cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ʜᴀʟᴀᴡᴇᴛᴇʟ ɪᴍᴀɴ♡

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمْ خَيْرُ ٱلْبَرِيَّةِ 🍃እነዚያ ያመኑትና መልካሞችንም የሠሩት፣ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ ናቸው፡፡ Al-Bayyinah 98:7 Channel created on may 6/2023E.C

Show more
Advertising posts
12 715
Subscribers
-124 hours
-227 days
+72030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ ምርጥ የምግብ ቻናል ላስተዋውቃችሁ እኔ ወደድኩ😍🥰 ለፆምና ለበአል ምን ልስራ ብሎ 🤔ማሰብ ቀረ እርሶ ምን ለመስራት አስበዋል? እንግዲያውስ ልዩ የሀገር ውስጥና የውጪ የምግብ አሰራር የሚለቀቅበት የTelegram ቻናል ልጠቁማቹ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ያገኛሉ፡፡
Show all...
🍕🍟 JOIN 🍕🍟
🍔🥞 ØPEN 🍔🥞
🍕🍟 JOIN 🍕🍟
---------------♡♡♡---------------               #ሁለት_ልብ ---------------♡♡♡---------------          ✰በ @hayhaf የተዘጋጀ✰ ☆በፀሀፊ፦ሀፍሳ☆ ☆ክፍል፦ስምንት(8)☆    "ለአሁኑ ማለቴ ነው ነው።ፈለክም አልፈለክም ተመልሼ መምጣቴ የማይቀር ነው"አለች። ከጎኑ የነበረውን መፅሀፍ አንስቶ ተመለከተው። ምናልባት ይሄን መፅሀፍ ካነበበው በህይወቱ ካነበበው መፅሀፍ ሁለተኛ ላይ ሊሰፈር ነው።እሷም መፅሀፍ አበርክተው ካነበበላቸው ተራ ቁጥር ውስጥ ሁለተኛ መሆኗ ነው። "ብዙ እንደማልቆይ ተስፋ አለኝ.... ስመጣ መፅሀፉን ጨርሰህ እንደማገኝህም ጭምር.... ሲቀጥል ስመለስ ህመሙን በትክክል የሚያወራ ሰው ሆነህ ባገኝህ ማለቴ በደንብ አስብበት ከዝምታ ወይስ ከመናገር የቱ የተሻለ እንደሆነ..." እሱ አሁንም በዝምታው እንደፀና ነው "እና.... መፅሀፉ ውስጥ ስልክ ቁጥሬ አለ ለማውራት ብትፈልግ እና ሰው ቢያስፈልግህ በምንም ሰአት አለሁ...."ወደ ወንበሯ ተራመደች። ቦርሳዋን እና በርከት ያሉ ወረቀቶችን ከተቀመጡበት አንስታ ሳትሰናበተው ክፍሉን ለቃ ወጣች።ኒሀልም በር ላይ ለአባቷ ያረፈደችበትን ምክንያት እያስረዳች ነው "ልትወጪ ነው እንዴ??"አለቻት ኒሀል በመገረም "አው ቆየሁ እኮ ከመጣሁ"አለች በደብዛዛ ፈገግታ "እሺ ልሸኝሽ..."ቦርሳዋን ለማስቀመጥ ወደ በሩ ተራመደች "አይ ገና መግባትሽ አደል እንዴ?ችግር የለም ራሴ እሄዳለው" "እሺ የኔ አሳቢ"ከሳቅ ጋር ታጅባ ዶክተሯ ሁለቱንም ተሰናብታ ወደ ውጪ ወጣች። ××× ከራት መጠናቀቅ ቡኋላ ረያን ወደ አሰድ ክፍል ሄደ። ኒሀልም ተከትላው መጣች።