cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

ግጥም '''ስሜቶች ከተደበቁበት ወረቀት ላይ ሰፍረዉ እልፍ ትዝታዎች ከተበተኑበት ተሰብስበዉ የሚቀመጡበት የጸሃፊያን ሀሳብ ማረፊያ የአንባቢያን መጽናኛ ነች''። በዚ ቻናል @betagitim ግጥሞች🔥💌 ደብዳቤዎች✍️💌 ያገኛሉ። ሃሳብ እና አስተያየቶን በዚ 👇👇👇 ያናግሩን @dawit_wegayew

Show more
Advertising posts
1 332
Subscribers
+1024 hours
+417 days
+13730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

00:34
Video unavailableShow in Telegram
#ገጣሚ_ህሊና_ደሳለኝ @🥰🙏👌❤ @betagitim @betagitim
Show all...
1.53 MB
4🙏 1
Repost from N/a
ተነጋግረን እንግባባ! ንጉስ የሆንክ እስኪመስለኝ ከበታችህ ተቀምጬ፤ አንዳች ነገር እስክትለኝ በዝምታህ ቃል ተውጬ። ይሁን መታገስ ነው ጥበብ ብዬ ምንም ብችልህ፤ አስታውስ እኔ ሚስትህ እንጂ ሴት አሽከርህ አይደለሁም! ለቃላትህ መደንገጤን መታዘዜን እንዲሁ አይተህ፤ ፍቅርን ሰቶ እንደመቀበል በዝምታ እኔን ቀጥተህ! አትቀጥልም አልቀጥልም ይሄን ነገር እንድታውቀው፤ አዋቂ ነን አትዘንጋ ችግር ካለም ተናገረው! ግና እንደ ልጅ አታኩርፈኝ አትገላምጠኝ ዝም ብለህ፤ ያልፋል ብዬ ታገስኩ እንጂ ትዕግስት አለኝ ከተረሳህ! ጥሎ መሄድ ላያቅተኝ እባክህን አትፈትነኝ፤ ተነጋግረን እንግባባ በዝምታህ አታርቀኝ! Kiya @zemenenbegetem @zemenenbegetem
Show all...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
🥰😍
Show all...
👍 4🔥 2
የተቀነጨበ ጨዋታ ከሳቅሽ ከለዛ አንደበትሽ ተደማምሮ ሳለ ከተፈጥሮሽ እንጂ ከልብሽ ምን አለ? . . . እንጃልን እኛማ ላወጋልን ሁሉ ለሳቀልን ሁሉ ሞትን ካልንማ። ዮኒ      ኣታን @betagitim @betagitim
Show all...
4👍 1
ከእለታት ባንቺ ቀን °°°°°°°°°°°°°°°°° ውል ለሌለው ጀንበር ለአሰመሳይ ጨረቃ የኔ እውነት እንዲ ነው አልወድሽም በቃ ጠብቄሽ ንቀሽኝ መጣው ስትይ ጠፋሽ ጠፋች ብዬ ሳምን በየት በኩል መጣሽ ውል ለሌለው ጀንበር ለአስመሳይ ጨረቃ የለሽም ነበረ አለሁ ባልሽበት ቤት ጠርተሽኝ ስነቃ የኔ እውነት እንዲ ነው አላምንሽም በቃ መገን አፈጣጠር እረ ጉድ ልቦና እያነሱ መጣል ላንቺ እውቀት ነውና አልከስሽም እንጂ ላበጀሽ ከኔ ጎን ገብቶሽማ ይሆናል ህመሜ አንድ ሰሞን በሚል ቁንጽል ሲቃ ናፍቆት እየሸመንኩ ከልብሽ ተጥዬ ስንት አመታትን ኖርኩ ዘመም ወለም ያለው የትዝታችን ቀን መምጣት መሄድ 'ሚሉት ትርጉም እየሰጠን መራቅ መቅረብ 'ሚሉት ትርጉም እየሰጠን መውደድ መጥላት 'ሚሉት ትርጉም እየሰጠን እንደ ማምሻ ጸሐይ እንደ ጠዋት ኮኮብ ለየቅል ለመብላት ምን ያደርጋል መሶብ አብሮነት ያለበት ጀንበር ብናነጋ መጣመር ያለበት ለሊት ብንዘረጋ ውል ለሌለው ጀንበር ለአስመሳይ ጨረቃ ትዝታሽ ነው ቀሪው ከእንቅልፌ ስነቃ የኔ እውነት እንዲ ነው አልረሳሽም በቃ በመናፈቅ ጸሎት ጠዋቴን ጀምሬ በትዝታ መዝሙር እለቴን ቀምሬ ከመራራቅ መሶብ እንድኖር ስበላ አንቺ እንደው ምንድነሽ የምትይኝ ችላ ርሀብ ያለበት መጥገብን ጠግቤ ተመስገን እንድለው እግዜር ይጠብቃል እኔ አንቺን ተርቤ አይ እግዜር ምስኪኑ ፍቅር መሳይ አንቺን ከልቤ ላይ ተክሎ መኖር ይከጅላል አንዱ ፍቅር ተብሎ አዬ እግዚያብሔር ደጉ ስለሷ ለመሞት እያጓጓ ልቤ እንድኖር ያዘኛል መሞቱን አስቤ አይ እግዜአብሔር ቸሩ እሷን በሚባርክ የዋህ ነብሴ መሀል መንግስትህን መውረስ ለኔ ምን ያደርጋል እያልኩኝ ስሞግት እያልኩኝ ስሟገት የተራራቅን እለት ሴጣን እስኪቀና በለበስኩት ድፍረት ይኸው እድሜ ለአንቺ እግዜርም 'ረገመኝ እሱን እየከዳው ለአመልክሽ አማረኝ ውል ለሌለው ጀንበር ለአስመሳይ ጨረቃ የኔ እውነት እንዲ ነው አላምንሽም በቃ ዱልዱም ስንኩል ብዕር ላይጽፍሽ እያወኩ ግጥም አይሉት ርሐብ ልጽፍልሽ ጀመርኩ ከዚ በላይ ያለው እያንዳንዱ መስመር ነበር ነበር ያለው ነበርነት ነበር በነበርነት ውስጥ ያለው ቀጭን ሲቃ አንድ አይነት እውነት ነው አልረሳሽም በቃ! ✍🏽 @betagutim 🌎 @betagitim
Show all...
👍 4🔥 2🥰 2
🥀ለናፈቀችህ/ሽ ልጅ ላክላት/ላኪለት!💔 @betagitim😍     @betagitim🥰
Show all...
_ለናፈቀችህ ልጅ ላክላት.mp35.13 KB
🔥 1
እንዴት ነው voiceu ❤️🎤 ♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️    ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ jᵒⁱⁿ⇝@betagitim☑️ jᵒⁱⁿ⇝@betagitim😍              
Show all...
Yene konjo.m4a2.45 MB
🥰 2
አለኝ ልብ የለሽም አለኝ ራሱን ጀግና አድርጎ እኔን ሊኮነነኝ ልብማ ልብማ እንደኔ የታደለ እንደእኔ በፈገግታ ሀዘኑን ሸፍኖ ችሎ ያቻቻለ ሀዘንን እያጠፋ ደስታን የሚያስነብብ እየደማም ቢሆን በፈገግታ የሚያብብ መቼ ተፈጠረ ልብማ ልብማ አለኝ እየሳቀ ሚያለቀስ እያለቀሰ ሚስቅ እየሞተ ኖሮ ነገን የሚናፍቅ * * * ✍️ስመርነሃ * * * @betagitim @betagitim
Show all...
4
ብኩን እውነት ድኩም እጣ አንቺን ስቦ ላያመጣ ይማማላል በየወንዙ እንደዋሾ ወዳጅነት አንቺን ጥዬ አነሳሽ ዘንድ እመኛለሁ ፈጣሪነት ፈጣሪነት አምላክነት ሰውን በቃል ከማስገኘት ሰውን ከቃል ማቆራኘት በቃል ትዛዝ ለሳት መጣል ስጋ ለብሶ ከሳት ማስጣል ቃልና አማኝ ዘመን አርጎን በቃል ጥዬ አነሳሽ ዘንድ እመኛለሁ አምላክ መሆን። ::::::::::::::::::::::::====:::::::::::::::::::::::::: ✍ ዳዊት @betagitim @betagitim
Show all...
5
Photo unavailableShow in Telegram
🔥 5
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.