cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

MILLENNIUM KOMBOLCHA PREPARATORY SCHOOL

QUALITY EDUCATION FOR ALL

Show more
Advertising posts
1 090
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የሚሊኒየም አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ 2015 ዓ.ም አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ ሲገቡ የሚያሳይ ፎቶ በከፊል ከዚህ በታች ይታያል።
Show all...
በ 2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍልየ ሚሊንየም ኮምቦልቻ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች አገር አቀፍ ፈተናዎችን ለመፈተን ወደ ወሎ ዩንቨርስቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ በጉዞ ላይ 23/11/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00
Show all...
Repost from N/a
ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች አቀባበል እየተደረገ ነው:: ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 22/11/2015 ዓ.ም ================== የማህበራዊ ሳይንስ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ሰርቲፊኬት ፈተና ተፈታኞችን አስተናግዶ ሽኝት በማደርግ ላይ የሚገኘው ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተያዘው የፈተና መርሃ-ግብር መሰረት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን  ለማስፈተን ሞቅ ያለ አቀባበል እያደረገላቸው ይገኛል:: ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በሚኖረው የተፈታኞች አቀባበል ከሰሜን ሸዋ፣ ከኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ከደቡብ ወሎ ፣ ከደሴና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ተቋሙ ላይ እንዲፈተኑ የተመደቡ 6141 ተማሪዎች ወደ ግቢው በመግባት ላይ ይገኛሉ ::
Show all...
Repost from N/a
Repost from N/a
የ2015 አ.ም የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ፈተና ክስተት ወ/ሮ ጸሃይ መሃመድ ኡመር እና ሁለቱ ልጆቻቸው፣ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 22/11/2015 ዓ.ም ==================== ትምህርት እድሜ እንደማይገድበው ማሳያ የሆኑት ወ/ሮ ጸሃይ መሃመድ ከሁለት ልጆቻችው ጋር የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ፈተናን በጋራ በመውሰድ ለቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ የ2015 ዓ.ም የፈተና ወቅት ገጠመኝ መሆን ችለዋል:: የግል ተፈታኝ የሆኑት እናት ከከሚሴ 02 መቶሆሮ አጠ/ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ከሆነችው ልጃቸው ሲሃም እንድሪስ ጋር የ12 ክፍል አገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ በግቢያችን ቆይታ ያደረጉ ሲሆን፣ ወንድ ልጃቸው ተማሪ ሪድዋን ሁሴን ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ በመሆኑ በዛሬው እለት ግቢውን የሚቀላቀል ይሆናል:: ከአንድ ቤት ውስጥ ወላጅ እናትን ጨምሮ ሶስት ተፈታኞች በአንድ ተቋም ውስጥ ለፈተና መቀመጣቸው ድምቀት ከመሆናቸው ባሻገር አስተማሪ ሆኖ አግኝተነዋል ። ተቋማችንም በዚህ አጋጣሚ መልካም ውጤትም ይቀናቸው ዘንድ ይመኛል !!!
Show all...
Repost from N/a
dormitory Placement Natural science male and Female (2015).xlsx3.56 KB
Repost from N/a
ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሰርትፍኬት ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ !!! ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 20/11/2015 ዓ.ም =================== በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ የሚገኝው የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሰርትፍኬት ፈተና  በ2ኛ ቀን የተሰጡት የአፕቲትዩድ እና ጆግራፊ ትምህርቶች ፈተና በሰላም ተጠናቋል:: እስካሁን ባለው ሂደት በተቋሙ የተመደቡት የ12 ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ የሚገኘው የ2 ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ፈተናን በጥሩ ስነ-ምግባር እየወሰዱ ይገኛሉ::
Show all...
Repost from N/a
እንኳን ለ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሰርትፍኬት ፈተና በሠላም አደረሳችሁ እያልን ፤  በወሎ ዩኒቨርስቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተመደባችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመኝታ ክፍላችሁን ከታች የተቀመጠውን ፋይል በመክፈት ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገልፃለን፣ ሁሉም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ስትመጡ  የትምህርት ቤታችሁን ደንብ ልብስ  መልበስ እንዳለባችሁ እናሳውቃለን !!!
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.