cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍኖተ ቅዱሳን

Advertising posts
1 017
Subscribers
+124 hours
+357 days
+15730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የነፍስ ምግብ እንጅ አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ጾም የሥጋ ሥቃይ ሰማዕትነት ወይም መስቀል አይደለም ሥጋ ከነፍስ ጋር የሚተባበርበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፍ ከፍ የሚልበት እንጂ። ስንጾም የመጾማችን ዕቅድ ሥጋችንን ለማንገላታት አይደለም ጠባዩን ለመግራት እንጂ። ይህ በመሆኑም አንድ የሚጾም ሰው መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ሰው አይሆንም ማለት ነው ። ጾም መናኝ ነፍስ ስለሆነ በምናኔ ውስጥ ያለ ባልንጀራ ሥጋውን ይዞ ይጓዛል እንጂ ብቻውን አይጓዝም። ጾም ማለት የተራበ ሥጋ ማለት አይደለም የመነነ ሥጋ እንጂ። ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የሥጋ ልዕልና እና ንጽህና እንጂ ለመብላት የሚናፍቅ የሚራብ ሰውነት ያለበት ሁኔታ ማለትም አይደለም፤ መብላት ዋጋውን የሚያጣበትና ሰውነት ለመብላት ካለው ፍላጎት ራሱን የሚያላቅቅበት ሁኔታ እንጂ። ጾም ነፍስ ከፍ ብላ ሥጋን ከእርስዋ ጋር ከፍ የምታደርግበት ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ሥጋ ጓዙንና ሸክሙን የሚያራግፍበት ጊዜ ስለሆነ እግዚአብሔር ያለ ምንም እገዳ ለመንፈሳዊ ዘላለማዊነት ደስታ የሚሠራበት ጊዜ ይሆናል። ጾም ማለት ነፍስና ሥጋ በኀብረት መንፈሳዊ ተግባር ለማከናውን የሚጠቀሙበት ጊዜ ነው። በጾም ወቅት ነፍስና ሥጋ የነፍስን ሥራ ለመሥራት ይተባበራሉ። ይህም ማለት  ለጸሎት ለተመስጦ ለክብርና ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ለመጋራት ይተባበራሉ ማለት ነው። ብጹዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
Show all...
ጾም እጅግ ግሩም የሆነ ነገር ነው፡፡ ኃጢአታችንን እንደማይጠቅም አረም ከውስጣችን ይነቅለዋል፡፡ እውነተኛው የጽድቅ ተክልም በውስጣችን ልክ እንደ አበባ እንዲያብብ ይረዳዋል፡፡  (ቅዱስ ባስልዮስ) ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጾም ነው፡፡ የምንጾምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጾም ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትን፤ ጥንካሬን ሰላምን፣ ንጽሕናን እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡ (ጻድቁ ዮሐንስ ዘክሮስታንድ)
Show all...
“ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡ አስቀድመህ እንደዚህ ካደረግህም፥ ወደ ትዳር ከገባህ በኋላ ፍቺ አይገጥምህም፡፡ ሚስትህ ሌላ ሰውን አትመኝም፡፡ በሌላ ሴት እንድትቀናም አታደርግህም፡፡ በመካከላችሁ [ለክፉ የሚሰጥ] ጠብና ክርክር አይኖርም፡፡ ከዚህ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከላችሁ ይሰፍናል፡፡ እነዚህ ካሉ ደግሞ ሌሎች በጎ ምግባራትን፣ ትሩፋትን ለመፈጸም አትቸገሩም፡፡” © ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ፣ ገጽ 33
Show all...
5👍 4
"ጠላት በመኾን የተነሣብህን ሰው የምትርቅበት መንገድ አለ ይህውም እርሱን ወዳጅ በማድረግ መቀየር ነው፡፡''      ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Show all...
