በምናብ ስሎ ማሳየት ነው። ይህ ሁሉ ድካም የአእምሮ ድህነት፥ እውነትኛ፥ ፍትሕና ሰብአዊነትን፥ ሁሉ አቀፍነትና ፍቅርን ያገናዘበ ፖለቲካዊ ርእዮተዓለም የመፍጠር አቅም ማጣት፥ የበታችንት ስነ ልቦና፥ የባእዳን አሽከርነትና በቡድን-ዕሳቤ እሥረኝነት የመያዝ እዳዎች ናቸው። ስምንት “የአማራ ብሔርተኝነት ይለምልም” ለሚሉ ለዐመሓራዎች የማቀርበው ጥያቄ፦ 1. የብሔረ-ሰብ ጠላት አበጅተሃል? ካበጀኽ ኢትዮጵያ ውስጥ ጠላቶችህ የትኞቹ ማኅበረሰቦች ናቸው? 2. ኢትዮጵያን ጠላትህ አድርገኻታል? ኢትዮጵያን ካልጠላህ ከኢትዮጵያ ያነሰ በቦታና በቋንቋ ክልል የሚወሰን የብሔር ማንነትና ቦታህ ምንድ ነው? 3. ግፍን፥ ኢፍትሐዊነትን፥ ህልውናህን፥ ሰብአዊ ክብርህን በመከላከል ራስህንና አገርህን ለማዳን የፖለቲካ ፍልስፍና ድህነት አጥቅቶሃል? 4. የበታችነት ስነ-ልቦና ሰለባ ያደረገህ ታሪካዊ ጠባሳና ሌሎችን በመጥላት፥ በመቀማትና ሐሰት በመተረክ የምትታከመው በሽታ አለብህ? 5. ከኦነግ/ብልጽግና እና ከሕወሃት የአፓርታይድ ሕገ-ምንግሥት ፥ አስተሳሰብ፥ የብሔርተኝነት ትርጓሜ ውጭ አገርን፥ ማኅበረሰብእን፥ ሰብአዊነትን፥ መብትና ነጻነት መተርጎም የሚያስችል ታሪካዊ፥ ባህላዊ፥ እምነታዊ መሠረት የለህም? 6. ዐሓራነት እሤት ነው ወይስ የደምና የአጥንት ጉዳይ ነው? ደምና አጥንት ከሆነ ከፋሽዝም በምን ይለያል? በፋሽዝም ውስጥ ነጻነት፥ ሰብአዊነት፥ ፍትሕ፥ እኩልነት እንዴት ይረጋገጣል? 7. “ኢትዮጵያኒሰት ኃይሎች” የሚለው በአሉታዊነት የሚነገረው ንግግር ከዐመሓራ፥ ከኢትዮጵያና ከኦርቶዶክሳዊነት ጠላቶች የመነጨ ነው ወይስ ከዐመሓራ ወዳጆች? 8. የዐመሓራ ብሔርተኝንት (ያለ ጠላት የማይፈጠር ፖለቲካ ሠራሽ ማንነት) ለዐመሓራ ህለውና አደጋን ለማስወገድ አሁን ማኅበረሰቡን ለማጥፋት ተደራጅተው የሚሠሩ አካላትን በትጥቅ ማሸነፍ ብቻ ከሆነ፥ የህለውናውን ዘለቄታዊነት ዋስተና ባለው መዋቅራዊና ሥርዓታዊ አውድ ለማስቀጠል ሁሉም የሚሳተፍበትን አገራዊ ሥርዓት፥ ቀጠናዊ ሰላም ታሳቢ ማድረግ ይኖርበታል፥ ይህ ግድ ከሆነ “ብሔርተኛ” ከሆነ እንዴት ከሌሎች ጋር የሚስማማበት ፖለቲካዊና መንግሥታዊ ሥርዓት ይፈጥራል? https://t.me/Wakie_EOTCissues
Show all...
ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

ይህ ገጽ " Fantahun Wakie ዋቄ" የሚለው ቻነል ጓደኞቼ እና ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን እድገትና ከሁለገብ ጥቃት በላይ መሆን የሚገዳቸው ክርስቲያኖች ምክረ ዐሳባቸውን የሚለጥፉበት ነው። በዩቲዩብ እንገናኝ

