cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ህብረ ቀለማት

ምርጥ ግጥሞችን፣ አጫጭር ታሪኮችን፣ የተለያዩ ልቦለዶችን፣ አነቃቂ መልዕክቶችን፣ አስተማሪና አዝናኝ ፁፎችን፣ ከፈለጉ አሁኑኑ ይቀላቀሉን። ህብረ-ቀለማት የሁሉ ድምቀት Cross & comment 👉 @Natiaba

Show more
Advertising posts
1 536
Subscribers
-224 hours
+17 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሁለቱ የትክክለኛ ለውጥ ምልክቱ በቤቷም ሆነ በስራ አካባቢ በባህሪይዋ እጅግ በጣም አስቸጋሪ የነበረች ሴት አንድ ቀን ወደ ሕሊናዋ ተመለሰችና ይህንን አስቸጋሪ ባህሪይዋን ለመለወጥ ውሳኔ አደረገች፡፡ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመውሰድ፣ የተለያዩ መጽሐፍትን በማንበብና ምክሮችን በመቀበል ራሷ ላይ በሚገባ ከሰራች በኋላ በሚያስገርም ሁኔታ ተለወጠች፡፡ ቀድሞ በአስቸጋሪ ባህሪይዋ ለሚያውቋት የቅርብ ወዳጆቿ ይህንን ለውጧን ስትነግራቸው ማመን አልቻሉምና ያንን ለማረጋገጥ አንድ ጥያቄን ጠየቋት፡፡ ጥያቄው እንዲህ የሚል ነበር፡- “እስቲ ቀድሞ አስቸጋሪ በነበርሺበት ጊዜ ታደርጊያቸው ከነበሩት ነገሮች መካከል በእርግጥም መለወጥሽን የሚያሳይ አንድ ምሳሌ ንገሪን” አሏት፡፡ እሷም እንዲህ አለች፡-“ የምሰራው በአንድ ሆቴል ቤት በጽዳት ሰራተኝነት እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡ ለምሳሌ፣ ከመለወጤ በፊት የክፍሎቹን ወለል ስጠርግ ግራና ቀኝ ዘወር ብዬ ማንም እንደማዬየኝ ካረጋገጥኩኝ በኋላ ጥራጊ ቆሻሻውን አፍሼ ከማውጣት ይልቅ ምንጣፉ ስር አስገብቸው ነበር የምሄደው፡፡ አሁን ከተለወጥኩኝ በኋላ ግን ሰው አየኝም አላየኝም ለህሊናዬ ስለምሰራ ጥራጊውን አፍሼ በመድፋትና ሁሉንም ነገር በተገቢው መልኩ በትጋት ነው የምሰራው”፡፡ ትክክለኛ የባህሪይ ለውጥ የማምጣታችን ሁለት ዋና ዋና ምልክቶች፡- 1. ቀድሞ የነበርንን ተገቢ ያልሆነ ተግባር በተገቢው መለወጥ፣ 2. ሰው ቢያየንም ሆነ ባያየን ለህሊናችን ብለን ትክክለኛውን ተግባር በትክክለኛው መንገድ መፈጸም፡፡ እነዚህን ሁለት የለውጥ ምልክቶች የግላችንን ባህሪ ለመለወጥ ከመጠቀም አንጻርና ዘወትር እለወጣለሁ የሚልን አስቸጋሪ የቅርብ ሰው በእርግጥም ለመለወጡ እንደመመዘኛ መጠቀም እንችላለን፡፡ እውነተኛ ለውጥ በአንደበት ከመገለጡ በፊትና ባሻገር በተግባር ይታያል፡፡ እውተኛ ለውጥ ሰው አየኘን አላየኝ፣ ሰው እውቅና ሰጠኝ አልሰጠኝ፣ ሰው አመሰገነኝ አላመሰገነኝ ሳይል በእውነተኛ የአመለካከት ለውጥ ኃይል የሚነዳ ለውጥ ነው፡፡ መልካም ቀን ይሁንላችሁ! @getmnaleloch
Show all...
3
የኔና የአንቺ መሆን ሲመዘን ከአሌክስ አብረሐም አልተዘዋወረችም መፀሀፍ የተቀዱትን ገፀ በሀሪያት ቁልጭ አድርጎ ከማሳየቱ በላይ አሌክስ ገፀ በሐሪያቱን ከኔና አንቺ ኑረት ውስጥ የቀዳቸው ያህል እየተሰማኝ ነው ብል ማን ያምነኝ ይሆን! አንቺ ማህደረ ሰላም እኔ ደግሞ አብርሐም 😥😥 በርግጥ የሁልግዜም መሻቴ ዮናስን መሆን ነበር......
Show all...