ምክረ አበው - ከመጽሐፈ መነኮሳት ድንቅ ነገር እነግርህ ዘንድ እወዳለሁና ወንድሜ ጸጥ ብለህ ስማኝ ኅሊናህን ከዝንጋዔ ወስነህ ስማኝ፡፡ ልብህን ከሥጋዊ ሁከት ለይ፡፡ እንዲህ የሆነ እንደሆነ በትሩፋት የተነገረውን ጸጋ ታገኛለህ በትሩፋት መዓዛ ጸጋን ታሸታለህ፡፡ ሕፃናትን የፈጠረ ጌታ ትሕትናን የዕለት ጽንስ በመሆን እንደ ጀመረ ዕወቅ፡፡ ትሕትናን ከሱ ተማር፤ ስላንተ የሠራውን ሥራ ሁሉ ታውቅ ዘንድ በትሕትና ኑር፡፡ እርሱን አስመስሎ ይወልድህ ዘንድ አንተን መስሎ ተወለደ፤ ዓለምን የፈጠረ፣ የሁሉ ማረፊያ ጌታ ቤት እንደሌለው በጎል ተወለደ፤ በጨርቅ  ተጠቀለለ፣ በተናቀ ቦታ በጎል አደረ፡፡ የሥጋ ሀብት የነፍስ ሀብት መገኛ ሲሆን ለዘለዓለሙ ነግሦ የሚኖር ንጉሠ ነገሥት ጌታ በጨርቅ ተጠቀለለ፡፡ የስደተኞች ማረፊያ፣ መጠጊያ የሚሆን እሱን እሽኮኮ ብለው አሸሹት፡፡ የሁሉ ደስታ የሚሆን ጌታ ሄሮድስ ይገድለዋል ብለው እየፈሩ አሳደጉት፣ መንግሥትን ሁሉ የሚያሳልፍ መከራን የሚያሳልፍ እሱን ጸብ ክርክርን የሚያጠፋ እሱን ይሙት በቃ እንደተፈረደበት ሰው ካገር አስወጥተው ሰደዱት፣ ሞትን የሚያጠፋ እሱ ሲሆን እንገለዋለን ከሚሉ ሸሽቶ አመለጠ፡፡ ከተለዩ የተለየ፣ ከከበሩ የከበረ ሲሆን አንተን ያከብርህ ዘንድ በውኃ ተጠመቀ፡፡ ልዕልናውንም አብ በዮርዳኖስ “የምወደው ልጄ ይህ ነው” ብሎ ሲመሰክር ተሰማ፤ መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ሲያርፍበት ታየ፡፡ ካባቱ ጋር ያዋህድህ ዘንድ አንተን ለመሻት የመጣ ወልድ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ከርሱ ጋር ለመኖር በበጎ ሥራ ብትመስለው ወደ አባቱ ያቀርብህ ዘንድ በትሩፋት መጋደልን፣ ድል መንሣትን ያስተምርህ ዘንድ አርባ ቀን ጦመ፡፡ አንተ ቡሩክ ተብለህ ትመሰገን ዘንድ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህስ…” ብለው አይሁድ ዘበቱበት። በአጋንንት እጅ በኃጢአት በትር የተመታ ርእሰ ልቡናህን ያከብር ዘንድ ራሱን መቱት። የሰይጣንን ምክር ሰምታ የሚያሳዝን ኃጢአት የሠራች ሰውነትህን ጣዕም እንዲገኝባት ያደርጋት ዘንድ መራራ ከርቤ ጠጣ፡፡ በዕፀ በለስ ምክንያት ከመጣ ሞት ያድንህ ዘንድ በመስቀል ተሰቅሎ ሞተ። ከመቃብር ያስነሣህ ዘንድ ወደ መቃብር ወረደ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣህ ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ይህን ሁሉ ስላደረገልህ ፈንታ አንተ የምትሰጠው ዋጋ ምንድን ነው? እስኪ ንገረኝ፤ ከዚህ ማዕረግ ደርሰህ እርሱን በማየት ደስ ይልህ ዘንድ ከወደድክ የእርሱን ነገር በመናገር የምታደንቅ ብቻ አይሁን እንደ ዮሐንስና እንደ ጴጥሮስ በዓይ ሕሊናህ ተመልከተው እንጂ። እኔ እንደነገርኩህ እሱን በማሰብ ፀንተህ ኑር። እንዲህ የሆነ እንደሆነ በእውነት ይገለጽልሃል፣ የተወደደ መልኩን ዓይቶ ለማድነቅ እንድትበቃ ያደርግኻል፡፡ በበጎ ፍቅሩ ሰውነትህን እንደ እሳት ያቃጥላታል፡፡ በሱ ዘንድ ባለሟልነትን ሰጥቶ ደስ ያሰኝኻል፡፡ እንደ እመቤታችን በክንድህ እቀፈው፣ ሰውነትህ እንደ እመቤታችን ለሱ ሞግዚት ትሁን። ሰብአ ሰገል እጅ መንሻን ይዘው ወደሱ በመጡ ጊዜ እጅ መንሻህን ይዘህ ከርሳቸው ጋር እጅ መንሻውን አቅርብለት፡፡ ከእረኞችም ጋር መወለዱን ተናገር፡፡ ምስጋናውን ከመላእክት ጋር ተናገር፣ ወደ ቤተ መቅደስም ባገቡት ጊዜ እንደ ስምዖን በክንድህ ታቀፈው፤ ወደ ግብጽ በወረደ ጊዜ አሽኮኮ ብለኸው ውረድ። አቅፈኸው ከዮሴፍ ጋር ሂድ፡፡እንደ ምድረ ግብጽ ያለች ሰውነትህን እንደ ኢየሩሳሌም ያደርጋት ዘንድ ከሕፃናት ጋር ሲድህ ሰርቀህ ሳመው፡፡ በመዓዛው ደስ ይላት እንደነበረች እንደ እመቤታችን የመላእክት፣ የጻድቃን መገኛ የሚሆን የጌታ መዓዛውን አሽት፡፡እንደ እመቤታችን ያቅፈው የነበረ፣ በመዓዛውም ደስ ይለው የነበረ አንዱን ሰው እንደማውቀው በእውነት እናገራለሁ፤ ሕፃናትን ምሰል፤ በሕፃንነቱ ሳለ ከሄደበት ሁሉ ተከተለው፡፡ እንዲህ የሆነ እንደሆነ ፍቅሩ ባንተ ታድራለች፡፡ ከሱ ጋር አንድ በመሆንህ ይዳሰስ በነበረ በማኅየዊ  ሥጋው ያለ መዓዛን ከሟች ሥጋህ ታሸታለህ፡፡ መምህራን በጠየቁት ጊዜ እሱም በመለሰላቸው ጊዜ አጠያየቁን አመላለሱን አድንቅ፡፡ ለማጥመቅ ከዮሐንስ ጋር ባንድነት ኑር፣ በዮርዳኖስ የሚደረገውን ሁሉ ስማ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ሲቀመጥበት እይ፡፡ በሚጾምበትም ጊዜ ከሱ ጋር ጹም፤ ውኃውን ለውጦ ወይን ባረገ ጊዜ ጋኖችን ውኃ እየመላህ ኑር፤ ከውኃ አጠገብ ከሳምራዊት ጋር በተነጋገረ ጊዜ ያስተማረውን ትምህርት ስማ፤ አብ የሚወደውን በመንፈስ የሚደረገውን ስግደት፣ የሚሰግዱ ሁሉ በመንፈስ ለአብ ይሰግዳሉ ብሎ ሲያስተምር ስማ፤ ሙታንንም ባስነሣ ጊዜ ትንሣኤ እሱ እንደሆነ እወቅ፣ ኅብስቱንም ባበረከተ ጊዜ እንቅቡን ይዘህ ለተሰበሰቡት አድል፣ ወደ ገዳምም በሄደ ጊዜ ሄደህ ሸኘው፡፡ በመርከብም በተኛ ጊዜ፣ ጌታ ሆይ አድነን ልንጠፋ ነው ብለህ አስነሣው፣ በጉባኤም ከሱ ጋር ኑር፣ በጎዳናም