https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_FantahunWakie/videos

Photo unavailableShow in Telegram
በሰብአዊነት፥ በክብረ-ስበእ፥ በአገርና ሕዝብ ሉዓላዊነት፥ በሰላም፥ በፍቅርና በአውነተኝንተ በሚመሩ ንቅናቄዎችና በብሔርተኛ ድርጅቶች መካከል ምንም አይንተ የጋራ እሤት፥ ግብን ርእይ የለም። እንዲህ ከሆነ ብሄርተኝነት ለሚያቀነቅኑና የዐመሓራ ለ50 ዓመታት በብሔርተኞች ሤራ ተከቦ መጠቃትና ለህልውና አደጋ መጋለጥ "በኢትዮጵያ ላይ በማተኮሩ ነው" ለምትሉና ለመፍትሔው ደግሞ "የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም" ለምትሉ ወገኖቼ የማቀርባቸው 8 ጥያቄዎች አሉኝ፦ (በጨዋ ደንብና በአምክንዮ እንከራከር) (ቀጥሏል)👇🏾👇🏾👇🏾 https://t.me/Wakie_EOTCissues
Show all...
💯 7
Show all...
ተስፋና ሥጋት በአዲሱ ዓመት! የአቡነ አብርሃም ተቃርኖ እና ተማጽኖ! #ቀሲስ_አስተርአየ #ቀሲስ_ሳሙኤል መ/ር #ፋንታሁን

#መልአከ_በርሃን_አስተርአየ_ጽጌ #መጋቤ_ጥበብ_ሳሙኤል_ግዛው #መምህር_ፋንታሁን_ዋቄ #ዮሴፍ_ከተማ Join this channel to get access to perks:

https://www.youtube.com/channel/UC23wkdfU9V0lCxWLYCPocFQ/join

#fantahun_wakie #ፋንታሁን_ዋቄ Join this channel to get access to perks:

https://www.youtube.com/channel/UC23wkdfU9V0lCxWLYCPocFQ/join

#ethiopia #ቤተክርስቲያን #ሲኖዶስ #eotc_one_holy_synod #ሻይ_ቡና #shay_buna #amhara #oromiya #ebc #tigray #somali #afar #fano #addisababaethiopia #amharic #abiyahmedali #ukraine #russia #amharicnews #shay #shorts #amharicmusic #yosef #getachewreda #sergegnawegoch #ሠርገኛ #ወጎች #ሰሎሞን #ሹምዬ #ethiopiannews #gurage #wolega #southafrica #europeanunion #europeanparliament #ofc #gebeyanu #usa #endf #አብይ #አህመድ #አሊ #solomon #shumiye #debretsion #addisababa #shay #buna #wolega #shorts #ola #shene #eritrea #War #invasionofukraine #nama #williamruto #joebiden #antonyblinken #jawarmohammed #mereragudina #demekemekonnen #ብልጽግና #ፓርቲ #prosperity #party #oromiya region #amhara region #wolkait #kenya #abelbirhanu #ebc #ebs #fetadaily #fanatv #artstv #ethioforumኢትዮፎረም #ኢትዮ_ቱንቢ #Ethio_Tunbi_Media

💯 5 1
Show all...
ተስፋና ሥጋት በአዲሱ ዓመት! የአቡነ አብርሃም ተቃርኖ እና ተማጽኖ! #ቀሲስ_አስተርአየ #ቀሲስ_ሳሙኤል መ/ር #ፋንታሁን

#መልአከ_በርሃን_አስተርአየ_ጽጌ #መጋቤ_ጥበብ_ሳሙኤል_ግዛው #መምህር_ፋንታሁን_ዋቄ #ዮሴፍ_ከተማ Join this channel to get access to perks:

https://www.youtube.com/channel/UC23wkdfU9V0lCxWLYCPocFQ/join

#fantahun_wakie #ፋንታሁን_ዋቄ Join this channel to get access to perks:

https://www.youtube.com/channel/UC23wkdfU9V0lCxWLYCPocFQ/join

#ethiopia #ቤተክርስቲያን #ሲኖዶስ #eotc_one_holy_synod #ሻይ_ቡና #shay_buna #amhara #oromiya #ebc #tigray #somali #afar #fano #addisababaethiopia #amharic #abiyahmedali #ukraine #russia #amharicnews #shay #shorts #amharicmusic #yosef #getachewreda #sergegnawegoch #ሠርገኛ #ወጎች #ሰሎሞን #ሹምዬ #ethiopiannews #gurage #wolega #southafrica #europeanunion #europeanparliament #ofc #gebeyanu #usa #endf #አብይ #አህመድ #አሊ #solomon #shumiye #debretsion #addisababa #shay #buna #wolega #shorts #ola #shene #eritrea #War #invasionofukraine #nama #williamruto #joebiden #antonyblinken #jawarmohammed #mereragudina #demekemekonnen #ብልጽግና #ፓርቲ #prosperity #party #oromiya region #amhara region #wolkait #kenya #abelbirhanu #ebc #ebs #fetadaily #fanatv #artstv #ethioforumኢትዮፎረም #ኢትዮ_ቱንቢ #Ethio_Tunbi_Media

💯 4
Photo unavailableShow in Telegram
🤣 2🏆 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.