ረያን ለኒሀል የዶክተሯን ረፍት መጠየቅ ሲነግራት በጣም ተከፍታ ነበር። ሲገቡ አሰድ አንድ መፅሀፍ እያገላበጠ ነበር። ዘወር ብሎ አያቸውና መልሶ ወደ መፅሀፉ ተመለሰ "መቼም አንተ ቆዪ ብትላት ኖሮ ትቆይ ነበር ራስህ ነህ በራስህ ህመምክን እድሜ ያረዘምክለት.."ረያን ነበር ያለው።አሰድ መልስ ሳይሰጥ መፅሀፉን አንዴ ወደ ፊት አንዴ ወደ ኋላ ያገለባብጠዋል።ከገፁ ብዛት ገና ሳይጀምረው የሰለቸው ይመስላል። ኒሀል አሰድ የያዘው መፅሀፍ ያ ደጋግሞ ያነበበው መፅሀፍ እንዳልሆነ ሲገባት በመገረም ተመለከተችው። ያስገባችለትንም ራት አለመብላቱን አስተዋለች።ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ስልኩ ላይ አፍጥጦ አላገኘችውም።አንገት አቀባበሩም እንደ ሌሎች ጊዜ የብቸኝነትና ላለማውራት እና ላለማየት ሽሽት አደለም።ወደሱ እየተጠጋች "ደና ነህ አደል??"አለችው።በአወንታ ራሱን ወዘወዘ "ዶክተሯ ነች የሰጠችህ?"ወደ መፅሀፉ እያየች "አው...."አላት በቀስታ።ለብዙዎች ሚነፍገውን ምላሹ ለሷ ጊዜ ለምን አንደበቱ እንደሚላቀቅ ለሱም አይገባውም።እሷም ከሱ ጋር ምንም ያህል ነገር ቢያፋልጋትም ረያንን አሳይታው የማታቀውን ትህትና ለሱ ታሳየዋለች። "ተመልሳ መምጣቷ አይቀርም እሱ ከሆነ ያስከፋህ"አለችው ከጎኑ እየተቀመጠች።ምላሽ ስላልነበረው ዝምም አለ "ያቺ ሴት አለመደወሏም ከሆነ ያስከፋህ መደወሏ አይቀርም...."አለችው።አሁንም መልሱ ዝም ነበር "እንድትበላ ነው የማባብልህ እኮ..."ምግቡን አንስታ ወደሱ አስጠጋችው።ረያን ቆሞ ሲመለከታቸው ነበር "እሺ.. እንወጣልሀለን ተመልሼ ስመጣ ግን በልተህ እንዳገኝህ...."አለችና ለረያን ምልክት ሰጥታው ቀድማው ወጣች። "እሺ ከሷ ተምረሽ ነው?አንቺ ነበርሽ ዶክተር መሆን የነበረብሽ እኮ..."እየሳቀ አያት "አንተ ደሞ በሽታው ነህ መሰል ዞሮም አላየህም" ሳቀችበት "እንደዚ አይነት ጥጋብ እረፊ በቃ..."መታ አደረጋት "እንዴ??"የመታትን ቦታ ይዛ ፊቷን አጨማዳ አየችው። "ውይ ብሰነዝሪ ታለቅሻለሽ ኒሀል..."ወደ ኋላ ሸሸት ሲል ሰንዝራ ምትፈልገውን ያህል መታችው።ትንሽ ተሯሯጡና አባቷ ስር ሳትገባ ቀድሞ ይዟት ልመናዋን ችላ ብሎ አስለቀሳት "ምፈልገውም ይሄን አደል??"በኩራት ለቋት ወደ ሳሎን አመራ "እንደ ህፃን ተላፍቶ ማልቀስ አልተው አልሻ?"አባቷ ለቅሶዋን ሲሰሙ በመሰላቸት።እያለቀሰች ሳሎን መጥታ ለማስረዳት ስትጣጣር ረያን ፊቷን እያየ መሳቅ ጀመረ "እሱ እንደሆነ የሚያዝን ፍጥረትም አደለ ከዚ ጨካኝ ጋር አትቃለጂ ስትባይም አትሰሚ..."አባቷ ነበር ያሉት።ፊቷ ላይ የነበረውን እምባ በሹራቧ ጫፍ ጠራርጋ ድጋሚ እምባ አንከባለለች "አረ በናትሽ ህፃን ነው ምትመስይው?"ረያን ሳቁን አቋርጦ አያት።እምባዋ ለማውራት ስለከለከላት ወደ ክፍሏ ከነ ለቅሶዋ አመራች ××× ዶክተሯ አልጋዋ ላይ ተቀምጣ ቁርአን እየቀራች ነበር። እንደተለመደው ሁሉ መተኛቷን ለማረጋገጥ ወንድሟ የክፍሏን በር ከፍቶ ገባ "እሺ ኡስታዛችን...."