8
[ድፍን ድርሰት] 🌍 ____ ¹ ትልሙንና ህልሙን —··· (በመቼት በሴራ)  እያጠላለፈው ፤ ወጉን ትረካውን  (በቀናቶች ክፍል) (በገፁ በአንቀፁ) እየሸራረፈው ፤ ዓለምን በቃሉ.... (በፈጠራው ቀለም) ነክሮ የነደፈው ደራሲው ፈጣሪ (ስለሁለታችን) ስለ እኔ ስላንቺ — ምን ይሆን የፃፈው? ² አፈር ከሞላበት (አመድ ከለበሰው) (ከመጣው ከሄደው) ከተመላለሰው ከአምና ከዘንድሮ (ከዛሬ ከድሮ) የተከመረውን (ጥራዝ እያወጡ ) (ሕይወትን ዘርግተው) ቢገልጡ ቢገልጡ ፤ የእግዜር ድፍን ድርሰት አይገኝም ጭብጡ ። ³ (“አትመጪም ወይ?” ስልሽ...) —··· “እመጣለሁ” ብትይ ፤ (ለመንገድ የሚሆን....) —··· ስንቅ ብታስከትይ ፤ ልብሽ ቢሰናዳ —·· እግርሽ ቢበረታ፤ (የጎዳናው ቀያሽ የመንገዱ ጌታ....) ደራሲው ፈጣሪ — ·· የመቼት የቦታ ፤ ምን እንደሚበጥስ ምን እንደሚቀጥል... ማንን እያነሳ ማንን እንደ ሚጥል.... አውቄው አላውቅም ገምቼው ቀድሜ የታል ስለ ነገ ፍፁም ድምዳሜ? ስንት ነው በምድር የተሰጠኝ ዕድሜ? ⁴ (ማን ይሄን አወቀ? አሁንስ ማን ያውቃል‽) “እመነኝ” ብትይኝ አፍሽ ቢያወጣ ቃል ፤ (ጠዋት "ለምለም" ያልነው ባመሻሽ ይደርቃል) ስውር ደራሲያችን የላይኛው አካል ነባሩን ቀይሮ አዲስ ይተርካል ። ይለየን ይሆናል... (ያርቀን ይሆናል) በጊዜ – በቦታ ፤ ከቃል የበለጠ — ጌታ ነው “ሁኔታ” ። (ይሆኑታል እንጂ...) ይኖሩታል እንጂ .... “ይግባኝ” አይባልም — እንዲህ ያለ ፍርጃ አንቺን አምንሻለሁ — እግዜሩን ግን እንጃ ። ___ 🌍 @getmnaleloch
Show all...
4
አንዲት ሴት የተራበ ትንሽ እባብ መንገድ ላይ አገኘች። እናም ከሚሰቃየው እራብ ልታድነው ወሰነች። ወደ ቤቷ ወሰደችውና አስጠለለችው።እባቡም አድጎ እስኪለምዳት ድረስ መመገብ ጀመረች። ወደ ቤት በገባችበት ቦታ ሁሉ ከኃላ ይከተላታል። ማታ ላይ በሙቀቷ እየተደሰተ አልጋው ላይ ከጎኗ ይተኛል ። ዓመታት አለፉ እና እባቡ አደገ። እናም አንድ ቀን ያቺ ሴት እባቡ ባልታወቀ ምክንያት መብላት በማቆሙ ተገረመች። አዛኟ ሴት እባቡን እንዲበላ ለማድረግ ብዙ ሞክራለች። እሱ እንዳይሞትና እንዳይጠፋ በመፍራት ፤ እባቡ ግን እምቢ አለ። እና ሙከራዎቿ ሁሉ አልተሳኩም። - እባቡ ለመመገብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለብዙ ሳምንታት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቆየ።ነገር ግን በቀን ይከተላታል ።