cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

AddisWalta - AW

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel. For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Show more
Advertising posts
46 701
Subscribers
+1224 hours
+847 days
+14930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ #ጤና_ደጉ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ማለት በተፈጥሮ አደጋ ወይም በሰው ሰራሽ ምክንያት ለተጎዳ ሰው ወይም በአጣዳፊ ህመም ለታመመ ሰው በህክምና ተቋም እስኪደርስ ድረስ የሚደረግ ወይም የሚሰጥ አፋጣኝና ጊዜያዊ የህክምና እርዳታ ነው፡፡ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በድንገተኛ አደጋ ወይም ባልተጠበቀ አጣዳፊ ህመም ውስጥ ያለ ሰውን ስቃይ መቀነስና ህይወት ለማትረፍ የሚሰጥ የህክምና ድጋፍ ማለት ነው፡፡ በዚህም የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ማለት የመጨረሻ ህክምና ማለት አይደለም፡፡ 👉ዓላማ 🔸አደጋ የደረሰበት ወይም በህመም ላይ የሚገኝ ሰውን የህክምና እርዳታ እስከሚያገኝ ድረስ ህይወትን ለማዳን (ለማትረፍ) 🔸 አደጋው እንዳይባባስ፤ የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስና ለከፋ ጉዳት እንዳይጋለጥ ማገዝ 🔸የህመም ስቃይንም ለመቀነስ 🔸 ተጎጂውን በፍጥነት ከህመሙ ወይም ከጉዳቱ እንዲያገግም የሚያስችል ስራ መስራት 👉የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ስልጠና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች 👇👇 https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid021mL5x439daCmRs1DXYkvkeXtX7ngoGrjzeVyReavj9gKeotJUykmphKSHRyfUabKl
Show all...
👍 11👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮን ሆኑ መስከረም 9/2017(አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የቱሪዝም ሻምፒዮን ሆነው ተመርጠዋል። “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲሱ የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮን መሆናቸውን ስንገልፅ ኩራት ይሰማናል” የኢጋድ ጽሕፈት ቤት በኤክስ ገጹ አስፍሯል። ጽሕፈት ቤቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለራዕይ መሪነት በቀጠናው ቱሪዝምን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው በመግለጽ አመራራቸውም በኢጋድ አባል ሀገራት የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት፣ ቅርሶችን እና አካባቢን ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብሏል።
Show all...
🙏 22👍 7👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል ኔታንያሁን ለመግደል ከኢራን ጋር ያሴረን ግለሰብ ያዘች መስከረም 9/2017(አዲስ ዋልታ) የእስራኤልን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትን ለመግደል ከኢራን ጋር አሲሯል የተባለው እስራኤላዊ ዜጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የእስራኤል የደህንነት መስሪያ ቤት አስታወቀ። የእስራኤል ፖሊስ እና የሀገር ውስጥ ደህንነት በጋራ ባወጡት መግለጫ ግለሰቡ ሁለት ጊዜ በድብቅ ወደ ኢራን በማቅናት በእስራኤል ተልእኮዎችን ለመፈጸም ክፍያ መቀበሉን ተናግረዋል። ኑሮውን በቱርክ ያደረገው እስራኤላዊ ነጋዴ የግድያ ሴራውን በተመለከተ በኢራን በተካሄዱ ውይይቶች በጥቂቱ ሁለት ጊዜ መሳተፉን መግለጫው ጠቁሟል። ኢላማዎቹም ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ እና የእስራኤል የውስጥ ደኅንነት ኤጀንሲ ኃላፊ መሆናቸውንም ገልጿል። ወደ ኢራን በማቅናት ተጠርጣሪው ከኢራን የደህንነት ባለስልጣናት ጋር እንዲገናኝ ተደርጎ ተልዕኮዎችን መቀበሉን የእስራኤል የሀገር ውስጥ ደህንነት አስታውቋል። በዚህም ተጠርጣሪው በእስራኤል ውስጥ የሽብር ተግባራትን ለመፈጸም በተጨማሪም በአውሮፓ እና በአሜሪካ የኢራን መንግስት ተቃዋሚዎችን ለመግደል አንድ ሚሊዮን ዶላር እንዲከፈለው የጠየቀ ሲሆን በግድያ ሴራ ስብሰባዎቹ ላይ በመሳተፉ ብቻ 5 ሺሕ 600 ዶላር እንደተከፈለው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ኢራን የሃማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ መገደልን ተከትሎ በእስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ብታስጠነቅቅም እስራኤል ግን እስካሁን ለግድያው ኃላፊነት አለመውሰዷ ይታወሳል፡፡
Show all...