እየሳቀ አያት "ግባ...ዛሬ ትፈትነኛለህ"አለችው በመተማመን። እሱም ፊቱ ላይ መጠነኛ ደስታ እየተነበበት ወደ ውስጥ ገባ።ቁርአን በነዝር ያኸትመችው ሰፈራቸው ካለው አንድ መድረሳ ነው።ከዛን በጣም ወጥ የሆነ ፀባይ ስለነበራት ተባረረች።እሷም ሌላ ቁርአን ቤት የመግባት ፍላጎት ስላልነበራት ቁርአኑን እርግፍ አርጋ ለመተው አስባ ነበር ወንድሟ ግን የዋዛ አልነበረም።ልክ ሱብሂ አዛን ሲል ከአልጋዋ ጎን ይቆማል።እየተነጫነጨችም ቢሆን ተነስታ ኡዱ አብራው ታደርጋለች እሱ መስጂድ ሲወጣ እያዳፋትም ቢሆን ትሰግዳለች አንዳንዴ ለመዋሸት አቅዳ የሰገደች እንዲመስለው ከመስገጃው ላይ ትተኛለች።እሱ ግን አይኗን አይቶ የሚረዳ ስለነበር ቀስ በቀስ መዋሸቱን ትታ ሰላት ጀመረች።እያደገባት ሲመጣ ወንድሟ ሊቀሰቅሳት ክፍሏ ሲሄድ እሷ ነቅታ ኡዱ ለማድረግ ስትወጣ ይገጣጠማሉ። ከመስጂድ መልስ ቁርአን ስለምታሰማው እያጠናች ትጠብቀው ጀመር።በተደጋጋሚ በሱ አስቀሪነት ካከተመች ቡኋላ ሂፍዝ አስጀመራት።እሱ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ቁርአን አለም የገባው የ9ነኛ ክፍል ተማሪ ሳለ ነበር።ሀፊዝ የሆነው ከሶስት አመት ቡኋላ ነበር።ያኔ እሷ የ7ተኛ ክፍል ተማሪ ነበረች።ከቁርአን የተባረረችው ሚንስትሪ ከተፈተነች ቡኋላ በነበራት ክረምት ጊዜ ነው። ከዛ ወቅት ጀምሮ እሷን በቃሏ ቁርአን ለማስያዝ 4 አመት ነበር የፈጀበት።የሀይስኩል ትምህርት ለመጨረስ ወር ሲቀራት ነበር ሙሉ የጨረሰችው። እንዲያም ሆኖ በየጊዜው ፈተና አላት። ከፈርድ ሰላት አልፎ ሱና ሰላት ላይም እጅግ እንድትበረታ ያደርጋል።ከብዙ ነገራቶች ለመራቅ እና በዲን ለመታነፅ ከአላህ ቀጥሎ የሱ ድርሻ አለ። ብቸኛ ማስተካከል ያቃተው ነገር የወላጅ ሀቅ እንድትጠብቅ ማድረግ አለመቻሉ ብቻ ነው። ዛሬም ቁርአን ሊፈትናት ከሷ አልጋ ጫፍ ሆኖ ቁርአኑን ተቀበላት። ### ከሱራፌል ጋር ወሬ ይዘው ሳለ ያ ያስወጣት አስተማሪ ሲገባ አየችው። "አሳልፈኝ መጣ...."አለችው በድንጋጤ።እሱም አስተማሪውን እንዳየ ቶሎ ቆሞ አሳለፋት። ከዛ ቦታ ብትወጣም የት መሄድ እንዳለባት አላወቀችም። ብዙ ሴት ተማሪዎች ከወንድ ጋር ተቀምጠው የሷ ላይ ለምን ቀልቡ እንደተሳበም አልገባትም "ቦታ መፈለግ አይጠበቅብሽም በኔ ክፍለ ጊዜ እንዳገቢ ቀርቶ ፈተናዬ ላይ እንዳትቀመጪ...." "ሀዬ...."አለችና ወደ በሩ ተራመደች።በመጀመሪያ ቀን የአስተማሪው ንግግር ሱራፌል ከተማሪው እኩል ስቆ ነበር ዛሬ ግን ትንሽ ነገሩ ክርክር ያለው ይመስላል።ኒሀል ክፍሉን ለቃ ስትወጣ ምድር ላይ የበላይ መምህሮች መኖራቸውን አስተዋለች። ከነሱ ጎን ካለው ክፍል ረብሻ ስለሚደመጥ አስተማሪ የለም በሚል ግምት ወደ በሩ በቀስታ አመራች። እንደሚያልፍ ሰው ሆና ስትመለከት አስተማሪ አልነበረም።የምታቀው ሰው ባይኖርም አማራጭ ስላልነበራት ወደ ውስጥ ገባች ...#ይቀጥላል ..... ከ200 like ቡኋላ
Show all...