ማታ አልጋዋ ላይ ከጎኗ ይተኛ ነበር። ሰውነቷ ላይ በመጠምጠም ሙቀት ከሰውነቷ እየወሰደ አብሯት ይተኛል ። - በመጨረሻም ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ሴትየዋ ወደ የእንስሳት ሐኪም ወስዳ እንዲመረምረው ወሰነች። ምናልባት ታሞ ህክምና ያስፈልገዋል ፤ በሚል እሳቤ። ሐኪሙ እባቡን ከመረመረ በኋላ ወደ ሴቲቱ ዞር ብሎ ጠየቃት። ሃኪሙ :- እባቡ ላይ የምግብ ፍላጎት ከማጣት እና ከምግብ ከመታቀብ በስተቀር ሌሎች ምልክቶችን አስተውለሻል ? ሴትየዋ መለሰች፡- እረ የለም። - ዶክተሩ በድጋሚ ጠየቃት: - አሁንም ለሊት ካጠገብሽ ይተኛል ? - ሴትየዋ መለሰች:- አዎ ፡ እሱ ከእኔ ጋር በጣም ይጣበቃል። ወደ ቤት ውስጥ በሄድኩበት ሁሉ ይከተለኛል። ሁልጊዜ ማታ በአጠገቤ አልጋ ላይ ይተኛል። - ዶክተሩ ጠየቃት፡- አንዳንድ ጊዜ ከጎንሽ ሲተኛ በሰውነትሽ ላይ እንደሚጠመጠም አላስተዋልሽም? - ሴትየዋ በጣም ተገርማ ለሐኪሙ: - አዎ ፡ አዎ ፡ ይጠመጠምብኛል አለችው። በቅርብ ጊዜ በህመሙ ምክንያት ሙቀት በመፈለግ እንዳዝንለት አንዳንዴ በእንቅልፍዬ ላይ እያለሁ ይጠመጠማል። ሲነቃም በአይኑ ይከተለኝና ምግብ ለሱ ለመስጠት እቸኩላለሁ። እንደ አለመታደል ሆኖ ለመብላት ፈቃደኛ አልሆነም እና በቦታው ይቀመጣል። - ዶክተሩ ፈገግ አለና እንዲህ አላት፡ - እመቤት ፦ ይህ እባብ አልታመመም ሊበላሽ ነው እንጂ!!! እሱ እባቡ አንችን ለመብላት አእስኪችል ድረስ ለመራብ እየሞከረ ነው። እንዲሁም ከአንቺ ጋር በፍቅር ሳይሆን በሰውነትሽ ላይ የሚጠቀለለው አንቺ እንደምታስቢው ሙቀት እና ርህራሄ ፍለጋ ሳይሆን ከሆዱ መጠን ጋር የሰውነትሽ መጠን ለመለካት እየሞከረ ነው። ይህም ሆዱ የአንቺን መጠን የሚበላ ምግብ ለማስተናገድ በትክክለኛው ጊዜ ሊያጠቃሽ እየተዘጋጀ ነው። እመቤቴ ይህን እባብ በፍጥነት አስወግጅው። ብሎ መከራት !! ከታሪኩ የምንማረው ፡- - አንዳንዶች በዙሪያው ያሉትን በፍቅር፣ በደግነት ወይም በበጎ አድራጎት ሊለውጥ ይችላል ብለው ያስቡ ይሆናል። ነገር ግን በአንዳንዶች ውስጥ በተፈጥሮ መርዝ ተሸክመው ጊዜ የሚጠብቁ ብዙ ሰዎች አሉ እናም ይጠንቀቁ ። ፈጣሪ ከክፋታቸው ይጠብቀን ። Bini Berhe @getmnaleloch
Show all...
👍 6 1👌 1
አድስ አመት ነው አሉ ዛሬን ምኑ ነው አድስ🥹
Show all...
👌 4
ደወለችልኝ፣ አነሳሁ! ሃሎ ነቲዬ፣ ቀደመችኝ ወ...ዬ ለምንድነው እንኳን አደረሰህ ብዬህ ያልመለስከው? ካርድ ስላልነበረኝ ነዋ አይቼ ዝም ያልኩት ኦሆ! በበዓል ምድርም ካርድ አታሞላም? ስላለተመቸኝ ነው'ኮ! እንደምንም ብዬ አንዳላሞላ በፍሪዬ ተስፋ አድርጌ ነበር ፍሪዬ ማናት ደግሞ? የቴሌ ናታ! አምና እና ከአቻምና የድምፅ እና የMB ስጦታ አብርክታልን ስለነበረ ዛሬም አትረሳንም ብዬ ብጠብቅ አሳፈረችኝ! ተናድጄ እንዳልገዛ ለካርድ የሚሆን በጀት የለኝም❗ እንደተናደድኩ ከድምፄ ለይተዋለች ወይኔ 0955327214 ይሄ ስልክ አይደል አሁን እየተጠቀምክ ያለሀው? አ...ው --- Min ---MB ተልኳልኛል አመሰግናለሁ!🫠 Anyhow፣ ቤተሰብ እንኳ አደረሳችሁ! አመቱ የተሻለ እንዲሆንም ምኞቴ ነው😍 [ Natman Ab] መስከረም ፩፡ ፪፲፩፮ ዓ.ም @getmnaleloch
Show all...
