cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ናታኔም ❤❤ ታናሽ አገልጋይ

◈◆◈◆◈◆◈◆◈◈◆◈◆◈◆◈◆◈◈◆◈◆◈◆◈◆◈ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ሰላም👐 የተዋህዶ ልጆች እንክዋን ወደ ናታኔም ቻናል በሰላም መጡ ይህ ቻናል ከሌሎች ቻናሎች ለየት የሚያደርገው ነገር ትኩረት አድርጎ የሚሰራው በገጠር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ቅርፆቻቸው እና ታሪኮቻቸው እንዳይጠፉና እንዳይበላሽ በማገዝና ገቢ በማሰባሰብ የበኩሉን በአቅሙ ያደርጋል።

Show more
Advertising posts
617
Subscribers
+724 hours
+537 days
+11530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ㅤ                                  ┊ ┊ ┊ ┊                                  ┊ ┊ ┊ ✟                                  ┊ ┊ ✞                                  ┊ ✟                                  ✞ ┏━━━°❀•°:🎀°•❀°━━━━┓     # መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር ┗━━━°❀•°:🎀°•❀°━━━━┛ መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር (፪) ይቀሰቅሰኛል ለስሙ እንድዘምር (፪)                    ፊቱን እያጣፉት እየተንገላታ በጦር እየወጉት ይሰጣል ይቅርታ     እነርሱ እየጠሉት እርሱ ይወዳቸዋል አስረው ሲጎትቱት ይከተላቸዋል          ፃድቁን ኃጥዕ ነው እውነቱን ሐሰት እያሉ ሲጮሁ ይሰቀል ይሙት እየመረመረው ፍጡር ፈጣሪን ክርስቶስን አስሮ ፈታው በርባንን           ጀርባውን ሲገርፉት በሚያቃጥል ጅራፍ በምህረት ያዛቸው በይቅርታው እቅፍ ጨክነው ሲያጠጡት መራራ ሐሞት ደም ውሃ ፈሰሰ ጎኑን ሲወጉት         ግምጃን አለበሱት ቀሚሱን ገፈው በራሱም አኖሩ እሾህ ጎንጉነው የአይሁድ ንጉስ ሆይ እያሉ ዘበቱ ለህይወት ሆናቸው የኢየሱስ ሞቱ             መዝሙር    ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ    ㅤ        ╔══ ❀•°❀°•❀ ═══╗    @orthodoxtewhdobetekrstyan                    💚💛❤️    @orthodoxtewhdobetekrstyan        ╚══ ❀•°❀°•❀═══╝
Show all...
edited_output.mp37.43 MB
በአንዲትም ዕለት ሆሎፎርኒስ የአሽከሮች የምሣ ግብዣ አድርጎ ሲያበላ ሲያጠጣ ያችን ዕብራዊት ጥሩ ብሎ አስጠርቶ ከፊቱ አስቀምጦ ሲበላ አብዝቶ ሲጠጣ ውሎ ሰከረ፡፡(ዮዲ12፥1-20) ከዚያም አሽከሮችን ከሁሉ አስወጥቶ ድንኳኑን ቆልፎ እንደተኛ ከባድ እንቅልፍ ያዘው ዮዲትም ከፀለየች በኋላ ከራስጌው ያለውን ሰይፍ አንስታ የራስ ጠጉሩን ይዛ አንገቱን ቆርጣ በድኑን ከመሬት ጥላ ቸብቸቦውን በአቁማዳ ቋጥራ ለብላቴናዋ አሸክማ ግንዱን በታች ገልብጣ ዙፋኑን በላይ አድርጋ ወደ ሃገሯ ተመለሰች፡፡ (ዮዲ13፥1-10) ሕዝበ እሥራኤል በዚህ ድርጊቷ እጅግ ተደነቁ፣ ጠላታቸውን በእጃቸው የጣለላቸውን አግዚአብሔር አምላካቸውንም አመሰገኑ፡፡ በኋላም የሆሎፎርኒስን ራስ በተራራው ላይ ሰቅለው መዋጋት ጀመሩ፡፡ እስከ ዮርዳኖስም እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም የዚህችን ቅድስት እናት በዓለ እረፍቷን በዚህች ዕለት አክብራ ትውላለች ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_መጥሮንያ በዚችም ቀን የከበረች መጥሮንያ በሰማዕትነት አረፈች። ይቺም የከበረች መጥሮንያ ለአንዲት አይሁዳዊት ሴት አገልጋይዋ ናት ። ይችም አይሁዳዊት እመቤቷ ከክርስትናዋ አፍልሳ ትክክል ወደ አልሆነ ሃይማኖቷ ልታስገባት ትሻ ነበር ስለዚህም ታጉሳቁላታለች በላይዋም የአገልግሎት ሥራንበታከብድባታለች ። ከዚህም በኃላ በአንዲት ቀን አይሁዳዊት እመቤቷን