👍 221 7😢 1
---------------♡♡♡---------------               #ሁለት_ልብ ---------------♡♡♡---------------          ✰በ @hayhaf የተዘጋጀ✰ ☆በፀሀፊ፦ሀፍሳ☆ ☆ክፍል፦ስምንት(8)☆    ..ምንም ቢሆን እኔ ወንድም የለኝም አልልም ምክንያቱም እንደዛ እንዳይሰማኝ የሚያረግ ወንድም ስላለኝ።ከወንድሜ ጎን አለመቆሙ እጅግ በጣም ያበሳጨኛል በጣም እከፋበታለው አሁንም ድረስ ግን ምን እንደሆነ ታውቃለህ??በእንዲ አይነት ሰአት ወንዶች እንዴት እንደሚረዱህ እና ጎንህ እንደሚሆኑ ስለማይገባቸው ነው።ሴቶች ናቸው ለእንደዚ አይነቱ ጉዳት መፍትሄ የሚያውቁት ለዛም ነው አባዬና ወንድሜ ላይ ያለኝ ጥላቻ ያን ያህል ያልሆነው እናቴን ደግሞ አብዝቼ የምጠላት" አለችው።ዘወር ብሎ እየሰማት እንደሆነ ያወቀችው ስትጨርስ ነበር።እሱ በዝምታ ሲቆይ ፈገግ እያለች "ማፅናኛም ምክርም የለህም....?" "በጣም አዝናለው ለወንድምሽ..."አላት ጀርባውን እየሰጣት።እሷም አቀርቅራ እጇን እያፍተለተለች ቆየችና "ረያን እንደነገረኝ ከሆነ ከልጅነትህ ጀምሮ ይህ ጉዳት ነበረብህ ካንተም የሰማሁት ከወንድሜ ጋር ተመሳሳይ ታሪክ እንዳለህ ነው፤ ግን መጨረሻህ ያ እንዳይሆን ስላንተ ለሚያስቡ ሰዎች ጀርባ አትስጥ። እህትህም ካለፈ ቡኋላ ልክ እንደኔ በፀፀት ከምታልቅ አንተም ያለ እድሜህ ከምትቀጭ አላህ ፊት ይዘህ የምትቀርበው ስራ ሳይኖርህ ሌላው ቀርቶ የምትወዳትን ሴት ብቻዋን ላታስቀራት ብለህ የሚሰማህን አውራ ህመምህን ተናገር።ቁስልህን ሳናውቅ መድሀኒት ልንሰጥህ አንችልም...." መልስ ሊሰጣት ስላልቻለ የብሸቀት ፈገግታ ፈገግ አለች። "ደስ የሚለው ነገር ሙያዬ ተስፋ መቁረጥን አላስተማረኝም...."አለችና እቃዋን እየሰበሰበች "ነገ እናወራለን...."ብላ ትታው ወጣች።ኒሀል ከአባቷ ጋር ወሬ ይዛ ስለነበር ከኒሀልም ጋር ሳታወራ ተሰናብታቸው ብቻ ወጣች። በየደቂቃው ስልኩን ይመለከታል።ሰአቱ በጣም ስለገፋ እነ ኒሀል ራሱ ተኝተዋል።ተስፋ እየቆረጠ ሲመጣ ስልኩን አስቀመጠውና እንቅልፍ ላይወስደው ነገር ጋደም አለ።ሰሞኑን በሚያገኘው ክፍት ሰአት በሙሉ አእምሮው በዶክተሯ ንግግር ይሞላል "እህትህም ካለፈ ቡኋላ ልክ እንደኔ በፀፀት ከምታልቅ አንተም ያለ እድሜህ ከምትቀጭ አላህ ፊት ይዘህ የምትቀርበው ስራ ሳይኖርህ ሌላው ቀርቶ የምትወዳትን ሴት ብቻዋን ላታስቀራት ብለህ የሚሰማህን አውራ"አእምሮው ላይ ደጋግሞ ያቃጭላል "ቁስልህን ሳትናገር መድሀኒቱን ልንሰጥህ አንችልም"ይሄ አረፍተ ነገር ላይ ለረጅም ጊዜ ቆየበት።ከተጋደመበት ቦታ ቁጭ እያለ እጆቹን ማፍተልተል ጀመረ "መዳን እፈልጋለው እንዴ???"ራሱን ይጠይቃል "ከምንድነው የምድነው?እኔ ጤነኛ ነኝ።" "ጤነኛ ከሆንኩ ለምን ምላሽ እነፍጋታለው??" ከራሱ ጋር ቃለ መጠይቅ ጀምሯል። ከዚ ንትርክ የስልኩ ጥሪ መንጭቆ አስወጣው ወደ ስልኩ ሲመለከት ነባት ናት።    የእህቱን ክፍል በር ከፍቶ ሲገባ አልጋዋ ላይ ላፕቶፕ እየነካካች ተመለከታት።ቀና ብላ እንኳን ስላላየችው እየሳቀ ወደ ውስጥ ገባ "ቡኋላ እናወራለን ረኢስ"ቀና ሳትል መለሰች "ምንድነው እንደዚ ያስመሰጠሽ??"