cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

Show more
Advertising posts
10 963
Subscribers
-524 hours
-347 days
-16230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startapp=ref_346783642&startApp=ref_346783642 Join the Moonbix Journey! Get 1000 Coins as a new player and stay tuned for exciting airdrops and special rewards from Binance! አዲሱ የBinance Air drop ነው join ይደረግ ተስፋ አለው።
Show all...
Moonbix

Moonbix is a Binance crypto-themed game on Telegram Mini App game. Explore the galaxy, collect items, and boost your score!

😁 1
ተአምረ ውኃ 💧💧💧 >>> «ውኃ ምንም ዓይነት ካሎሪም ሆነ የምግብ ንጥረ ነገር ባይኖረውም የምግብ ሁሉ ምንጭ በመሆኑ ተአምራዊ ፍጥረት ያደርገዋል። ውኃ ቀለም አልባ፣ ሽታ አልባ፣ ጣዕም አልባ ቢሆንም የቀለም መበጥበጫ፣ የሽታ መቀመሚያ፣ የጣዕም ማምጫ የሆነ ወሳኝ ነገር ነው። በኢኮሎጂ ውኃ ሲፈለግ በጠጣር (በረዶ) ወይም በፈሳሽ (ውኃ) አለዚያም በተን (ደመና) መልክ ሆኖ የሥርዓተ ምኅዳር ሚዛንን ጠባቂ ወሳኝ ቁስ አካል ነው።» ... «ውኃ ድልዳል ሆኖ ግዙፍ መርከብን ያንሳፍፋል፣ አንዲት ትንሽ ጠጠርን ግን ያሰጥማል። ውኃ መስኖ ሆኖ በቦይ ተመርቶ ከድርቅ፣ ከረሃብ ይታደግሃል፤ እርሱ ምን ቸግሮት ውኃ ጎርፍ ማዕበል ሆኖ ሊጠራርግህም ይችላል። ከአካባቢው ጋር ባለው ፈጣን ተራክቦ ቀዝቃዛ ሆኖ ሊያኮማትርህ ይችላል፣ ፍል ሆኖ ሊገሸልጥህ ይችላል። ውኃ ያቀዘቅዝኻል፣ ውኃ ያሞቅኻል። ውኃ ያነፃኻል፣ ውኃ ተበክሎ ቆሻሻ ሆኖ ይበክልሃል።» «ውኃ በተቃርኖ የሚገለጽ ብቻ ሳይሆን ከምትገምተው በላይ ልዩ ጉልበት የተጎናጸፈ፣ በግዙፍ አካላት ከመስረግ ጀምሮ በማንኛውም ቅርጽ ባለው ቀዳዳ መሹለክ የሚችል ተፈጥሮ ያለው ነው። ውኃን ከአሸዋ ቀላቅለህ በኃይል ብታፈሰው የመጋዝ ያህል ሊቆርጥ ይችላል።» «ውኃ ብዙ ሰው የማያስተውለው የተለየ ባሕርይም አለው። በዘመናዊው ሳይንስ ውኃ ድርጊቶችን በበጎም ሆነ በክፉ የመመዝገብ ትውስታን (memory) የመያዝ አቅም እንዳለው ተደርሶበታል። ውኃ በብርጭቆ አድርገህ ስትረግመውና ስትሰድበው ቆይተህ ወደ በረዶነት እንዲቀየር አድርገህ ብታየው የበረዶው ግግር አስፈሪ ቅርጽና ጉድፍ የበዛበት መልክ ይዞ ብቅ ይላል። በአንጻሩ እያመሰገንክና እየመረቅክ በጎ ቃላትን እያስተማርከው ቆይተህ ወደ በረዶ ብትቀይረው ቀለሙ ጸዐዳና አስደሳች ቅርጽ ይዞ ታገኘዋለህ። በዚህ ጠባዩ ውኃ የአካል ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ንጽሕናን ያጎናጽፋል። ... «ይህንን ልዩ የውኃ ባሕርይ መረዳትና መግራት ከተቻለ ውኃ የስልጣኔ፣ የልማት፣ የብልጽግና፣ የመንፈሳዊነት ምንጭ ይሆናል። ምስጢሩን ባግባቡ የተረዱ ሀገሮች በልጽገዋል። የአውሮፓ፣ የአሜሪካ፣ የመካከለኛው ምሥራቅና፣ የሩቅ ምሥራቅ ስልጣኔ ከውኃ የተቀዳ ነው። ከተሞቻቸው ያጌጡት፣ ህልውናቸው የተመሰረተው በሐይቅና በወንዝ ነው።» >>> ━━━━━━━━━━ 📔 ሚተራሊዮን ✍ ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ 📄 185 - 186 📖 📖 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
Show all...
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን

