cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ልዩ መረጃ

#ልዩ መረጃ #በዚህ ቻናል ለኢትዮጵያ ፍቅር ሰላም አንድነት ስለ ፍትህ የምናወራበት ድምፅ ላጡ ድምፅ የምንሆንበት ነው #መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ #ጥቆማ ለመስጠት 👇👇👇👇 @Liyumereja999bot

Show more
Advertising posts
15 828
Subscribers
+5224 hours
+1477 days
+5 56730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የ ኤርትራ ሠራዊት በ ትግራይ ክልል ጉሎምካዳ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጽመው አፈና ተባብሶ ቀጥሏል ተባለ‼️ የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ክልል ጉሎምካዳ ወረዳ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ አፈና መፈጸሙን አባብሶ ቀጥሏል ሲሉ የተጎጂ ቤተሰቦች አስታወቁ። "የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ባለመመለሱ ለአፈናና ለከፋ የጸጥታ ስጋት ተጋለጠናል” ሲሉ በወረዳዋ የሚገኙ የተለያዩ ቀበሌ ነዋሪዎች መናገራቸውን ከትግራይ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል። “የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ ባለመደረጉ፣ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ባለመመለሱ፣ በርካታ የክልሉ አከባቢዎች በወራሪዎች እጅ የሚገኝ መሆኑ ለአፈናና ለጸጥታ ስጋት ተጋልጠናል” ሲሉ በጉሎ መቅዳ ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ጣቢያ ነዋሪዎች ተናግረዋል ብሏል ዘገባው። ተጎጂዎቹ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እና የትግራይን ግዛታዊ አንድነት እንዲመልስ መጠየቃቸውንም ተገልጿል። “የኤርትራ ሠራዊት ተቆጣጥሯቸው ከሚገኙ የጉሎመካዳ ወረዳ ጣቢያዎች ውስጥ ነዋሪዎችን በየጊዜው እያፈና እየወሰደ ይገኛል” ሲሉ የጉሎ መቅዳ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነብዩ ስዩም መግለጻቸውንም ዘገባው አካቷል። Addis Standard ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ባለፈዉ ዓመት ህይወታቸዉ ባለፈዉ ቢሊየነሩ ሞሃመድ አል ፋይድ የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ተፈጽሞብናል ያሉ ሴቶች ቅሬታ አቀረቡ‼️ አምስት ሴቶች በለንደን የቅንጦት ምርቶች መሸጫ መደብር ውስጥ ሲሰሩ በቀድሞው የሃሮድስ አለቃ መሀመድ አል ፋይድ እንደተደፈሩ ተናግረዋል ።ባለፈው አመት በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ቢሊየነሩ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ ጾታዊ ጥቃት የፈጸሙባቸዉ ሴቶች ቁጥር ከ20 በላይ እንደሚደርስ የቀድሞ ሰራተኞች ምስክርነታቸውን ተሰምቷል። ከ 20 በላይ ጥቃት የደረሰባቸዉ ሴቶች ሁሉም የፋይድ የቀድሞ ሰራተኞች የነበሩ ሲሆን ወሲባዊ ጥቃት እና በደል እንዳይጋለጥ ተሸፋፍኖ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡የቅንጡ መደብሩ የአሁን ባለቤቶች በክሱ "በጣም መደናገጣቸዉን በመግለጽ" ተጎጂዎችን ይቅርታ ጠይቀዋል። እ.ኤ.አ. በ2010 ሃሮድስን የሸጠው ፋይይድ ባለፈው አመት በ94 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ዘ ጋርዲያን ላይ በሟች ህይወት ላይ በቀረበዉ መጽሃፍ በሴት ሰራተኞች ላይ የፆታዊ ትንኮሳ ተደጋጋሚ ክሶች እንደነበሩ ተናግሯል። ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
Show all...