አለና ከፊቷ ቁጭ አለ "ያው ቅር ይልሀል... ማወቅ ከፈለክ ግን ልነገርህ እንደተለመደው ሁሉ መልሴ 'ታካሚዎቼ'ናቸው" ቀና አለች።እሱም በፈገግታ እያያት "አው ቅር ብሎኛል ግን ይህን ያህል ምንድነው ለምን??"ወደ ላፕቶፑ እየተመለከተ "አሁን ላይ ብዙ patient አለብኝ።እና ሀሳቤ ከመብዛቱ የተነሳ ምንም መረዳት ሁላ እያቃተኝ ነው ይመስለኛል በግል የማየው ልጅ ቀላል ታካሚ ስላልሆነልኝ ብቃቴን በመጠራጠር የፈጠረብኝ ጭንቀት መሰለኝ" "ረፍት ውሰጂያ..." "የምን ረፍት??....ታካሚዎቼም እንዲብስባቸው ረፍት ልስጣቸው?" "ሌላ ሳይኮሎጂ ባለሙያ የለም እንዴ??አንቺ ረፍት መውሰድ አለብሽ ያለዛ ላንቺም ለነሱም ችግር ነው" "ልክ ነህ"አለች አንገቷን እየደፋች። "በቃ ተኚ አሁን ሁሉም ቀስ ብሎ ይደርሳል"አላት እሷም በመስማማት ራሷን ነቅንቃ ላፕቶፑን ዘጋግታ ወደ መኝታዋ ገባች ××× ከወንድሟ ጋር እንደተስማማችው ታካሚዎቿን free ለሆኑ የስራ ባልደረቦቿን እንዲሸፍኑላት ካረገች ቡኋላ ፍቃድ ወስዳ ለረያን ደወለችለት። ረያንም የነገረችው ነገር ምንም ደስ ባይለውም ላይጫናት ብሎ ተስማማ "ሌላ ሚተካለት ሰው አነጋግራለው"አለችው በመጨረሻ "አይ ሌላ ሰው መልመድ እንኳን ማይሆን ነገር ነው አንቺ ስትመለሺ ብትቀጥዪ ይሻላል..." "ዛሬ ሄጄ አወራዋለው እና ሁኔታውን አይተን  እንወስናለን"አለች።   አስተማሪ የሌለ እስኪመስል ድረስ ሱራፌል እና ኒሀል ወሬ ይዘዋል።ሱራፌል ብዙ ተማሪ የሚያወራለት የክፍሉ አስቂኝ ሰው ነው።ኒሀልም እንደማንኛውም ተማሪ የሱ ንግግር ያስቃታል። ከንግግሩ የአወራር ስልቱ እና አወራሩ ለማሳቅ ምቹ ነው።ለኒሀል ባወራው ነገር ከፊት የሚቀመጡት ወንዶች እንኳን ይስቃሉ። "ከኋላ.... ተማሪ እየረበሻቹ ነው"የአስተማሪው ድምፅ ከወሬያቸው አስቆማቸው "አንቺ ደሞ ከወንዶች መሀል ምን ትሰሪያለሽ??" አስተማሪው በንቀት አያት።ከጎኗ የሚቀመጠውም ከፊቷ የሚቀመጡትም ሶስት ወንዶች በአጠቃላይ አራት ወንድ ከቧት ስለምትቀመጥ ትኩረት ትስባለች።ተማሪው ዞሮ ሲመለከታት ተሸማቃ ጎንበስ አለች "ውጪ ከሱ ውስጥ"ጠንካራ ድምፅ ነበር ሳታንገራግር እቃዋን ይዛ ሱራፌልን አልፋው ወጣች። ከነሱ ትይዩ የነበረው ወንበር ላይ ከተቀመጡት ሶስት ሴቶች ጋር ልትቀመጥ ስትል "ለ4 ልትቀመጪ ነው?"ብሎ አንባረቀ። ተማሪው በሳቅ ሲያጅበው እግሯ ሳይቀር ከዳት።እንደምንም ለሁለት የተቀመጠ ተማሪ ቀና ብላ ቃኘች።ሶስተኛ መደዳ ላይ ሁለት ወንዶች የተቀመጡበት ክፍት ቦታ ስታገኝ ወደዛ አመራች ለመቀመጥ ስትል "አይ የወንድ ፍቅር..."አለ አስተማሪው።ክፍሉ ስታዲየም እስኪመስል ድረስ በሳቅ ተሞላ ከሱ ንግግር የተማሪው ሳቅ አበሸቃት። "የት ልቀመጥልህ ታዲያ?"እጅግ ስለተናደደች ዞራ በንቀት አየችው "ቦታ አጥተሽ እንደሆነ ውጪያ..." "በደስታ ነዋ..."ቦርሳዋን አንድ ዴክስ ላይ አስጩሃ አስቀምጣ ወደ በሩ በኩራት ተራመደች። ለአስተማሪው ንግግር ሲስቁ የነበሩት በሙሉ በድንጋጤ ጭጭ ብለዋል "ጋጠወጥ ድጋሚ በኔ ክፍል ትገቢያለሽ ቆይ"አላት ወደ በሩ እየተራመደ።በሩንም በግዴለሽነት ዘግታው ወጣች።      እነ አሰድ ቤት ስትደርስ ኒሀልም ረያንም አልነበሩም።