👍 6
አየር መንገዱ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት መስከረም 9/2017(አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን ሁለት የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ ሽልማቱ የተበረከተው ኮርፖሬሽኑ 35ኛ ዓመቱን ባከበረበት ደማቅ መርኃ ግብር ላይ ሲሆን አየር መንገዱ ላባረከተው የላቀ አገልግሎት እና የላቀ የስራ አጋርነት ዕውቅና የተሰጠበት መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል። ይህ ሽልማት ለዛምቢያ ኤርፖርት ዕድገት በመንገደኛ እና በዕቃ ጭነት አገልግሎት ዘርፎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያበረከተው አስተዋፅዖ እና ያልተቋረጠ ድጋፍ ማሳያ መሆኑም ተመላክቷል፡፡ ሽልማቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ ለሚጓዙ መንገደኞች እንከን የለሽ ጉዞን ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም አየር መንገዱ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን ሊሚትድ ጋር ያለውን ጠንካራ እና ፍሬያማ አጋርነት የሚያጠናክር ነው ተብሏል።
Show all...
👍 7👏 2👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ መስከረም 9/2017(አዲስ ዋልታ) የአንጋፋው ፖለቲከኛ የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ሥርዓተ ቀብር በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡ በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ባደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 6 ቀን 2016 ዓ.ም በተወለዱ በ75 ዓመታቸው ማረፋቸው ይታወቃል።
Show all...
😢 13
የፍቅር ስጦታ አበባ ወይስ ችግኝ? ኬልሲ እና ዌስ ዲክሰን ይባላሉ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በትውልድ ከተማቸው በአሜሪካ ፔንስልቬኒያ ውስጥ በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበሩበት ጊዜ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ የፍቅር ግንኙነት የጀመሩበት ጥንዶቹ የግንኙነታቸውን ቀን አስመልክቶ ዛፍ ይተክላሉ፡፡ ታዲያ የተከሉትን የዛፍ እድገት ጉዞ ከራሳቸው የሕይወት ጉዞ ጋር በማጣመር የተለያየ ፎቶ በማጋራታቸው መነጋገሪያ ሆነዋል። ጥንዶቹ በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቆይታቸው እርስ በርሳቸው ሲፈላለጉ የነበሩ ሲሆን ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲገቡ ግንኙነት መጀመራቸውን ኬልሲ ዲክሰን ታስታውሳለች። ፍቅር የጀመሩበት አንደኛ ዓመት ሲያከብሩ ዌስ ለፍቅረኛው በአበባ ፋንታ የዛፍ ችግኝ በስጦታ መልክ ያመጣላታል፡፡ የኬልሲ እናትም የልጇ ጓደኛ ባመጣው ስጦታ በመገረም በቤታቸው ጀርባ እንዲተክሉት ሃሳብ ታቀርብላቸዋለች። በሀሳቡም ይስማማሉ፡፡ 👇👇 https://www.facebook.com/share/p/K9uTZtZ21LQ6TRN4/
Show all...