ተከትላ ወደ አይሁድ ምኩራብ ሔደች ተመልሳም ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ገብታ ጸለየች። ወደ ቤት በገቡም ጊዜ ወዴት ሒደሽ ነበር ወደእኛ ምኩራብ ለምን አልገባሽም ብላ ጠየቀቻት ቅድስት መጥሮንያም ከእናንተ ምኩራብ እግዚአብሔር ርቋል እኮን እንዴት ወደርሱ እገባለሁ። በውስጧ ልገባባት የሚገባኝ ቦታዬ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በከበረ ደሙ የዋጃት ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት ብላ መለሰችላት። እመቤቷም ይህ ነገር በሰማች ጊዜ ተቆጣቻት እጅግም ደብደባ በጨለማ ቤት ውስጥ አሠረቻት ያለ መብልና መጠጥም አራት ቀን ኖረች። ከዚህም በኃላ ከእሥር ቤት አውጥታ በጅራፍ ታላቅ ግርፋትን ገርፋ ሁለተኛ ወደ እሥር ቤት መልሳ አሠረቻት በዚያም አረፈች። እመቤቷም በድኗን አንሥታ ከቤቷ ደርብ ላይ አውጥታ በውጭ ወደታች ጣለቻት። ወድቃ የሚያዩዋት ሰዎች በገዛ ፈቃድዋ እንደወደቀች አድርገው እንዲናገሩ ብላ ነው ስለ መገደሏ ዳኞች እንዳይመራመርዋት ፈርታለች። በዚያንም ጊዜ በዚያች አይሁዳዊት ሴት ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ወረደ ከደርቧ ላይ ስትወርድም በድንገት ወድቃ ሞተች ወደ ዘላለማዊም እሳት ሔደች ይህች የከበረች መጥሮንያ ግን የሰማዕታትን አክሊል ተቀብላ ወደ ዘላለም ሕይወት ሔደች። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ንግሥተ_ሳባ ይሕቺ ደግ ኢትዮዽያዊት ከ3 ሺ ዘመናት በፊት የነበረች ደግ እናት ናት። በሥጋዊ ደረጃ ከታንዛንያ እስከ የመን ያስተዳደረች ስመ ጥር ንግሥት ስትሆን በመንፈሳዊው ደረጃ ደግሞ እግዚአብሔር የቀባውን ሰው ፍለጋ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛለች። ከዚያውም አምልኮተ እግዚአብሔርን ከሥርዓተ ኦሪት ጋር አምጥታለች። ድንግልናዋን ለታላቁ ንጉሥ ሰሎሞን ሰጥታ ምኒልክን ወልዳለች። ይህቺ ንግሥት በጌታችን (በፈጣሪ) አንደበትም ተመስግናለች። (ማቴ. 12:42) በስምም "ሳባ: አዜብና ማክዳ ተብላ ትታወቃለች። ዛሬ ዕለተ ዕረፍቷ ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ተቀጸል_ጽጌ /#አጼ_መስቀል/ 'ተቀጸል ጽጌ' ማለት 'መስቀል ሆይ! በአበባ አጊጥ' እንደ ማለት ሲሆን 'አጼ መስቀል' ደግሞ አጼ ገብረ መስቀልን አንድም አፄ ዳዊት ቀዳማዊን ይመለከታል። ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ በሃገራችን ኢትዮዽያ የነገረ መስቀሉ ትምሕርት ከመጣ ጀምሮ መስቀል ይከበራል። በአደበባባይ ግን እንዲከበር ያደረጉት የቅዱስ ካሌብ ልጅ አፄ ገብረ መስቀል ናቸው። በወቅቱ ንጉሡ፣ ሠራዊቱ፣ ዻዻሱና ሕዝቡ በተገኙበት ቅዱስ ያሬድ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር ያድኅነነ እምጸር።" "መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው: ከጠላትም ያድነናል።" እያለ ይዘምር ነበር። የአበባ ጉንጉንም ለመስቀሉና ለንጉሡ ይቀርብ ነበር። ከ800 ዓመታት በሁዋላም አፄ ዳዊት ግማደ መስቀሉን ባስመጡ ጊዜ መስከረም ቀን ተተክሎ ታላቅ በዓልም ሆኖ ተከብሯል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ㅤ      ➠ For any suggestions or questions👇                        『 usernamishn 』                  ╔════ ❀•°❀°•❀ ════╗              @orthodoxtewhdobetekrstyan                                  💚💛❤️.........................5             @orthodoxtewhdobetekrstyan                  ╚════ ❀•°❀°•❀ ════╝                           💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟
Show all...