👍 3
ትንሽ ቦታ…! * በዚህ ዓመት… ብንጣላ መታረቂያ ብንታረቅ ለመጣያ ትንሽ ቦታ መጠለያ ትንሽ ብቻ መሰደጃ… ምን-አለበት…? ለምን-አልባት ብንተውለት…? ፍጹም መሆን ስለማንችል… ትንሽ ባዶ እንዋዋል በልባችን ደግ በኩል ለአንጎላችን መላወሻ - ትንሽ ቦታ እንተውለት “ምን-አልባት” የምንልበት…! ልክ እንደ አምና ለዚህ ዓመት ብንጣላ መታረቂያ ብንታረቅ ለመጣያ ብንታሰር ይቅር ማያ ይቅር ብንል መታሰሪያ ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ ጥግ ድረስ የለም ስራ ጥግ ድረስ የለም ፋታ በልባችን ደግ በኩል እንፈልግ ባዶ ቦታ የጳጉሜ ዓይነት ትንሽ ቦታ ለዘመን መለዋወጫ -------- ነቢይ መኮንን ነፍስ ይማር 🙏 @getmnaleloch
Show all...
3
ሰብለወንጌል እና በዛብህን በቴሌቪዥን በሁሉም ኢትዮጵያን ልብ ውስጥ ታትመው የኖሩት ሰብለውንጌል እና በዛብህን በቴሌቪዥን ልናያቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ እንዳስታወቁት “ፍቅር እስከ መቃብር” ተከታታይ ፊልም በአዲሱ ዓመት በኢቢሲ ለተመልካች መቅረብ ይጀምራል፡፡ በኢትዮጵያ የሥነ-ፅሁፍ ታሪክ ውስጥ በብዙዎች ልብ ውስጥ ታትሞ የቀረው፣ ብዙዎቻችሁ የምትናፍቁት፣ የትዝታችሁ እና የንባብ ልምምዳችሁ መጀመሪያ የሆነው ፍቅር እስከ መቃብር መፅሀፍ ወደ ፊልም ተቀይሮ ማየት የብዙ ጥበብ አፍቃሪ ኢትዮጰያውያን ጥያቄ ሆኖ መቆየቱን አንስተዋል። ይህ ጥያቄ ተመልሶ ፍቅር እስከ መቃብር ወደ ፊልም ተቀይሮ ለእይታ የሚበቃበት ቀን መስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን አስታውቀዋል አቶ ጌትነት። የፊልሙ የመጀመሪያ ክፍል ጷግሜ 5 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በኢቢሲ የዩቲዩብ ቻናል @EBCworld ይተላለፋል፡፡ በኢቢሲ ዜና ቻናል መስከረም 1 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት፤ እና በመዝናኛ ቻናል ደግሞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ ይተላለፋል፡፡ እንዲሁም በድጋሚ ምሽት ከዜና በኋላ በሁለቱም ቻናሎች ይተላለፋል፡፡ @EBCworld
Show all...
👌 2👍 1
ይገርማል ነገ 2017 መሆኑ🤭
Show all...
👍 7👀 2
"ሊያብብ ሲል" ሱስ ሳይበላው፣ ሲጋራ መግዣ መለመን ሳይጀምር፣ ጉስቁልና ሳያፈዘው፣ ለልብሱ መቆሸሽ ደንታ ቢስ ከመሆኑ በፊት፣ ሰዎችም ሲጣራ ባልሰማ መሄድ ሳይጀምሩ፣ ቃል አባይ ከመሆኑ በፊት፣ ክብሬ ማለት ሳያቆም፣ ለትንሽ ለትልቁ መላክ ሳይጀምር በፊት… ቆንጆ፣ ተወዳጅ እና ዘናጭ ነበር። ከጓደኞቹ በላይ ድምቅ ያለ ልጅ ነበር፤ የፀጉሩን ፍሪዝ በመስታወት አስር ጊዜ እያየ አስር ጊዜ ያስተካክል ነበር። ሕልመኛ ነበር። እንደ ሁሉም ወጣት ሀብታም መሆን፣ አዋቂ መሆን፣ ቤተሰቦቹን የመርዳት ሕልም ነበረው። የተንሸዋረረ አራድነት አሳስቶት የለኮሳት ሲጋራ፣ ለሳቅ ብሎ የተጎነጫት አረቄ፣ ለሙድ ብሎ የቀነጠሳት የጫት ቅጠል ስትደጋገም አፈዘዘችው፤ ሕልሙን፣ ወጣትነቱን፣ ክብሩን አረገፈችው። ማንም ብርቱ ነኝ ቢል ታግሎ የማያስመልሳትን ወጣትነቱን ለማያውቀው ጣዖት እየሰዋት ነው። ጥግ ላይ ተቀምጦ፤ ዘመን ሄዶ ዘመን በመጣ ቁጥር የሚመጡ ለውጦችን ከዳር በትዝብት እየተመለከተ 'ጊዜው እንዴት ነው የሚሮጠው?' የሚል ይመስለኛል። "አዎ! እሱ ጋ ያመኛል!" ገጽ-41 (አድኃኖም ምትኩ)
Show all...
👍 6
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.