cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዜና አበው ቅዱሳን

በዚህ ቻናል ላይ ያላችሁ አስተያየት @ Kiduse Solomon2324 ብሎ በተጨማሪም ስልክ ቁጥር 0989740239 የአብሥራ ብሎ ማገኘት ይችላል ስንክሳር ምስባክ የቅዱሳን ታሪክ መተረክ ነገረ ሃይማኖት ድርሳናት ወረብ እና ዚቅ ብሒል አበው ዜና አበው ምክር አበው መንፈሳዊ ግጥሞች የጉባኤ ቤት ስብከቶች መዝሙሮች የቤተክርስቲያን ታሪክ የተለያዩ ነገሮች በዚህ ቻናል ማገኘት ይችላል

Show more
Advertising posts
623
Subscribers
No data24 hours
+37 days
+730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም ፱ 

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ        አሜን

#ትሕትና ልቡ አብዝቶ የጸለየውን ያህል በዚህ መጠን ልብ ትሑት ይሆናል፡፡ ትሑት ቢሆን እንጂ ትሑት ካልሆነ የሚለምን፣ የሚማልድ የለም፡፡ ፈጣሪ ጽኑ፣ ክቡር፣ ትሑት፣ ኅዙን፣ ልቡና የጸለየውን ጸሎት አልቀበልም አይልምና፡፡ ልቡናም በመከራ ትሑት ካልሆነ ትዕቢትን መተው አይቻለውም፡፡ ትሕትና መከራን ያርቃልና፤ ሰው ትሑት በሆነ ጊዜ ይቅርታን ያገኛል፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር እንደተሰጠችው ያውቃል፡፡ ያድነኛል ብሎ በማመን ዕውቀት ገንዘብ ያደርጋል፡፡ ሰው ረድኤተ እግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠችው ያወቀ እንደሆነ ያድነኛል ብሎ ያምናል፡፡ የድኅነት መገኛ እንደሆነች፣ የሃይማኖት መገኛ እንደሆነች፣ ከመከራ ማዕበል ሞገድ ከውስጧ የሚያድን ወደብ እንደሆነች፣ በመከራ ድንቁርና ላሉ ዕውቀታቸው እንደሆነች፣ የድኩማን መጠጊያ በመከራ ጊዜ የሚያርፉባት ክንፍ እንደሆነች፣ በጽኑ ደዌ ጊዜ የሚድኑባት ረድኤት እንደሆነች፣ በጭንቅ ጊዜ የሚያርፉባት የሕይወት ተክል እንደሆነች፣ በጠላት ፊት የተቃጣ ፍላጻ እንሆነች ያውቃል፡፡ (#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ)
Show all...
Show all...
ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም ፰

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ        አሜን

Show all...
ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም ፯

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን

🌿🌿🌿✨✨🌿✨✨🌿✨✨🌿✨✨✨ "ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ 🌿✨✨🌿 እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡ 🌿✨✨🌿 ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡" 📝ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 📚ወደ ኦሎምፒያስ መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ 🌿🌿🌿✨✨🌿✨✨🌿✨✨🌿✨✨✨
Show all...
🥰 1
Show all...
ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም ፮