ከሱ ጋር ሂድ፣ ወደ ገዳም ከሱ ጋር ሂድ፣ በመርከብም ከሱ ጋር ኑር፣ ወደ  ደብረ ዘይትም ከሱ ጋር አብረኸው ውጣ፣ በምኩራብም፣ ብፁዓን እያለ ሲያስተምር ትምህርቱን ስማ፣ ያስነሣህ ዘንድ ከአልዓዛር ጋር በመቃብር ኑር፣ በኃጢአት ከመጣ ፍዳ ትድን ዘንድ እንደ ማርያም በዕንባህ እግሩን እጠበው፤ በራስህም ጠጉር አድፈው፡፡ የኃጢአትህን ሥርየት ኃጢአትህ ተሰረየልህ ሲል ትሰማ ዘንድ፤ በማዕድም ጊዜ እንደ ዮሐንስ ባጠገቡ ተቀመጥ። ኅብስቱን በባረክ ጊዜ ሥጋውን ደሙን ከጁ ተቀበል፡፡ የደቀ መዛሙርቱን እግር ባጠበ ጊዜ ከኃጢአት ያነጻህ ዘንድ ቀርበህ እጠበኝ በለው፡፡ ማኅደረ እግዚአብሔር ሰውነትህን ንጽሕት አድርጋት፡፡ እሱን ለማመስገን ብቃ፣ በምግባር በሃይማኖት ተከናወን፡፡ነገረ ጰራቅሊጦስን ለመማር የበቃህ ትሆን ዘንድ፣ ካምስት ገበያ ሰዎች ጋር ከፊቱ ቁም፣ ከሱ ጋር መከራ ተቀበል፡፡ ይህ አሳች መባልን፣ ሳምራዊ መባልን፣ መዘበቻ መሆንን ተቀበል፡፡ ወሪቀ ምራቅን ተቀበል፤ በቀኖት መቸንከርን ተቀበል፣ ከሱ ጋር እንደ እሱ በመስቀል ተሰቀል፡፡ በተነሣ ጊዜ (በመዋሐድ ጊዜ) ደስ ይልህ ዘንድ ከሱ ጋር መፃፃውን ከርቤውን ጠጣ፡፡ ራሱን ዘለፍ እንዳደረገ አንተም ዘለፍ አድርግ፣ እርሱ እንደ ተነሣ ትነሣ ዘንድ እንደሱ፣ ከሱ ጋር ሙት እኩያን አይሁድ በሱ ያደረጉትን ሁሉ ተቀበል፡፡ የማትመረመር ቸርነቱን ፈጽመህ አድንቅ፣ ምን አደረገ ትለኝ እንደ ሆነ፣ መላእክትን አታጥፉ ብሎ ከለከላቸው፣ ዓለምን፣ በዓለም የሚኖሩትን ሁሉ ያጠፏቸው ዘንድ አላሰናበታቸውም፡፡ ዓለቶች ተሰነጣጠቁ፣ ሙታንም ተነሡ ልቡናችን ግን ከጽናቱ አልተለየም፣ ማለት አላመነም፡፡ ሕዋሳተ ነፍስም ትንሣኤ ኅሊና አልተነሡም። ሰውነትህ እንደ ማርያም መግደላዊት በፍርሀት፣ በረዓድ ሁና ከመቃብሩ አጠገብ ትቁም፡፡ መላእክት ምን ያስለቅስሻል ብለው ይጠይቋት ዘንድ፣ ጌታን ባየችው ጊዜ የት ወሰድከው ብላ ተክል ጠባቂውን እንደ ጠየቀችው ትጠይቀው ዘንድ ያን ጊዜ እንድታውቀው ሆኖ ይናገራታል፡፡ በዝግ ደጅ ወደ ጽርሐ ጽዮን በገባ ጊዜ ተነሥተህ ተቀበለው፡፡ በጥብርያዶስ ቁሞ ልጆቼ የሚበላ አላችሁን? ብሎ በጠየቀ ጊዜ ጴጥሮስን ምሰለው፡፡ መላእክት ያዘጋጁትን ማዕድ ከሱ ጋር ብላ፡፡ ባረገም ጊዜ በአንብሮተ እድ ይባርክህ፣ ይሾምህ ዘንድ ራስህን ዘንበል አድርግ ወዳየር ተመልከት፡፡ ጌታ ባረገ ጊዜ በመላእክት ብርሃን ያበራልና፡፡ ጥቂት ቀን በጽርሐ ጽዮን ኑር፡ ቋንቋ የሚገልጽ መንፈስ ቅዱስ ያድርብህ ዘንድ ወንድሜ በፍጹም ትጋት ሁነህ በልቡናህ ይህን አስብ፡፡
Show all...
የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በሕይወት ላይ ያተኮሩ ጽሑፎችና ሌሎች ኦርቶዶካሳዊ ትምህርቶች በጽሑፍና በድምጽ ይቀርብበታል

የጸሎት ጊዜ የለኝም በጃፓን ሀገር የምትኖር አንዲት አረማዊ የነበረች ሴት በኋለኛዋ ዘመን ክርስቲያን ትሆናለች፡፡ ነገር ግን ከድህነቷ የተነሳ የጸሎት ጊዜ አልነበራትም፡፡ አንድ ቀን ክርስቲያን ጎረቤቶችዋ መጥተው አንቺ ክርስቲያን ሆኛለሁ ብለሽ የለ እንዴ? ታድያ እንደ ክርስቲያኖች ስትጸልይ ድምጽሽን ሰምተን አናውቅም አሏት፡፡ እርሷም እኔ ድሃ ስለሆንኩ ስራ ስለሚበዛብኝ ጸሎት ለማድረስ የእረፍት ጊዜ የለኝም አለቻቸው፡፡ ነገር ግን በየጊዜው ጸሎት አቋርጬ አላውቅም፤ ጠዋት ከመኝታዬ ስነሳ ቀሚሴን ስለብስ አቤቱ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን እንደዚህ አልብሰኝ እለዋለሁ፡፡ ውሃ አቅርቤ ፊቴን ስታጠብ አቤቱ የልቤን እድፍ በመንፈስ ቅዱስ አጥበህ ንጹህ አድርግልኝ እለዋለሁ፡፡እሳት አቅርቤ ብዙ እንጨት ጨምሬ ሲነድ ባየሁ ጊዜ አቤቱ ልቤ በፍቅረ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ እንዲቃጠል አድርግልኝ እለዋለሁ፡፡ መልካም ሩዝ ቀቅዬ በስሎ በምበላበት ጊዜ አቤቱ ከረሀበ ነፍስ እንድድን መንፈሳዊ ምግብ አዘጋጅልኝ እለዋለሁ፡፡ ልብሴን አጥቤ በመተኮሻ ተኩሼ ቀጥ ሲል ባየሁት ጊዜ አቤቱ ቀጥ ያለና የቀና ልብ ስጠኝ እለዋለሁ፡፡ እንደዚህ እያደረግሁ ሥራዬንና ጸሎቴን በአንድነት እጨርሳለሁ እንጂ የተወሰነ የጸሎት ጊዜ የለኝም አለቻቸው፡፡ ምንጭ፡- ጎሀ ጽባህ ገጽ 97 ✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧ (ሳናቋርጥ መጸልይ እንዳለብን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይለናል "ሥራ የሚሠራ ሰው ቀኑን ሙሉ በጸሎት ተፀምዶ መዋል አይችልም አትበለኝ፤ ይችላል። በጸሎት የሚያስፈልገው ድምፅ ሳይኾን አሳብ ነው፤ እጅ ሳይኾን እደ ልቦናን ማንሣት ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ ቦታም ጊዜም አይገድብህም። በጉልበትህ ባትንበረከክ፣ ደረትህንም ባትደቃ እንኳ መንፈስህ ትጉ ከኾነ ጸሎትህ ሥልጡን ነው።")
Show all...