👍 1
ፕሬዝዳንት ፑቲን 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ድሮን እንዲመረት አዘዙ ‼️ የሩሲያ ጦር ባሳለፍነው ዓመት 140 ሺህ አዲስ የተመረቱ ድሮኖችን ታጥቋል ተብሏል ፕሬዝዳንት ፑቲን በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ የሚገኝ የድሮን ማምረቻ ማዕከልን ጎብኝተዋል ፕሬዝዳንት ፑቲን 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ድሮን እንዲመረት አዘዙ፡፡ ለጥቂት ቀናት በሚል የተጀመረው የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ሶስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ እዚህ ደርሷል፡፡ ጦርነቱን በድል ለማጠናቀቅ ሁለቱም ሀገራት ቴክኖሎጂዎችን አብዝተው በመጠቀም ላይ ሲሆኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ደግሞ በትንሽ መስዋዕትነት ብዙ ድሎችን ያስገኛሉ፡፡ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ባለ የሰው አልባ አውሮፕላን አልያም የድሮን ማምረቻ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ሩሲያ የድሮን ምርቶችን ባለፈው ዓመት ከነበረው 10 እጥፍ እንዲጨምር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ተብሏል፡፡ እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የሩሲያ ጦር ባሳለፍነው ዓመት 140 ሺህ አዲስ ድሮኖችን የታጠቀ ሲሆን ህ ቁጥር በዚህ ዓመት ወደ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን እንዲያድግ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በጉብኝቱ ወቅት ሰው አልባ አውሮፕላኖች የጠላትን እንቅስቃሴ ለመለየት፣ ወታደራዊ መጋዝኖችን ለማውደም እና ከዩክሬን የሚነሱ ድሮኖችን ለማምከን ጥቅም ላይ ለማዋል ይረዳሉ ማለታቸውም ተገልጿል፡፡ ዩክሬን ድሮኖችን በመጠቀም በሩሲያ ግዛቶች ላይ ጥቃቶችን በማድረስ ላይ ስትሆን ወታደራዊ ማዕከላት፣ የነዳጅ ማጣሪያዎች እና ሌሎች ኢላማዎችን እየመታች መሆኗን አስታውቃለች፡፡ የአሜሪካ አየር ሀይል ከፍተኛ አመራር ከሰሞኑ የሩሲያ ጦር ከዩክሬን ጦርነት በፊት ከነበረው የበለጠ ጠንካራ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ዩክሬን ከሩሲያ የሚደርስባ የአየር ላይ ጥቃቶች ለማክሸፍ በሚል ከምዕራባዊን ሀገራት ኤፍ-16 የተሰኘው የውጊያ አውሮፕላን እንዲሰጣት ከጠየቀች በኋላ ሀገራት ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ አሁን ደግሞ ዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳኤል ድጋፍ እንዲደረግላት እና በሩሲያ ምድር ጥቃት ማድረስ እንድትችል ሀገራት ይሁንታ እንዲሰጧት እየጠየቀች ሲሆን የተወሰኑ ሀገራት ሲፈቅዱ የተወሰኑት ደግሞ በመቃወም ላይ ናቸው፡፡ ፕሬዝዳንት ፑቲን በበኩላቸው የኔቶ ሀገራት ዩክሬን በረጅም ሚሳኤሎች ሩሲያን እንድታጠቃ ከፈቀዱ የቀጥታ ጦርነት ከኔቶ ጋር ሊጀመር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
Show all...
