cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

DW Amharic

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Show more
Advertising posts
48 190
Subscribers
+8924 hours
+5117 days
+1 83930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

https://p.dw.com/p/4krPT?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
በህወሃት መሪዎች መካከል የቀጠለው ውዝግብ

ህወሃት ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብ እያደር እየጋለ መሄዱ እየታየ ነው። ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቃራኒ በቅርቡ ስብሰባ ያካሄደው ህወሃት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተወሰኑ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ይፋ አድርጓል። አቶ ጌታቸውም ህወሃት የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ከሥልጣን ለማውረድ እየሠራ ነው በማለት ከሰዋል።

https://p.dw.com/p/4krVW?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ወቅታዊ ሁኔታ

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር በቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን ተወያይተዋል። ኢጋድ በሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መከበር ላይ ግልጽ አቋም እንዳለውና ይህም የድርጅቱ አባል ሃገራት እና መንግሥታት መሪዎች ያረጋገጡት መሆኑን ዋና ጸሐፊው ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4krjy?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
ከጀርመኑ የብራንድንቡርግ ፌደራዊ ግዛት ምርጫ ምን ይጠበቃል?

AFD ግዛቲቱን ለ34 ዓመታት የመራውን SPDን ሊያሸንፍ ይችላል የሚል ሰፊ ግምት አለ። ምሥራቅና ምዕራብ ጀርመን ከተዋሀዱአንስቶ ግዛቲቱን ሲመራ የቆየው የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ SPD በእሁዱ ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ስልጣኑን ሊለቅ ይችላል ተብሏል። የግዛቲቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲትማር ቮይድከ ይህ እንዳይሆን የምችለውን ሁለ አደርጋለሁ ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4krae?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
ኢትዮጵያን ዲጂታል የማድረግ ውጥን፡ ኢትዮ ቴሌኮም

በ2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን መሰረተ ልማት ለመዘርጋት ከአንድ ቢሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር መመደቡን የኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ። ኩባንያው የኔተዎርክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ጥራት ላይም በዚህ ዓመት አተኩሮ እንደሚሠራ አሳውቋል።

https://p.dw.com/p/4krTU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot https://p.dw.com/p/4krTU
Show all...
በሊባኖስ በመልዕክት መቀበያ ስልኮች የደረሱ ፍዳታዎች ያደረሱት ጉዳት

በሊባኖስ ባለፈው ማክሰኞ በአነስተኛ የኤሌክትሮኒክስ መልክት ማስተላለፊያ መሳሪይዎች ወይም ፔጀርስ፤ በትናንትናው ዕለት ደግሞ በመገናኛ የእጅ ሬዲዮኖችና ኮምፕዩተሮችና መኪናዎች ጭምር በደረሱ ፍንዳታዎች እስካሁን 32 ሰዎች ሞተዋል፤ 3,500 የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።

https://p.dw.com/p/4krXe?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
“አቴቴ አያና ሐዎታ” - በገዳ ስርዓት ለሴቶች የሚሰጥ ያልተገደበ መብት

ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበት እና ከሁለት ዓመታት በላይ የምርምር ጊዜን የወሰደው “አቴቴ አያና ሐዎታ” የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ተመረቀ፡፡ ፊልሙ የገዳ ስርዓት አካል የሆነው አቴቴ የኦሮሞ ህዝብ ባህሉን፣ ትውፊቱንና ወጉን በአፈታሪክ እና በጽሁፍ እንዲሁም በዜማ፣ በስነቃል ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገሩ አንዱ ማሳያመም ተደርጎ ተወስዷል፡፡

https://p.dw.com/p/4kriZ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
Show all...
የሐሙስ መስከረም 9 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና

*ባለፈው ማክሰኞ የተኩስ ድምፅ ሲያጓራባት የቆየችው የጎንደር ከተማ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ በአብዛኛው ወደነበረበት መመለሱን ነዋሪዎች ተናገሩ ። በትንሹ 5 ሰዎች መገደላቸውንም አክለዋል  ።

Photo unavailableShow in Telegram
ጤና ይስጥልኝ እንደምን አላችሁ። የዛሬዉ ሥርጭታችን የሚከተሉትን ጉዳዮች ያስተነትናል። በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት ላይ ያጠላው ውጥረት፤ በሕወሃት መሪዎች መካከል የቀጠለው ውዝግብ፤ በግጭት ወቅት የሚቋረጠው የቴሌኮም አገልግሎት ተጽዕኖ፤ በሊባኖስ በመልዕክት መቀበያ መሳሪያዎች የደረሱ ፍዳታዎች ያደረሱት ጉዳትና ዓለም አቀፍ ምላሹ፤ እንዲሁም የፊታችን እሑድ በጀርመን የብራንድንቡርግ ክፍለ ግዛት የሚካሄደውን ምርጫ። አብራችሁን ቆዩ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አንካራ-ቱርክ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ባለሥልጣናትን በተናጥል ልታነጋግር ነዉ ኢትዮጵያና ሶማሊያ የገጠሙትን ፍጥጫ በድርድር ለማስወገድ የምትጥረዉ ቱርክ የሁለቱን ሐገራት ባለሥልጣናት ዳግም ግን በተናጥል ለማነጋገር ማቀዷን አስታወቀች።ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የመንግሥትነት ዕዉቅና ከሌላት ሶማሊላንድ ጋር ወደብ ለመኮናተር የመግባቢያ ስምምነት በፈራረሟ የአዲስ አበባና የሞቃዲሾ ጠብ ተካርሯል።ግብፅ ለሶማሊያ ጦር መሳሪያ ማስታጠቅ መጀመሯና ሶማሊያ ዉስጥ ወታደር ለማስፈር ማቀዷ ደግሞ አዲስ ግጭት ሊያስከትል ይችላል የሚል ሥጋት አሳድሯል። ጠቡን ለማርገብ ቱርክ ከዚሕ ቀደም የሁለቱን ሐገራት ባለሥልጣናት አንካራ ዉስጥ ሁለቴ በስማበለዉ (በተዘዋዋሪ) አነጋግራለች።በቱርክ ሸምጋይነት የሚደረገዉ የስማበለዉ ድርድር ባለፈዉ ማክሰኞ ለሶስተኛ ዙር ይቀጥላል ተብሎ ነበር።ይሁንና ቀጠሮዉ ተሰርዟል።የቱርክ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሐካን ፊንዳን ዛሬ እንዳሉት ሐገራቸዉ የሶማሊያና የኢትዮጵያ ሚንስትሮችንና መሪዎችን ማነጋገሯን ትቀጥላለች።ሚንስትሩ እንዳሉት ከዚሕ ቀደም በተደረጉት ተዘዋዋሪ ድርድሮች ሁለቱም ወገኖች መጠነኛ መለሳለስ በማሳየታቸዉ ድርድሩ ዉጤት ያመጣል የሚል «ተስፋ አለኝ» ብለዋል።በፊዳን መግለጫ መሠረት ቱርክ የወደፊቱን ሽምግልና ለመቀጠል ያቀደችዉ «የሁለቱን ሐገራት ባለሥልጣናት እዚሕ ብንጋብዛቸዉም ፊትለፊት ሥለማይነጋገሩ እኛ በተናጥል እናነጋግራቸዋል።» ብለዋል።
Show all...
02:13
Video unavailableShow in Telegram
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ተደረገ በሽኝቱ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው ተገኝተዋል።(የቪዲዮ ዘገባ፣ ሰለሞን ሙጬ)
Show all...
DWVGAMH240919_Beyene_II_01SMW.mp4158.92 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.