ㅤ💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟                                                      ┊ ┊ ┊ ┊ ┊                                                      ┊ ┊ ✫ ˚♡                                                      ┊ ☦⋆ ┊。                                                      ⊹   ⋆ ❀                                                      ┊ . ˚                                                      ✞ ㅤ ㅤ         ┏━━━━━°❀•°:🎀:°•❀°━━━━━┓                      #የእለቱ ስንክሳር መስከረም 10...............1                               ┗━━━━━°❀•°:🎀:°•❀°━━━━━┛ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥር በዚች ቀን #ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር ተገለጠ፣ የሜራሪ ልጅ #ቅድስት_ዮዲት እረፍቷ ነው፣ የከበረች #ቅድስት_መጥሮንያ በሰማዕትነት አረፈች፣ #ንግስት_ሳባ እረፍቷ፣ #ተቀጸል_ጽጌ #አጼ_መስቀል ይከበራል። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ጼዴንያ መስከረም ዐሥር በዚህች ቀን ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር ተገለጠ። ይቺንም ሥዕል የሣላት ወንጌላዊ ሉቃስ ነው ይባላል። ወደ ጼዴንያ አገርም የመጣችበት ምክንያት አንዲት ስሟ ማርታ የሚባል መበለት ሴት ነበረችና ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች ናት። አምላክን የወለደች እምቤታችን ድንግል ማርያምንም እጅግ ትወዳት ነበር። በሚቻላትም ሁሉ ታገለግላታለች። በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኩሴ ከእርሷ ዘንድ እንግድነት አደረ በመልካም አቀባበልም ተቀበለችው በማግሥቱም ስተሸኘው አባት ሆይ የምትሔደው ወዴት ነው አለችው። እርሱም በከበሩ ቦታዎች ውስጥ ልሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም እሔዳለሁ አላት እርሷም ከእኔ ገንዘብ ወስደህ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ግዛልኝና በመመለሻህ ጊዜ አምጣልኝ አለችው። እርሱም በራሴ ገንዘብ ገዝቼ አመጣልሻለሁ አላት። ከዚህም በኋላ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከቅዱሳት መካናት ተባረከና ሥዕሏን ሳይገዛ ወደ ጎዳናው ተመለሰ። ያን ጊዜም ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰማ ወደ ገቢያም ተመልሶ ላሕይዋና መልኳ ያማረና የተወደደ የሆነ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል አግኝቶ ገዛት በሐርና በንጹሕ ልብስም ጠቀለላት። በጎዳናውም እየተጓዘ ሳለ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወንበዴዎች ተነሡበት ሊሸሽም ወደደ ከዚያቺም ሥዕል መንገድህን ሒድ የሚል ቃል ወጣ የተከተለውም ሳይኖር መንገዱን