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
✝✞✝ #አቡነ_አሮን_መንክራዊ (ዘመቄት) ✝✞✝ ☞መናኔ ብዕል፡ ሐዋርያዊ ጻድቅ ወሰማዕተ ብርሃን፡፡ ☞በዚህ ክቡር ገዳም ፀሐይ እንጂ ዝናብ አይገባም:: ✝✞✝ የጻድቁ በረከት ከማደሪያቸው ይምጣልን !!! ✝✞✝ DnYordanos Abebe 💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠      /ማቴ፫:፫/ ✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር✝ " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
✝ጻድቅ ንጉሥ አፄ ልብነ-ድንግል✝ ✿በመካከለኛው ዘመን የነገሡ መሪዎቻችንን ስዕል ማግኘቱ ከባድ ቢሆንም ይህ የልብነ ድንግል ምስል በመላው ዓለም ታዋቂ ነው፡፡ (በእርግጥ ንብረትነቱ የእኛ አይደለም) ✿ልብነ ድንግል ከ1500-1533 በቆየ ዘመነ ንግሥናቸው፡- ✝ለድንግል እመቤታችን በነበራቸው ፍቅር ✝አድባራትን እና ገዳማትን በማነጽ ✝በደራሲነት (መልክዐ ኤዶምን ፡ ተፈስሒ ማርያምን ፡ ለአዳም ፋሲካሁን ፡ ለኖኅ ሐመሩን ፡ ስብሐተ ፍቁርን . . .) ✝በፍጹም ንስሃቸው (ባጠፉት ጥፋት ጌታ ግራኝን አስነስቶ ሲቀጣቸው በመጸጸታቸው) ✝ለነዳያን በመራራታቸው ✝ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ቀናዒ ✝ለጋብቻቸውም ፍጹም ታማኝ በመሆናቸው . . . ይታወቁ ነበር፡፡ ✿በ1533 መስከረም 5 ቀን በደብረ ዳሞ (ትግራይ) ከማረፋቸው በፊት እመቤታችንን እያለቀሱ ለመኑ፡፡ "በእንተ ፍቅረ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኬንያ፡፡ እስእለኪ ማርያም በሃሌ ሉያ፡፡ ሐዘና ስምዒ ወብካያ፡፡ ለሃገሪትነ ኢትዮጵያ፡፡" (ስብሐተ ፍቁር) ✿እመቤታችንም "ልመናህን ተቀብየዋለሁ፡፡ ግን በምድር ደስታ የለህምና ለልጅህ ማር ገላውዴዎስ ኃይልን እሰጠዋለሁ፡፡ እርሱም የሃገሪቱን ክብር ይመልሳል" አለቻቸው፡፡ ✿ከዚህ አያይዛም በኢትዮጵያ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚሆነውን ሁሉ ነግራ ነፍሳቸውን ከሥጋቸው ለይታለች፡፡ ✝የእመቤታችን ጣዕመ ፍቅሯ ፡ የጻድቁ ንጉሥም በረከት በዝቶ ይደርብን፡፡✝ ✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር✝ 💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠      /ማቴ፫:፫/ " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Show all...
✨✨✨🍂✨🍂✨✨✨🍂✨🍂✨✨✨🍂✨🍂 ወዳጄ ሆይ! ገንዘብ የለህምን? ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርግ፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ የምታደርግ ከኾነ ገንዘብ ካላቸው በላይ ባለጠጋ ነህ፡፡ “እንዴት?” ትለኝ ይኾናል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- የእነዚያ (የባለጠጐቹ) ገንዘብ ያልቃል፡፡ ያንተ ግን ብል አይበላውም፡፡ ጊዜ አይለውጠዉም፡፡ አያልቅም፡፡ ወደ ሰማያት፣ ወደ ሰማየ ሰማያት፣ ወደ ምድር፣ ወደ አየራት፣ ወደ እንስሳቱ ዓይነት፣ ብዙ የብዙ ብዙ ወደሚኾኑት ዕፅዋት፣ ወደ ደቂቀ አዳም በጠቅላላው፣ ወደ መላዕክት፣ ወደ መላዕክት አለቆች፣ ወደ ኀይላት ተመልከት፡፡ እነዚህ ኹሉ የአምላክህ ፍጥረቶች ናቸው፡፡ የእነዚህን አምላክና መጋቢ ባሪያ መኾን ድኻ መኾን አይደለምና ድኻ አይደለህም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡ ✨🍂✨🍂 ተወዳጆች ሆይ! ቀናትን ቆጥሮ በዓል ማድረግ የክርስቲያን ግብር አይደለም፤ የአሕዛብ ግብር እንጂ፡፡ እንዴት? የክርስቲያኖች ተፈጥሮ በቀንና በወር የተገደበ አይደለምና፡፡ አገራችን ሰማይ ነው፡፡ ግብራችን ሰማያዊ ነው፡፡ ኅብረታችንም ከሰማያውያን መላዕክት ጋር ነው፡፡ በዚያ መዓልት ለሌሊት ስፍራውን አይለቅም፡፡ ሌሊትም በተራው ለመዓልት አይለቅም፡፡ እዚያ ኹሌ መዓልት ነው፡፡ እዚያ ኹል ጊዜ ብርሃን ነው፡፡ ስለዚህ
“ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ” ቈላስ.3፡1
እንደተባልን ኹል ጊዜ ማሰብ ያለብን ይህንን ነው ፡፡ ✨🍂✨🍂 ክርስቲያናዊ ተፈጥሮአችን ከዚህ ምድራዊ አቈጣጠር በላይ ነው፡፡ በንጽህና በቅድስና እየኖርን ዘወትር በዓልን የምናከብር ከኾነም የዚሁ ዓለም ሌሊት ለእኛ ሌሊት አይደለም፤ መዓልት ነው እንጂ፡፡ ዘመናችንን በሙሉ በገቢረ ኀጢአት፣ በስካር፣ በዘፈን የምናሳልፈው ከኾነ ግን መዓልቱ ለእኛ መዓልት አይደለም፤ ሌሊት ነው እንጂ፡፡ ፀሐይዋ ብትወጣም ልቡናችን ገና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ይኖራልና ቀን እንደወጣ አይቈጠርም፡፡ 📚ሰማዕትነት_አያምለጣችሁ 📝 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው 🖋ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው ✨✨✨🍂✨🍂✨✨✨🍂✨🍂✨✨✨🍂✨🍂
Show all...
🥰 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.