👍 4
ፕሬዝዳንት ፑቲን 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ድሮን እንዲመረት አዘዙ ‼️ የሩሲያ ጦር ባሳለፍነው ዓመት 140 ሺህ አዲስ የተመረቱ ድሮኖችን ታጥቋል ተብሏል ፕሬዝዳንት ፑቲን በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ የሚገኝ የድሮን ማምረቻ ማዕከልን ጎብኝተዋል ፕሬዝዳንት ፑቲን 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ድሮን እንዲመረት አዘዙ፡፡ ለጥቂት ቀናት በሚል የተጀመረው የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ሶስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ እዚህ ደርሷል፡፡ ጦርነቱን በድል ለማጠናቀቅ ሁለቱም ሀገራት ቴክኖሎጂዎችን አብዝተው በመጠቀም ላይ ሲሆኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ደግሞ በትንሽ መስዋዕትነት ብዙ ድሎችን ያስገኛሉ፡፡ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ባለ የሰው አልባ አውሮፕላን አልያም የድሮን ማምረቻ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ሩሲያ የድሮን ምርቶችን ባለፈው ዓመት ከነበረው 10 እጥፍ እንዲጨምር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ተብሏል፡፡ እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የሩሲያ ጦር ባሳለፍነው ዓመት 140 ሺህ አዲስ ድሮኖችን የታጠቀ ሲሆን ህ ቁጥር በዚህ ዓመት ወደ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን እንዲያድግ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በጉብኝቱ ወቅት ሰው አልባ አውሮፕላኖች የጠላትን እንቅስቃሴ ለመለየት፣ ወታደራዊ መጋዝኖችን ለማውደም እና ከዩክሬን የሚነሱ ድሮኖችን ለማምከን ጥቅም ላይ ለማዋል ይረዳሉ ማለታቸውም ተገልጿል፡፡ ዩክሬን ድሮኖችን በመጠቀም በሩሲያ ግዛቶች ላይ ጥቃቶችን በማድረስ ላይ ስትሆን ወታደራዊ ማዕከላት፣ የነዳጅ ማጣሪያዎች እና ሌሎች ኢላማዎችን እየመታች መሆኗን አስታውቃለች፡፡ የአሜሪካ አየር ሀይል ከፍተኛ አመራር ከሰሞኑ የሩሲያ ጦር ከዩክሬን ጦርነት በፊት ከነበረው የበለጠ ጠንካራ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ዩክሬን ከሩሲያ የሚደርስባ የአየር ላይ ጥቃቶች ለማክሸፍ በሚል ከምዕራባዊን ሀገራት ኤፍ-16 የተሰኘው የውጊያ አውሮፕላን እንዲሰጣት ከጠየቀች በኋላ ሀገራት ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ አሁን ደግሞ ዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳኤል ድጋፍ እንዲደረግላት እና በሩሲያ ምድር ጥቃት ማድረስ እንድትችል ሀገራት ይሁንታ እንዲሰጧት እየጠየቀች ሲሆን የተወሰኑ ሀገራት ሲፈቅዱ የተወሰኑት ደግሞ በመቃወም ላይ ናቸው፡፡ ፕሬዝዳንት ፑቲን በበኩላቸው የኔቶ ሀገራት ዩክሬን በረጅም ሚሳኤሎች ሩሲያን እንድታጠቃ ከፈቀዱ የቀጥታ ጦርነት ከኔቶ ጋር ሊጀመር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
Show all...
ልዩ መረጃ

#ልዩ መረጃ #በዚህ ቻናል ለኢትዮጵያ ፍቅር ሰላም አንድነት ስለ ፍትህ የምናወራበት ድምፅ ላጡ ድምፅ የምንሆንበት ነው #መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ #ጥቆማ ለመስጠት 👇👇👇👇 @Liyumereja999bot

Photo unavailableShow in Telegram
አንዲት እናት አራት ህፃናት በሠላም ተገላገሉ ‼️ ዕድሜያቸው 42 ዓመት የሆኑት አንዲት እናት በፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል አራት ህፃናትን በሠላም ተገላግላለች። ወይዘሮ አደባባይ የሺነህ የሚባሉ ሲሆን  ነዋሪነታቸው በአዊ ብሔረሰብ ዞን ጃዊ ወረዳ አሊኩራንድ ቀበሌ ናቸው። በዛሬው ዕለት በፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል ሶስት ወንድና አንድ ሴት በድምሩ አራት ህፃናትን በሰላም ተገላግላለች፥ ጨቅላ ህፃናቱ በሰባት ወራት ጊዜያቸው ሳይደርስ የተወለዱ ስለሆነ በህፃናት ፅኑ ህሙማን ክፍል በዶ/ር አብዮት ጎበና እና ሳቀታ ማሩ የጨቅላ ህፃናት