👍 2
ወዳጄ ሆይ መልካም ወዳጅ ትባል ዘንድ እግዚአብሔር አምላክህን ካላወቅክና ካልመሰልከው በቀር ባልንጀራህን፣ ወንድምህን፤ እኅትህን ከዛም አለፍ ሲል እናትህን አባትህን ከዚህም ሲከፋ የገዛ ሚስትህን ጤናማ በሆነ መውደድ ልትወዳቸው አትችልም፡፡ ስለዚህ ወዳጄ ይህን እርከን ተከትለህ ወደ እውነተኛው ወዳጅነት እለፍ፡፡ “በእምነት ላይ በጎነትን፤ በበጎነት ላይ እውቀትን፤ በእውቀት ላይ ራስን መግዛትን፤ ራስንም በመግዛት ላይ መጽናትን፤ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፤ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማች መዋደድ፤ በወንድማማች መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ” (2ጴጥ.1÷7) እንዲህ አድርጎ ራሱን በቅድስና ያበቃ ሰው ራሱን ከራስ ወዳድነት በጠራ መልኩ ይወዳል፡፡ ስለዚህም ባልጀራውንም መውደድ ለባልንጀራው መልካም ወዳጅ መሆን ይቻለዋል፡፡
Show all...
ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለሥጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አደከምካት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ። ልጄ ሆይ ..... በአዲስ ዓመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ። ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ሥጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ። ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አጽዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከዓለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ። ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ። ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ። ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት  እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ። ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ይህን ዘመን ከወትሮ በተለየ ወደ እግዚአብሔር ቀርበን በንስሐ አምላክን የምንማጸንበት ጥሩ እና መልካም ዘመን ያድርግልን🙏🙏🙏
Show all...
👍 3 2
"መንፈሳዊ ብቃት፥ የማይደረስበት እሩቅ፣ ወይም ከሰው ልጅ ችሎታ በላይ ነው፥ ብለን ማሰብ የለብንም። ሰዎች ባሕር አቋርጠው የሌላ ሀገር ፍልስፍና ሊማሩ ይሄዳሉ። የእግዚአብሔር ከተማ ግን በልባቸው ውስጥ ነው። እግዚአብሔር የሚጠብቅብን መልካም ምግባርም እዚያው ልባችን ላይ ነው ያለው። የሚጠበቅብን መሻታችንን ከእግዚአብሔር መሻት ጋር ማስማማት (አንድ ማድረግ) ብቻ ነው።" 🔥🔥🔥የአባ እንጦንስ ምክር...🔥🔥🔥
Show all...
2
"አቤቱ ሆይ ከሰማየ ሰማያት ወርደህ በማህፀኗ ማደርህን ድንግል ስትሆን ከእርሷ መወለድን ንጽህትም ስትሆን በጡቷ ማደግህን አስብ! አቤቱ ሆይ በጎል መጣልህን በጨርቅ መጠቅለልህን አስብ! አቤቱ ሆይ ይህንን ሁሉ አስበህ እኔን ባሪያህን ስለ ኃጢአቴ አትናቀኝ! በማዳንህ እርዳኝ በመድኃኒትነትህም ጋሻ ጋርደኝ፡፡ አቤቱ ሆይ ስለ ወለደችህ ማርያም አማላጅነት ስለ አሳደጉህ ጡቶቿ ስለ ሳሙህ ከንፈሮቿ ስላቀፉህ እጆቿ ስለ ተቀበለህ ጎልበቶቿ አካልም ይሆን ዘንድ ስለነሣኸው ነፍስና ሥጋዋ እርዳኝ ጠብቀኝ፡፡ አንጋጥቼ እንዳላፍር አምኜህ ተስፋ እንዳልቆርጥ አድረገኝ፡፡"          መፅሐፈ አርጋኖን
Show all...
1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.