ተጓዘ። ሁለተኛም ነጥቆ ሊበላው አንበሳ ተነሣበት ያን ጊዜም ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረው። አባ ቴዎድሮስም ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምር ባየ ጊዜ ያቺን ሥዕል ወደ አገሩ ሊወስዳት ወደደ ግዛልኝ ላለችው መበለት ይሰጣት ዘንድ አልፈለገም። ከዚህም በኃላ በመርከብ ተሳፍሮ በሌላ አቅጣጫ ሲጓዝ ታላቅ ነፋስ ተነሣበት ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያም ወሰደው ከመርከቡም ወርዶ ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ሔደ ማንነቱንም አልገለጠላትም እርሷም አላወቀችውም። በማግሥቱም ተሠውሮ ወጥቶ ወደ አገሩ ሊሔድ በፈለገ ጊዜ የቅጽሩን ደጃፍ አጥቶ ሲያጥመሰምስ ዋለ በመሸ ጊዜም ወደ ማደሪያው ተመለሰ። ያቺም መበለት በአየችው ጊዜ ታደንቃለች እንዲህም ሁኖ እስከ ሦስት ቀን ኖረ በመሸ ጊዜ በሩን ያየዋል ነግቶ መሔድን ሲሻ የበሩ መንገድ ይሠወረዋል። ያቺም መበለት ያዝ አድርጋ አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን ስትቅበዘበዝ አይሀለሁና ምን ሆነህ ነው አለችው። ከዚህም በኋላ ከዚያች ሥዕል የሆነውን ሁሉ ነገራት ራሱንም ገለጠላት። ያቺንም ሥዕል ሰጣት ተቀብላም የተጠቀለለችበትን ልብስ ፈታች ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች። ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የዚያን መነኩሴ እጆቹንና እግሮቹን ሳመች። ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር የምትቀመጥበትን አዘጋጅታ አኖረቻት ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት በቀንና በሌሊትም የሚበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች ከመቅረዞችም ውጭ የሐር መጋረጃን ጋረደች። ከሥዕሊቱ በታችም ከሥዕሊቱ እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች ያም መነኩስ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችንን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ። የሀገሩም ሊቀ ጳጳሳት የዚያችን ሥዕል ዜና በሰማ ጊዜ ከኤጲስቆጶሳትና ከካህናት ከሕዝቡም ሁሉ ጋር መጣ በሠሌዳውም ውስጥ በአዩዋት ጊዜ ሥጋ የለበሰች ሁና አገኙዋት ከዚህ ከአምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ ከዚህም ቅባት ቀድተው ለበረከት በተካፈሉ ጊዜ ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ ይመላል። ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜ ንውጽውጽታ ሆኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ በዚያች አገር ትኖራለች። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_ዮዲት ዳግመኛም በዚህች ቀን ባሏ ምናሴ ሞቶባት፣ ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም፣ በቀኖና፣ በትኅርምት፣ በኀዘን፣ በጸሎት ተወስና የምትኖር የሜራሪ ልጅ ቅድስት ዮዲት አረፈች። ቅድስት ዮዲት ከከሀዲው ሆሎፎርኒስ እጅ በጥበቧ እስራኤልን ያዳነቻቸው ጥበበኛ የከበረች፣ በእግዚአብሔር ኃይል ራሱን እስከ ቆረጠች ድረስ በልቧ ተራቀቀች ወገኖቿንም ያዳነች ናት። ነገሩም እንዲህ ነው፦ ለፋርስ ንጉሥ ለናቡከደነፆር የጦር አበጋዝ የነበረው ሆሎፎርኒስ ፈቃድ ተሰጥቶት እስራኤልን ለመውረር ሲመጣ በሠራዊቱ (ዮዲ2፣2-7) የእሥራኤል ልጆችም ሆሎፎርኒስ የአሕዛብን አገር እንዳጠፋና ንብረታቸውን እንደዘረፈ ሰምተው ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስና ሰለ ንዋያተ ቅድሳት መርከሰ ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው ከቤተ መቅደሱ በር ወድቀው አለቀሱ።(ዮዲ4፡2-15) ሆሎፎርኒስ ግን የሚጠጡትን ምንጫቸውን በመያዙ ፣ የእሥራኤል ልጆች በውኃ ጥም ከመቸገርና ከመሞት ይልቅ እጃቸውን ለጠላት ለመስጠት ወሰኑ፡፡ ነገር ግን ዖዝያን የአባቶቻቸው አምላክ መልስ እስኪሰጣቸውና ቸርነቱን እስኪመልስላቸው መከራውን በትዕግሥት እንዲቀበሉ ስለመከራቸው ጸኑ፡፡ ዮዲ 7፥10-32) በዚህ ጊዜ ዮዲት ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትቢያ ነስንሳ፣ ሱባዔ ገባች! አምላክም ሕዝቡን የሚያድንበትን ዕውቀትና ጥበብ ግብር በገባች በሦስተኛ ቀን ገለጸላት፡፡(ዮዲ8፡2) ከዚያም “ወዴት ትሔጃለሽ አትበሉኝ አምላክ እሥራኤል ይከተልሽ ብሉኝ” ብላ የኀዘን ልብሷን ጣለች፡፡ ሰውነቷን ታጠበችና ሽቱ ተቀባች ባሏ በሕይወት ሳለ የምትለብሰውን የክት ልብሷን ለበሰች፣ የጠላት ሰዎች ሁሉ እስኪወዷት ድረስ ፈጽማ አጊጣ ሄደች፡፡ (ዮዲ.10፥2-3) እነርሱም ለእኔ ትገባለች ለእኔ ትገባለች እያሉ ተሻሙባት፡፡ የንጉሥ ጃንደረባ ጋይ የሚባል ይህችስ ለጌታዬ ትገባለች አለ፣ ለምን እንደመጣች ጠይቀዋት ለመልካም ነገር እንደመጣች ሲረዱ ከጦር አበጋዙ አደረሷት፡፡ (ዮዲ10፥12-22)
Show all...
ㅤ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ✟ ┊ ┊ ✞ ┊ ✟ ✞ ┏━━━°❀•°:🎀:°•❀°━━━━┓ #_ነይ ነይ  ማርያም ነይ ነይ (2) ┗━━━°❀•°:🎀:°•❀°━━━━┛ ነይ ነይ  ማርያም ነይ ነይ (2)        ድንግል ሆይ ነይ ነይ ያን የእሳት ባህር ከቶ እንዳላይ(2)              አዝ በሀመረ ኖህ የተመሰልሽው፣ በአሮን በትር የተመሰልሽው፣ የምስራቋ በር(2) ቶሎ ድረሽ።               አዝ በተራራው በኤፍሬም ሀገር፣ እንግዳ የሆንሽ ለኤልሳቤት በክብር፣ ነይልኝ ወደኔ(2)  ከአንቺ ጋር ልኑር።                  አዝ አለም ከብዳብኝ ተጨንቄአለሁ፣ ሀዘን በዝቶብኝ ብቸኛ ሆኛለሁ፣ ኧረ ነይ ድንግል ሆይ (2)እጠራሻለሁ።                     አዝ ጥበቡ አንች ነሽ ለሲሎንጢስ፣ ነይ ብሎ ሚጠራሽ ሱላማጢ፣ አትርሽኝ ድንግል ሆይ (2)በእጅሽ ልዳሰስ።                      አዝ ምስጢር የገለጽሽ ለህርያቆስ፣ ፈጥነሽ ይማለድሽ ለቤተ ዶኪማስ፣ ነይልኝ እናቴ(2) ልቤ ይፈወስ።                       አዝ ድንግል ቀርባለች ጩኸቴን ስሞታ፣ የሀጢአቴ ገመድ እስሩ ተፈታ፣ አከብራታለሁ(2) ልጇ በእልልታ። ╔══ ❀•°❀°•❀ ═══╗ @orthodoxtewhdobetekrstyan 💚💛❤️........................3 @orthodoxtewhdobetekrstyan ╚══ ❀•°❀°•❀═══╝
Show all...