👍 9👏 5🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከ1ሺሕ 200 በላይ የሞባይል ጣቢያዎች ሊገነቡ ነው መስከረም 9/2017(አዲስ ዋልታ) የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በተያዘው በጀት ዓመት 1 ሺሕ 298 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች እንደሚገነቡ ገለጹ። ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት ዲጂታል የቴሌኮም መሰረተ ልማትን ለመገንባት ማቀዱን ገለጸዋል። በተጨማሪም 4G እና አድቫንስ 4G አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የታቀደ ሲሆን የቴሌኮም ተጠቃሚ ያልሆኑ የገጠር ቀበሌዎች ላይ ሰፊ ማስፋፊያ ለማድረግ ውጥን መያዙን አስታውቀዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ተቋሙ በ2015 ዓ.ም የ3 ዓመት መሪ ስትራቴጂክ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰው ይህ ስትራቴጂ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከእቅድ በላይ ተፈፅሟል ብለዋል። በተያዘው በጀት ዓመት የሚጠናቀቀው መሪ ስትራቴጂክ እቅዱ ላይ በመወያየት እቅዱ ለቀጣይ በጀት ዓመትም መደላድልን የሚፈጥር እንዲሆን ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢን 163 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ መታቀዱንም ገልጸዋል። የደበኞችን ቁጥር ከ78 ሚሊዮን ወደ 83 ሚሊዮን ከፍ ለማድረግ መታቀዱን ያስታወቁት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የቴሌብር ተጠቃሚዎችን ቁጥር 55 ሚሊዮን ለማድረስ እንደሚሰራ ጠቁመዋል። በብሩክታዊት አፈሩ
Show all...
👍 7
ሁላችንም ጊዜ ሳናባክን እንደ በየነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ለሀገራችን መሥራት አለብን - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መስከረም 9/2017 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የበየነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አስክሬን ሽኝት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በሽኝት መርኃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች የተገኙ ሲሆን በወንድማቸው ዋቸሞ ጴጥሮስ የሕይወት ታሪካቸው ተነቧል። በየነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በኤች አይ ቪ ቫይረስና በወባ በሽታ በርካታ ምርምሮችን አድርገዋል። ጥናቶቻቸው በዩኒቨርስቲዎች ማስተማሪያ ከመሆን ባሻገር የምርምሩን ዘርፍ ከፍ እንዲል ጉልህ ሚና ነበራቸው። በዐምደወርቅ ሽባባው
Show all...
👍 6👎 1😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ በመርህ ላይ የተመሰረተ ምላሽ ትሰጣለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስከረም 9/2017 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ መስመር ለማሳት የሚሰነዘሩ አስተያየቶችን በሰከነ እና መርህን በተከተለ መልኩ ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ገለጹ። በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ተከትሎ በአንዳንድ አካላት ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ንግግሮች እየተደመጠ መሆኑን የገለፁት ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ በሰከነ እና መርህን በተከተለ መልኩ ምላሸ ትሰጣለች ብለዋል። አምባሳደር ነብያት በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ጉባኤውን ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ትጠቀምበታለች ብለዋል። በሁለትዮሽ ግንኙነት በሶማሊያ (አትሚስ) ስምሪት ላይ ከወታደር አዋጭ ሀገራት ጋር ኢትዮጵያ ውይይት ታደርጋለች ሲሉም አክለዋል፡፡ 79ኛው የተባበሩ መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 14 እስከ 20 በኒውዮርክ ከተማ ይካሄዳል። በመስከረም ቸርነት
Show all...
👍 4
ሦስት ሕገ ወጥ የከረሜላ ምርቶች ከገበያ ታገዱ መስከረም 9/2017 (አዲስ ዋልታ) ሦስት ሕገ ወጥ የከረሜላ ምርቶች ገበያ ላይ እንዳይውሉ መታገዳቸውን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ ሃኒ ስዊት፣ ላቭሊ ካንዲ እና ጎግል ካንዲ የተሰኙ የከረሜላ ምርቶች ናቸው ገበያ ላይ እንዳይውሉና ሕብረተሰቡም እንዳይጠቀማቸው የታገዱት፡፡ ምርቶቹ ብሔራዊ አስገዳጅ ገላጭ ጽሑፍ ደረጃ CES 73/2013 ሳያሟሉ ገበያ ላይ የተገኙ ሲሆን ማን እንዳመረታቸው፣ የት ሀገር እንደተመረቱና የአምራቹ አድራሻ እንደማይታወቅ እንዲሁም የምርቱ ባች ቁጥር የሌላቸው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ሕብረተሰቡ መሰል ጤናን የሚጎዱ ምርቶች ሲያጋጥመው በነጻ የስልክ መስመር 8482 ወይም በአቅራቢያ ላሉ የጤና ግብዓት ተቆጣጣሪ ተቋማት አሊያም ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ባለስልጣኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡
Show all...
👍 9
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.