cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dire Dawa government communication affairs office

government organization

Show more
Advertising posts
1 436
Subscribers
+324 hours
+157 days
+6930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ዜና በድሬዳዋ አስተዳደር በመስኖ ልማት የተሰሩ ስራዎች አበረታችና የአርሶ አደሩን ህይወት የቀየሩ መሆናቸው ተገለጸ በዛሬው ዕለት ከኢጋድ፣ ከወርልድ ባንክና ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ግብርና ሚኒስተር የተውጣጣው ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ገጠር ቀበሌዎች በምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም /በኤፍ ኤስ አር ፒ / የተሰሩ ስራዎችን ከአስተዳደሩ አመራሮችንና ከሚመለታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱም በሁሉ ሞጆ፣ በዱጁማ በኢጃናኒና በገንደ ሬጌ ገጠር ቀበሌዎች በመስኖ ልማትና በወንዝ ጠለፋ፣ በመስኖ ካናል ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ እርሻዎችንና የዶሮ እርባታ ስራችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ያነጋገርናቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማእድን ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የኃላፊ ተወካይ አቶ መሀመድ አሚን በአስተዳደሩ በመስኖ ልማት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው፤ አርሶ አደሩም በተለምዶ ከሚያለማው ከማሽላና ከበቆሎ ወደ አትክልትና ፍራፍሬ በመግባት አበረታች ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናገረዋል፡፡ የምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም /ኤፍ ኤስ አር ፒ /ፕሮጀክት የድሬዳዋ ማናጀር አቶ ስሻው አያሌው በበኩላቸው ቡድኑ ወደ ድሬዳዋ በመምጣት ስራዎችን ተዘዋውሮ በመጎብኘቱ አመስግነው፤ በጉብኝቱም በፕሮጀክቱ በተሰሩ ስራዎች አርሶ አደሩ በተጨባጭ እየተጠቀመ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀዋል፡፡፡ በድሬዳዋ በተለይም በመስኖ ልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ወንዝን ጠልፎ በማልበማትና በዶሮ እርባታው ዘርፍ አበረታችና ይበል የሚያስበሉ ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹት ደግሞ በጉብኝቱ ወቅት ያነጋገርናቸው የልኡክ ቡድኑ አባላት ናቸው፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ አያይዘውም ድሬዳዋ ላይ ስራዎች በህብረተሰብ ተሳትፎ በርብርብና በቅንጀት በመሰራቱ የአርሶ አደሩ ህይወት እንደተቀየረና ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ ነው ሲሉ ተናገረዋል፡፡ በኤደን ሳሙኤል ፎቶ፤- ቴድሮስ ልኡልሰገድ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.diredawacommunication.org ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DDGCAB ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCQNCC5tcc6Jd9zCKcmzQ-eA ቴሌግራም፦ https://t.me/DDGCAB ትዊተር፦ https://twitter.com/DawaOffice በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...

👍 2
👍 2
#Oduu "Barri haaraan dhufu Magaalaa teenya Ismaarti Sitii gochuuf hojjanna'' Kabajamoon Kantiibaa Bulchiinsa Dirree Dhawaa Obbo Kadiir Juhaar #DGC Qaammee 5/2016 Qaammeen 5, Guyyaan egeree "Tattaaffiin har'aa Bu'aa hegereef" dhaadannoo jedhuun kurfii gara garaan kabajame. Bulchiinsa Dirree Dhawaatti kurfii kabaja Guyyaa Qaammee 5, Guyyaa hegeree faaruu Biyyaalessa Itoophiyaan kan jalqabame yoo ta'u Eebbi Abbootii Amantaa, Abbootii Gadaa fi Ugaazotni taasisaniin erga ittifufeen booda Saganticha irratti ergaa fi haasaa Baniinsaa kan taasisan Kantiibaan Bulchiinsa Dirree Dhawaa Obbo Kadiir Juhaar akka ibsanitti Barri haaraan 2017 bara Magaalaa teenya Ismaarti Sitii gochuuf xiyyeeffannoo addaan bara itti hijjannuu jedhan. Dabalataanis Kabajamoon Kantiibaa Bulchiinsa Dirree Dhawaa Obbo Kadiir Juhaar jiraattota Dirree Dhawaa maraan, Lammiiwwan biyya teenya Itoophiyaa fi Dhalattoota Dkrree fi Kan biyya teenyaa kan biyya keessaa fi biyyoota alaa gara garaa jiran maraan baga bara haaraa 2017 isin ga'e barri haaraan bara Magaalaa, Kan Gammachuu, Kan kan Guddinaa fi Badhaadhi akka isiniif ta'uun haqa jedhuun Ergaa hawwii gaarii fi baga Bara haaraa 2017 isin ga'ee erga dabarsan. Saganticha irratti Barruun qorannoo Abdii Guddaa hegeree Bulchiinsa Dirree Dhawaa fi biyya teenya Itoophiyaa mul'isu dhiyaatee mariin irratti taasifameera. Abdii Adamiin Suuraan Aganyahu Shawaaragaa
Show all...
👍 4
#ዜና /የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በመዘመን እያሰራ ያለው ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተገለጸ #DGCጳጉሜ 5/2016 በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለተቋሙ ሰራተኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከጊዜ ወደ ጊዜ አዳዲስ በቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጡን እያቀላጠፈ መሆኑን ተናግረው ይሄም የሚበረታታና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ስራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር አያይዘውም በበዓሉ የውሃ እጥረት ሳይከሰት ማህበረሰቡ በዓልን እንዲያሳልፍ በርብርብና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ጠቁመው የውሃ አጠቃቀምም በአግባቡና በፍትሀዊነት ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናገረዋል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር መሃመድ ሙሴ በበኩላቸው የውሃ ፍላጎትን ለመስተዳደሩ ነዋሪ ተደራሽ ለማድረግ በበጀት አመቱ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም የመስመር ማሻሻልና የመቀቀየር፣ የውሃ ጥራት ላይ ቁጥጥር የማድረግ እንዲሁም የጥገና ስራዎች በስፋት መሰራታቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ከመልካ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጋር በተያዘም ስራዎች በተቀላተፈ መልኩ እየተሰሩ እንደሚገኝ ስራ አስኪያጁ ተናገረው፤ በአጠቃላይም በ 2017 ዓ.ም ተቋሙ በ 2016 በጀት ዓመት የጀመራቸውን ጠንካራ ስራች የሚያስቀጥልበት እንዲሁም ደግሞ ክፍተት የታዩ ቦታዎች ላይ አትኩሮ የሚሰራበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በመጨረሻም ኢንጂነር መሃመድ ማህበረሰቡ የውሃ ሀብቱን ሳያባክን በአግባቡ እንዲጠቀም ተናግረው ለመላው የድሬዳዋ ህዝብና ለተቋሙ ደንበኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በኤደን ሳሙኤል ፎቶ፤- አብይ ሽመልስ
Show all...
2017 የሚለውጠን ሳይሆን የምንለውጠው ዓመት እንዲሆን ነው ምኞቴ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ******************************************* እንኳን ለ2017 የዘመን መለወጫ በዓል ዕንቁጣጣሽ በዓል አደረሳችሁ። ዘመን ዕድል ነው፡፡ ዘመንን መጠቀም ግን የሥራ ውጤት ነው፡፡ ዘመንን ፈጣሪ ለሁላችንም በእኩልነት ሰጥቶናል፡፡ ልዩነት የሚፈጠረው በዘመን በመሥራትና ባለመሥራት ነው፡፡ በታሪካችን ውስጥ የምንኮራባቸው ምእራፎች አሉ፡፡ በሕይወታችን ውስጥም ደስ የሚያሰኙን ጊዜያት አሉ፡፡ እነዚያ ምእራፎችና ጊዜያት ሌላ ነገር አይደሉም፡፡ የተሰጠንን የዘመን ዕድል በሚገባ ተጠቅመን የሠራንባቸው ወቅቶች ናቸው፡፡ እኛ ብንፈልግም ባንፈልግም ዘመን ይለወጣል፡፡ ጊዜ ወደፊት ብቻ የሚሄድ ማሽን ነውና፡፡ ማንም አያስቆመውም፤ አቅጣጫም አያስቀይረውም፡፡ የሚቻለው በጊዜ መጠቀም ብቻ ነው፡፡ “ክረምት ለሰነፍ ገበሬ መዓት፤ ለጎበዝ ገበሬ ምሕረት ነው” ይባላል፡፡ ምሕረትና መዓቱ ከዝናቡ የሚመጣ ሳይሆን ከገበሬዎቹ ዝግጅትና ሥራ የሚገኝ ነው፡፡ በሰነፍ ገበሬ ላይ ዘመን ይለወጥበታል፤ ብርቱው ገበሬ ግን ዘመንን ራሱን ይለውጠዋል፡፡ በ2016 ለኢትዮጵያ ምን አሳክተናል? በ2017ስ ለኢትዮጵያ ምን ተዘጋጅተናል? የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የዘመን መለወጥን ትርጉም ይቀይረዋል፡፡ ዘመን እየተለወጠብን ነው ወይስ ዘመኑን እየለወጥነው ነው? የሚለውን ያመለክተናል፡፡ ኢትዮጵያን ዘመን እየለወጣት ብዙ ጊዜ ኖራለች፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ በብርታትና በትጋት ዘመኑን ለውጣው ታውቃለች፡፡ ዘመን ሲለውጠን፣ ከተራራ እንደተፈነቀለ ድንጋይ፣ ወዳሰብነው ሳይሆን ወደ ፈለገው ነው የሚወስደን፡፡ 2017 የሚለውጠን ሳይሆን የምንለውጠው ዓመት እንዲሆን ነው ምኞቴ፡፡ ዕቅዶቻችንን ተግብረን፤ ፕሮጀክቶቻችንን በጊዜና በጥራት አጠናቅቀን፤ ግጭቶቻችንን በውይይትና በድርድር ፈትተን፤ የዘመናት ስብራቶቻችንን በምክክርና በሽግግር ፍትሕ ጠግነን፤ በብዙ ነገሮች ራሳችንን ችለን፤ ሪፎርሞቻችንን በብቃት አሳክተን፣ የምንለውጠው ዘመን እንዲሆን ነው ምኞቴ፡፡ 2017ን በኢትዮጵያ ታሪክ የሚጠቀስ ዘመን ለማድረግ እንዘጋጅ፡፡ የዘመናት ዕዳዎቻችን የምናወራርድበት፤ የኖሩ ቁስሎቻችን የምናክምበት፤ የዘመናት ሕልሞቻችንን ሥር መሠረት የምናስይዝበት፤ የታሪክን መኪና መሪና ማርሽ የምንቆጣጠርበት ዘመን ለማድረግ እንነሣ፡፡ ወደፊት የሚመጡት ልጆቻችን “ይሄ ታሪክ የተሠራው፣ የዛሬ ስንት ዓመት በ2017 ነው” እንዲሉን እናድርገው፡፡ በወጀብና በዐውሎ ውስጥ አስገራሚ ሥራዎችን እንድንሠራ የፈቀደ ፈጣሪ ዛሬም ከእኛ ጋር ነው፡፡ ነገም ከእኛ ጋር ነው፡፡ መሥራት የእኛ ማከናወንም የእርሱ ነው፡፡ እኛ ከተነሣን ዘመኑን እንድንለውጠው እርሱ ይረዳናል፡፡ በድጋሚ እንኳን ለ2017 የዘመን መለወጫ በዓል ዕንቁጣጣሽ አደረሳችሁ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ጳጉሜን 5፣ 2016 ዓ.ም
Show all...
#ዜና "በመጪው አዲስ ዘመን ከተማችንን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እንሰራለን" የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር #DGC ጳጉሜ 5/2016 ጳግሜ 5 የነገው ቀን "የዛሬ ትጋት፣ ለነገ ቱርፉት" በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተከበረ። መርሀ ግብሩንም የሀይማኖት አባቶች መጪው የኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ብሩህ እንዲሆን በጸሎት እና በምርቃት አስጀምረዋል። በመርሀ ግብሩም የድሬዳዋ አስተደደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በመልዕክታቸው በ2017 አዲስ ዘመን በሀገር ደረጃ የተጀመረውን በቴክኖሎጂ የታገዙ ስማርት ሲቲ የመፍጠር ተልእኮን ለማሳካት በቀጣይ ዓመት ከተማችንን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። በተጨማሪም በአስተዳደሩን የኮሪደር ልማት ስራዎችን በቀጣይ አመት ለመተግበር ዝግጅት መደረጉን እና በአስተዳደሩን በሰላም ና ጸጥታ የተገኙትንውጤቶች በማስጠበቅ እና በተሻለ ሁኔታ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን በማድረግ የከተማውን ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሰራም ነው የገለጹት። በመርሀ ግብሩም የኢትዩጵያ ና የድሬዳዋን ብሩህ ነገ ለመቀበል፤ በባለፉት አመታት የተመዘገበውን ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን በማስቀጠል ወጣቱ አሻራውን እንዲያሳርፍ፣ የነገው የከተማ እድገት የትውልድ ቅብሎሽ እና የመደመር ትውልድ ሚና በሚል የተዘጋጁ የፓናል ውይይቶች ተካሂደዋል በሰላም ለማ ምስል፡- አገኝው ሸዋረጋ
Show all...
#ዜና የድሬዳዋ አስተዳደርና ዳሽን ባንክ በቀጣይ ሁሉን አቀፍ በሆኑ ስራዎች ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ #DGC ጳጉሜ 5/2016 ስምምነቱንም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ከዳሽን ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ይህንአለም አቅናው ጋር ተፈራርመዋል:: በመድረኩም ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ዳሽን ባንክን ለድሬዳዋ ከተማ ትኩረት በመስጠት አብሮ ለመስራት ያሳየው ቁርጠኝነት የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው ለዚህ ስምምነት መሳካትም የበኩላቸውን አስተዋፆ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል:: የዳሽን ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ይህንአለም አቅናው በበኩላቸው ባንኩ በድሬዳዋ በርካታ ማህበራዊ አገልግሎቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረው ከተማዋ በአሁኑ ሰአት የንግድና የኢንቨስትመንት ከተማ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ከድሬዳዋ ጋር አብሮ መስራቱ ውጤታማ እንደሚያደር ጠቁመዋል:: በኤደን ሳሙኤል ፎቶ:- አብይ ሽመልስ
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.