ጥብቅ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል ። በዚሁ ሆስፒታል መንታ መውለድና አልፎ አልፎም አንዲት እናት እስከ ሶስት ህፃናትን በአንድ ጊዜ መገላገል የተለመደ ሲሆን በዛሬው ዕለት የተከሰተው በአንድ ጊዜ አራት ህፃናትን መገላገል ግን በሆስፒታሉ አዲስ ክስተት መሆኑ  ሚድዋይፍ ባለሙያ ሞገስ ጌታቸው ተናግረዋል። ወላጅ እናት የአሁኑን ጨምሮ ለስድስተኛ ጊዜ የወለዱ ሲሆን በአሁኑ ስዓት በሙሉ ጤንነት እንደሚገኙ ገልፀው በሰላም እንድትገላገል ለረዷቸው  ለሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎችና የፓዊ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ላደረጉላቸው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያመላክታል። ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
አዲሱን የአማራ ትውልድ/ወርቃማውን ትውልድ የሚመጥን ሚዲያ  ጎልደን ዐማራ ይሰኛል ጥራት ፍጥነትን አሟልቶ መጥቷል ይቀላቀሉን አንበሳዬ ጎልደን ዐማራ👇👇👇 https://t.me/GoldenAmhara
Show all...
💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
ልዩ የቴሌግራም ቻናል ጥቆማ‼️👇 መረጃ ለማድረስ እንዲሁም ለመከታተል ቴሌግራም ተመራጭ እየሆነ ነው‼️ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ያልተሰሙ እና አዳዲስ መረጃዎችን ለመከታተል ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው join በማድረግ ተከታተሉ። ብዙ አዳዲስ መረጃዎችን ታገኛላችሁ እንዲሁም በቻናሉ ማስታወቂያ ብታሰሩ እጅግ አዋጪ ነው። ቻናሉን ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ👇👇👇👇👇 https://t.me/fannomedia27 https://t.me/fannomedia27 https://t.me/fannomedia27
Show all...
ሊባኖስ ፔጀርስን፣ ዎኪ-ቶኪዎችን በሁሉም በረራዎች ላይ ጥቅም ላይ እንዳይዉሉ አገደች‼️ የሊባኖስ የሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ተሳፋሪዎች በማንኛውም አውሮፕላን ላይ ፔጀር እና ዎኪ ቶኪዎችን ይዘዉ እንዳይሳፈሩ የሚያግድ አዲስ መመሪያ ማውጣቱን የመንግስት የዜና ወኪል ኤን ኤን ዘግቧል።እገዳው በቤሩት ራፊክ ሃሪሪ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚያልፉ ጭነት ፣የሚፈተሹ እና በእጅ ሻንጣዎች ላይ የሚተገበር ሲሆን የአየር ማረፊያው ጥበቃ እነዚህን መሳሪያዎችን ይዞ የተገኘ ማንኛውንም መንገደኛ ይወርሳል። አዲሱ ህግ ወዲያውኑ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን የማሻሻያ ማስታወቂያ እስኪወጣድረስ ተግባራዊ ይሆናል።ፔጀር የሬዲዮ ዌቭ የሚጠቀም የመገናኛ ዘዴ ነው። ሰዎች መረጃ ሲልኩ የሚተላለፈውም የሬዲዮ ፍሪክዌንሲ በመጠቀም ነው። መልዕክት የተላከለት ሰው መልዕክቱ እንደደረሰው በንዝረት መልዕክት መስጠት የሚችል ሲሆን አጭር የጽሑፍ ወይም የድምፅ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ይችላል።እ.አ.አ 1980ዎቹ እንዲሁም 90ዎቹ በስፋት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ የግንኙነት መሳሪያ አሁን ላይ በሞባይል ስልክ ቢተካም አሁንም ድረስ በተለያዩ ቦታዎች ጥቅም ላይ ይውላል። በሌላ መረጃ ቱርክ እስራኤል በጋዛ ያለውን ጦርነት ወደ ሊባኖስ ለማስፋት እየፈለገች ነው ስትል ከሳለች።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን በመንግስት የሚተዳደረው ቲአርቲ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበዉ በሰጡት መግለጫ "በአካባቢው ያለው ዉጥረት መባባስ አሳሳቢ ነው" ብለዋል። እስራኤል ጥቃቷን በደረጃ ወደ ሊባኖስ ስትወስድ እናያለን ሲሉ አክለዋል።እስራኤል በፍንዳታው ዙሪያ የተናገረችው መረጃ ባይኖርም ቱርክ ሀገሪቱን ተጠያቂ አድርጋለች። በእስራኤል የተከናወኑ ጸብ ቀስቃሽ ተግባራት በአጸፋ ምላሹም ኢራን፣ ሂዝቦላህ እና ለእነሱ ቅርብ የሆኑ አካላት ዝምታን አይመርጡም ሲሉ ፊዳን ተናግረዋል። ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
Show all...