@orthodoxtewhdobetekrstyan.m4a10.18 KB
ㅤ                                  ┊ ┊ ┊ ┊                                  ┊ ┊ ┊ ✟                                  ┊ ┊ ✞                                  ┊ ✟                                  ✞ ┏━━━°❀•°:🎀°•❀°━━━━┓        # እሰይ አበራ ┗━━━°❀•°:🎀°•❀°━━━━┛ እሰይ አበራ መስቀሉ ለአለም ሁሉ ይለኮስ ችቦ ደመራው ጨለማው ይብራ አ.ዝ………… የጥል ግድግዳ ፈረሰ እሰይ አበራ ዳግም እንባችን ታበሰ ›› ›› ሕይወት ነው ለኛ መስቀሉ›› ›› ታምነናልና በቃሉ ›› ›› አ.ዝ…………….. አይሁድ በክፋት ቢነሱ ›› ›› የሀሰት ካባ ቢለብሱ ›› ›› እሌኒ ሄደች ገስግሳ ›› ›› ቆስጠንጢኖስን አንግሳ ›› ›› አ.ዝ………………… ዛሬምሀይል አለው መስ እሰይአበራ አንድ አልፎበታል ለሁሉ ›› ›› አንሸሽገውም ከእውነት ›› ›› መውጊያውን ስለወጋበት ›› ›› አ.ዝ……….. የመስቀሉቃል ላመነው እሰይአበራ ከሞት ማምለጫ ስንቅ ነው ›››› ለአለም ቢመስልም ሞኝነት ››› ተከፍሎበታል ስርየት ›› ››     ╔══ ❀•°❀°•❀ ═══╗    @orthodoxtewhdobetekrstyan                    💚💛❤️    @orthodoxtewhdobetekrstyan        ╚══ ❀•°❀°•❀═══╝
Show all...
Meskel abeba መስቀል አበባ.mp33.02 MB
ድንግል_ማርያም_ብዬ_ሊቀ_መዘምራን_ኪነጥበብ_@DNZEMA_ዜማ_ቅዱስ_ያሬድ.mp32.55 MB
ㅤ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ✟ ┊ ┊ ✞ ┊ ✟ ✞ ┏━━━°❀•°:🎀:°•❀°━━━━┓ #በቤተ_መቅደስህ ┗━━━°❀•°:🎀:°•❀°━━━━┛ በቤተ መቅደስህ ያሳደከኝ፤ ለአፌ ጥበብን ያስተማርከኝ፤ የልጅነቴ አምላክ ወዴት አለህ፤ በዚ አለም ሀሳብ ክንዴ ዛለ፤ አዝ======= ያሸዋ ላይ ህንፃ ሆኗል ቤቴ፤ ያረገርጋል መሰረቴ፤ ጠላት ሰልጥኖብኝ ደክምያለሁ፤ ዛሬ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ አዝ======== አባካኝ ሆኛለሁ አመፀኛ፤ ለዚ አለም ሀጢያት የማልተኛ፤ ነፍሴ ተንገላታች በመከራ፤ ማን ያገናኛት ካንተ ጋራ፤ አዝ======== ሰላሜ ነህ አንተ ትዝታዬ፤ ፅፌ ያኖርኩህ በእንባዬ፤ አለም ወስዳኛለች በዘፈኗ፤ እባክህ ስራኝ እንደገና፤ አዝ======== አመፀኞች ሁሉ ቤትህ ገቡ፤ ምህረት ፍቅርህን እያሰቡ፤ እጅህን ዘርግተህ አቀፍካቸው፤ ባንተ ቀለጠ ልቦናቸው! ╔══ ❀•°❀°•❀ ═══╗ @orthodoxtewhdobetekrstyan 💚💛❤️........................3 @orthodoxtewhdobetekrstyan ╚══ ❀•°❀°•❀═══╝
Show all...
በቤተ_መቅደስህ.....mp34.03 MB
ጋሜል- ዘ ኦርቶዶክስ - ባርክ ለነ.mp32.63 MB
👍 1
ㅤ💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟💠⃟ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ┊ ✫ ˚♡ ┊ ☦⋆ ┊。 ⊹ ⋆ ❀ ┊ . ˚ ✞ ┏━━━°❀•°:🎀:°•❀°━━━━┓ #ምስባክ_9 ┗━━━°❀•°:🎀:°•❀°━━━━┛ ⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘ ⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘ ምስባክ አመ ፱ ለመስከረም         ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥   ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧       ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ ⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘⚘ ➠For any suggestions or questions 👇 『 @mytglink2721 』 ╔══ ❀•°❀°•❀ ═══╗ @orthodoxtewhdobetekrstyan 💚💛❤️ ╚══ ❀•°❀°•❀═══╝
Show all...
ምስባክ_መስከረም_፱_ዘነግህ_ዘወቀትርቅዳሴ_ወዘሠርክMP3_128K_1_1.mp36.39 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.