የነ ኒሀል አባት ደጅ ላይ ተቀምጠው እያብሰለሰሉ ነበር።ለኢስላሚዊ ሰላምታዋ ምላሽ እንደሰጧት "ኒሀል አልመጣችም እንዴ??"አለቻቸው "አው ልጄ.... ግቢ መምጣቷ አይቀርም"አሏት። እሷም በመስማማት ራሷን ነቅንቃ ገባች። አሰድ ከመፀዳጃ ቤት ወደ ክፍሉ እየገባ ነበር።የክፍሉን በር ክፍት አድርጎ ሲተውላት እሷም በፈገግታ አፀፋውን መልሳ ገባች። "ደስ በሚል ሁኔታ ልትገላገለኝ ነው"አለችው ከወንበሩ ላይ እየተቀመጠች።እሱ በግራ መጋባት እንዳቀረቀረ ፊቱን አጨማደደ "ለስራ ረፍት ልወስድ ነው እና ሌላ ዶክተር ልተካልህ ወይስ እኔ ረፍት ስጨርስ ብቀጥል ትመርጣለህ??"አለች መልስ የለም። "መልስ ስጠኝ ለጥያቄዬ?"ቁጣ ያዘለ ጥያቄ "እኔ ምንም ዶክተር አልፈልግም" "እኔም ረፍት ስጨርስ እንድመለስ አትፈልግም ማለት ነው?"በእርጋታ ጠየቀች።መልስ ሳይሰጣት ዝም አለ "እሺ.."አንድ መፅሀፍ አውጥታ ወደሱ ሄዳ ከጎኑ እያረገች "የመጨረሻ ስጦታዬ ነው?"አለችው። ዘወር ብሎ አየውና "የመጨረሻ??"አላት ልምምጥ ባጀበው የጥያቄ ድምፅ ...... #ይቀጥላል ...... ከ200 like ቡኋላ
Show all...
👍 350 5
.❤️ ያ አላህ በምመኘው ነገር ላይ አብስረኝ ካንተ ውጪ መልካምን አብሳሪ የለምና @hayhaf
Show all...
66🙏 11👍 3
.💔 ምድር ላይ ለእኔ በጣም ከባዱ ነገር እናቴ ምትፈልገውን ነገር እያወኩ ያን ለሷ ማድረግ አለመቻሌ ነው ። @hayhaf
Show all...
💔 122👍 20
.😁 የፍቅር ጥያቄ በጓደኛቹ ምታስጠይቁ ተማሪዎች ምን ጉድ ናቹ class ሊጀመር ነው አዲስ ተማሪ ከገባች እናንተን አያገባቹም አርፋቹ ተማሩ ሀይስኩል እንጂ American አይደለም የገባቹት 😑 @hayhaf
Show all...
በደንብ አውቀዋለው ብለህ ከምትወራረድበት ሰው ውስጥ ሌላ የማታውቀው ሰው አለ!!! @hayhaf
Show all...
👍 63💔 5
---------------♡♡♡---------------               #ሁለት_ልብ ---------------♡♡♡---------------          ✰በ @hayhaf የተዘጋጀ✰ ☆በፀሀፊ፦ሀፍሳ☆ ☆ክፍል፦ሰባት(7)☆     "እስካሁን መልስ እየሰጠሽ አደለማ??" "ሁሉም ታካሚዎቼ እኮ መዳን አይፈልጉም። ካወሩማ ምኑን የስነ ልቦና ተጎጂ ሆኑ"አለችው ቀስ በቀስ የአሰድን ዝምታ በጥሩ እየወሰደችው መጥታለች "እሱ መዳን ይፈልጋል..." "አይመስለኝም..."አለች እይታዋን ከመንገዱ እንዳደረገች "አንደኛው የህመሙ ምክንያቶች እናንተ እንደሆናቹ ብነግርህስ?"አለችው በእርጋታ "ምን ማለት ነው ደሞ??" "በአንድ ቤተሰብ ምሳሌ ሰጥቼ ልነገርህ አንድ እናት እና አባት ሶስት ልጆች አላቸው እንበል። የመጀመሪያው ልጅ 'እንዲ አድርገሀል እንዲ አጥፍተሀል'ሲባል ቁጡ ይሆናል።እህቶቹም ወንድሞቹም በሱ እንዲያሾፉ አይፈልግም ግንፍል ነው ራሱን ማስከበር ይፈልጋል ለቀልድ እንኳን እሱን እንዲናገሩት አይፈልግም ያ አይነት ባህሪ ያለው ሰው አለ.... ሁለተኛ ቸልተኛ!!ማለትም ተቀልዶበት እንኳን አብሮ የሚስቅ አይነት ልጅ ሰዎች ላይ ያሾፋልም ሲሾፍበትም ምንም የማይመስለው!