👍 3
የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በደቡብ ጎንደር ዞን ከሚገኙ ከአምስት ወረዳዎች ለቀው ወጡ‼️ በደቡብ ጎንደር ዞን በሚገኙ ከአምስት ወረዳዎች ከ2016 ዓ.ም ማብቂያ ጀምሮ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ለቀው መውጣታቸውን ዋዜማ ዘግባለች።   የፌደራል እና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች እስቴ መካነ ኢየሱስ፣ አንዳቤት፣ ሙጃ፣ ስማዳ እና ታች ጋይንት ከሚባሉ ወረዳዎች ከነሐሴ ዕኩሌታ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ መጨረሻ ባሉት ጊዜያት ሙሉ በሙሉ ለቀው መውጣታቸውን ዋዜማ ተገንዝባለች።  የመንግስት ኀይሎች ለምን ከአካባቢው እንደወጡ በይፋ አልተናገሩም። በወረዳዎቹ የነበሩ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ሙሉ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር ወደ ዞኑ መቀመጫ ደብረታቦር ገብተዋል። ይህን ተከትሎም በወረዳዎች ኹሉም ዓይነት የመንግሥት አገልግሎቶች የተቋረጡ ሲሆን፣ በፖሊስ እና በሚሊሻ የሚሰጡ አገልግሎቶችም በተመሳሳይ ቆመዋል።  በአንጻሩ በእነዚህ ወረዳዎች ባንኮች እና የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ነው ተብሏል። ትምህርት ቤቶች እስካሁን ምዝገባ አላከናወኑም።  የአማራ ክልል መንግስት የኮምኒኬሽን ቢሮ ስለጉዳዩ ላቀረብንለት ጥያቄ ጉዳዩን መመለስ የሚችለው የኮማንድ ፖስቱ ነው ከማለት ውጪ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀደም። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከወረዳዎቹ ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ በቦታው የተተኩት የፋኖ ታጣቂዎች የራሳቸውን የአስተዳደር መዋቅር ለመዘርጋት ጥረት እያደረጉ ነው። በአንጻሩ የዞኑ ዋና መቀመጫ ደብረታቦር እንዲሁም ንፋስ መውጫ፣ ፎገራ እና ደራ ወረዳዎች ዋና ከተሞቻቸው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ስር ይገኛሉ። ሆኖም በዞኑ ዋና ከተማ ደብረታቦር ዙሪያ ታጣቂዎች በብዛት እንደሚገኙ ሰምተናል።  በሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደር እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖችም ሰሞኑን በኹለቱ ኃይሎም መካከል ከፍተኛ ውጊያ ሲካሄድ ቆቷል።  ሰሞኑን በመንግስት ወታደሮች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የዞን አስተዳደር መቀመጫ በሆኑት በጎንደር እና በደባርቅ ከተሞች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ ሲካሄድ ሰንብቷል። ይህን ተከትሎም በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ተገንዝበናል። በክልሉ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ግጭት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ለሞትና ለአካል ጉድት መዳረጋቸውን ብሎም ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት የሚያወጧቸው ሪፖርቶች ያሳያሉ።   Via ዋዜማ ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
Show all...
👍 5 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.