https://t.me/Ethiobooks

ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

👍 6
sticker.webp0.08 KB
📔 ሱፊዝም >>> ከብዙ ዓመታት በፊት ከኦቶማን ሱልጣኖች የአንዱ እናት የሆነች ሴት ራሷን በበጎ አድራጎት ሥራ በእጅጉ የተጠመደች አድርጋ ትኖር ነበር። በቱርክ ግዛት ውስጥ ታላላቅ መስጊዶችና ሆስፒታሎች እንዲሁም የውሃ ጉድጓዶችን በማስቆፈር ሕዝቡ የተሻለ ሕይወት በሁሉም አቅጣጫ እንዲኖር ትጥራለች። አንድ ቀን በከተማ ውስጥ በማሠራት ላይ የምትገኘውን ሆስፒታል ለመጎብኘት ወደዚያ አምርታ እየተዘዋወረች ስትመለከት መሠረቱ ገና ባልደረቀ የሲሚንቶ ልስን ላይ አንዲት ጉንዳን ስትወድቅ ተመለከተች። በፍጥነትም እጇን ሰንዝራ ጉንዳኗን ከወደቀችበት ሲሚንቶ ላይ በማንሳት በምድር ላይ አስቀመጠቻት። ይህች ሴት ከጥቂት ዓመታት በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ትለይና በዚያው ቀን ለብዙ ጓደኞቿ በሕልማቸው ትታያለች። በመልኳ እጅግ ተውባና በውስጧም በደስታ የተሞላች ሆና የተመለከቷት ጓደኞቿ ያለጥርጥር በሠራቻቸው በጎ ምግባሮችና ቸርነቶች ገነት ገብታለች ማለት ይጀምራሉ። ይህን ጊዜ ይኽች ሴት ለሁሉም ሴቶች በሕልማቸው የነገረቻቸው ነገር ቢኖር፦
«እኔም እንደ እናንተው በበጎ ሥራዬ ገነት እንደምገባ ስመካና ስታበይ ኖሬ ነበር። ነገር ግን በፈጣሪ ዘንድ ታላቅ ሥራ ተደርጎ የተቆጠረልኝ በእኔ ልብ ውስጥ ቦታ ያልነበረውና አንዲት ጉንዳንን ከሲሚንቶ ላይ አንስቼ ሕይወቷን ማትረፌ ነበር» አለች።
እንሆ ሱፊዎች ሲመክሩ «በሰው ልጅ ዐይን ትንሽ መስሎ የሚታየው ድርጊት በፈጣሪ ዐይን ታላቅ ይሆናል። ሰው የሚመካበት ሁሉ በፈጣሪው ዘንድ ከንቱና የከንቱም ከንቱ ነው» ይላሉ። >>> ━━━━━━━━ ✍ ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ጲላጦስ) 📄 144 - 145 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
Show all...
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን

https://t.me/Ethiobooks

ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

👍 13
sticker.webp0.08 KB
አቤ ጉበኛ - 2 የመጨረሻው!
Show all...
@ethiobooks አቤ ጉበኛ 2.mp35.27 MB
👍 7
አቤ ጉበኛ - 1
Show all...
@ethiobooks አቤ ጉበኛ 1.mp36.53 MB
👍 6
▶        ደራሲ አቤ ጉበኛ              ━━━━━━             @ethiobooks
Show all...
sticker.webp0.08 KB
ሠለስቱ ምስጢራት ═══✦═══ ✍ ኤፍሬም ስዩም ' እናም ... እኒህን ሦስት ምስጢሮች ስነግርሽ አልገባኝም እንዳትይ ነው ... አደራ የምልሽ ፩ ... አንደኛ ልንገርሽ ምንም ያልነገርኩሽ አንዳች ምስጢር የለም ሁሉን ሰምተሽዋል ... አብረን ከዚህ ቀደም። ፪ ... ሁለተኛም ያው ነው ራሱ ምስጢሩ ... ከየት የመጣ ነው? ፫ ... ሦስተኛው ነገር ግን የልቤ ላይ ፍሬ የገመትሽው ካለ ... እሱ ነው ምስጢሬ። ════════ 📔 ኑ ግድግዳ እናፍርስ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
Show all...
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን

https://t.me/Ethiobooks

ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።

👍 5
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.