ቤተሰቡ በጥፋቱ ወንጅለውትም ያለ ጥፋቱ ተቆጥተውትም መስሎም የማይታየው ሌላውን ተወው እና እህቶቹ ወይ ወንድሞቹ አብረው ቢሰድቡት እሱም በራሱ የሚሳለቅ ምንም መብሸቅ ማይችል ልጅ...እንደዚ አይነትም ልጅ አለ! ሶስተኛ ሆደ ባሻ... ይህ አይነቱ ሰው ለቁስል እጅግ ቅርብ ነው።ጥፋት ሲያጠፋ ምክንያቱን ለማስረዳት እምባ ሚቀድመው።ያለ ጥፋቱ እየተሰደበ እንኳን ማስረዳት ማይችል።ለስድብም ለቀልድም ቀልቡ ስስ የሆነ!ቀርቶ ተመሳጥረህ ብቻህን ሆነህ እንኳን ልቡን መስበር የምትችለው አይነት ልጅ!!አሰድ ሶስተኛው ልጅ ነው በቃ ምንም አይችልም።ያን ቀን ኦቲዝም ይባል እንደነበር ስታወራ ወንድነቱ ተፈታተነው ከፊቴ እኮ ነበር ያለቀሰው እምባውን ለመደበቅ ሲጥር ነበር...." "እሱ ባህሪው ነው ድሮም ቀልድ ያስለቅሰዋል" አላት በእርጋታ "ላንተ ቀልድ ነው እሱ ልብ ላይ ግን ቀልድ አደለም። እንደምታስብለት አውቃለው እንደምትወደውም ጭምር ግን በዚ ከቀጠለ ጉዳቱ እንዲጠላቹ ነው የሚያደርገው በወንድሜ አይቼዋለው እና ሁሉም ካለፈ ቡኋላ ፀፀት ነው የሚሆንብህ ሳይረፍድ አገናዝብ..." እንደመቻኮል ብላ "እስከዚ ከሸኘኸኝ በቂ ነው እዛ ጋር ታክሲ እይዛለው ደና እደር...."አለችው።ቆሞ እስክትርቅ ተመለከታት። ××× "ዶክተሯ ግን ምንም እየቀየረች አደለም ልጁ እንደ ድሮ ነው ዝም ብላቹ ብር ባትጨርሱ ጥሩ ነው" አለቻት የኒሀል ጓደኛ የነ ኒሀል ክፍል ለእረፍት በተቀመጡበት "እስኪ ፊ ደሞ ምንም ማይባል አታውሪ 2 አመት የተፀናወተው ነገር ወር ባልሞላ ጊዜ ይድናል እንዴ??"ኒሀል ከመስኮቱ አሻግራ ወደ ውጪ እያየች "ቢሆንም ትንሽ ለውጥ ካላየሽ እኮ ደስ አይልም" "እኔ ግን ከአላህ ቡኋላ እንደምትቀይረው አቃለው አሰድ እኮ መምጣቷን ባይወደው እና እንድታወራው ባይፈልግ እኮ በዛ ሰአት መነሳቱን ያቆም ነበር። በቃ እሱም ሚያወራው ሰው ስለሚፈልግ ነው ሁሌ በምትመጣበት ሰአት መነሳቱን የቀጠለው...." "ልክ ነሽ የምር...."አለች እሱ ነገር ትዝ ሲላት "በዛ ላይ ለኔም እንደ እህት ናት።ንግግሯ ማር በይው..."ኒሀል ሳቅ አለች "እንዴ በጣም ያኔ ቡና ሲጠጣ የመጣች ቀን እንዴት ነው በአንዴ ቤቱን ያደመቀችው ረያን ራሱ እንደዛ ሲያወራ አይቼው አላቅም" "እሱማ ፎንቅቋል መሰለኝ"ኒሀል ሳቅ አስከተለች "ከምርሽን ነው ??እንዴት??"እሷም ለወሬ ሰፍ እያለች "በቃ ነገረ ስራው ነዋ....በያዘውና ሙድ እንድይዝበት ቢያበቃኝ" "ፊዮሪ ይላል ምን እግር ጣለሽ..."የአንድ ወንድ ድምፅ ከወሬያቸው አቋረጣቸው።ዘወር ሲሉ ከኒሀል ጎን የሚቀመጠው ልጅ ነው።እጁን ዘርግቶ በፈገግታ እያያት ነበር "እንዴ ሱራ..."እሷም በፈገግታ ጨበጠችው "ኒ...." ወደ ኒሀል እየሳቀ ዘረጋ "አሰግጥ ባክህ"ገለመጠችው "ኡዱ አለሽ??"አላት እየሳቀ እጁን እየሰበሰበ። "Geo የቤት ስራ አለ ምትሰራ ከሆነ ስራ...." አለችው ደብተር እየሰጠችው "ከምታወሪ አትፅፊም ነበር" "እዳ አለብኝ...."በንቀት መለሰች።ከነሱ ፊት ተቀምጦ መገልበጥ ጀመረ።ሲደወል ፊዮሪ ወደ ክፍሏ ለመሄድ ስትነሳ ሱራፌል ከኒሀል ጎን ለመቀመጥ ተነሳ። ××× አሰድ እንደ ልማዱ ጀርባ ሰጥቷት ነበር የተቀመጠው እሷ ለረጅም ደቂቃዎች ስታወራ ነበር።በመሀል እንደምንም ራሱን አደፋፍሮ "ታሪክሽን ጨርሺልኝ..."አላት።ስጠብቀው የነበረው ጥያቄ ስለነበር ፈገግ አለች "ከዛ በፊት አንድ መስፈርት አለ"አለችው።መልስ አልሰጣትም "እነግርሀለው ታሪኩን ምክንያቱም ጓደኝነታችንን ስለምፈልገው አንተም እንደ ጓደኛ ያንተን ህመም ትነግረኛለህ" "እኔ ጓደኛ አልፈልግም" "እሺ እህት" "እሱንም ቢሆን አልፈልግም...." "እሺ... ማን ያቃል የሆነ ሰአት ጓደኛ እንደምትፈልግ ትነግረኝ ይሆናል።ግን ለምን ታሪኩን እንድነግርህ ፈለክ??" በድካም ተነፈሰ "ይሄን ከመለስክ ጓደኛ መሆንም አይጠበቅብንም እነግርሀለው... "የወንድምሽ ከኔ ጋር ይመሳሰላል መጨረሻው ምናልባት የኔም መጨረሻ ሊሆን ይችላል ልወቀው ቀድሜ"አላት "አይ መጨረሻውማ አይመሳሰልም.... አንተ እኮ ጎንህ ሰው አለ ሊረዳህ የሚፈልግ የሚጥር እሱ እኮ ማንም አልነበረውም...." "ማን አለኝ እኔ??" ለራሱ የሚጠይቅ በመሰለ ዝቅ ያለ ድምፅ "አይመስልህም እንጂ ወንድምህ ከማንም በላይ ያስብልሀል።ምናልባትም የምትወዳት ሴት ጎንህ ናት ማለት እችላለው።ሌላ ደሞ እኔም ልረዳህ እየሞከርኩ ነው።እሱ እኮ ማንም አልነበረውም...." "ታሪኩን ንገሪኝ..." "እሺ... እሱ ያው ጭንቀቱም መገፋቱም ብቸኝነቱም ሀሳቡም ብቻ በጣም ውስጡ ተደማምረው አድጎ ስለነበር በስትክክል አብዶ ነበር። ከዛን የአእምሮ ህክምና ጀመረ እኔም በተቻለኝ መጠን ራሴን ላለማምደው ሞከርኩ ስሜን እንኳን አያውቅም።ከሱ በታች አንድ ወንድም አለኝ ከኔ ታላቅ ነው እና እሱም በጣም ሞክሮ ነበር።ብዙ ነገር አይተናል ማለቴ ሲነሳበት አደገኛ ሰው ይሆናል አንዳንዴ ደሞ በጣም ፀፀት ውስጥ የሚጨምርህ አሳዛኝ ሰው ይሆናል። አዲስ ሰው ሲያይ ተማታ ተማታ ይለዋል ሰዎች በጣም ይፈሩት ነበር አንድ ሰሞን እጅግ ሲበረታበት መታሰር ጀምሮ ነበር።ብቻ አንድ ጊዜ ጭራሽ ባልጠበቅነው ጊዜ ማለቴ ማንም ያላሰበው ነገር ተፈጠረ።ራሱን አጥፍቶ አገኘነው።ሲጀምረው እንደ እብድ ያሸሹት ቤተሰቦቼ አለቀሱ።የእናቴ እምባ የአዞ እምባ ይመስለኛል አሁንም ድረስ...." ከማለቷ ጀርባ ሰጥቶ ከነበረበት ቦታ ዘወር ብሎ ይመለከታት ጀመር "እነሱ እንደገደሉት ተሰማኝ።ታቃለህ ለሱ ማዝነው አብዶ ስለነበረው ማንነቱ ተወው ቢያንስ ቀለም ከሱ ተነስቶለታል ይባል...ከዛ በፊት ከአላህ ሸሽቶ ነበር።በጤናው ጊዜ ስለነበረው ህይወቱ ሲጠየቅ ምንድነው ምላሹ ብዬ እጨነቃለው! ያኔ ሰው ጎኑ ቢኖር ቢያንስ መጨረሻውን እንዲ አይሆንም ብዬ አስባለው...... ...... #ይቀጥላል ...... ከ200 like ቡኋላ
Show all...
👍 407 4🥰 4🔥 1
አላህ ሆይ ይመጣሉ ብዬ የምጠብቃቸውን ቀናቶች ቅርብ አድርግልኝ ። @hayhaf
Show all...
90👍 5🙏 4🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
#የቅዠት ህልም😭 የቅዠት ህልም  የተሰኘዉን አጉዋጊ😱 አስተማሪ ልብ አንጠልጣይ😍 ታሪክ ልናስነብባችሁ ወደድን❤️ ታሪኩን ለማግኘት join ሚለዉን ንኩ👇👇
Show all...
join
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.